TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ " ህገ ወጥ የቤቶች ግንባታ " ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ያልተረጋጋ ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የህግ ማእቀፉን ቀድሞ መረዳት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ከከተማ መሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የወጣ ህግ መኖሩን እና በህጉ ላይ ያለውን የግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሀላፊዎች ሊረዱት እንደሚገባ በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል።

የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ ለአሀዱ ሬድዮ ፍና ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለሚሰራው ስራ እጃቸው የሚያርፍበት #በርካታ_የመንግስት_ሀላፊዎች በመኖራቸው ከግንባታ ፍቃድ አስጣጥ አንሰቶ የሚስተዋለው ችግር አንዱና ዋንኛው ምክንያት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በመሰረታዊነት በህግ ማዕቀፉ ላይ ያለውን አሰራር በሚገባ በመረዳት ግንባታ ከመከናወኑ አስቀድሞ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ እንደሆነም ነው የተናገሩት።

ከህገወጥ የቤቶች ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች በዛን ረገድ የሰዎችን ህይወት ያልተገባ ሁኔታ ውስጥ ከማስገባታቸው አስቀድሞ አሰራሩን በመረዳት ተገቢው ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮና ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
" በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም "

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት የተንዛዛ ድግስንና ያለ እድሜ ጋብቻን ፣ ሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው ያላቸውን ድርጊቶች ለማስቆም አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የተላለፉት አዳዲስ ውሳኔዎች ፦

- ያለ እድሜ ጋብቻ እና የህግ ማእቀፍ ያላቸው ሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ በወጣው ህግ መሰረት ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆን፤

- ከአለባበስ ባህል አኳያ በዞኑ ስር ያሉ ሁሉም ወረዳዎች የሚመሩት ህዝብ አንድም ሰው በባዶ እግሩ እንዳይሄድና ቁምጣ ለብሶ የሚሄድ ሰው እንዳይኖር እንዲሰሩ፤

- በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም ፤ ስርአተ በቤተክስቲያን በሚያዝዘው መሰረት ስርአተ ፍትሃት ላደረጉ ካህናት አባቶች ብቻ ቤተክርስቲያን ላይ 1 በግ/ፍየል እና 2 ሌማት ብቻ እንዲቀርብ፤

- ጋብቻ አንዱ ባህላዊ እሴት መሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ እና ትውልድ መቀጠል ስላበት " ጋብቻ ይቁም " እንደማይባል የገለፀው ም/ቤቱ ነገር ግን በጋብቻ ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስን በተመለከተ ለአጋቢ ሽማግሌዎችና ለቤተሰብ የሚሆን 1 በግ/ፍየል እና  2 ሌማት ብቻ እንዲሆን መወሰኑን እና የቀንድ ከብት ማረድ ፍጹም #የተከለከለ መሆኑ አሳውቋል።

በውሳኔው መሰረት በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ እና የጸጥታ አመራሮች ከፍትህ ተቋሙ ጋር ተቀናጅተድ ውሳኔዎቹን እንዲያስፈፅሙ ጥብቅ መመሪያ ተሰዝትቷል።

አፈጻጸሙንም በጋራ እየገመገሙ የተገኘውን ውጤት እና የመጣውን ለውጥ እስከ ጥር 15/2015 ዓ/ም እንዲያሳውቁም መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሕዝበ_ውሳኔ

በደቡብ ክልል ከሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ጋር በተያያዘ የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

- የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ 2.9 ሚሊየን መራጮች ተመዝግበዋል።

- ቦርዱ ይህን ምርጫ ለማካሄድ የሚያግደው ምንም ነገር የለም ፤ አስፈላጊ ዝግጅቶች እንደተደረጉ ነው ብለዋል።

- የመራጮች ምዝገባ በዛሬው እለት የተጠናቀቀ ሲሆን መራጮች በ3,769 የመደበኛ፣ 11 የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አማካኝነት ተመዝግበዋል።

- የአሰራር ጥሰት የተፈጸመባቸው 24 ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ነበር ፤ ጥሰቶቹ መራጮች ካርድ መሰጠት ለሌለባቸው ሰዎች ተሰጥቷል፣ ምርጫ ጣቢያ ያልተገኙ ሰዎች በመራጭነት ተመዝግበዋል፣ ከጣቢያ ውጪ ካርዶች ሲታደሉ ተገኝተዋል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#Mekelle #AddisAbaba

• " ክልከላው ላይ የለንበትም ፤ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች

• " ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም። ... ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

• " ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን " - የፌዴራል ፖሊስ

ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚደረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች በረራ ላይ በተለይም #ወጣት መንገደኞች እንዳይጓዙ ክልከላ ስለመኖሩ መንገደኞች እየገለፁ ይገኛሉ።

ትናንት ታህሳስ 30/2015 ዓ/ም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የአየር ቲኬት ቆርጠው አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የተገኙት #በርካታ_ወጣቶች ጉዟቸው መሰረዙ ተሰምቷል።

መንገደኞች እንደሚሉት ከሆነ ክልከላው ከ16 ዓመት በላይ እና ከ64 ዓመት እድሜ በታች በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ነው።

አንድ ቃሉን ለቢቢሲ የሰጠ መንገደኛ (የአዲስ አበባ ነዋሪ) ፤ " የልጆች እናት፣ የህክምና ሪፈር ያላቸው እና በእድሜ የገፉት ግን መሄድ እንደሚችሉ ነው የፌደራል ፖሊስ አባላቱ የነገሩን " ብሏል።

ይኸው መንገደኛ ፤ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚኖር ፤ መታወቂያውም የአዲስ አበባ እንደሆነ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንደሄደና አስፈላጊውን መረጃ እንዳረበ ነገር ግን ሊቀበሉት እንዳልቻሉ አመልክቷል።

የአየር መንገዱ ሠራተኞች ክልከላው ከቁጥጥራቸው ውጪ እንደሆነ ነግረውናልም ብሏል።

አንድ መንገደኛ ደግሞ አዲስ አበባ የሚያስተዳድረው ተቋም መኖሩን የሚገልፅ መረጃ ካሳየ በኃላ በረራ እንደተፈቀደለት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ክልከላው ከመቐለ በተጨማሪም #በሽረ ኤርፖርትም ስለመኖሩ ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ ማን ምን አለ ?

የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉ አካላት ፤ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ትግራይ ቴሌቪዥን) በሰጡት ቃል በዚህ ክልከላ እንደሌሉበት እና የክልከላው እርምጃ በፌደራል መንግስት የተወሰደ እንደሆነ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙርያ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገረ መሆኑን አሳውቋል።

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም።

እንደምታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድሜና ጾታ ክልከላ የለውም። ምክንያቱም በሕግ እና በሥርዓት ነው የሚተዳደረው። እስከ ዛሬ እንዲህ አይነት ክልከላ የለንም። ወደ ድረ ገጻችን ብትገቡም ምንም አይነት ክልከላ እንደሌለ ታያላችሁ።

በተጨማሪም ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም።

ምናልባት #የአካባቢው_መመዘኛ_ወጥቶ እንደሆነ የክልሉ ባለሥልጣናትን ብትጠይቁ የሚሻል ይመስለኛል።

በእኛ በኩል ግን እስካሁን የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም። ከመንግሥት የተሰጠ ትዕዛዝም የለም። "

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" መረጃው የለኝም።

ተጓዦች በእድሜ ተለይተው በአውሮፕላን እንዳይጓዙ ተከልክለዋል የሚለውን መረጃ አሁን ከእናንተ ነው የምሰማው።

ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን። "

በጦርነት ምክንያት ለረጅም ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ እና ሽረ እንደስላሴ የሚደረገው የመንገደኞች በረራ በቅርቡ ዳግም መጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#Mekelle

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ነገ ማክሰኞ ጥር 2/ 2015 ዓ/ም ወደ ትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ እንደሚጓዝ " ኢትዮጵጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

የልዑካን ቡድኑ የሚመራው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሲሆን ወደ መቐለ የሚጓዘው የክልሉ ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት መሆኑ ተነግሯል።

ቡድኑ ወደ መቐለ ነገ ረፋድ በአውሮፕላን የሚጓዝ ሲሆን በመቐለ ከተማ የሚኖረው ቆይታ የአንድ ቀን ብቻ መሆኑን በጉዞው ላይ ተሳታፊ የሆነ አንድ አትሌት ተናግሯል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ለገሰ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ፤ የፌዴሬሽኑ አመራሮች እና አባላት በአንድ ቀን ቢመለሱም እዚያው የሚቆዩ አትሌቶች ግን ይኖራሉ ሲሉ አረጋግጠዋል።

በዚህ ጉዞ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የተለያዩ የስራ ክፍል አባላት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በነገ ጉዞ ከሚሳተፉ የትግራይ ክልል ተወላጅ ከሆኑ አትሌቶች መካከል ፦

- አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣
- አትሌት ጎተይቶም ገብረ ስላሴ
- አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ እንደሚገኙበት ተናግሯል።

ምንጭ፦ https://ethiopiainsder.com/2023/9310/

@tikvahethiopia
#ግሬስ

ከሆስፒታል እንደወጡ ለማገገም የት እንደሚሄዱ ግራ ገብቶታል ? የቤትዎ አለመቸት ፣ የህክምና መሳሪያ እና ባለሙያ አለመኖር እንዲሁም ያስታማሚን ችግር ለመፍታት ወደተቋቋመው ግሬስ የህሙማን እና የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ብቅ ይበሉ።

ሁሉን ነገር ባሟላ ማገገምያ ማእከላችን ልምድ ባላቸው ዶክተር እና ነርሶቻችን ቤተሰብዎን ከሆስፒታል እንደወጡ በመንከባከብ እናግዝዎታለን ፤ በነፋሻ ግቢያችን ውስጥ 24/7 የNursing Home አገልግሎት ያገኛሉ።

አድራሻ ፦ አያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው መንገድ ላይ በቀኝ በኩል በፍሬሽ ኮርነር ገባ ብሎ 2ኛ ቅያስ ወደ ቀኝ በድጋሚ 3ኛ ቅያስ ወደ ቀኝ ታጥፈው ያገኙናል።

ለበለጠ መረጃ በ0967-03-42-42 ወይም በ0954-99-11-90 ይደውሉ።
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የሚመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ አምርቷል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ ያመራው የልዑካን ቡድኑ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት ያለመ ጉዞ ነው ያደረገው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የቢሮ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የትግራይ ክልል ተወላጅ አትሌቶች የጉዞው አካል ናቸው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ላሊበላ ለልደት በዓል ዝግጅቷ ምን ይመስላል ? የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ታህሳስ 29/2015 የሚከበረውን የልደት በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቁቁን አሳውቋል።   የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ተስፋ ሃብቴ በሰጡት ቃል፦ - ከወትሮው በተለየ መልኩ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚመጡ ዕንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ተደርጓል።…
በዘንድሮው የልደት በዓል #በላሊበላ ምን ያህል ሰው ተገኘ ?

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት የተነሳ ባለፉት 3 ዓመታት የገና በዓል በታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ማክበር ሳይቻል ቀርቶ ነበር።

የዘንድሮው በዓል ግን በተፈጠረው ሰላም የተነሳ በተሳካና በሰላማዊ ሁኔታ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ታጅቦ መካሄዱ ተገልጿል።

የላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ፤ በቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በተከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ላይ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች (1,975,745) መገኘታቸውን አሳውቋል።

ለበዓሉ ከተገኙት መካከል 418ቱ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው።

ከጦርነት በኃላ ሰላም በመስፈኑ ትልቅ ለውጥ መኖሩን የገለፀው ፅ/ቤቱ ባለፈው ሙሉ ዓመት ላሊበላን የጎበኙት 776 የውጭ ዜጎች ብቻ እንደነበሩ አስታውሶ ዘንድሮ ግን በገና በዓል ብቻ 418 የውጭ ዜጎች በዓሉን አክብረዋል።

በበዓሉ በተሳተፉ ቱሪስቶች አማካኝነት የአገልግሎት ዘርፉ #የተሻለ_ገቢ እንደተፈጠረለት ተመላክቷል።

በተለይ ሆቴሎች፣ ምግብና መጠጥ አቅራቢ ድርጅቶች እንዲሁም አስጎብኚዎች በኮቪድና በጦርነቱ ምክንያት ተዳክሞ የነበረው ሥራቸው መነቃቃት እንደፈጠረላቸው ፅ/ቤቱ ገልጿል።

ወደላልይበላ የመጡት ቱሪስቶች ከበዓሉ አከባበር ባለፈ በከተማዋ የሚገኙ ቅርሶችን ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ጥረት ስለመደረጉ ተገልጿል።

Lalibela Communication
Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia