" ለመውጫ ፈተና ራሳችሁን አዘጋጁ " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ለዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳሰበ።
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ይሰጣል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም የመውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሰሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡
ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርስቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ዶክተር ሳሙኤል በአሁኑ ወቅትም የፈተና ንድፈ ማሳያና / Blueprint / የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
በውይይቱም ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል። በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ…
#ማስታወሻ
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያመጡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን የማስተካከያ ጊዜ ዛሬ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ያበቃል።
በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡና በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየት/ ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እንዲያስተካክሉ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ ያበቃል።
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውና እና ደጋፊ ሰነዶቻቸውን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ ይችላሉ 👇
https://student.ethernet.edu.et
More : @tikvahuniversity

Video
#Update
በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 16,000 አልፏል።
በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ16,000 በላይ መድረሱ ተነግሯል።
ባለስልጣናት እና የህክምና ሰዎች እንዳሉት ከሆነ ከቱርክ በኩል 12,873 ሰዎች ሲሞቱ ከሶሪያ በኩል 3,162 ሰዎች ሞተዋል።
ሰዎችን ከህንፃዎች ፍርስራሾች ውስጥ የመፈለጉ ሂደት እና የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።
ፎቶ፦ AFP

Photo
#Update
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር በተገናኘ የተከሰተው ክስተት ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች ውጥረት እንዲፈጠር አድርጎ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።
የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ፤ " በኦሮምያ ክልል ባሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ዛሬም ኦርቶዶክሳውያንን የማሰር ተግባር እንደቀጠለ ነው " ብለዋል።
ለአብነት የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት መቀመጫ በሆነችው አምቦ ከተማ የሀገረ ስብከቱ የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አባ ጴጥሮስ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ከሚገኘው ማረፊያቸው በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባም ትላንት ረቡዕ " በወቅታዊ ጉዳይ ወጣቶችን ታነሳሳላችሁ " ተብለው የቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የአካባቢ ወጣቶች የሆኑ ዘካርያስ ዓለማየሁ እና ጸጋ ደምሴ መታሰራቸውን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ፤ ዛሬ በወለቴ እና በዓለም ገና አካባቢዎች የጸጥታ አካላት በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ማዋከብ እና ድብደባ እያሳደሩ መሆኑን የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
በወለቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በመሳሪያ የታገዘ ድብደባ እየተፈፀመ መሆኑን የገለፁት የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙሃን እስከ አሁን ሁለት ሰዎች በፀጥታ ኃይል እንደተመቱ አስረድተዋል።
እስካሁን ግን ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የታየ ምላሽ የለም ሲሉም ወቅሰዋል።
ከዚህ ባለፈ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ወሊሶ ከተማ ምእመናን፣ ወጣቶች በፀጥታ ኃሎች እየታፈሱ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል።
በዚሁ ቀጠና ውጥረት ሊፈጠር የቻለው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸው አካላት ወደ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት " ወሊሶ ከተማ " ይመጣሉ መባሉን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

ከሰሞኑን ከጥቁር ልብስ ጋር በተገናኘ በአንዳንድ ተቋማት ጫናዎችን የማሳደር ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበር መግለፁ ይታወሳል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎችም ሰራተኞች ጥቁር ለብሰው እንዳይገቡ ከልክለዋል የተባሉ መስሪያ ቤቶች ትችት ተሰንዝሮባቸዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ስማቸው ከተነሳው ውስጥ አንዱ " አዋሽ ባንክ " ከጉዳዩ ጋር በተያየዘ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል ብሏል።
" ሠራተኞቼ ጥቁር እንዳይለብሱ አልከለከልኩም " ሲል ባንኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በፎቶ አስደግፎ መልዕክት ልኳል።
ባንኩ " በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል " ያለ ሲሆን ማንኛውንም ቀለም የሆኑ ነገር ግን #የባንክ_ሠራተኛ_ፕሮቶኮል የጠበቁ አለባበሶችን ሠራተኞቼ ለብሰው እየሰሩ ነው ሲል ገልጿል።

#Kenya
የኬንያ ፖሊስ 41 ኢትዮጵያውያንን ናይሮቢ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።
ግለሰቦቹ ወደ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች አገራት ለመዘዋወር በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ቀናት ያህል ሲጠባበቁ ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም መያዛቸውን ገልጿል።
ኢትዮጵያውያኑን በሕገ ወጥ መንገድ ሊያዘዋውሩ ነበሩ የተባሉ ሁለት አዘዋዋሪዎችም በዚሁ አጋጣሚ የተያዙ ሲሆን አንደኛው #ኢትዮጵያዊ መሆኑም ፖሊስ አሳውቋል።
ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው እነዚህ የሕገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች በርካታ ዝውውሮች ጀርባ እንዳሉበት ተገልጿል።
ኢትዮጵያውያኑ በዚህ ሳምንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ወደ ኬንያ እንዴት እንደገቡ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት በእስር እንዲቆዩ መታዘዙን #ቢቢሲ ዘግቧል።

iCog-ACC ሕፃናትን ገና በለጋ ዕድሜያቸው መሠረታዊ የኮምፒዩተር እና የኮዲንግ ሥልጠናዎችን በመስጠት ለወደፊት ለሚጠብቃቸዋል ዲጂታል ዓለም የሚያዘጋጃቸው ሲሆን ይህ እድል ልጆች ጠቃሚ የኮዲንግ ክህሎቶችን እንዲማሩና የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ያስችላል።
ስልጠናው ከቤት በኢንተርኔት (ኦንላይን) ወይም በአካል የሚሰጥ ሲሆን ክፍያው፦
- በኦንላይን ለሚወስዱ 1850 ብር
- በአካል ለሚወስዱ ደግሞ 2200 ብር ብቻ ነው።
ስልጠናው የሚካሄደው ለ3 ወር ቅዳሜ ቅዳሜ በቀን ለ3/2 ሰዓታት ነው።
ልጆችዎ በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ወላጆች በስልክ ቁጥራችን +251904262728 በመደወል ወይም ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመንካት የምዝገባ ቅፁን በመሙላት መመዝገብ ትችላላችሁ።
https://icogacc.com/register

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ " በአየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን " የተከሰተ አዲስ ነገር አረጋግጫለሁ ሲል መግለጫ ሰጥቷል።
ፖሊስ በመግለጫው ፤ " ዛሬ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ወደ አየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ' አዲስ አስተዳዳሪዎች ' እየመጡ ነው በሚል የተሳሳተ መረጃ የቤተ ክርስቲያኗን ደወል በማሰማት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲወጣ ተደርጓል " ብሏል።
ፖሊስ መረጃው እንደደረሰው ከፌዴራል ፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በቦታው መድረሱንና የቤተ ክርስቲያኗ ደወል ከመደወሉ በስተቀር የተፈጠረ አዲስ ነገር እንደሌለ ማረጋገጡን ገልጿል።
አካባቢውን እና ህብረተሰቡን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አሳውቋቃ።
በተሳሳተ መረጃ መጠነ ሰፊ ጉዳቶችን ሊያሥከትሉ የሚችሉ ዱላን ጨምሮ በርካታ ድምፅ አልባ መሳሪዎች ወደ ቦታው ይዞ በመምጣት ከፍተኛ ብጥብጥ ለማስነሳት ሙከራ የተደረገ ቢሆንም " የፀጥታ ሃይሉ በሆደ ሰፊነት " አልፎታል ብሏል።
በሌላ በኩል ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሰጠው መግለጫ በዛሬው እለትም በክ/ከተማው ወረዳ 05 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ምንም አይነት አዲስ ጳጳስ ባልተሾመበት ፤ " አዲስ ጳጳስ ተሹሞ እየመጣ ነው " በሚል የተሳሳተ መረጃ ደውል በመደወል የተሰባሰቡ ሀይሎች ግጭትና ሁከት የመፍጠር እንቅስቃሴዎች አድርገዋል ብሏል።
በቦታው ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ የፀጥታና አስተዳደር አካላት ችግሩን የማረጋጋትና ሠላማዊ በሆነ መንገድ የመፍታት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብሏል።
በተመሳሳይ በወረዳ 02 እና 03 የተደረጉ ብጥብጥና ሁከቶች በሠላማዊ መንገድ ችግሩን መፍታት ተችሏል ብሏል በመግለጫው።

#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ የፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገሙን ገልጿል። አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለኝ ብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ " በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት…
#Update
ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ " ትላንት ምሽት የመንግስት የጋራ ግብረኃይል የሰጠውን የ " ሰልፍ ክልከላ መግለጫ " እንደማይቀበለው አስገንዝቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስ የትላንቱ የመንግስት መግለጫ " መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል።
(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)