TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ላሊበላ ለልደት በዓል ዝግጅቷ ምን ይመስላል ? የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ታህሳስ 29/2015 የሚከበረውን የልደት በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቁቁን አሳውቋል።   የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ተስፋ ሃብቴ በሰጡት ቃል፦ - ከወትሮው በተለየ መልኩ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚመጡ ዕንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ተደርጓል።…
በዘንድሮው የልደት በዓል #በላሊበላ ምን ያህል ሰው ተገኘ ?

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት የተነሳ ባለፉት 3 ዓመታት የገና በዓል በታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ማክበር ሳይቻል ቀርቶ ነበር።

የዘንድሮው በዓል ግን በተፈጠረው ሰላም የተነሳ በተሳካና በሰላማዊ ሁኔታ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ታጅቦ መካሄዱ ተገልጿል።

የላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ፤ በቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በተከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ላይ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች (1,975,745) መገኘታቸውን አሳውቋል።

ለበዓሉ ከተገኙት መካከል 418ቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው።

ከጦርነት በኃላ ሰላም በመስፈኑ ትልቅ ለውጥ መኖሩን የገለፀው ፅ/ቤቱ ባለፈው ሙሉ ዓመት ላሊበላን የጎበኙት 776 የውጭ ዜጎች ብቻ እንደነበሩ አስታውሶ ዘንድሮ ግን በገና በዓል ብቻ 418 የውጭ ዜጎች በዓሉን አክብረዋል።

በበዓሉ በተሳተፉ ቱሪስቶች አማካኝነት የአገልግሎት ዘርፉ #የተሻለ_ገቢ እንደተፈጠረለት ተመላክቷል።

በተለይ ሆቴሎች፣ ምግብና መጠጥ አቅራቢ ድርጅቶች እንዲሁም አስጎብኚዎች በኮቪድና በጦርነቱ ምክንያት ተዳክሞ የነበረው ሥራቸው መነቃቃት እንደፈጠረላቸው ፅ/ቤቱ ገልጿል።

ወደላልይበላ የመጡት ቱሪስቶች ከበዓሉ አከባበር ባለፈ በከተማዋ የሚገኙ ቅርሶችን ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ጥረት ስለመደረጉ ተገልጿል።

Lalibela Communication
Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) እንደሚመጡ ተሰምቷል። የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ በቅርቡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እንደሆነ ተሰምቷል። ኪንግ ጋንግ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።…
#ETHIOPIA #CHINA

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሆነ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ከምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሚኒስትሩ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ባሰራጩት አጭር ፅሁፍ ፤ " የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል " ብለዋል። " የዛሬው ውይይት ይህንን እና በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል " ሲሉ ገልፀዋል።

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአቶ ደመቀ ጋር በተገናኙበት ወቅት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት እና ከፊል የዕደ ስረዛ ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱ የሁለቱን አገራት ጠንካራ ግንኙነትን ለማስቀጠል እና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋጋር እንደሚረዳ ተገልጿል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሁለትዮሽ ፣ቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

ቺን ጋንግ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በ #ኢትዮጵያ እያደረጉ ናቸው።

መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ልዑካን ቡድኑ በሰላም መቐለ ደርሷል። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዜዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተመራው የትግራይ ተወላጅ አትሌቶችን ያቀፈው የልዑካን ቡድን መቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም ደርሷል። Photo Credit : Demtsi Woyane @tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን 2 ሚሊዮን ብር አበረከተ።

ዛሬ መቐለ የገቡት የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና በእሷ የተመራው ልዑካን ቡድን ከዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር እና ከሌሎች የትግራይ ክልል አስተዳደር አካላት ጋር ተገናኝቶ ተወያይቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉቱ ለትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን 2 ሚሊዮን ብር አበርክተዋል።

የፎቶ ባለቤቶች ፦ የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia