TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Afar

የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለሰላምና ግንባታ የመጠቀም ልምድ ደካማ በሆነበት ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ጉዳታቸው ትልቅ ነው።

በተለይ እነዚህ አደገኛ መረጃዎች በከተማም ሆነ ከተማ ወጣ ባሉ አከባቢዎች የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከፍ ያለ ነው።

ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከጥር 13 ጀምሮ ለ4 ቀናት በዲጂታል ሰላም ግንባታ እንዲሁም መሰረታዊ የሚዲያ ክህሎት ላይ ትኩረቱን መሰረት ያደረገው የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሂዷል።

በስልጠናው 20 ወጣቶች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ 4 ወረዳዎች (አሚባራ፣ አፋንቦ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ) ለተወጣጡ ሰልጣኞች የዲጂታል ሚዲያ ክህሎትን ስለማሳደግ፣ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ስለመስራትና ከሀሰተኛና ጥላቻ ንግግሮችን ራስንና ማኅበረሰብን ስለመከላከል በዚህም ምክንያት የሚደርስን ጉዳት መቀነስ በሚቻልበት አግባብ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።

በቀጣይም ወጣቶቹ በወሰዱት ሥልጠና መሰረት ወደ ማኅበረሰባቸው ተመልሰው ለሌሎች እኩዮቻቸው ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን እንዲሰጡ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በአከባቢያቸው አወንታዊ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ለማስቻል ታቅዷል።

በተለይ የመረጃ ተደራሽነቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለተገደበባቸው አከባቢዎች መሰል የአቻ ሥልጠናዎች ትርጉም ያለው ለውጥ ከማምጣቱም በዘለለ ወጣቱን አሳታፊ ያደረገ የመፍትሔ ሀሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ እድሉን በሰፊው ያመቻቻል።

ይህንን ስልጠና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ Mercy Corps Ethiopia ጋር በጋራ በመሆን ለሥልጠናው ከሚያስፈልገው የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ ጀምሮ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።

በቀጣይ በድሬደዋና በጅጅጋ ከተሞች መሰል ሥልጠናዎችን የሚሰጡ ይሆናል።

@tikvahethiopia
" በብሔራዊ ፈተናው ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንሸፍናለን " - አማራ ባንክ

በ2014 ዓም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንደሚሸፍን አማራ ባንክ አሳውቋል።

ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ ገልጸዋል።

ይህ ውሳኔ የባንኩ የማኀበረሰባዊ አገልግሎት አካል መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለአሚኮ ጠቁመዋል።

በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅናና ሽልማት ይሰጣቸዋል መባሉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#ግሬስ

በሀገራችን በአይነቱ የመጀመርያ የአረጋውያን እና ህመሙማን እንክብካቤ ማእከል  (Nursing Home) የሆነው ግሬስ የህሙማን እና አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል የህሙማንን ስቃይ እንዲሁም የአስታማሚዎችን እንግልት ለማቅለል አገልግሎት እየሰጠ ነድ።

በሙያው እውቀት እና ልምድ ባካበቱ ባለሞያዎች ፣ ንፅህናቸውን በጠበቁ የግል እና የጋራ ክፍሎች ፣ አዕምሮን በሚያድስ አርንጓዴ ስፍራ ፣ በቀን 24 ሰአት ከሳምንት እስከሳምንት በቋሚነት አገልግሎት እያቀረበ ነው።

" አላማችን ታካሚዎችን  የሚገባቸውን እንክብካቤ መስጠት አስታማሚዎችን ደግሞ ማሳረፍ  ነው "

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0967-03-42-42 / 0954-99-11-90.
አድራሻ - አያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው መንገድ ላይ በቀኝ በኩል በፍሬሽ ኮርነር ገባ ብሎ

ቴሌግራም ግሩፕ - https://t.iss.one/gracenursinghome
#ከቀረጥ_ነፃ

የገንዘብ ሚኒስቴር በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በግብርና ፣ በሎጀስቲክስ፣ በኮንስትራክሽን፣ የባለኮከብ ሆቴሎች ኢንቨስትምንትን ጨምሮ ለልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መፍቀዱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው አዲስ መመሪያ " ለልማት ፕሮጀክቶች ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ " የሚል ስያሜ የተሰጠው ነው ተብሏል።

ይህም የደረቅ፣ የፍሳሽ ወይም ማቀዝቀዣ የተገጠመለት የጭነት መኪናን ወይም ለተለየ አገልግሎት ተብለው የሚዘጋጁ አውቶብስን፣ ሚኒባስን፣ ሚዲባስን፣ ሽፍን የዕቃ ማጓጓዣ ተሽከርካሪንና የሞተር ብስክሌቶችን ይጨምራል፡፡

መመሪያው የማበረታቻው ተጠቃሚ የኢንቨስትመንት መስኮች ብሎ ከለያቸው ውስጥ ፦

- በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣
- የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት፣
- በግብርና
- በሎጀስቲክስ
- በኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጭነት፣
- ባለ ኮከብ ሆቴሎች (የሪዞርት ሆቴሎችን ጨምሮ)
- በባቡር መሠረተ ልማት
- ሞቴሎች
- ሬስቶራንቶችና ሎጆች የተሰማሩ ባላሀብቶች ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም ፦

- በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ልማት፣
- በአስጎብኝ ሥራ
- በኤክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያና ማሠራጫ፣
- በትምህርትና ሥልጠና፣
- የጤና አገልግሎት የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ባለሀብቶች ተሽርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ይፈቅዳል።

የአርክቴክቸርና ኢንጂነሪንግ ሥራዎች የቴክኒክ ምርመራና ትንተና አገልግሎትና ንግድ የሥራ መስኮች አዳዲስ ፕሮጀክቶችን የሚያቋቋሙ ወይም ነባር ደርጅታቸውን የሚያስፋፉ ባለሀብቶችም የዕድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-01-29

Credit : Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
በመቆጠብ ከፍተኛ ወለድ ያግኙ!
አፖሎ የ9% ወለድ ተጠቃሚ የሚሆኑበት የዲጂታል መተግበሪያ ነው። የቁጠባ ሂሳብዎን አሁኑኑ ይክፈቱ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollo #OurNewProduct #highinterestrate #9% #exciting, #interestrate #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all  #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #thechoiceforall
#ETHIOPIA #GERD

" አሁን ላይ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የኮንቮይ ጉዞ ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ ችሏል " - ኢ/ር በላቸው ካሳ

የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ቀጠና በተገኘው ሰላም የግድቡ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተገልጿል።

የግድቡ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጂነር በላቸው ካሳ ፤ " በቀጠናው የተገኘው አስተማማኝ ሰላም የግድቡን የግንባታ ሂደት #እያፋጠነው ይገኛል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" የፀጥታው ጉዳይ ለግድቡ ግንባታ መሠረታዊ ፍላጎት መሆኑን በመገንዘብ #የሀገር_መከላከያ_ሰራዊት ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ተልዕኮውን በጀግንነት በመፈፀም በቀጠናው የከፈለው መስዋዕትነት የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት ያኮራ በታሪክ የሚኖር ነው  " ብለዋል።

ኢ/ር በላቸው፤ በቀጠናው በነበረው የሰላም ችግር ምክንያት ወደ ግድቡ የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች ከሁለትና ከሶስት ቀን በላይ በመቆም መስተጓጎል ይፈጥር እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ የኮንቮይ ጉዞ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ መቻሉን አስረድተዋል።

የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ ሌት ተቀን ሃያ አራት ሰዓት ያለ ዕረፍት የሚተጉ የግንባታዉ ሰራተኞች የአካባቢውን የሙቀት ሁኔታ ተቋቁመው ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን በደማቅ ሞራል እየተወጡ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

በስፍራው ከሚገኙ የሀገር መከላከያ አባላት የቀጠናውን ዘላቂ ሰላም በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ በማረጋገጥ ሰራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በሞራል እየተወጣ እነደሆነ ተናግረዋል።

ሰራዊቱ የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ ፀረሠላም የሆኑ ኃይሎችን ፍላጎት በማምከን የግድቡን የፍፃሜ ትንሳኤ ለማብሰር ደከመኝ ሳይል ሀገራዊ ተልዕኮዉን እየተወጣ ነው ብለዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ስነ ምግባር ስራ ክፍል የምርምር ስነ ምግባር ግምገማን የተቀላጠፈ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ያስችላል ያለድን ድረ-ገፅ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋቃ።

ድረ-ገፁ ተመራማሪው ስራዎቹን ለማመልከት እንዲሁም ገምጋሚው ዶክመንቶቹን አይቶ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷታ።

የሚሰሩ የምርምር ስነ ምግባር ስራዎችን በተመለከተ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው “NRERB Research Ethics Review Portal በመጠቀም በኦላይን : https://nrerb.ethernet.edu.et ላይ አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
በመቆጠብ ከፍተኛ ወለድ ያግኙ!

አፖሎ የ9% ወለድ ተጠቃሚ የሚሆኑበት የዲጂታል መተግበሪያ ነው። የቁጠባ ሂሳብዎን አሁኑኑ ይክፈቱ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollo #OurNewProduct #highinterestrate #9% #exciting, #interestrate #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #thechoiceforall
" ኮርፖሬሽኑን ለእዳ የዳረጉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የሕግ እርምጃ ይወሰድባቸው " - የሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በቀጣዮቹ 3 ወራት #የአዳማ_አዋሽ መንገድ ጥገና የውል ስምምነት ላይ አስቸኳይ እልባት እንዲሰጥ አሳሰበ።

ቋሚ ኮሚቴው " ያልተገባ ውል ባለው " ስምምነት ኮርፖሬሽኑን ለእዳ የዳረጉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የሕግ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል።

ቋሚ ኮሚቴው ይህ የጠየቀው የኮርፖሬሽኑን የ2013 እና 2014 ዓ.ም የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ በተወያየበት ወቅት ነው።

ኮርፖሬሽኑ ከደንበኞች በውል የተረከባቸውን ፕሮጀክቶች ውል በተገባበት ጊዜ ገደብ የማይፈጸሙ መሆናቸው ተመላክቷል።

በአዋጅ ወደ ሌሎች የመንግስት ተቋማት እንዲተላለፉ የተወሰኑ ሃብቶች ግምትና ዕዳ ያልተገመተና በውሳኔው መሰረት ርክክብ እንዳልተደረገ ተገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ ኮንትራት ወስዶ ለሰራቸው ስራዎቹ በአጠቃላይ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ አለመሰብሰቡም ተጠቁሟል።

በኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ግንባታቸው የሚጠናቀቅ መሆኑ ቢቀመጥም ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው መሰረት ያልተከናወኑ ናቸው ተብሏል።

ከግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የአዳማ አዋሽ መንገድ ጥገና እና መንገዱን ለማስተዳደር ስምምነት ገብቶ እየሰራ ቢሆንም በውሉ መሰረት ሥራውን ባለማከናወኑ ለበርካታ ዕዳ መጋለጡ ነው የተነገረው።

ከዚህም አልፎ ኮርፖሬሽኑ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ከአሰሪ ተቋም ክፍያ መሰብሰብ አልቻለም ተብሏል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ENA-01-31

Credit : ENA

@tikvahethiopia
በመቆጠብ ከፍተኛ ወለድ ያግኙ!

አፖሎ የ9% ወለድ ተጠቃሚ የሚሆኑበት የዲጂታል መተግበሪያ ነው። የቁጠባ ሂሳብዎን አሁኑኑ ይክፈቱ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollo #OurNewProduct #highinterestrate #9% #exciting, #interestrate #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #thechoiceforall
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል 2ተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይም ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል።

ለ3ተኛ ጊዜ በተዘጋጀው ሽልማት 46 ሰዎች የህዝብ የተሰጣቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 17 የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተብለው ተለይተዋል።

ከእነዚህም መካከል ከተለያዩ ተቋማት በተወጣጡ 5 ዳኞች 3ቱ የ2023 ምርጥ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተብለው ተመርጠዋል።

በዚህም ፦

1ኛ. ወ/ሮ ብርሀነወርቅ ዘውዴ

ከ30 ዓመት በላይ በሰብአዊ መብቶች ትግል ላይ ቆይተዋል፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ አባልና የኢሰመጉ መደበኛ አባልም ነበሩ።

ለመምህራን መብት መታገል እጅግ የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ ጠንካራ ሴት የመብት ተሟጋች ናቸው።

2ኛ. አቶ መለሰ ሸሽጌ

በደቡብ ጎንደር ጋይንት የተወለዱ ሲሆን ለሴቶችና ሕጻናት መብት ተግተተው ሲሰሩ ቆይተዋል፤ ከ50 በላይ ወጣት ሴቶችን ካልተፈለገና ያለእድሜ ጋብቻ ታድገዋል።

3ኛ. ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ

የብሔር እና የሀይማኖት ግጭቶችን ለማስወገድ ሰርተዋል፤ ለ5 ዓመታት የፓርላማ አባል ሆነው አገልግለዋል፤ በሁሉም የስራ ጊዜያቸው ለሰብዓዊ መብት መከበር ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ለ565 የፖለቲካ እስረኞች በነጻ ጥብቅና ቆመዋል፤ 165ቱን ደግሞ ነጻ አውጥተዋል። በተጨማሪም በነጻ በዓመት ከ 5 -10 ለሆኑ ሴቶች እና ህጻናት ነጻ ጥብቅና ይቆማሉ።

@tikvahethiopia