" ኮርፖሬሽኑን ለእዳ የዳረጉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የሕግ እርምጃ ይወሰድባቸው " - የሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በቀጣዮቹ 3 ወራት #የአዳማ_አዋሽ መንገድ ጥገና የውል ስምምነት ላይ አስቸኳይ እልባት እንዲሰጥ አሳሰበ።
ቋሚ ኮሚቴው " ያልተገባ ውል ባለው " ስምምነት ኮርፖሬሽኑን ለእዳ የዳረጉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የሕግ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል።
ቋሚ ኮሚቴው ይህ የጠየቀው የኮርፖሬሽኑን የ2013 እና 2014 ዓ.ም የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ በተወያየበት ወቅት ነው።
ኮርፖሬሽኑ ከደንበኞች በውል የተረከባቸውን ፕሮጀክቶች ውል በተገባበት ጊዜ ገደብ የማይፈጸሙ መሆናቸው ተመላክቷል።
በአዋጅ ወደ ሌሎች የመንግስት ተቋማት እንዲተላለፉ የተወሰኑ ሃብቶች ግምትና ዕዳ ያልተገመተና በውሳኔው መሰረት ርክክብ እንዳልተደረገ ተገልጿል።
ኮርፖሬሽኑ ኮንትራት ወስዶ ለሰራቸው ስራዎቹ በአጠቃላይ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ አለመሰብሰቡም ተጠቁሟል።
በኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ግንባታቸው የሚጠናቀቅ መሆኑ ቢቀመጥም ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው መሰረት ያልተከናወኑ ናቸው ተብሏል።
ከግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የአዳማ አዋሽ መንገድ ጥገና እና መንገዱን ለማስተዳደር ስምምነት ገብቶ እየሰራ ቢሆንም በውሉ መሰረት ሥራውን ባለማከናወኑ ለበርካታ ዕዳ መጋለጡ ነው የተነገረው።
ከዚህም አልፎ ኮርፖሬሽኑ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ከአሰሪ ተቋም ክፍያ መሰብሰብ አልቻለም ተብሏል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/ENA-01-31
Credit : ENA
@tikvahethiopia

በመቆጠብ ከፍተኛ ወለድ ያግኙ!
አፖሎ የ9% ወለድ ተጠቃሚ የሚሆኑበት የዲጂታል መተግበሪያ ነው። የቁጠባ ሂሳብዎን አሁኑኑ ይክፈቱ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollo #OurNewProduct #highinterestrate #9% #exciting, #interestrate #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #thechoiceforall

#Ethiopia
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል 2ተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይም ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል።
ለ3ተኛ ጊዜ በተዘጋጀው ሽልማት 46 ሰዎች የህዝብ የተሰጣቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 17 የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተብለው ተለይተዋል።
ከእነዚህም መካከል ከተለያዩ ተቋማት በተወጣጡ 5 ዳኞች 3ቱ የ2023 ምርጥ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተብለው ተመርጠዋል።
በዚህም ፦
1ኛ. ወ/ሮ ብርሀነወርቅ ዘውዴ
ከ30 ዓመት በላይ በሰብአዊ መብቶች ትግል ላይ ቆይተዋል፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ አባልና የኢሰመጉ መደበኛ አባልም ነበሩ።
ለመምህራን መብት መታገል እጅግ የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ ጠንካራ ሴት የመብት ተሟጋች ናቸው።
2ኛ. አቶ መለሰ ሸሽጌ
በደቡብ ጎንደር ጋይንት የተወለዱ ሲሆን ለሴቶችና ሕጻናት መብት ተግተተው ሲሰሩ ቆይተዋል፤ ከ50 በላይ ወጣት ሴቶችን ካልተፈለገና ያለእድሜ ጋብቻ ታድገዋል።
3ኛ. ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ
የብሔር እና የሀይማኖት ግጭቶችን ለማስወገድ ሰርተዋል፤ ለ5 ዓመታት የፓርላማ አባል ሆነው አገልግለዋል፤ በሁሉም የስራ ጊዜያቸው ለሰብዓዊ መብት መከበር ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ለ565 የፖለቲካ እስረኞች በነጻ ጥብቅና ቆመዋል፤ 165ቱን ደግሞ ነጻ አውጥተዋል። በተጨማሪም በነጻ በዓመት ከ 5 -10 ለሆኑ ሴቶች እና ህጻናት ነጻ ጥብቅና ይቆማሉ።

#ቻይና
በኦሮሚያ ክልል፤ ሰሜን ሸዋ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አንድ የቻይና ዜጋ መገደሉን ተከትሎ እዚህ አዲስ አበባ የሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ ለቻይና ዜጎች የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።
ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ ፤ ከአዲስ አበባ በሰሜን በኩል 160 ኪ/ሜ ርቀት ላይ " ገብረ ጉራቻ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የነበሩ 9 ቻይናውያን ተኩስ ተክፍቶባቸዋል።
በዚም ጥቃት አንዱ ቻይናዊ ተገድሏል። በሌሎቹ ላይ ጉዳት ስለመድረስ አለመድረሱ እንዲሁም ስለታጣቂዎቹ ማንነት በኤምባሲው በኩል የተገለፀ ነገረ የለም።
የቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ዜጎቹ ለአደጋ ከሚያጋልጡ ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል።
NB. ጉዳዩን በተመለከት ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።
ምንጭ፦ በአዲስ አበባ የቻይና ኤምባሲን ዋቢ አድርገው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ / የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ናቸው የዘገቡት።

#ሶማሊያ
ዛሬ ሶማሊያ ውስጥ ከሶማሊያ ጋር ጎረቤት የሆኑ ሀገራት መሪዎች በ " አልሸባብ " ጉዳይ ስብሰባ ያካሂዳሉ።
እንደ ሶማሊያ መንግስት መረጃ በስብሰባው የሶማሊያ፣ የኬንያ፣ የኢትዮጵያ፣ እና ጅቡቲ መሪዎች ይካፈላሉ።
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት የሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ይመሩታል በተባለው ስብሰባ የሀገራችን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም እንደሚካፈሉ በሶማሊያ መንግስት በኩል ተገልጿል።
ለዛሬው ስብሰባ ዝግጅት ለማድረግ የሶማሊያ፣ የኢትዮጵያ፣ የኬንያ ፣ ጅቡቲ መከላከያ አመራሮች ሞቃዲሾ ይገኛሉ።
ሙቃዲሾ ለስብሰባው ሰላም እና ደህንነት ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ጥበቃ እያደረገች ትገኛለች ተብሏል።
ፎቶ ፦ ፋይል

የ866,000 ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?
ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች አማራጮች እንዳላቸው አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በሰጡት ቃል ፤ ለተማሪዎች የሚቀርበው አንዱ አማራጭ በመንግስት ውሳኔ በሚወሰን ነጥብ " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪ " መሆን ነው ብለዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል፤ " አንድ ዕድል እንሞክርና የተወሰኑ ተማሪዎችን በመንግስት / በመንግስት ተቋማት ዩኒቨርሲቲ እንደገቡ ግን ገና ፍሬሽ ማን እንዳልሆኑ እንድቀበል፤ ሌለው ደግሞ በራሳቸው ከፍለው በግል ተቋማት እንደዚሁ remedial ተከታትለው ካሳኩ ወደ ፍሬሽ ማን የሚገቡበትን እድል እንፍጠርላቸው፤ ሊገቡ ይችሉ የነበሩ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት 50% ያላሟሉትን እንዳናጣቸው እንደዜጋ እሱን እድል መፍጠር ጥሩ ነው፤ ይሄ ለአንድ ጊዜ የሚሆን የአንድ ጊዜ ውሳኔ ብቻ ሆኖ ማለት ነው። " ሲሉ ተናግረዋል።
ትግበራውን በተመለከተም ተማሪዎች የፍሬሽ ማን ዕጩ ተማሪዎች እንደሚሆኑ ነው ያስረዱት።
ከ50% በታች ያመጡ ተማሪዎች በግል በመፈተን ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችል ውጤት ማምጣት / በፍላጎት እና ምርጫ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መውሰድ መሆኑ ተመላክቷል።
Credit : ፋና ቴሌቪዥን

TIKVAH-ETHIOPIA
የ866,000 ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ? ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች አማራጮች እንዳላቸው አሳውቋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በሰጡት ቃል ፤ ለተማሪዎች የሚቀርበው አንዱ አማራጭ በመንግስት ውሳኔ በሚወሰን ነጥብ " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪ " መሆን ነው ብለዋል። ዶ/ር ሳሙኤል፤ " አንድ…
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር፤ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ50% በታች ያመጡና በዩቨርሲቱ የቅበላ አቅም " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ ከ10 እስከ 15 ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስት በሰጡት ቃለ ምልልስ ፤ " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ በጥቂት ቀናት ለማሳወቅ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " 10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሄንን ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን። በ10 ቀን ውስጥ የትኞቹ ተማሪዎች ዕጩ በመንግስት ተቋማት ሄደው እንደ ስኮላርሺፕ ተማሪ ዶርም ይዘው ምግብ ቀርቦላቸው በቅተው ለሚቀጥለው ዓመት ፌሬሽ ማን የመሆን ዕድል ይሰጣቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ በሌሎች አማራጮች ይማራሉ የሚለውን ጉዳይ ቢገፋ በ10 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን በጣም ቢገፋ በ15 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን " ብለዋል።
" ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ተደርጎ ራሳቸውን የሚያበቃቸውን ትምህርት ተከታትለው በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በመሆን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ነው የትምህርት ሚኒስቴር አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የታወቀው።

#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
@berhanbanksc

" ዕድሜ አጭበርብረዋል " የተባሉት አትሌቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።
ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም ከ #ሃያ (20) ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።
በዚሁ ውድድር ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መነጋገሪያ ጉዳዮች ተፈጥረዋል፤ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወሩ የነበሩ ፎቶዎችም በርካቶችን " እንዴት እኚህን የሚያክሉ አትሌቶች ከ20 ዓመት በታች ይወዳደራሉ " በሚል አስገርመዋል።
ይህን በተመለከተ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት ፤ ከእድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ ከውድድር ውጭ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።
ፌዴሬሽኑ ቁጥራቸው ከ80 የሚልቁ አትሌቶችም ስማቸውን ይፋ አድርጓል።
ተግባሩን በፈፀሙ ቡድኖች አሰልጣኞች ላይም እርምጃ እንዲወሰድ ለየክልላቸው፣ ከተማ አስተዳደራቸው፣ ክለባቸውና ተቋሞቻቸው ፌዴሬሽኑ ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ እንደሚልክ አሳውቋል።
ማጣራቱ እስከ ውድድሩ ማብቂያ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ የገለፀው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዚህ ሲያልፍ ከሳምንትም ሆነ ከወር በኋላም ቢሆን ተጨማሪ መረጃ ከተገኘ አትሌቱ የተሸለመው ሜዳልያም ሆነ የገንዘብ ሽልማት ተመላሽ እንደሚደረግ በጥብቅ አሳስቧል።
የእድሜ ተገቢነት ችግር ውስጥ የተገኙ አትሌቶችን ዝርዝር ከሥር ከላይ ተያይዟል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ መላው ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት በደሉን ለዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚገልጽ አስታወቀ።
ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ያሳወቀው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።
" መንግሥታችን በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልና፣ በሕግ የተሰጣትን መብትና ጥቅም ያስከብር " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " ሕገወጡን ድርጊት ተገቢውን እርምት በመስጠት ኃላፊነቱን ይወጣ " ሲል አሳስቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን " ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ጭምር የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ በደላችንን ለዓለም ሕዝብ ችግሩ ተፈቶ የቤተ ክርስቲያኒቱ መብት እስኪረጋገጥ ድረስ ያለማቋረጥ እስከ ሕይወት መስዋዕትን ድረስ በመክፈል የምናሳውቅ ይሆናል " ብሏል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫ ሰሞኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ የተናገሩትንና በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨውን ንግግራቸውን በማንሳት እንዲታረም አሳስቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተይይዟል)