TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ አጠራጣሪ ነገሮችን ስትመለከቱ በአቅራቢያችሁ ላሉ የፀጥታ አካላት ጥቆማ ስጡ " - ፌዴራል ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፤ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።

በተለይ በበርካታ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በዓሉ በድምቅት በሚከበርባቸው አካባቢዎች ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን የጸጥታ ጥበቃ ስራ መሰራት የሚያስችለውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

በቁልቢ የሚከበረው በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር ፌዴራል ፖሊስ፣ ከኦሮሚያ፣ ከሐረሪና ድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመቀናጀት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሰርተዋል።

በሐዋሳ የሚከበረውን በዓል በሚመለከትም የፌዴራል ፖሊስ ከሲዳማ እንዲሁም ከደቡብ፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ህብረተሰቡ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ አበባ 🛫 መቐለ ! #ከአዲስ_አበባ ወደ #መቐለ ከነገ ጀምሮ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ " ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት ይጀምራል " ብለዋል። " በፌዴራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ…
#Mekelle

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ታሕሳስ 19 ጀምሮ ወደ መቐለ መደበኛ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ማሳወቁ ይታወቃል።

አየር መንገዱ ፤ ወደ መቐለ ከተማ መደበኛ በረራ መጀመሩን ተከትሎ በደንበኞች አገልግሎት ጥሪ ማዕከሉ እና ትኬት ሽያጭ ቢሮዎቹ ላይ ከፍተኛ መጨናነቅ መስተዋሉን ገልጿል።

ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ሆነው የአየር መንገዱን ድረ ገፅ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪ ተጠቅመው ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን አሳውቋል።

ትኬት መቁረጫ ፦
www.ethiopianairlines.com
bit.ly/ET-android-app
bit.ly/ET-iOS-App

በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ መቐለ በረራ እንደሚጀምር ባስታወቀ በአንድ ሰዓት ገደማ ነው ለረቡዕ ጉዞ የትኬት ሽያጭ የተጠናቀቀው።

ለነገው በረራ የትኬት ሽያጭ የተጀመረው ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ ሶስት ሰዓት ገደማ እንደነበር " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ አስነብቧል።

እጅግ በርካታ በመቐለ ቤተሰቦቻቸው የሚገኙና ያሉበትን ሁኔታ ለማየት እየተጠባበቁ ያሉ ዜጎች አየር መንገዱ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨርም ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ታሕሳስ 19 ጀምሮ ወደ መቐለ መደበኛ በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ማሳወቁ ይታወቃል። አየር መንገዱ ፤ ወደ መቐለ ከተማ መደበኛ በረራ መጀመሩን ተከትሎ በደንበኞች አገልግሎት ጥሪ ማዕከሉ እና ትኬት ሽያጭ ቢሮዎቹ ላይ ከፍተኛ መጨናነቅ መስተዋሉን ገልጿል። ደንበኞቹ ባሉበት ቦታ ሆነው የአየር መንገዱን ድረ ገፅ እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪ ተጠቅመው ምዝገባ…
#Tigray

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ የተናገሩት ፦

- ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ የሚያስጀምሩት በዋና መ/ቤት የሚገኙ ሰራተኞች በጊዜያዊነት በከተማዋ በማሰማራት ነው። በአሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት የሚሰሩ ሰራተኞችን የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው። ለጊዜው ከዚህ ሰዎች እየሄዱ ይሰራሉ፤ ይመለሳሉ። እዚያም ጥቂት ሰዎች አግኝተናል። ጥቂቶቹ ሰዎች እዚያ ያሉትም አብረው ይሰራሉ።

- አየር መንገዱ የመቐለ በረራን በቀን አንድ ጊዜ በማድረግ የሚያስጀምረው፤ ወደ ከተማዋ ለመጓዝ ፍላጎት ያለው መንገደኛ ቁጥር ባለመታወቁ ነው።

-  በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሽረ ከተማ የመንገደኞች በረራ ይጀምራል። ወደ ሽረ ከተማ የባለሞያዎች ቡድን በመላክ፤ በዚያ ያለውን አውሮፕላን ማረፊያ ያለበትን ሁኔታ ተገምግሟል።

- አክሱምን በተመለከተ አውሮፕላን ማረፊያውን አላየነውም። በወሬ የምንሰማው አውሮፕላን መንደንደሪያው ጉዳት አለው ስለተባለ፤ በደንብ አይተን በደንብ ተጠግኖ ነው በረራ የምንጀምረው። በየደረሰውን የጉዳት መጠን የሚያጠና ቡድን ወደ አክሱም ከተማ የሚላክበት ጊዜ ገና አልተወሰነም።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የጤና ሚኒስቴር፤ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ለመደበኛ አገልግሎት #በኮንትራት ተቀጥረው የነበሩ የጤና ባለሙያዎችን በተመከለተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ፦

" የባለሙያዎቹ ኮንትራት ለ6 ዙር (በአጠቃላይ ለሶስት አመት) በየ6 ወሩ በተደጋጋሚ እየታደሰ እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን ካለዉ የሀብት ዉስንነትና የወረርሽኙ ትርጉም ባለዉ ደረጃ መቀነስ ጋር ተያይዞ በዚህ ወረርሽኝ ዙሪያ የነበረዉ የአጋር ድርጅቶች የበጀት ድጋፍም ስለቆመ ኮንትራታቸዉ እስኪያበቃ ድረስ በዘርፉ ስር ባለዉ በጀትና ክፍታ ቦታ ወደቋሚነት እንዲዘዋወሩ ሲሰራ ቢቆይም በኮንትራት ቆይታ ጊዜ ዉስጥ ቋሚ መሆን ያልቻሉትን እንደ ሀገር 436 ባለሙያዎች ኮንትራታቸዉን ለማቋረጥ ተገደናል፡፡

አገልግሎታቸዉን ታሳቢ በማድረግና ወደ ቋሚነት መዛወር የሚችሉበት እድል እስከ መጨረሻዉ እንዲሞከር ለሶስት ዓመት አራዝመን በቅጥር ብናቆይም የተቀሩትን እነዚህ ባለሙያዎች በኮንትራት በተሰጠው ጊዜ ገደብ መሰረት ለማቋረጥ ተገደናል፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ኮንታራታቸዉ የተቋረጠባቸዉ ባለሙያዎቻችን በተለያዩ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት ባሉ ክፍት መደብ አመልክተው የመቀጠር ዕድሉ አላቸዉ።

በተለይ ሐኪሞችን አስመልክቶ በማቺንግ ፈንድ የተመቻቸ የስራ እድል በክልሎች ደረጃ ስላለ እድሉን በቀላሉ መጠቀም የሚያስችላቸዉ ሲሆን፣ሌሎች ባለሙያዎቻችንም ቢሆኑ ወደ ክልል በመሄድ ባሉት የስራ እድሎች መቀጠር የሚችሉ መሆናቸውና በወሳኝ ሰዓት ያገለገሉበት እና ያካበቱት ልምድ በዉድድር ጊዜ ታሳቢ የሚደረግ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመጠቆም እንወዳለን።"

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ከቀናት በፊት የጤና ባለሞያዎች ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይድረስልን ብለው የፃፉት ግልፅ 👉 ደብዳቤ

@tikvahethiopia
#ታህሳስ19

የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በቁልቢ እና በሐዋሳ እጅግ ከፍተኛ ምዕመን በተገኘበት በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የንግስ በዓሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

ቅዱስነታቸው እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በደረሱበት ወቅት እጅግ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ወደ ቁልቢ እና ሀዋሳ ለዚሁ የንግስ በዓል ያመሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንደገለፁት ከሆነ የበዓሉ ታዳሚ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሆኑንና በዓሉ በሰላም እየተከበረ ስለመሆኑን አመልክተዋል።

Photo Credit : የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት Social Media /

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በትግራይ መዲና መቐለ ዛሬ ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ/ም

" እንኳዕ ንዓመታዊ ክብረ በዓል ቁዱስ ገብሪኤል ኣብፀሓኩም
እንዳ ገብሪኤል መቐለ።
ሎሚ ታሕሳስ 19, 2015 ዓ.ም "

Credit : ቢንያም ግርማይ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ የተናገሩት ፦ - ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ የሚያስጀምሩት በዋና መ/ቤት የሚገኙ ሰራተኞች በጊዜያዊነት በከተማዋ በማሰማራት ነው። በአሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት የሚሰሩ ሰራተኞችን የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው። ለጊዜው ከዚህ ሰዎች እየሄዱ ይሰራሉ፤ ይመለሳሉ። እዚያም ጥቂት ሰዎች አግኝተናል።…
#Mekelle

መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ።

ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች።

ትላንት የበረራ ቴኬት ለማግኘት ብሞክርም አልተሳካልኝም፤ በቀጣይ ቀናትም ያሉት ከወዲሁ ተይዘዋል" ያለችው ሄርሞን አየር መንገዱ በየዕለቱ የሚያደርገድን በረራ እንዲያሳድ ጠይቃለች።

" የምወዳትን እናቴን ድምፅ ከሰማሁ ወራት ተቆጥረዋል፣ አባቴም በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም፤ ቤተሰቦቼም ምን ገጥሟቸው እንደሆነ የማውቀው ነገር የለኝም፤ ወደ መቐለ ሄጄ ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ቸኩያለሁ፤ በረራው ቁጥሩ ጨምሮ ብሄድ ደስ ይለኛል ይሄ የኔ ብቻ ሳይሆን እጅግ የብዙ የትግራይ ተወላጆች ጥያቄ ነው " ስትል ገልፃለች።

ሌላው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ካህሳይ፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በረራ እንደሚጀምር መስማቱ በዛው ያሉትን ቤተሰቦቹን ለማያት ትልቅ ተስፋ እንዳሳደረበት ገልጿል።

ካህሳይ በመቐለ ያሉ ቤተሰቦቹን ሳያይና ድምፃቸውን ሳይሰማ ከዓመት በላይ እንደሆነው ገልጾ ወደመቐለ ለመጓዝ ትኬት ለመቁረጥ ቢሞክርም መሙላቱን አመልክቷል አየር መንገዱም ፤ የበረራ ቁጥር እንዲያሳድግ  ጠይቋል።

በተጨማሪ " በዚህ ወቅት በአውሮፕላን የሚኬደው አማራጭ መንገድ ባለመኖሩም ጭምር በመሆኑ የትኬት ዋጋ አስተያየት ይደረግበት " ብሏል።

በተመሳሳይ ሌሎችም በርካቶች የበረራ ቁጥር እንዲጨምርና የትኬት #ዋጋ ላይ አስተያየት እንዲደረግ እየጠየቁ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ። ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች። ትላንት…
#AddisAbaba #Mekelle

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቐለ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንደተስተካከለ በየዕለቱ የሚካሄደውን በረራ እንደሚያሳድግ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በሰጡት ቃል አየር መንገዱ የአውሮፕላን ችግር እንደሌለበትና በቀን አራትም፣ አምስትም በረራ ማድረግ እንደሚችል ገልፀዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን የተቸገርነው መቀለ የቴሌኮም አገልግሎት ስለሌለ የስልክ ግንኙነት እንኳን ማድረግ አልቻልንም። ከእዛ ለሚመለሱት እንኳን የ boarding pass እና የ baggage process እየተደረገ ያለው አዲስ አበባ ነው። የቴሌኮም ጥገናው እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ስለዚህ ይህ እንደተስተካከለ እኛም በራራውን እንጨምራለን። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ይህ ምናልባት በመጪው #ሶስት እና #አራት ቀናት ሊስተካከል ይችላል። " ሲሉም አክለዋል።

በሌላ በኩል ከየአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ጋር በተያያዘ 3 ሺህ የነበረው አሁን እስከ 9 ሺህ እየተሸጠ እንደሆነ ይነገራል ይህ ለምን ሆነ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

" ዘጠኝ ሺህ የተሸጠው business class ነው " ያሉት አቶ መስፍን " የeconomy class ትኬት ቀድመው የገዙ ሶስት ሺህ ብር ገደማ ነበር፣ በአለም አቀፍ አሰራር መሰረት ትንሽ ዘግይቶ የሚገዛ ደግሞ ወደድ ይላል፣ አራት ሺህ ገደማ ገብቷል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ለበረራ የሚጠቀምበት አውሮፕላን 138 ሰው የሚጭን ቦይንግ 737 መሆኑን ጠቁመዋል።

" ወደፊት ፍላጎቶችን እያየን ከዛም በላይ የመጫን አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖችን መጠቀም እንችላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

#ኤልያስመሰረት

@tikvahethiopia