TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ በመመስረት ሂደት ላይ መሆኗን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ ከህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በሰጠችው መግለጫ ነው። ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ጥያቄ የቀርበ ሲሆን ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግ ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅርቡ ታውቋል። ክሱ / እግዱ የቀረበው በልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ…
" ቤተ ክርስቲያኗ ቡድኑ ለጊዜው በአመልካች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ንብረቶች ፣ቅጥር፣ቅርስና ዐብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳይደርስ እግድ እንዲሰጥ ነው የጠየቀችው " - ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የክስ ሂደት መጀመሯ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያኗ አውግዛ የለየቻቸው ፣ኤጲስ ቆጶሳትን የሾሙት የቀድሞ ሥስት ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ሹመቱን የተቀበሉ አካላት ወደ አብያተ ክርስቲያናት ከመግባት እንዲታገዱ ያቀረበችው ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት ነው።

የቤተክርስቲያኗ የጠበቆች ቡድን አባላት ዛሬ ብይን ለመስማት ቢቀርቡም እገዳ እንዲጣልበት ጥያቄ የቀረበበት ቡድን ጠበቃ መሆኔ አይቀርም ብለው በችሎቱ የቀረቡት ግለሰብ እግድ ከተጠየቀባቸው ወገኖች ሕጋዊ የጥብቅና ውክልና ይዘው የካቲት 3 ቀን 2015 ዓም ለክርክር ይቅረቡ ሲል ፍርድ ቤት መቅጠሩን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ከቤተክርስቲያኗ ጠበቆች አንዱ የሆኑትን አቶ አንዷለም በእውቀቱ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

አቶ አንዷለም ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቡድኑ ለጊዜው በአመልካች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ንብረቶች ፣ቅጥር፣ቅርስና ዐብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳይደርስ እግድ እንዲሰጥ ነው የጠየቀችው ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን በማስመልከት ያወጀው ጾምና ጸሎት ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ያበቃል።

ቅዱስ ሲኖዶስ " ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ " ሲል ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ምዕመኑን ይህንኑ ተግባራዊ ሲያደርግ ነበር።

ቤተክርስቲያኗ ፤ " ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው " ማለቷ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በጸሎትና በምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰልፍ ይደረጋል ያለው በየካቲት 5/2015 ዓ.ም ሲሆን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ፤ ቤተክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንዲሁም እየተፈፀመ ያለው ህገወጥ ድርጊት ለዓለም ህዝብ የሚገለፅበት እንደሆነ ማስረዳቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገሙን ገልጿል።

አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለኝ ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ " በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ " ብሏል።

ግብረሃይሉ ሰልፎቹ በሃይማኖቱ ሽፋን የሚደረጉ እና ሕገወጥ ሰልፎች ናቸው ያለ ሲሆን " በሚመለከተው አካል የተፈቀደ ሰልፍ የሌለ መሆኑ ታውቆ ኅብረተስቡ ከዚህ ሕገ ወጥ ሰልፍና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት ራሱን ይጠብቅ " ብሏል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ " ከዚህ ውጭ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሎ በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ኃይል እንዲሁም ሰልፎቹን ለማስተባበር እና ለመሳተፍ የሚሞክሩ አካላት ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ ናቸው " ያለ ሲሆን " ለዜጎችና ለሀገር ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ሲባል ሕጋዊእርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

ግብረ ኃይሉ " በየክልሉ የምትገኙ የፀጥታ ኃይሎችም በአካባቢያችሁ ሕገወጥ ሰልፎች እንዳይካሄዱ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያኗ፣ለእምነቱ አባቶች እና ተከታዮች በአጠቃላይ ለሕዝቡ ተገቢውን የደኅንነት ጥበቃ እንድታደርጉ " ሲል አዟል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 11,000 ደረሰ። ሰኞ በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11,000 መድረሱን አልጀዚራ ዘግቧል። ከ11 ሺህ ሟቾች መካከል በትንሹ ከቱርክ 8,574 ሲሆኑ ከሶሪያ ደግሞ 2,530 ሆነው መመዝገባቸው ተመላክቷል። ሰዎችን ከህንፃ ፍርስራሾች ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ…
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 11,600 በላይ ሆኗል።

አስከፊ በሆነው የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክ ከ9 ሺህ በላይ ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን ዛሬ ሩቡዕ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶባቸዋል የተባሉትን ስፍራዎች በአካል ሄደው ተመልክተዋል።

ኤርጎዳን እና መንግስታቸውን ለእንዲህ መሰል አስከፊ አደጋ ቅድመ ዝግጅት አላደረገም ፤ ከአደጋውም በኃላ የታየው ምላሽ ደካማ ነው በሚል በተቃዋሚ ኃይሎች እንዲሁም በሌሎች ትችት እየተሰነዘረባቸው ይገኛል።

አንዳንድ የተቃዋሚ አመራሮች ለዚህ ሁሉ ከፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ውጭ ማንም ተጠያቂ አይደለም እስከማለት ደርሰዋል።

ነገር ግን ፕሬዜዳንቱ ይህንን ትችት የማይቀበሉት ሲሆን " ይህ ጊዜ የአንድነት እና የአብሮነት ጊዜ መሆን አለበት " ብለዋል።

በዚህ ጊዜ ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ አሉታዊ ዘመቻዎችን ለሚያደርጉ ሰዎች ቦታ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከተከሰተ በኃላ በመንግስት በኩል የተሰጠው የአደጋ ጊዜ ምላሽ ከተቃዋሚ ኃይሎች ባለፈ በርካቶችን እንዳስቆጣ የተነገረ ሲሆን ኤርዶጋን ከአደጋው በኃላ የመጀመሪያ ቀን ምላሽ ወቅት ችግሮች /መዘግየት እንደነበሩ አምነዋል፤ ነገር ግን መዘግየቱ በተበላሹ መንገዶች እና የአውሮፕላን ማረፊያዎች ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።

ሁለተኛው ቀን እና ዛሬ ችግሮች ታርመው ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር መሆኑን ተናግረዋል።

ኤርዶጋን የሀገሪቱ ዜጎች የባለስልጣናትን መልዕክት እንዲያዳምጡ ከዛ በዘለለ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ አሉታዊ መልዕክት የሚያሰራጩትን ችላ እንዲሉ ጥሪ አቅርበዋል፤ የሀገሪቱ መንግስት መስራት ያለበትን ስራ እየሰራ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ቴሌብርን ጨምሮ ከተለያዩ አካውንቶች ገንዘብ ወደ አፖሎ ማስተላለፍና በዚያም ማስቀመጥ በመቻሉ አፖሎን ብዙዎች እየመረጡት ነው። እናንተስ?
የአፖሎን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/apollodigitalproduct
#ሃይላንድ

በኢትዮጵያ  የታሽገ ውሃ  ፈርቀዳጅ እና ታዋቂ የሆነው  ሃይላንድ በአውሮፓ ስታንዳርድ ማሽኖች ታግዞ ሲጠጡት ቀለል ብሎ አንጀት እንዲያርስ ተደርጎ  ለየት ባለ አስተሻሽግ እና በነጭ ክዳን በ0.3ሊ፣ በ0.6ሊ፣ በ 1ሊ እና በ2ሊ ለገበያ ቀርቧል።

ለማከፋፈል ወይም ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0911233552 ይደውሉ  " ሃይላንድ የህይወት ስንቅ "

የሃይላንድ ውሃ ትክክለኛ ማህበራዊ ትስስር ገጾችን ይከተሉ፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100087976315526

https://www.tiktok.com/@highlandwaterethiopia?_t=8ZVmAJPFkfd&_r=1

https://instagram.com/highlandwater_?igshid=OGQ2MjdiOTE=

https://www.linkedin.com/company/highland-%E1%8B%89%E1%88%83/

#ማስታወሻ፡ አስኩ ኃ/የተ/የግ/ማ ሃይላንድ የታሸገ ውኃን ከተረከበ በኋላ የንግድ ምልክቱን በ2013 በባለቤትነት አስመዝግቧል።
" ለመውጫ ፈተና ራሳችሁን አዘጋጁ " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ለዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳሰበ።

የዩኒቨርስቲ መውጫ  ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች  ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የመውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሰሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርስቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ዶክተር ሳሙኤል በአሁኑ ወቅትም የፈተና ንድፈ ማሳያና / Blueprint / የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው  ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በውይይቱም ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል። በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ…
#ማስታወሻ

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያመጡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን የማስተካከያ ጊዜ ዛሬ የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ያበቃል።                        

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡና በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየት/ ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እንዲያስተካክሉ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ ያበቃል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውና እና ደጋፊ ሰነዶቻቸውን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ ይችላሉ 👇

https://student.ethernet.edu.et

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 16,000 አልፏል።

በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ16,000 በላይ መድረሱ ተነግሯል።

ባለስልጣናት እና የህክምና ሰዎች እንዳሉት ከሆነ ከቱርክ በኩል 12,873 ሰዎች ሲሞቱ ከሶሪያ በኩል 3,162 ሰዎች ሞተዋል።

ሰዎችን ከህንፃዎች ፍርስራሾች ውስጥ የመፈለጉ ሂደት እና የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።

ፎቶ፦ AFP

@tikvahethiopia