TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ መንግሥት ነው፣ ያለው #እኔ የምመራው መንግሥት። አንድ ዓመት ተኩል በኋላ እኔ እና ድርጅቴን ካልመረጣችሁ አቅፌ ስሜ እሰጣችኋለሁ። ከምርጫ በፊት በ 3 ወር በ 5 ወር መንግሥት እሆናለሁ የሚል #ቅዠት ኢትዮጵያ ውስጥ #አይሰራም። ይሄ ቅዠት የማይሰራበት ምክንያት እኔ እንኳን ብፈቅድ አንድ ዓመት ተኩል ታግሶ ማሸነፍ ያልቻለ ፓርቲ ነገ መጥቶ እዚህ ቢገባ ያምሰናል እንጂ እንዴት ይመራናል? 30 ዓመት 20 ዓመት የኢትዮጵያን ምድር መርግጥ ያልቻሉ ሰዎች ይብቃ ብለን ሕግ ቀይረን፣ ባሉበት አናግረን፣ ለምነን አምጥተን ስናበቃ #ልንወጋ አይገባም” ጠ/ሚ #ዐብይ_አሕመድ (ዶ/ር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር #ዐብይ_አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሽልማትን ወስደዋል!!
ዶክተር አብይ አህመድ ተሸለሙ!
.
.
ዶክተር #ዐብይ_አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሽልማትን ወስደዋል፡፡ ሽልማቱ በስርዓተ ጾታ እኩልነት ዙሪያ ጥሩ ተግባራትን ለፈጸሙ ግለሰቦች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍናቸው ወራት ውስጥ በአመራር ስፍራዎች ላይ #የሴቶችን_ተሳትፎ አሳድገዋል፡፡ ለአብነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግማሽ አባላት ሴቶች እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ ሴት ፕሬዝደንት፣ መከላከያ ሚንስትር፣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት መሾማቸው ተነስቷል፡፡

#ሴቶች በሙስና ወንጀሎች የመሳተፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን እና በስራቸው ውጤታማ መሆናቸውን በተደጋጋሚ እንደተናገሩ ተገልጿል፡፡ በስርዓተ ጾታ አቀንቃኞች ዘንድ ዶክተር ዐብይ እንደሚወደሱም ተመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ያገኙት ሽልማት በአፍሪካ ህብረት እና በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ የሚዘጋጅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹እየተገነባ ያለው #የመከላከያ_ሠራዊት ዛሬ የሁሉንም #ሉዓላዊነት የሚጠብቅ ነገ ደግሞ የሕዝብ ውክልና አግኝታችሁ ሥልጣን የምትይዙ ተረክባችሁ የምታስቀጥሉት ተቋም ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር #ዐብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች #የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ተናገሩ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ትልልቅ ሐሳብ ላላቸው ሳይሆን ትልልቅ ሀብት ላላቸው ብቻ ከፍተኛ የብድር አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች፤ በዚህም የሚፈለገው ለውጥ ሳይመዘገብ ቀርቷል፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ🔝

ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች #የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አሕመድ ተናግረዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ትልልቅ #ሐሳብ ላላቸው ሳይሆን ትልልቀቅ #ሀብት ላላቸው ብቻ ከፍተኛ የብድር አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች፤ በዚህም የሚፈለገው ለውጥ ሳይመዘገብ ቀርቷል፡፡ ይህንን ችግር በመረዳትም ለተማሩ ዜጎች ሐሳባቸውን በማዬት ብድር ለመስጠት እንዲቻል ፖሊሲዎች እንደሚመቻቹና አነስተኛና መካከለኛ ባለሀብቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በዓለም ባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ መለኪያ መሠረት ኢትዮጵያ 159ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ 5 ዓመታት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ #በማሻሻል በመለኪያው ከ100 በታች ለማድረግ በእርሳቸው የሚመሩ 10 ተቋማት ተለይተው ወደ ለውጥ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የአሠራር ፖሊሲዎች፣ የሕግ ማዕቀፎች እና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት በተቃርኖ የተሞላ አሠራርን መከተላቸው ኢትዮጵያ በቀላሉ ሥራ (ቢዝነስ) የማይሠራባት ሀገር እንድትሆን ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ወር ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትሩ #የሚመራው እና 10 ተቋትን ያካተተው ልዩ ኮሚቴ (ስትሪንግ ኮሚቴ) አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግ የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች በየወሩ የውጤት ግምገማ እያደረገ ይገኛል፡፡

ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ዕድገት እንዲመዘገብ ‹‹ያለንን የተፈጥሮ ሀብት #በአግባቡ መጠቀምና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ አዳዲስ ሐሳብ፣ ዕውቀትና ክሕሎትን በተቀናጀ መልኩ አሟጦ መጠቀም ይጠይቃል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

እስካሁን ያለው አካሄድ በተቃርኖ የተሞላ፣ ዘመናዊ አሠራርን ያልተከተለ፣ ተወዳዳሪነት የሌለውና በአነስተኛ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎችን በቀላሉ የማይጠቅም በመሆኑ ውጤት ማምጣት እንዳልቻለም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩት፡፡ ለዚህ ደግሞ ውስብስብ የሆነ አካሄድን መጠቀምና የገንዘብ አቅርቦት ችግር ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ከችግሩ ለመውጣት የአሠራር ሥርዓትን ማቅለል፣ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ማድረግና ምቹ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ ነው ያብራሩት፡፡

ለሥራዎች ገንዘብ የማቅረብ ሂደቱን ቀላል ማድረግ፤ እስካሁን ቋሚ ንብረት ይያዝ የነበረበትን የባንኮች አሠራር በቀጣይ ሐሳብን በማስያዝ ወጣቶች ብድር የሚወስዱበት ሁኔታ እንዲፈጥር ማድረግና የግል ተቋማት ውስጥ በቀላሉ ወደ ሥራ ተገብቶ ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡

‹‹በአዲስ ዕውቀትና ሐሳብ ዕድገታችን ማስቀጠል አለብን፤ ለዚህ መንግሥት ማድረግ የሚገባውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ለግል ዘርፍ መስጠት አለበት፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ቀላልና ሳይንሳዊ የሆነ የአሠራር ሥርዓትን መዘርጋት ይገባል›› ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር ዐብይ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹አይቻልም›› ወይም ‹‹ሕጉ አይፈቅድም›› የሚሉ አመለካከቶችን በመስበር ሁሉም ተቋማት ለሀገር ሲሉ ቀና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ጅምሮቹ ወደ ውጤት እንዲያድጉ አሁንም ተቋማት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸውም መክረዋል፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያለፈው አንድ ወር አፈጻጸም ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መሪዎቹ አርባምንጭ ገብተዋል...

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ እና የኬንያው ፕሬዘዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል። መሪዎቹ አርባምንጭ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ፎቶ፦ Gamo Zone Administration Public Realtion office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🛬አመሻሹን የኢ.ፌ.ዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ ባህር ዳር ከተማ ገብተዋል። በምን ጉዳይ ባህር ዳር እንደሄዱ ግን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ፎቶ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር #ዐብይ_አህመድ (ዶ/ር) ጋር በሸራተን አዲስ እየተወያየ ነው፡፡

#etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ቤተ መንግስት ውስጥ እንዲሆኑ ሊደረግ ነው። ቤተ መንግስቶችን በማደስና ህዝብ እንዲጎበኛቸው በማድርግ ለገቢ ማስገኛነት እንዲውሉ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ አስታውቀዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 386 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ሆኖ በተዘጋጀው ረቂቅ በጀት ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው ቤተ መንግስቶችን በማደስ ለገቢ ማስገኛነት አገልግሎት እንዲውሉ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት።

🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia