TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቅዱስ_ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አጭር መግለጫ ከተናገሩት የተወሰደ ፦ " ... ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በደንብ አውርተናል። በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን መሪነት በመንፈሳዊ ግርማ ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ክብር ሆነን እግዚአብሔርም አክብሮን ብዙ ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል እነዛን አጠቃላይ ነገ ነው የምንገልፀው። የነበረን…
#Update

" ተረጋግታችሁ ጠብቁ " - ቤተክርስቲያኗ

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ዛሬ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ይሰጣል ቢባልም መግለጫው ሳይሰጥ ሰዓታት አልፈዋል።

ቤተክርስቲያኗ መግለጫው እንደሚሰጥ እና ምዕመኑ ተረጋግቶ እንዲጠብቅ አሳስባለች።

በአሁን ሰዓት ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫውን ይሰጣል ተብሏል።

ጉዳዩ ትልቅ አጀንዳ ስለሆነ እና ትልቅ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ መግለጫው የዘገየ ሲሆን መግለጫው እስኪሰጥ ምዕመናን ተረጋግተው እንዲጠብቁ ቤተክርስቲያና መልዕክቷን አስተላልፋለች።

ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሲሰጥ 7ኛው ሲሆን ትላንት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በተደረገው ውይይት ስለተገኘው አጠቃላይ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫውን መሰጠት ጀምሯል። መግለጫው ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት ነው እየተሰጠ የሚገኘው። @tikvahethiopia
" ሰልፉ ተራዝሟል "

ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳን የአቋም ለውጥ ባያደርግም ትላንት በነበረው ውይይት መንግስት የቤተክርስቲያኗን ጥሪ በመቀበል የቤተክርስቲያኗን ችግር ለመፍታት #በመስማማቱ ነገ ሊደረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሰልፉ ተራዝሟል " ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳን የአቋም ለውጥ ባያደርግም ትላንት በነበረው ውይይት መንግስት የቤተክርስቲያኗን ጥሪ በመቀበል የቤተክርስቲያኗን ችግር ለመፍታት #በመስማማቱ ነገ ሊደረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙን አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update


ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም #ሙሉ_በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Credit : EOTC TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም #ሙሉ_በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በነበረው ውይይት ስለተደረሰበት ስምምነት አሳውቋል።

በዚህም ከመንግስት ጋር፦

- የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱ መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲያደርግ፤

- አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
#ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ ለነገ እሁድ የተጠራው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንዲያሳልፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፉ ለተወሰኑ ቀናት እንዲተላለፍ የተደረገው የአቋም ለውጥ ተደርጎ አለመሆን በመግለፅ አስቀድማ ቤተ ክርስቲያኗ በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት መሆኑን አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል " ብሏል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ይዘጋሉ።

የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል መንገዶች የሚዘጉት ለ " ፀጥታ ስራ ሲባል " መሆኑን ገልጾ ለተሽከርካሪም ሆነ ለእግረኞች ዝግ እንደሚደረጉ ነው ያመለከተው።

የጋራ ግብረ ሃይሉ ከቀናት በኋላ በአ/አ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚከናወነው #የአጀብ እና #የፀጥታ ስራዎች ምክንያት በማድረግ #ሁሉም_የፀጥታ_አካላት_የሚሳተፉበት ወታደራዊ የተግባር ልምምድ እንደሚከናወን አሳውቋል።

ለዚሁ ሲባል የሚከተሉት መንገዶች ለተሽከርካሪ እና ለእግረኞች ዝግ ይደረጋሉ ፦

🚘 ከጎተራ መሳለጫ ወይም ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ጎተራ መሳለጫ ጋር፤

🚖 ከቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሀር የሚወስደው ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መስቀለኛ  ላይ ፤

🚘 ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ቡልጋሪያ ማዞሪያ፤

🚖 ከሳር ቤት በአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ሳር ቤት አደባባይ፤

🚘 ከካርል አደባባይ በልደታ ፀበል ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት  ለሚመጡ ካርል አደባባይ፤

🚖 ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ፤

🚘 ከአብነት ወደ ጌጃ ሰፈር አብነት አደባባይ፤

🚖 ከሞላ ማሩ ወደ አብነት ፖሊስ ጣቢያ ለሚመጡ ሞላማሩ መስቀለኛ ፤

🚘 ከበርበሬ በረንዳ ወደ ቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ  ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤

🚖 ከተ/ሃይማኖት ወደ ጎማ ቁጠባ ተ/ሃይማኖት አደባባይ፤

🚘 ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ዝግ የተደረገ ሲሆን ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡ 

🚖 ከሽሮ ሜዳ ወደ 6 ኪሎ እና ወደ 4ኪሎ የሚያስኬደው መንገድ  ሽሮ ሜዳ ጋር የሚዘጋ ሲሆን ከ4 ኪሎ ወደ ቤተ መንግስት የሚወስደው መንገድ ዝግ ተደርጓል፡፡ 

🚘 ከቀበና ወደ 4ኪሎ ቀበና አደባባይ ፤

🚖 ከጀርመን አደባባይ እና ከሲግናል አካባቢ ወደ 4 ኪሎ ጥይት ቤት ለሚመጡ ጀርመን አደባባይ ፤

🚘 ከካዛንቺስ መናህሪያ ወደ 4ኪሎ እና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሴቶች አደባባይ፤

🚖 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ፤

🚘 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደበባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል መስቀለኛ ፤

🚖 ከቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ ወደ መስቀል ፍላወር ቅዱስ መርቆሪዮስ አደባባይ፤

🚘 ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ አፍንጮ በር፤

🚖 ከፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው 6 ኪሎ ዝግ ይሆናል፤

🚘 ከሚኒሊክ ሆስፒታል ወደ 6 ኪሎ የሚያመጣው መንገድ 6 ኪሎ ቶታል ጋር ዝግ የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም ወደ 4 ኪሎ እና በቅርበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመጡ አቋራጭ መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።

በተጨማሪም #ለእግረኛ ተጠቃሚዎች፦

🚶መስቀል አደባባይ 4ተኛ ክፍለ ጦር ወይም ጥላሁን አደባባይ ዙርያ፣
🚶‍♂ኦሎምፒያ ዙርያ፣
🚶‍♂ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ ከቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከሀራምቤ ወደ መሰቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ፣
🚶‍♂ከትምህርት ሚኒስቴር በአራት ኪሎ ብሔራዊ ቤተ መንግስትና ወደ ቦሌ እንዲሁም ከቀበና ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ዝግ መሆኑ ተነግሯል።

ዝግ ሆኖ የሚቆየው ከለሊቱ 11፡ 00 እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ህብረተሰቡ #አማራጭ_መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ተላልፏል።

(የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትምህርት_ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ ይወስዳሉ ብሏል። የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ፤ " እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ያ ማለት በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሯቸውን…
#MoE

የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ዛሬ የካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ይፋ ይደረጋል።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማወቅ ተከታዮቹን አማራጮች ይጠቀሙ፦

Website:  https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር ያሳውቃሉ ተብሏል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል። በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ዛሬ የካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ይፋ ይደረጋል። የተመደባችሁበትን ተቋም ለማወቅ ተከታዮቹን…
#MoE

ትላንት ለሊት ጀምሮ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባቸውን እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በተከታዮቹ አማራጮች ማየት ይችላሉ፦
Website:  https://result.ethernet.edu.et
SMS: 9444
Telegram bot: @moestudentbot

ከዚሁ ከዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ያላቸው ተማሪዎች result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ #በአካል የማይቀበል መሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ የሬሚዲያል ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ/ም ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላስመዘገቡና የተሻለ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት ተማሪዎች በሬሚዲያል ፕሮግራም እንደሚካተቱ መገለጹ ይታወቃል።

የሬሚዲያል ፕሮግራሙን ለአራት ወራት ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ለመስጠት ታቅዷል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
" አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤

ቤተክርስቲያኗ ከባንክ አገልግሎት ጋር በተያያዙ የሚነገሩባት #አሉባልታዎች ትክክል እንዳልሆኑ ገለፀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ ከቤተክርስትያኗ የባንክ አገልግሎት  ጋር በተያያዘ በርካታ አሉባልታ ይነሳል ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን የምትሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው። " ያሉት ብፁዕነታቸው " ከዓባይ ባንክ ጋር ሥራ የጀመርነው በህጋዊ አሰራር በጨረታ በተደረገ ሂደት  አሸናፊ ሆኖ በመገኘቱ ነው። " ብለዋል።

" ከዓባይ ባንክ ይልቅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኦሮሚያ ባንክ ያለን ገንዘብ ይበልጣል። " ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ " ዓባይ ባንክ ያለን ገንዘብ ተንቀሳቃሽና ለሰራተኛው የብድር አገልግሎት በማቅረብ ለሰራተኛው የመኪና፣ የቤትና የልዩልዩ ግዤዎችን ለመፈጸም የሚያስችል አገልግሎት የሚሰጥበት የባንክ አገልግሎት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፤ ቤተክርስቲያኗ በኦሮሚያ ባንክ የማይንቀሳቀስ ገንዘብ ማስቀመጧን ብፁዕነታቸው ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው " በጣም መጠነኛ ገንዘብ በአዋሽ፣ በሕብረትና በአቢሲኒያ ባንኮች አስቀምጣለች ፤ ከዚህ ውጪ በሌላ ባንክ  ወይም በአማራ ባንክ የተቀመጠ  ምንም አይነት የማዕከላዊ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ገንዘብ የለም። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" የተቀመጠ ገንዘብ አለ ከተባለም  #በማስረጃ  ማቅረብ ይቻላል " ያሉ ሲሆን " አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው ። " ሲሉ ገልጸዋል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

@tikvahethiopia