#USA
ዛሬ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ይጀመራል።
ለዚሁ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አሜሪካ ላይ ተሰባስበዋል።
ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ይኸው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች ፦
- የአየር ንብረት ቀውስ፣
- መልካም አስተዳደር፣
- የምግብ ዋስትና እና የዓለም ጤናን የሚጨምር ሲሆን፣ እንዲሁም የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል።
አሜሪካ ጉባዔው አፍሪካ ቁልፍ የጂኦፖለቲካል ተጫዋች እንደሆነች ዕውቅና በመስጠት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጻለች።
በአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ባይደን በቡድን 20 ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ቦታ እንዲያገኝ ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
በተጫማሪም የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ከአፍሪካ አገራት መካከል " ቋሚ አባል እንዲያካትት " ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ፕሬዝዳንት ባይደን ቁርጠኛ እንደሆኑ ተነግሯል።
በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ለአፍሪካውያን አገራት ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል (#አጎዋ) ጋር በተያያዘ ከተጠቃሚ አገራቱ ንግድ ሚኒስትሮች ጋር የሚካሄደው ጉባኤ ዛሬ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ቢቢሲ ዘግቧል።
#DrAbiyAhmed - " አፍሪካ ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት " በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንትና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።
@tikvahethiopia

በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ?
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦
" ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት።
ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም።
ስርዓተ ትምህርት ከኦሮሚያ ተዋስን አፋን ኦሮሞ የሚሰጠው ኦሮሚያ ነው ይህ በዘመነ ኢህአዴግ ነው።
እዛ ላይ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ምን አለ ትምህርት ክፍል ከመጀመሩ በፊት የክልሉ መዝሙር ይዘመራል፤ የክልሉ ባንዲራ ይሰቀላል የሚል አለ።
ይህን ሙሉ ስርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ነው 4 ትምህርት ቤቶች (አ/አ ያሉ) የጀመሩት። በውቅቱ አጀንዳ ያደረገውም የለም። በዚህ ምክንያት በተለየ ሁኔታ ኦሮሞ ይጠቀማል ተብሎ የታሰበ ነገር አልነበረም።
ከዛ ተማሪዎች እያደር እየሰፉ መጡ ፣ ከየአካባቢው ፍላጎት ያላቸው ፣ በየአካባቢው ተመዝጋቢ እየበዛ መጣ ኦሮሞም የሆነ ያልሆነ መማር የሚፈልግ እየተመዘገበ መጣ።
እና እንዴት አድርገን ነው የካ ላይ የተመዘገበን ሄደህ ኮልፌ ላይ ነው የምትማረው የምንለው ? ለምን በአካባቢው ላይ ባለ ት/ቤት ክፍል የማንከፍትለት ?
በአካባቢው ትም/ቤት ላይ ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር እንዲችሉ ትምህርት ቤት እየተከፈተ (በ403 ትምህርት ቤት ውስጥ) በአፋን ኦሮሞ መማር ተጀመረ ሲጀመር ይኸው ካሪኩለም / ስርዓተ ትምህርት ነው አብሮ እየሄደ ያለው።
መማህራኖች፣ ትምህርት ቤቶች እጃቸው ላይ ያለው ስርዓተ ትምህርት እሱ ነው ስርዓተ ትምህርቱን ተግብሩ ተብሎ ስለተሰጣቸው ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ያለውን ሙሉ ነገር እየተገበሩ መጡ ይኸው ነው። "
የአ/አ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፦
" የሆኑ ት/ቤቶች ላይ ይሄንን ቋንቋ አንሰማም የሚል ይህ መዝሙር መዘመር የለበትም የሚል ጥያቄ ያነሳ አለ። ሌላ ትምህርት ቤቶች ላይ በተለይ አፋን ኦሮሞ ተማሪዎች የሚበዙበት ላይ ሌላ ጥያቄ።
በአማርኛ የሚማሩ/ የአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች ቁጥር ባነሰበት በባንዲራ መዝሙር አላማው አንድ ያደረገ ግን በተለያየ ስትራቴጂ መጥቶ የከተማውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ማደፍረስ ነው። "
ወላጆች እና ተማሪዎች የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ምን ይላሉ ?
ደስ ታቲሌስ ፦
" ... ትምህርት በ ' #አፍ_መፍቻ_ቋንቋ ' መማር እና የአንድ ክልልን ባንዲራን መስቀልና መዝሙር ማዘመር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
ለምሳሌ ያህል ፦ አብዛኛዎችን የትምህርት አይነቶች የምንማረው በእንግሊዘኛ ነው። ነገር ግን የእንግሊዝን መዝሙር አልዘመርንም ፣ ባንዲራቸውም በትምህርት ቤቶቻችን ላይ አልተሰቀለም።
ይህንን ያልኩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወይንም በመንግስት የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።
የግል ትም/ቤትን አይጨምርም። አሁን ግን የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እየተዘመረ እና ባንዲራው እየተሰቀለ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በራሱ ወጪ በሰራቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።
ሲቀጥል ቋንቋውን ማስተማርም ካስፈለገ የሌላውን ክልል መዝሙር እንዲዘምሩ በማስደረግ መሆን የለበትም።
በከተማው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ እኮ የአማራ ክልል ባንዲራ አልተሰቀለም ፤ የአማራ ክልልን መዝሙር አልተዘመረም።
አሁን ላይ እየታየ ያለው ነገር እና ለድርጊቱ የከተማ አስተዳደር እየሰጠ ያለው መልስ ፍፁም የተለያየ ነው። "
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/ADDIS-ABABA-12-13

Telegraph
ADDIS ABABA
#ADDIS_ABABA በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት ከኦሮሚያ ክልላዊ ባንዲራ እና መዝሙር ጋር ተያይዞ የነበረው ሁኔታ ዘንድሮ በተለይም ደግሞ ከሰሞኑን ተባብሶ ነበር። ይኸውም ችግር በተለያዩ ወገኖች እና በመንግስት አካላት የተለያየ ማባራሪያ እየተሰጠበት ነው። ወላጆችም የሚሉት አላችሁ። ነዋሪዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር…
ሀሰተኛ የትምህርት መረጃ ...
(በዳውሮ ዞን)
በዳውሮ ዞን ፤ ከጪ በተባለው ወረዳ ለመጀመሪያ ዙር በተደረገ ማጣራት ከ264 የትምህርት መረጃ 127 #ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱ ተሰምቷል።
ሀሰተኛ ሆኖ ከተገኘው የትምህርት መረጃ መካከል 6ቱ #የአመራርና ቀሪው #የመንግስት_ሰራተኞች ነው።
የሁለተኛ ዙሪ የማጥራት ስራ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በዚሁ ዞን ፤ ቶጫ በተባለው ወረዳ በመጀመሪያ ዙር ከተደረገው ማጣራት ከ565 የትምህርት መረጃ የ218 ሰዎች #ሀሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
መረጃቸው ወደ ግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኮ ከተጣራው ከ565 የመንግስት ሰራተኞች መካካል የ210 ባለሙያዎችና የ8 #አመራሮች የትምህርት መረጃ ነው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘው።
ይኸው የማጣራት ስራ ይቀጥላል ተብሏል።
መረጃው ከዳውሮ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ? የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦ " ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት። ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም። ስርዓተ…
#AddisAbabaPolice
አዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በህጋዊ ሽፋን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በሚያውኩ ልዩ ልዩ ህገወጥ ተግባር ላይ ይሳተፋሉ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦችን አስጠነቀቀ።
ፖሊስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ ዛሬ ታህሳስ 4 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩ ተግባር በሰላም ሲካሄድ መዋሉን ገልጿል።
ፖሊስ በመግለጫው ፤ በህጋዊ ሽፋን የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በሚያውኩ ልዩ ልዩ ህገወጥ ተግባር ላይ ይሳተፋሉ ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድኖችና ግለሰቦች " አጥፊ " ሲል ከጠራው ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቋል።
አዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን የረብሻ እና የጥፋት ብሎም የውድመት መድረክ ለማድረገው በታቀደ ህገወጥ ተግባር ላይ አንዳንድ የባልደራስ ለእውነተኛዲሞክራሲ አባላት ቀጥታኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በማስረጃ እንደተረጋገጠ ገልጿል።
በጥፋት ድርጊቱ ላይ ቀጥተኛ ተሣትፎ የነበራቸው አንዳንድ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውጭ ሆነው ችግሩን በማቀጣጠል እና ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ሰብረው በመግባት በትምህርት ቤት ሀብት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስ ያደረጉ የጥፋት አጀንዳ የተቀበሉ ሌሎች ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ ተይዘው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው ብሏል።
" የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንንት በማረገገጥ የከተማዋን ፀጥታ የማስጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎብኛል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ገልጾ ይህን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።
የተማሪ ቤተሠቦችና ህብረተሰቡ እውነታውን በመረዳት ልጆቹን በመምከር ሃላፊነቱን እንዲወጣ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ቀደም ታስራ ከእስር የተፈታችው መስከረም አበራ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ባለቤቷ መናገሩን ቢቢሲ ዘግቧል።
የመስከረም አበራ ባለቤት አቶ ፍጹም ገ/ሚካኤል እንደተናግረው ፤ ከሰዓት 10፡30 አካባቢ " ሃያ ሁለት / 22 " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አብረው ሳሉ ሲቪል እና የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች መጥተው መስከረምን ይዘው ሄደዋል።
መስከረም የግለሰቦቹን ማንነት ስትጠይቅ የፌደራል ፖሊስ አባላት መሆናቸውን ከገለጹ በኋላ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መሥሪያ ቤት ይዘዋት እንደሚሄዱ ተናግረው በመኪና እንደወሰዷት ባለቤቷ ፍጹም ገ/ሚካኤል አስረድቷል።
ፍጹም እንደሚለው ባለቤቱ ታስራ ወደምትገኝበት ሜክሲኮ የፌደራል ወንጀል ምርመራ አቀንቶ መስከረምን ማግኘቱንና በምን ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር እንደዋለች እንደማታውቅ ተናግረዋል።

Photo
" መቼም በሰው ሞት የሚደሰት ያለ አይመስለኝም። ይሁንና እያንዳንዱ ሰው በሰራው ወንጀል በሕግ መቀጣት አለበት። " - የሟች እናት
ባለፈው ጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑትን ወ/ሮ ጁዋሪያ መሐመድ ሱብእስ ጅግጅጋ አየር ማረፊያ ውስጥ ተኩሶ የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል በሞት እንዲቀጣ እንደተፈረደበት ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።
ትናንት በጅግጅጋ ከተማ የጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩትን ጁዋሪያ መሐመድን በመግደል ተጠርጥሮ ክስ የተመሰረተብት የፌደራል ፖሊስ አባል በሞት እንዲቀጣ የወሰነ ሲሆን፣ ጥፋተኛ የተባለ ግለሰብ ይጋባኝ የማለት መብት እንዳለውም አመላክቷል።
ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው የሞት ቅጣት ውሳኔን ተከትሎ የሟች እህት የሆኑትን ፈሂማ መሐመድ በሰጡት ቃል ፥ የተሰጠው ፍርድ ተገቢ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
“ መቼም በሰው ሞት የሚደሰት ያለ አይመስለኝም። ይሁንና እያንዳንዱ ሰው በሰራው ወንጀል በሕግ መቀጣት አለበት። እንደ ቤተሰብ ውሳኔው ብርታት ሆኖናል። ይህ ውሳኔ ደግሞ የሚያሳየው መንግሥት፣ ሕዝብ እና ሕጉ ከእኛ ጎን እንደሆኑ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ሶማልኛው ክፍል ተናግረዋል።

#ETA
የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሁን በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ አሳሰበ።
ባለሥልጣኑ አሁን በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን አግባብ ማየት አስፈላጊ ሆኖ በማግኝቱ እውቅና በሰጣቸው የትምህርት መስኮች በትምህርት ላይ የሚገኙ የተማሪዎችን የስም ዝርዝር የያዘ መረጃ በሶፍትና በሀርድ ኮፒ በማጠናቀር በ30 ቀናት ውስጥ እንዲልኩ አሳስቧል፡፡
የሚላከው የተማሪዎች መረጃ #በፕሬዝዳንት ወይም #በበላይ_ኃላፊ ተፈርሞ መውጣት እንዳለበት ከዚህ ውጪ ፈራሚ አካል ካለ ስምና ኃላፊነት የሚገልጽ ደብዳቤ በነዚሁ የበላይ ኃላፊዎች እንዲገለጽ እና የተማሪዎችን መረጃ በተናጥል በሚልኩ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

#USA ዛሬ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ይጀመራል። ለዚሁ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አሜሪካ ላይ ተሰባስበዋል። ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ይኸው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች ፦ - የአየር ንብረት ቀውስ፣ - መልካም አስተዳደር፣…
#USA #ETHIOPIA
በአሜሪካ ፤ የአሜሪካ-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ትላንት መካሄድ ጀምሯል። ይኸው ሶስት ቀን እንደሚቆይ የተነገረው የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ።
ከዚሁ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ምክክር አድርገዋል።
- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሳሊቫን ጋር የተወያዩ ሲሆን ውይይቱ በጦርነቱ ማቆም አተገባበር፣ በመንግሥት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ሥራዎች እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማደስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።
- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር የተወያዩ ሲሆን ይህን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው እንዲሁም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገፁ ውይይቱን በተመለከተ መረጃ አጋርተዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦
ከብሊንከን ጋር ውጤታማ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልፀዋል። ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት አሜሪካ ላበረከተችው አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል። ለበርካታ አስርት አመታት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ሆና ቆይታለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን አጋርነታችንን ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተናል ብለዋል።
አንቶኒ ብሊንከን ፦
ዶ/ር ዐቢይ በጉባኤው ላይ እና በዋሽንግቶን በመገኘታቸው በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። የስምምነቱ ዜና ለመላው ሀገሪቱ ጥሩ ዜና መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ንግግር በማድረጋቸው (በስልክ) በጣም ደስተኛ እንደነበሩና አሁን ደግሞ በአካል መገናኘታቸው ጥሩ መሆኑን ገልፀዋል።

#USA #ETHIOPIA በአሜሪካ ፤ የአሜሪካ-አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ትላንት መካሄድ ጀምሯል። ይኸው ሶስት ቀን እንደሚቆይ የተነገረው የመሪዎች ጉባኤ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ። ከዚሁ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ምክክር አድርገዋል። - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት…
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፦
• አንቶኒ ብሊንከን የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸምን አድንቀዋል።
• የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ አቅርቦትን ለማሻሻል እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት ለመመለስ የወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል።
• ብሊንከን የስምምነቱ ተፈፃሚነት የተፋጠነ እንዲሆን አሳስበው ፤ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሰብአዊ መብቶች ተቆጣጣሪዎች ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች እንዲንቀሳቀሱ ጠይቀዋል።
• እንደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ብሊንከን የኤርትራ ኃይሎች በፍጥነት ከኢትዮጵያ ለቀው መውጣት አስፈላጊነት ላይ የተወያዩ ሲሆን ይህም ከትግራይ ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት ጋር ጎን ለጎን መሆኑ ተመላክቷል።
• አሜሪካ፣ በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ስምምነት ለማሳለጥ እንዲሁም ስምምነቱ መተግበሩን ከሚያረጋግጠው ኅብረቱ ጎን ለመቆም ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች።

" የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት ይደረግ "
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የፌዴራል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን #በተሿሚዎች፣ #በተመራጮች ወይም #በመንግሥት_ሠራተኞች ላይ እያከናወነ ያለው የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።
በ2002 ዓ/ም በወጣው የሀብት ማሳወቂያና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ድንጋጌ መሠረት፦
👉 የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣
👉 ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
👉 ሚኒስትሮች፣
👉 ሚኒስትር ዴኤታዎች፣
👉 ኮሚሽነሮች፣
👉 ምክትል ኮሚሽነሮች፣
👉 ዋና ዳይሬክተሮች፣
👉 ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፣ እንዲሁም #ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ #ግዴታ ጥሎባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ለኮሚሽኑ ያስመዘገቡትን ሀብት መረጃ በሚስጥር መያዝና ለሕዝብ ይፋ አለማድረግ ከአዋጁ ጋር የሚፃረር ድርጊት እንደሆነ አስረድቷል፡፡
በተለይም በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሥነ ምግባር መከታተያ የሥራ ክፍሎች በየተቋማቸው ያለውን የሀብት ምዝገባ መረጃን ለማንኛውም መረጃ ጠያቂ እንዲሰጡ አለማድረግ፣ ወይም ምቹ ሁኔታ አለመፍጠር የሕገ መንግሥቱን የግልጽነትና ተጠያቂነት ድንጋጌንና የሀብት ማስመዝገቢያና ማሳወቂያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ጽንሰ ሐሳብና መሠረታዊ ዓላማን ግምት ውስጥ ያላስገባ መሆኑን አስታውቋል፡፡
መረጃ ያለመስጠት ድርጊት ለተጀመረው የሙስና ትግል ምንም ዓይነት አበርክቶ የሌለው በመሆኑ የሀብት ምዝገባ መረጃ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድ ተቋሙ ጠይቋል፡፡
(የኢ/ሕ/ዕ/ጠ/ተቋም ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ ከላይ ተይይዟል)
#Reporter
#EthiopiaInstitutionoftheOmbudsman