TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle #AddisAbaba • " ክልከላው ላይ የለንበትም ፤ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች • " ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም። ... ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ • " ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን "…
" ወጣቶች እንዳይንቀሳቀሱ የማድረግ ዓላማ የለንም " - የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ

" የኢትዮጵያ መንግስት ሆነ የትግራይ ክልል ወጣቶች  #እንዳይንቀሳቀሱ_የማድረግ_አላማ_የላቸውም " ሲል የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቀ።

ቢሮው ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን እስከ 4 ጊዜ በረራ በማድረግ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጾ ፤ ከተጓዦች ቁጥር አንፃር ሲታይ በረራው አነስተኛ በመሆኑ ቅድሚ የህክምና ወረቀት ላላቸው፣  ለእድሜ ባለፀጎች ፣ ለእናቶች ፣ አጣዳፊ ጉዳይ ላላቸው እየተሰጠ ነው ብሏል።

በችግር ላይ ላሉ ሰዎች ቅድሚያ ለመስጠት ሲባል እንጂ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የትግራይ ክልል ወጣቶች እንዳይንቀሳቀሱ የማድረግ ዓላማ የላቸውም ሲል ቢሮው አሳውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ገብረፃድቅ ፦

" የአየር ትራንስፖርት ልክ እንደተጀመረ ወዲያው ነው ህዝቡ መንቀሳቀስ የፈለገው ካዛ ወደዚህ መምጣት ከዚህ ወዳዛ መሄድ።

የተመዘገበው ሰው በጣም ብዛት ስላለው ወጣቱም ትልቁም፣ ህፃኑም ሴቶችም የተለያየ ማህበራዊ ችግር ያለባቸው ህክምና ሪፈር ያላቸውና ሌሎችም ነበሩ ስለዚህ ቅድሚያ ለመስጠት አጣዳፊ ነገር ያላቸው ስራቸው ታይቶ እነሱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል። ከፌዴራል ጋር ስንነጋገርም እንደዚህ ነው፣ እዚህ ካሉ የደህንነት አካላትም ጋር።

#ከወጣቱ_ይልቅ ለሽማግሌዎች ፣ የህክምና ኬዝ ላለባቸው፣ እናቶች እርጉዞች ፣ ህፃን ያላቸው ለነሱ ነው ቅድሚያ እየተሰጠ ያለው፤ በጊዜ እየተፈታ ይሄዳል። " ብለዋል።

በትግራይ በኩል ወጣት እንዲቆይ ሌላው እንዲሄድ የሚል እቅድ የለም ፤ እንዲህ የሚል መመሪያም ያወረደ የለም በፌዴራል መንግስት በኩልም የለም ሲሉ አክለዋል።

ችግሩ ከትራንስፖርት ማነስ እንጂ ሌላ የፖለቲካ ጉዳይ የለውም ሲሉ ገልፀዋል።

" መጀመሪያ ላይ ሲጀመር ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በአንድ በረራ ነበር የተጀመረው የህዝቡ ፍላጎት ታይቶ እስከ አራት የደረሰበት ሁኔታ አለ አሁንም ፍላጎት ስላለ አሁንም እንዲጨምር ግፊት እናደርጋለን ያለው " ቢሮ ፥ " የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሁኔታውን እያየን እየጨመርን እንሄዳለን " የሚል ምላሽ እንደሰጠ አሳውቋል።

ከቀናት በፊት ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ የነበሩ ወጣቶች በረራ እንደተከለከሉ ከተገለፀ በኃላ የክልሉ አስተዳዳሪዎች እነሱ እዚህ ውስጥ እንደሌሉበትና ችግሩን ለመፍታት እንዲቻል ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተናጋገሩ እንደሆነ ለክልሉ ቴሌቪዥን መግለፃቸው አይዘነጋም።

ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/75705

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወጣቶች እንዳይንቀሳቀሱ የማድረግ ዓላማ የለንም " - የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ " የኢትዮጵያ መንግስት ሆነ የትግራይ ክልል ወጣቶች  #እንዳይንቀሳቀሱ_የማድረግ_አላማ_የላቸውም " ሲል የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን ፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቀ። ቢሮው ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን እስከ 4 ጊዜ በረራ በማድረግ አገልግሎት…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ከመቐለ በረራ ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥቶ ነበር።

ምን አለ ?

- ወደ መቐለ በረራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እና ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞችን እያገለገለ መሆኑን ገልጿል።

- አየር መንገዱ ቲኬት ገዝተው ወደ ቼክኢን ካውንተር የሚመጡ ተጓዦችን በአግባቡ እያስተናገደ መሆኑን አመልክቷል።

- የመቐለ በረራ በቀን አንድ ጊዜ የነበረ ሲሆን አሁን በየእለቱ የሚደረገው በረራ ወደ ሶስት ከፍ ማለቱን አሳውቋል።

- እለታዊ የበረራ ብዛት ቀንሷል የሚለው የተሳሳተ መረጃ ነው ብሏል፡፡ ወደፊትም የሚኖረውን የበረራ ፍላጎት እየታየ የበረራውን ብዛት ለመጨመር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

- #ከአዲስ_አበባ  ወደ  #መቐለ የሚጓዙ መንገደኞች የአየር መንገዱን የጥሪ ማእከል እና ቲኬት ቢሮዎች በመጠቀም ቲኬት መግዛት የሚችሉ ሲሆን ከመቐለ የሚነሱ ተጓዦች ደግሞ ከመቐለ የአውሮፕላ ማረፊያ የሽያጭ ቢሮ ቲኬቱን መግዛት ይችላሉ፡፡

በተጨማሪ ፦

የበረራ ቲኬቱን አ/አበባ በሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በኩል መግዛት የሚፈልጉ ደግሞ ቦሌ በሚገኘው " የኢትዮጵያ ኤርፖርት ኢንተርፕራይዝ ህንጻ " የምድር ወለል ከሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት እስከ ከሰአቱ 11፡00 ሰአት ድረስ መግዛት ይችላሉ ብሏል።

- አየር መንገዱ ባለፉት ስምንት ወራት የመቐለ በረራን ጨምሮ በሌሎች የሃገር ውስጥ በረራዎች ቲኬት ዋጋ ላይ ጭማሪ እንዳላደረገ ገልጿል።

- የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው ተጓዦች እና የኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች የመቐለ በረራ የቲኬት ዋጋ ለመሄጃ ብቻ ከ3450 ብር ጀምሮ ሲሆን፣ የደርሶ መልስ ቲኬት መነሻ ዋጋ ደግሞ 6895 ብር ነው፡፡ 

- " ሻንጣን " በተመለከተ #ከገና_በዓል ጋር ተያይዞ የተጓዦች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ የሻንጣ አገልግሎት ላይ መለስተኛ መጨናነቅ ተፈጥሯል።  በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ ተጨማሪ (ትርፍ) ሻንጣዎችን ለመቀበል ተቸግሮ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን የካርጎ በረራ በመመደብ ችግሩን መፍታት ስለተቻለ ተጨማሪ ሻንጣ መቀበል ጀምሯል፡፡

Credit : Ethiopian Airlines

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ20/80 እና 40/60 ውል እንዴት እየሄደ ነው ? " በሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራሞች 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን መውሰድ ችለዋል " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/ 60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ " በጥሩ ሁኔታ " እየተካሄደ ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ። ኮርፓሬሽኑ በ20/80 14ኛ ዙር …
#Update

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለዕድለኞች ውል ማዋዋል ከተጀመረ በአምስት (5) ቀናት ውስጥ 14,005 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእደለኞች ተመዝግበው ቅፅ 09ን እንደወሰዱ ዛሬ አሳውቋል።

ኤጀንሲው ቅፅ 09 ወስደው በመኖሪያ ቀበሌያቸው አስፈላጊውን መረጃ አስሞልተው የመጡ እና ቅፅ 03 የባንክ ክፍያ የመፈፅሙበትን ሰነድ የወሰዱ ተዋዋዬች ብዛት 699 ሰዎች እንደሚሆኑ አመልክቷል።

ከነዚህ መካከል #የባንክ_ክፍያቸውን አጠናቀው ውል የፈፀሙት 66 ሰዎች እንደሆኑ ገልጿል።

በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤቶች እድለኛ የሆኑ ሳይዘናጉ ወደ አንድ ማእከል በመምጣት ቅፅ 09ኝን በመውሰድ ከሚኖሩበት ቀበሌ አስሞልተው ሊመጡ እንደሚገባና በወጣው ውል የማወያያ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀርበው ሊዋዋሉ እንደሚገባ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በ60 የስራ ቀናት ውል የማይፈፅሙ ባለዕድለኞች ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እየተላለፈ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#Nepal

በኔፓል #የመንገደኞች_አውሮፕላን ተከስክሶ በርካቶች ህይወታቸው አለፈ።

72 ሰዎች አሳፍሮ የነበረ የመንገደኞች አይሮፕላን በማዕከላዊ ኔፓል የአውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስክሶ እስካሁን ባለው 40 አስከሬኖች መገኘታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ማሳወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

አውሮፕላኑ ንብረትነቱ የ " የቲ አየር መንገድ " ሲሆን ከካትማንዱ ተነስቶ ወደ ቱሪስት መዳረሻ ከተማ ወደሆነችው ፖክሃራ ያቀና ነበር።

አውሮፕላኑ ፖክሃራ ኤርፖርት አቅራቢያ ነው የተከሰከሰው።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ አንድ ቪዲዮ አውሮፕላኑ በአንድ በርካታ ሰዎች በሚኖሩበት መንደር አካባቢ ዝቅ ብሎ ሲበር አሳይቷል።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ቢያንስ 15 የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 68 ተሳፋሪዎች እና አራት የበረራ አባላት ነበሩ ተብሏል።

ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ 53ቱ የኔፓል ዜጎች መሆናቸው ተነግሯል።

በተጨማሪ ፦
- አምስት ህንዳውያን፣
- አራት ሩሲያውያን
- ሁለት ኮሪያውያን
- አንድ የአየርላንድ ፣
- አንድ የአውስትራሊያ፣
- አንድ የአርጀንቲና እና
- አንድ የፈረንሣይ ዜጎች በአውሮፕላኑ ውስጥ እንደነበሩም ተጠቁሟል።

ከአውሮፕላን መከስከሱ በኃላ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፑሽፓ ካማል ዳሃል ፤ ካቢኔያቸውን ለአስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸው ታውቋል።

Video : Aerowanderer

@tikvahethiopia
#Tigray

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከሰኞ ጀምሮ የሞባይል ባንኪንግ፣ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ ማስተላለፍ ሌሎችንም አገልግሎቶችን እንደሚጀምር ለትግራይ ቴሌቪዥን አሳውቋል።

ባንኩ ፤ በአንበሳ ባንክ ሂሳብ ከፍቶ የሚጠቀም ደንበኛ ሁሉ በሚመቸው ቦታ መጠቀም እንደሚችል የገለፀ ሲሆን ይኸው አገልግሎት ሰኞ በመቐለ ሙሉ በሙሉ እንደሚጀምር ገልጿል።

በዓድዋ  ፣ ኣክሱም  ፣ ሽረ እንደስላሰ ላይም እንደሚጀምር ጠቁሟል።

ውቕሮ እና ዓዲግራት የቴሌ አገልግሎት የማስጀመር ስራ እየተጠናቀቀ ስለሆነ በሚቀጥሉት ቀናት ይጀምራል ያለ ሲሆን በዓዲጉደም፣ ማይጨውና መኸኒ ለማስጀመር ባንኩ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

አገልግሎቱ በተለይም ነጋዴዎች ገንዘብ በማስተላለፍ ስራቸው ያበለጠ እንዲሳለጥ እንደሚያደርገው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ፤ ባንኩ የብር ችግር ስላለበት ደንበኞቹ ከሂሳባቸው እንዲያወጡ እያደረገ ያለው የተወሰነ መጠን (እስከ 2 ሺህ ብር) ነው። ይህ ደግሞ ደንበኞች የራሳቸውን ብር በፈለጉት ልክ አውጥተው እንዳይጠቀሙ አድርጓል።

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደንበኞቹን በተወሰነ መልኩ እያስተናገደ የሚገኘው በመንገደኞች አውሮፕላን በተጓዥ ወንበር ላይ እየመጣ ባለ ብር መሆኑ ገልጾ በጭነት አውሮፕላን የመጣ ብር እንደሌለ አመልክቷል።

ያለው የብር ችግር ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኘው የብሔራዊ ባንክ ብር ሲልክ ብቻ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GONDAR የጥምቀት በዓል እጅግ በድምቀት የሚከበርባት ጎንደር ከተማ ዝግጅቷ በማጠናቀው እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው። በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና በክብር ለማስተናገድ ዝግጅታችንን ሁሉ አጠናቀናል ብለዋል። ዘንድሮ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። የከተማ አስተዳደሩ " የጥምቀት…
#ጎንደር

ከቀናት በኃላ ለሚከበረው የጥምቅት በዓል እንግዶች ከወዲሁ ወደ ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ መግባት መጀመራቸው ተሰምቷል።

የጎንደር ከተማ እና አካባቢው ሆቴሎች፣ ሎጂዎችና ሪዞርቶች ማኅበር ፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት በኮረና ቫይረስና በጦርነት ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የቱሪዝም እንቅስቃሴ አሁን ላይ መልሶ እየተነቃቃ መሆኑን አመልክቷል።

ጎንደር እንግዶቿን በምቾት ተቀብላ ለማስተናገድ ሆቴሎቿ በቂ ዝግጅት እንዳደረጉም ተገልጿል።

ካለው ሀገራዊ የሰላም ሁኔታ ጋር ተያይዞ ለዘንድሮው ጥምቀት በዓል ወደ ጎንደር የሚገባው እንግዳ ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል።

ይህ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የማረፊያ እጥረት ለመቅረፍ ታሳቢ ያደረጉ የመፍትሔ ተግባራትን በከተማው ሆቴሌች እየተሰራ ስለመሆኑ ተገልጿል።

በሆቴሎች ደረጃቸውን የጠበቁ ተጨማሪ የድንኳን መጠለያ አገልግሎት ለመስጠት እንደታሰበ ከአሚኮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ 500 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባች እንደሆነ ፕሬዜዳንቷ ገልፀዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደራቸው በመላ አገሪቱ 500,000 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባ እንደሆነ አሳውቀዋል። በአሜሪካ የኤሌክትሪክ መኪና ተገልጋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን ሀገሪቱም ይህንን በእጅጉ እያበረታታች ነው። በአሜሪካ…
#EV

አሁን ላይ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ።

ከዓለማችን ሀገራት መካከል #አሜሪካ በ2050 ከካርቦን-ነፃ እንድትሆን አሽከርካሪዎች በነዳጅ ኃይል ከሚሰሩ ወደ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች እንዲቀይሩ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ታምናለች።

በ2030 ከአዳዲስ የመኪና ሽያጭ ግማሹ የኤሌክትሪክ/ ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች እንዲሆኑ ግብ አላት፤ እ.ኤ.አ. በ2030 ግማሹ ኤሌክትሪክ ከሆኑ፣ በ2050 በአሜሪካ ጎዳናዎች ከሚሽከረከሩት መኪኖች ከ60-70 በመቶ የኤሌክትሪክ / ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች ሊሸፍኑ ይችላሉ።

ለዚህም የመኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች በስፋት እየተገነቡ ይገኛሉ (እስከ 2030 ደረስ 500,000 የመገባት እቅድ አላት) ።

አሁን ላይ አሜሪካ ምን ያህል ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች አሏት ?

(እንደ ኤስ ኤንድ ፒ ሞቢሊቲ መረጃ)

- 126,500 ደረጃ ሁለት (የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በ5 ሰዓት ሙሉ የሚያደርጉ) ጣቢያዎች፤

- 20,431 ደረጃ 3 (ከ15-20 ደቂቃ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን 80% የሚያደርጉ)  ጣቢያዎች፤

- 16,822 የቴስላ ሱፐርቻርጀር እና የቴስላ ቻርጅ ማድረጊያ መዳረሻዎች አሉ።

ኤስ ኤንድ ፒ ሞቢሊቲ፤ በ2025 እስከ 7.8 ሚሊዮን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ሊኖሩ እንደሚችሉ ተንብዮ ለዚህም 700,000 ደረጃ ሁለት እና 70,000 ሶስት የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ሊኖሩ ይገባል ብሏል።

በ2030 ደግሞ 28.3 ሚሊዮን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይኖራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለዚህም 2.13 ሚሊዮን የደረጃ 2 እና 170,000 ደረጃ 3 የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ያስፈልጋሉ።

ይሄ የመኪና ባለቤቶች በቤታቸው ከሚገጥሙት የቻርጅ ማድረጊያ ተጨማሪ ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጥር 08 ቀን 2015 ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሐሙስ ጥር 11 ቀን 2015 አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌትን ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር ሥራ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶችን በሙሉ የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል።

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንኑ ክልከላ መሠረት በማድረግ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግሥት እንዲጠብቁም የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የጠየቀ ሲሆን፤ ክልከላውን በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ አስፈፃሚ ሰራተኞችን በጊዜያዊነት መቅጠር እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ባልተካሄደባቸው የተወሠኑ ምርጫ ክልሎች ላይ በተያዘው ዓመት ምርጫውን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

በዚሁ መሠረት በአማራ ክልል ፦
- በሮቢት፣
- በኤፌሶን፣
- በማጀቴ፣
- በሞላሌ እና በአርጎባ ልዩ  ምርጫ ክልሎች ለሚያካሄደው ምርጫ፤ ምርጫ  የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን #በጊዚያዊነት_ለመቅጠር እንደሚፈልግ ገልጿል።

በተጠቁሱት አካባቢዎች የሚኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የሚፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆኑ ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲያመልክቱ ጥሪ አቅርቧል።

የምልመላ መሥፈርቱ ፦
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• መኖሪያ አድራሻ፦ በምርጫ ክልሉ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ ውስጥ የሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ በተጠቀሱት የምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን ብር 250 በድምሩ፣ 
• በክልሉ የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆኑ እንደሚመረጥ ቦርዱ አመልክቷል።

ሴት አመልካቾች ይበረታታሉም ተብሏል።

መሥፈርቱን የሚያሟሉ በዚህ ማስፈንጠሪያ https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment  ከዛሬ ጀምሮ እስከ  ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ለ8 ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

 @tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ በከተማው ውስጥ በአዋኪ ድርጊቶች ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን ሆቴሎች እና ላውንጆች እንዲታሸጉ ማድረጉን አስታወቀ።

አስተዳደሩ ፤ በትናንትናው እለት ከምሽቱ 4፡00 እስከ ለሊቱ 8.30 በፀጥታ ግብረ ሀይል (ኦፕሬሽኑ ላይ የተሳተፉየአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ የሠላምና ፀጥታ ፣የደንብ ማስከበር) ተወስዷል ባለው እርምጃ ፦

በቂርቆስ ክ/ከተማ ፦

1. ሪቮ አዲስ ላወንጅ :- 87 የሺሻ ዕቃና በድርጊቱ ተሳታፊ 200 ወጣቶች
2. አቤም ሆቴል 22 የሺሻ ዕቃና 8 ወጣቶች
3. ናሽናል ሆቴል 16 የሺሻ ዕቃና 67 ወጣቶች
4. ሞሲሳ ሆቴል 7 የሺሻ እቃ

በቦሌ ክ/ከተማ ፦

5. ቀነንሳ ሆቴል 35 የሺሻ እቃ
6. ዘባንክ ላውንች 28 የሺሻ እቃ

የካ ክ/ከተማ ፦

7. ቤልቪው ሆቴል 86 የሺሻ ዕቃ እና 54 ሠው የተያዘ በሶስቱ ክ/ከተሞች በጥቅሉ 7ቱ ቤቶች #ታሽገዋል

በተጨማሪ ፤ 281 የሺሻ እቃ እና 330 ሰው በቁጥጥር ስር ከተደረጉ በኋላ 200 ወጣቶች በምክር እንዲለቀቁ መደረጉን 130 ሰዎች ግን በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን አመልክቷል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia