TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

የሀገራችን እና የመላው አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ታስተናግዳለች።

በቅርቡ የሚካሄደው 36ኛው የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛው የህብረቱ የስራ አስፈፃሚዎች ጉባኤ ሲሆን በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ተሰምቷል።

የዘንድሮው የህብረቱ ስብሰባ የንግድ ግንኙነት እና ኢኮሮሚያዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

ይኸው ጉባኤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ ከተደረገ በኃላ በአዲስ አበባ የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ በቱሪዝሙ ዘርፍ እየታየ የመጣውን ከፍተኛ መነቃቃት ያሳድገዋል ተብሎ ይታመናል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በመልካም መስተንግዶ ለመቀበል ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን እያሳውቁ ይገኛሉ።

Photo Credit ፦ Abel Gashaw

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መገናኘታቸው ተሰማ።

የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ " ሐላላ ኬላ " እንደሆነ ተነግሯል።

NB. ሐላል ኬላ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ነው።

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ #ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አድርገዋል ተብሏል።

በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት መገምገሙና በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ መቀመጡን ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መገናኘታቸው ተሰማ። የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ " ሐላላ ኬላ " እንደሆነ ተነግሯል። NB. ሐላል ኬላ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ነው። ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ #ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት…
#Update

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፦

- ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች እንዲጨምሩ፣

- የባንክ አገልግሎት እንዲፋጠን

- ሌሎች እርስ በርስ መተማመንን የሚያጎለብቱ እና የዜጎችን አኗኗር ቀላል የሚያደርጉ አገልግሎቶች እንዲፋጠኑ መመሪያ ማስተላለፋቸውን የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያውን ያስተላለፉት ፤ ከፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተው ከመከሩ በኃላ መሆኑ ተመላክቷል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ በመመስረት ሂደት ላይ መሆኗን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ ከህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በሰጠችው መግለጫ ነው።

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ጥያቄ የቀርበ ሲሆን ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግ ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅርቡ ታውቋል።

ክሱ / እግዱ የቀረበው በልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ምድብ ችሎት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ክስ የቀረበባቸው ተጠሪዎች በቀድሞ ስማቸው 1ኛ. አባ ሳዊሮስ ፣ 2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ ፣ 3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ ፤ እንዲሁም ኤጲስቆጶሳት ተብለው ተሹመዋል ተብሎ መግለጫ የተሰጠባቸው 25 ግለሰቦች ያሉበት መሆኑን ቤተክርስቲያኗ ገልጻለች።

አንድ ግለሰብ ተፀፅተው ስለተመለሱ ክሱ እንደማያካትታቸው ቤተክርስቲያን ጠቁማለች።

በተጨማሪ ፤ ጠበቃ ኃይለሚካኤል ከፈሌ ተጠሪ ሆነው የተካተቱ መሆኑ ተገልጿል።

ሌሎች ፦
- የፌዴራል ፖሊስ
- የኦሮሚያ ክልል መንግስት
- የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ የክሱ / የአቤቱታው አካል መሆናቸውን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

ክስ የቀረበው ለምንድነው ? ቤተክርስቲያኗ ክስ ያቀረበችው ህጋዊ ሰውነቷን የጣሰ ህገወጥ ድርጊት ስለተፈፀመ፣ በአገልጋዮች አባቶች ፣ ካህናት እና ምዕመናን ላይ በደል ስለተፈፀመ መሆኑ ገልጻለች።

ቤተክርስቲያኗ ህገወጥ ብላ በይፋ የፈረጀችው ቡድን ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር እንዳይደርስ፣ ንብረት እንዳያንቀሳቅስ፣ የቤተክርስቲያኗ ጥቅምና መብት እንዲከበር ይህ ክስ በዝርዝር እስኪታይ የዕግድ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ ለፍርድ ቤት ጠይቃለች።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ በመመስረት ሂደት ላይ መሆኗን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ ከህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በሰጠችው መግለጫ ነው። ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ጥያቄ የቀርበ ሲሆን ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግ ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅርቡ ታውቋል። ክሱ / እግዱ የቀረበው በልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ…
#Update

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ዛሬ ምሽት 3:45 አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሚገኘው መንበረ ጵጵስናቸው ተወስደው ታስረው እንደነበር ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት ማምሻውን ነበር ከአዲስ አበባ ወደ ሀገረ ስብከታቸው መድረሳቸው የተጠቆመው።

ዘግየት ብለው የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ባወጡት መረጃ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በአሰላ #መቆየት_አይችሉም ተብለው በዚህ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉን አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል፤ " በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስናና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት በምእመናን ላይ ስጋት ተፈጥሯል ። " ሲሉ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ለሚመለከተው የዞን ፀጥታ አካል ለማሳወቅና ጥበቃ እንዲያደርጉ ብንደውልም ፣ መልእክት ብንጽፍም ሊመልሱልን አልቻሉም ብለዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኦሮምያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ጥበቃና ከለላን በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስቀድሞ ደብዳቤ ቢጻፍም ምንም አይነት የቃልም ሆነ የተግባር መልስ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ " መንግሥት በሕገ ወጡ ቡድን የሚደረገውን ድርጊት ማስቆም ካልቻለ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል" ብለዋል። ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁም መልእክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።

ቤተክርስቲያኗ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገለፃለች።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በተመለከተ ፤ " እየሞተ ያለው ሕዝብ ነው ቅጠል አይደለም እየተበጠሰ የሚወድቀው ፤ #ይሄ_ፖለቲካ ነው። የፌደራል መንግሥት በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል። " ብለዋል።

በሻሸመኔ ምንድነው የሆነ ?

ተ/ሚ/ማ የተባለው የቤተክርስቲያኗ ሚዲያ " በዛሬው ዕለት ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ሻሸመኔ ይመጣል መባሉን ተከትሎ ጠዋት ሁለት (2:00) ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል " ሲል ገልጿል።

" ጥሪው ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ይጀምል ፤ በዚህ ጊዜ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሔዱ ምእመናን የቤተክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆመው ነበር።

በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ ከፍያል ፤ እስካሁን ድረስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፤ በውል ያልታወቀ ሰውም በጥይት ተመቷል " ሲል የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል።

በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ " ትናንትና ሌሊት ሊቀ ጳጳሷን አስሮ ከከተማ ያባረረው ኃይል   በአርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻ አሰላ ኦርቶዶክሳውያንን እያሠረ  ይገኛል " ብላለች።

በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተዝቶባቸዋል ብላለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ያሉት ሁኔታዎች እየከረሩ መጥተው ለሰው ህይወት #መጥፋት ምክንያት እስከመሆን የደረሱ ቢሆንም መንግስት እስካሁን ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለም።

ቤተክርስቲያን በበኩሏ ለዚህ ሁሉ መሆን ህገወጥ ሲመት አከናውነዋል ፤ ተቀብለዋል ባለቻቸው ግለሰቦች እና የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ ነች።

@tikvahethiopia
#Mettu

1.3 ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረግበታል የተባለው የመቱ-ጎሬ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።

በ166 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በሶስት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።

ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች በተለያዩ መስኮች የስራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር የተገለፀ ሲሆን የመንግስት አካላት እና ሕብረተሰቡ ለስራው ስኬታማነት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#GetachewReda

ትላንት ለመጀመሪያ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ከመከሩ በኃላ አቶ ጌታቸው ረዳ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን (etv) ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ በጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን የማህበራዊ ስብራትን ከማከም ጋር በተያየ ይህን ብለዋል ፦

" በመጀመሪያ ደረጃ ጎረቤቶቻችንን መምረጥ አንችልም፤ ከማንም ሰው ጋር ያለን ግንኙነት ፈለንግንም አልፈለግንም አብረን መኖራችን ስለማይቀር አብረን እስከኖርን ድረስ መከባበር መኖር መቻል አለበት።

አንዱ ፍላጎቱን ሌላው ላይ ጭኖ የሚያረጋግጠው መብት አንዱ አንዱ ላይ ፍላጎቱን ጭኖ የሚያስከብረው ጥቅም ለጊዜው ሊመስል ይችላል ግን ዘለቄታ ሊኖረው እንደማይችል ሊታወቅ ይገባል።

የተፈጠረው የማህበራዊ ስብራት (በጦርነት ምክንያት ማለታቸው ነው) እያስታወሱ እሱን ቁስል እያከኩ መኖር ከባድ ነው የሚሆነው መጠየቅ ባለብን መጠየቅ አለብን ፤ መጠየቅ ያለበት ሰው መጠየቅ መቻል አለበት ፤ እኔ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ያጠፋሁት ጥፋት ካለ ልጠየቅ እችላለሁ።

ዞሮ ዞሮ ማህበረሰቦቻችን በሰላም ወጥተው የሚገቡበትን ሁኔታ መፍጠር፡ አለ የሚባለውን ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት መቻልን መማር አለብን ።

ስብራቱን ለመጠገን ሙሉ ቁርጠኝነት ይዘን ካልተንቀሳቀስን በስተቀር ቁስል እያከክ ቁስል መረሳት የለበትም ግን ቁስሉን እያከኩ መኖር አይደለም መፍትሄ የሚሆነው ይሄ ነገር እንዳይደገም ያሉብን ልዩነቶች ምንድናቸው ፣ እዚህ ያደረሱን ነገሮች ምንድናቸው የሚለውን በደንብ ተንትኖ ይሄ ነገር የማይደገምበት ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ነው። "

@tikvahethiopia