ፎቶ ፦ " የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና/ቻን " እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅት ዛሬ ሞሮኮ ካዛብላንካ በሰላም መድረሱን የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።
ቡድኑ ወደ ሞሮኮ ከመሄዱ በፊት በሀገር ውስጥ ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል።
በሞሮከ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚያደርግ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ እና ሰኞ ከሞሮኮ #የቻን ቡድን ጋር #ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ውድድሩን የተመለከቱ መረጃዎችን በስፍራው ከሚገኙት የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት በ @tikvahethsport ማግኘት ይቻላል።
ፎቶ ፦ Tikvah Sport
@tikvahethiopia

#የጥንቃቄ_መልዕክት
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣ የምግብ ደኅንነት ኢንስፔክተር መሀመድ ሁሴን ፦
" ሕብረተሰቡ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦችን የመጠቀሚያ ጊዜያቸውን እያስተዋለ መግዛት አለበት።
በተለይ መጪዎቹን የበዓል ወቅቶችን አስታኮ በርካታ ጊዜያቸው ያለፋባቸው ምግቦችና መጠጦች በቅናሽ ዋጋ ወደ ገበያ ሊወጡ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።
ከምግብ ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል አላስፈላጊ ትርፍ ለማጋበስ ከሚጥሩ ሕገ-ወጦችም ራስን መጠበቅ ይገባል።
ሕብረተሰቡ የሚገዛቸውን የምግብና የመጠጥ ምርቶች በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ምርቶቹን ከመግዛቱ በፊት ማን እንዳመረታቸው ? መቼ እንደተመረቱና ? የመጠቀሚያ ጊዜያቸው መቼ እንደሚያልቅ? በአግባቡ ማየት አለበት።
ከእነዚህ ምግቦችና መጠጦች መካከል #ጁሶች ፣ የተለያዩ የታሸጉ #ብስኩቶችና ሌሎች #መጠጦች ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል።
በተለይ ሕገ-ወጥ የሆኑና ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ወይም በክልል ጤና ቢሮዎች ሥር ባሉ ተቆጣጣሪ የፈቃድ ማረጋገጫ ሳይወስዱ የምግብ ንግድ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሕገ-ወጦች አሉ።
ባለሥልጣን መ/ቤቱ የራሱን መቆጣጠሪያ ስልቶችን ነድፎ ቁጥጥር ያደርጋል ፤ ሕብረተሰቡ ለዚህ ሥራ የሚሰጠው መረጃ ቀላል ባለመሆኑ የተለመደ ትብብሩን ሊያደርግ ይገባል። "
#ENA
@TIKVAHETHIOPIA

የ3 ዓመት ህፃን ልጅን አስገድዶ ለመድፈር የሞከረው የ31 ዓመት ግለሰብ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።
ተከሳሽ አቶ ሙላት ይርጋ ደስየ ዕድሜው 31 ዓመት ሲሆን ግለሰቡ ከእሱ ጋር ተቃራኒ ፆታ ያላትን የ3 ዓመት ዕድሜ ያላትን ህፃን ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 11:30 ሰዓት አካባቢ ከታላቅ እህቷ ጋር እየተጫወተች እንዳለ ቤተሰብ መስሎ በመጠጋት ጎንጯን አዟዙሮ በመሳም ልዩ ቦታው " አደንጉር " ከተባለው ስፍራ አዳዲስ ከተሰሩ ቤቶች ውስጥ እጇን ይዞ ሰው ከማይኖርበት ቤት አስገብቶ ሊደፍር ሲል ሰዎች ይደርሱበታል።
በዚህም ወቅት ግለሰቡ ሩጦ ለማምለጥ ሲሞክር ሊያዝ ችሏል።
ህፃኗ በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎላት ክብረ ንፅህናዋ ያለና በግራ በኩል የብልት ቆዳ መላጥ የደረሰባት መሆኑን በህክምና መረጃ ተረጋግጧል።
ክስ የቀረበበት ተጠርጣሪው የወንጀል ድርጊቱን ክዶ ቢከራከርም ዓቃቤ ህግ ባቀረባቸው የሰው ምስክሮችና የህክምና ማስረጃ ጥፋተኝነቱ #ሊረጋገጥ ችሏል።
ሆኖም ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የወልድያ ከተማ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ ተከሳሽን ያስተምራል ሌላውን ማህበረሰብ #ያስጠነቅቃል ያለውን የ16 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት አሳልፏል።
መረጃው ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ ክልል ለጤና አገልግሎት እንዲውሉ አስራ አምስት (15) አምቡላንሶችን ድጋፍ አድርጓል።
Photo Credit : Tigrai Television
@tikvahethiopia
Photo Credit : Tigrai Television
@tikvahethiopia
#የፖሊስ_ማሳሰቢያ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በትራፊክ መብራቶች እና በመስቀለኛ መንገዶች ላይ የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ንግድ እና የልመና ተግባራት ላይ በተሰማሩ ግለሰቦችና #ገንዘብ_በሚሰጡና በሚገበያዩ አሽከርካሪዎች ላይ በህጉ መሰረት ጠንካራ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ።
በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሚሰጡ እና ግብይት የሚፈፅሙ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።
በሚኒስትሮች ም/ቤት የወጣው የትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 #በትራፊክ_መብራት ላይ ወይም #በመስቀለኛ_መንገድ ላይ በልመና ተግባር ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሰጠ ወይም ግብይት የፈፀመ አሽከርካሪ ቅጣት እንደሚጣልበት ይደነግጋል፡፡
" ይሁን እንጂ #የአሽከርካሪዎች ደንብ አክባሪ አለመሆን በእነዚህ መንገዶች ላይ የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ንግድና የልመና ተግባራት እንዲስፋፉ ምክንያት ሆኗል " ሲል ፖሊስ ገልጿል።
የትራፊክ ደንቡ አለመከበር #ለትራፊክ_አደጋ መጨመር እና ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዳይኖር እንቅፋት ከመፍጠሩ ባሻገር በተለይ የትራፊክ መብራቶች ባሉባቸው ጎዳናዎች የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች የሚፈፀምባቸው ቦታዎች እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስረድቷል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Addis-Ababa-Police-01-04

ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ዙሪያ ቤቶች እየፈረሰባቸው እንደሆነ ከሚገለፅባቸው አካባቢዎች አንዱ ወደ ዓለም ባንክ ሲሆን ቤታቸው የፈረሰባቸው በአንድ ስፍራ ላይ ተሰብሰበዋል።
በርካታ ቤቶችም እንደሚፈርሱ የሚገልፅ ምልክት መደረጉ ተሰምቷል።
መንግስት እርምጃውን እየወሰደ ያለው ህገወጥ ቤቶች ናቸው በሚል እንደሆነ ተነግሯል።
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያነጋገሯቸው ነዋሪዎች እየተወሰደ ባለው እርምጃ የሰው ህይወት መጥፋቱንም አመልክተዋል።
በአካባቢው በርካታ አመታትን የኖሩ ዜጎች (እናቶች ፣ ህፃትናት ፣ አዛውንቶች) ቤታቸው ፈርሶባቸው ሜዳ ላይ ብርድና ፀሀይ እየተፈራረቀባቸው ይገኛሉ ፤ መፍትሄ እንዲፈልግላቸውም ጠይቀዋል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ፤ ቤቶችን የማፍረስ እንቅስቃሴ ካለባቸው አካባቢዎች መካከል " አለም ገና ዳለቲ " ተጠቃሽ ነው።
ከላይ በአፋን ኦሮሞ የተያያዘው መልዕክት ከሰሞኑን አለም ገና ዳለቲ የተላለፈ ሲሆን መልዕክቱ ፤
" ጥር 24 ቀን 2005 በወጣው የሊዝ ውል መሠረት ከዚህ አመት በኋላ የሚገነቡ ግንባታዎች ሕገወጥ ስለሆኑ ማስረጃ ያላችሁ ሰዎች ማስረጃችሁን በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ እንድታቀርቡ ያሌላችሁ ደግሞ ንብረታችሁን እንድታነሱ በአክብሮት እንጠይቃለን። " የሚል ነው።
@tikvahethiopia
ከላይ በአፋን ኦሮሞ የተያያዘው መልዕክት ከሰሞኑን አለም ገና ዳለቲ የተላለፈ ሲሆን መልዕክቱ ፤
" ጥር 24 ቀን 2005 በወጣው የሊዝ ውል መሠረት ከዚህ አመት በኋላ የሚገነቡ ግንባታዎች ሕገወጥ ስለሆኑ ማስረጃ ያላችሁ ሰዎች ማስረጃችሁን በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ እንድታቀርቡ ያሌላችሁ ደግሞ ንብረታችሁን እንድታነሱ በአክብሮት እንጠይቃለን። " የሚል ነው።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ዙሪያ ፤ ቤቶችን የማፍረስ እንቅስቃሴ ካለባቸው አካባቢዎች መካከል " አለም ገና ዳለቲ " ተጠቃሽ ነው። ከላይ በአፋን ኦሮሞ የተያያዘው መልዕክት ከሰሞኑን አለም ገና ዳለቲ የተላለፈ ሲሆን መልዕክቱ ፤ " ጥር 24 ቀን 2005 በወጣው የሊዝ ውል መሠረት ከዚህ አመት በኋላ የሚገነቡ ግንባታዎች ሕገወጥ ስለሆኑ ማስረጃ ያላችሁ ሰዎች ማስረጃችሁን በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ እንድታቀርቡ ያሌላችሁ…
በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በዘመቻ መልክ ቤቶች እየፈረሱ ይገኛሉ።
የመንግስት አካል እነዚህ ቤቶች እያፈረሰ ሚገኘው ፤ " ህገወጥ ቤቶች ናቸው " በሚል እንደሆነ ተሰምቷል። በተለያዩ አካባቢዎች በ3 ቀን ለቃችሁ ውጡ የሚል መልዕክትም መለጠፉን ተመልክተናል።
ነዋሪዎች በበኩላቸው ፤ ለረጅም ያህል ጊዜ የኖሩበት ቤት እየፈረሰ መሆኑን ገለፀው ልጆቻቸው ሜዳ ላይ በመውደቃቸው መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ተማፅነዋል።
ከሰሞኑን በለቡ ባቡር ጣቢያ በነበረ ቤት የማፍረስ እርምጃ ወቅት ደግሞ ነዋሪዎች ቤቱ አይፈርስም በማለት ባሰሙት ተቃውሞና በተከሰተ ግጭት በሰው ላይ ጉዳት ደርሶ እንደነበር ተሰምቷል።
ቤት ፈረሰብን ካሉት መካከል ቤቱን ከዓመታት በፊት ከገበሬ ላይ እንደገዙ ፤ ከ2005 በፊት ለተሰሩት ቤቶችም የቤት ቁጥር ሲሰጥ እንደነበር ፤ " ህጋዊ ካርታ ይሰጣችኃል ጠብቁ " የተባሉም እንደነበሩ አመልክተዋል።
ቤቶች እየፈረሰባቸው ናቸው ከተባሉበት አካባቢዎች አንዱ በሆነው " ዓለም ባንክ " አካባቢ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካል ሄደው ሁኔታውን ለመመለከት ችለዋል።
ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ዜጎች ሜዳ ላይ በአንድ ስፍራ ተሰባስበዋል ፤ ነዋሪዎቹ አዳራቸውን በዛው እንዳደረጉም ገልፀዋል። ቤቶች በሚፈርስበት ወቅት ጉዳት መድረሱንና ተኩስም እንደነበር ጠቁመዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላት ፤ በስፍራው ላይ በተገኙበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎችን ተመልክተዋል ፤ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሠቦችም " ከአካባቢው እንዲበተኑ " መልዕክት ሲያስተላለፍ ነበር።
አንድ ቤቱ የፈረሰበት ግለሰብ እሱን ጨምሮ ልጆቹና ባለቤቱ እንዲሁም ሌሎችም አዳራቸውን ውጭ (ሜዳ ላይ) ማደርጋቸውን ገልጾ ፤ በርካቶችም መጠጊያ ይሆነናል ወዳሉት ቤተዘመድ ምሽቱን ሲጓዙ እንደነበር ገልጿል።
በስፍራው ላይ ተሰብስበው የነበሩት ዜጎች መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን 10 ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የኖሩበት ቤት እንዲፈርስ የተደረገባቸውም አሉ።
" ህገወጥ ቤቶች ፈርሶባቸዋል የተባሉ አካባቢዎች ህጋዊ ካርታ፣ መብራት፣ ውሃ የሌላቸው ናቸው " ሲሉ ደግሞ በወቅቱ ስፍርው ላይ የነበሩ አንድ የመንግስት አካል ነግረውናል። እነዚህ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን የማስከበር ብቻ ነው ከሌላ ከምንም ጉዳይ ጋር የሚያያዝ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።
" አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ወቅቱን ያገናዘበ አይደለም ፤ እነዚህ ዜጎች ምንም መሄጃ የሌላቸውም ፣ በዚህ በበዓል ወቅት ይህ መደረጉ ፍፁም ህሊና ቢስነት ነው ፤ እርምጃም ከተወሰደ በኃላ መሄጃ ያጡትን ማብላት እና ውጭ ብርድ ላይ እንዲያደርጉ ከማድረግ አንድ ቦታ ላይ እንዲጠለሉ ማድረግ ይገባ ነበር " ሲሉ አንድ ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል።
" ከህገወጥ ግንባታ ጋር በተያያዘም ከላይ እስከ ታች ያለው ሁሉም አካል ተጠናቂ መሆን ይገባዋል ይህ ሲደረግ ነው ህግ ተከበረ የሚባለው ፤ ይህ ሁሉ ሰው እየተንገላታ እየተጎዳ በወቅቱ ይህን ሲመለከቱ የነበሩ እና በይሁንታ ያለፉ አካላት ሁሉ ከህግ ተጠናቂነት ማለፍ የለባቸውም ሲል አክሏል።
ከላይ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ባለፈ በተለያዩ የአዲስ አበባ ዙሪያ አካባቢዎች ቤቶች እየፈረሱ እንደሆነ እየተሰማ ሲሆን እስካሁን ስለጉዳዩ ለህዝብ ማብራሪያ የሰጠ አካል የለም።

#ማሳሰቢያ
(ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ)
የአፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የመንግስትም ሆነ የግል ቀጣሪ ድርጅቶች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመራቂ ሠራተኞቻቸው እና አዲስ ሰራተኞች ከመቅጠራቸው በፊት የተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃዎች ህጋዊነትና ትክክለኛነት መረጋገጥ ይኖርበታል ብሏል።
ተገልጋዮች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በኩል ይህን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባለሥልጣኑ ከመምጣታቸው በፊት የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት አገልግሎቱን ማግኝት ይችላሉ ብሏል።
1. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ዲግሪ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤
2. በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤
3. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤
4. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ከሆነ በትምህርት ምዘናዎችና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ፤
5. ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የስራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ(COC) ካገኙበት ማዕከል የተረጋገጠ መሆን አለበት ከኮፒ ጋር በማያያዝ እና
6. የስም ለውጥ ካለ የፍርድቤት ውሳኔ ከኮፒ ጋር በማያያዝ ናቸው፡፡
የማስተርስ ዲግሪ ለማረጋገጥ በቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለጸው መንገድ መረጋገጥ ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳስቧል።
#ETA