TIKVAH-ETHIOPIA
" እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " - ተፈናቃይ በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ባለው የፀጥታ ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለዋል ፤ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል። እንደ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ዘገባ ተፈናቃይ ወገኖች / ህይወታቸውን ለማትረፍ የሸሹ ወገኖች ሰላምን ፍለጋ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ በእግር ታጉዘው ጊዳአያና ወረዳ መግባት ችለዋል። በወረዳው…
" ለሌላው ሰሞነኛ ወሬ ሆኖ ቢያልፍም ለእኛ ለቤተሰቦች ግን ዘውትር ሀዘን እና ጭንቀት ነው " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል
በኦሮሚያ ውስጥ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ፣ ብዙሃንን ከቄያቸው እያፈናቀለ፣ እያስራበ ሰርተው እንዳይበሉ ወጥተድ እንዳይገቡ እያደረገ ያለው ሁኔታ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰብ አባላቶቻችን ጠይቀዋል።
በነቀምቴ ከተማ ተወልዶ ያደገና ቤተሰቦቹ ምስራቅ ወለጋ የሚገኙ አንድ የቤተሰባችን አባል፤ " ምንም እንኳን የንፁሃን ግድያ፣ መፈናቀል፣ መንገላታት ለሌላው የአንድና የሁለት ቀን ወሬ/አጀንዳ ሆኖ ቢያልፍም እኛ ቤተሰቦቻችን በችግር ውስጥ ያሉ ግን በየዕለቱ ሀዘን፣ ሰቆቃ፣ ጭንቀት እንደተደራረበብን ነው፤ ይህ ደግሞ ዓመታትን አስቆጥሯል " ብሏል።
" የዜጎች ሞትና ስቃይ በማንነታቸው መጠቃት መንገላታት መዋከብ ከቀናት ዜና እና ከመግለጫ አያልፍም ስቃዩ የደረሰበት፣ ልጁን ያጣ ወላጆቹን ያጣ በብዙ ሀዘን ውስጥ ነው እየኖረ ያለው አሁንም ካለው ሌላ ችግር ሳይደረብ መፍትሄ ይፈለግ " ብሏል።
በቀጣናው ያለው ችግር እየተወሳሰበ ተዋናይ ወገኖችም እየበዙ ተጎጂዎችም ቁጥራቸው እያየለ መምጣቱን ጠቁሟል።
አንድ በአዲስ አበባ ነዋሪነቱን ያደረገ የቤተሰባንች አባል ፤ በወለጋ ባለው ሁኔታ ከዚህ ቀደም ቤተሰቦቹን እንዳጣ ገልጾ፤ ፍትህ እንዳለገኘ፤ ዛሬም የቀሩት ቤተሰቦቹ በችግር ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል።
" በጣም የሚያስገርመው ይሄን ሁሉ ጊዜ ያለውን ችግር መፍታት እንዴት አይቻልም መንግስት ዋናው ስራ ይሄ አይደለም ወይ? በመንግስት ውስጥ ሆነው ይሄ ችግር እንዲቀጥል የሚያደርጉ፤ ስልጣን ላይ ያሉ ለጥፋው ጥፋት የሚጠየቁትስ መቼ ነው? " ሲል ጠይቋል።
አሁንም ያለው ችግር እንዲፈታ ንፁሃን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ድምፁን አሰምቷል።
@tikvahethiopia

Photo
" አሁን ላይ ቅድሚያ የተሰጠው ለድምፅ አገልግሎት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም
የኢትዮ ቴሌኮም ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሳይ ውብሸት ፤ ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል በዚህ ሳምንት በሽረ ከተማ ሙሉ የስልክ አገልግሎት መጀመሩን ተናግረዋል።
አቶ መሳይ ፤ " ሽሬ ሙሉ በሙሉ ጀምሯል። ሰው በደንብ እየተጠቀመ ነው። ባገኘናቸው የኃይል አማራጮች ተጠቅመን አሁን ሙሉ ማህበረሰቡ አገልግሎት ማግኘት ጅምሯል በተለይ ደግሞ ከእሁድ ጀምሮ። በዋናነት ኦፕቲካል ፋይበር መሬት ስር ትራንስሚሽን የምንጠቀምበትን ፋይበር ጥገና ነው ያከናወነው 270 ኪ/ሜ በላይ የሆነ ጥገና ተሰርቶ ኮር ሳይቱን የማገናኘት ስራ ነው የተጠናቀቀው መልሶ ደግሞ ኃይል የመስጠትና ያሉ ጄነሬተሮቻችን ጠግነን ከነዳጅ ኃይል እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ነው የተሰራው " ብለዋል።
ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡ ቤተሰቦቻቸው ሽረ የሚገኙ ነዋሪዎች የስልክ አገልግሎት ከጀመረ ሳምንት እንዳሆነው ገልፀው የጥራት ችግር ግን እንዳለ አመላክተዋል። አንድ በአክሱም ቤተሰቦቹ ያሉ የአክሱም ተወላጅ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጠው ቃል፤ በሙከራ ላይ ባለው ኔትዎርክ በአክሱም ያሉ ቤተሰቦቹን እንዳገኘ ገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም በአድዋ እንዲሁም በአክሱም አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን የገለፁት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ መሳይ ውብሸት ፤ መላውን ትግራይ የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ ቅድሚያ የተሰጠው ለድምፅ አገልግሎት ሲሆን በቀጣይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት ይታያል ሲሉ ለሬድዮ ጣባያው ተናግረዋል።

#Tigray መቐለን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ከ18 ወራት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት ማግኘት እንደጀመሩ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በመቐለ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ሪጅን ሠራተኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ሰራተኞቹ ከትናንት ማክሰኞ ምሽት ጀምሮ መቐለን ጨምሮ ፦ - መኾኒ ፣ - ውቅሮ፣ - ዓዲግራት፣ - ዓብይዓዲ እና ሌሎች በአካባቢው…
ከረጅም ጊዜ በኃላ ሽረ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷ ተገለፀ።
ሽረ ከተማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ማስታወቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
ሽረ ከተማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ማስታወቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
@tikvahethiopia
የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያ "ብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ " ተብሎ እንዲጠራ የከተማው ም/ቤት አጸደቀ።
የሰቆጣ ከተማ ም/ቤት ባካሔደው አስቸኳይ ጉባኤ ነው የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያን " በብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ" በሚል ስያሜ እንዲፀድቅ ያደረገው።
ጤና ጣቢያው በብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ስም እንዲሰየም የተደረገበትን ዋነኛ ዓላማ ለም/ቤቱ የተብራራ ሲሆን በዚህም፦
- ብፁዕነታቸው ባለፈው ዓመት ማኅበረሰቡ በጦርነት ምክኒያት ተፈናቅሎ በነበረበት ወቅት ያበረከቱት አስተዋጽኦና መልካም ሥራቸው ሕያው ሆኖ እንዲቀጥል፤
- ብፁነታቸው ሙስሊም፣ ክርስቲያን ዘርና ቋንቋ ሳይለዩ ሁሉም እናቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያንና ማኅበረሰብ የሚበሉትና የሚጠጡት አጥተው ሲቸገሩ ካለው ለምነው የሌለው በመስጠት፣ መንግስት ሠራተኞች ለዐራት ወራት ያህል ደሞዝ በመቋረጡ ምክኒያት ሲቸገሩ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ከባለሃብቱና ከበጎ አድራጊዎች ገንዘብ አፈላልገው በመስጠት ታሪክ የማይረሳው ሥራ በመሥራታቸው፤
- ከሕዝባቸውና ማኅበረሰባቸው ጋር ችግሩን ሁሉ ተጋፍጠው በየቦታው ገንዘብ እያሰባሰቡ፣ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ ለምዕመናን ትምህርት በመስጠትና በማጽናናታቸው፤
- የጤና ተቋማት እንዳይዘነጉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ከ160 በላይ እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በማድረጋቸው፤ ያበረከቱትን ሕያው ሥራ እውቅና ለመስጠትና ትውልዱ ከመልካምና ከማይሞት ሥራቸው እንዲማርና የእሳቸውን ፈለግ እንዲከተል፣ በጤና ተቋም አገልግሎት የሚያገኙ አካላት እንዲዘክሩ የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያ የሚለው ስም" ብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ" ተብሎ እንዲሰየም ተደርጓል።
መረጃው የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ነው።

#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት፤ ከትናንት ኀዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ በጊዜያዊነት መታገዱ ተገልጿል።
አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መሰጠቱንም የከተማ አስተዳደሩን ዋቢ አድርጎ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#ExitExam የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፦ " የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል። ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ። በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው…
#MoE
• መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።
• 200, 000 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።
መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።
መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር ) በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ እንደገለጹት መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ ይሰጣል።
የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ አስረድተዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት አቶ ሰይድ " ይህ የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ነው " ብለዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው #ከወዲሁ_ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።
በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
(ትምህርት ሚኒስቴር)

" ሰሞኑን ባምቢሲ ወረዳ በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ብቻ 16 ሺህ ሰላማዊ ሰዎች ገብተዋል " - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ሰላምን ፍለጋ እና ህይወታቸውን ለማትረፍ እየሸሹ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ባምቢሶ ወረዳ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ዶቼ ቨለ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ፣ ቤጊ ፣ መንዲ አካባቢ በሚደረጉ ግጭቶችና በዘር ላይ ባነጣጠሩ ጥቃቶች በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል ፤ በርካቶችም ከቄያቸው ተፈናቅለዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃል ፤ ከግጭትና ጥቃቱ አምልጠዉ ሰሞኑን ባምቢሲ ወረዳ በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ብቻ 16 ሺህ ሰላማዊ ሰዎች ገብተዋል።
ኮሚሽኑ ከባለፈው ዓመት ህዳር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከምዕራብ ወለጋ ሰዎች ወደ ባምባሲ መፈናቀላቸውን አመልክቶ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከዞኑ ማናስቡ ወረዳ፣ ቤጊና ቆንዳላ ወረዳዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ባምባሲ መፈናቀላቸውን ገልጿል።
በዚህም በወረዳው ያለው የተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የገለፀው ኮሚሽኑ ፤ በወረዳው 16 ሺህ በላይ ከምዕራብ ወለጋ እና ማኦ ኮሞ ወረዳ ተፈናቅለው በመጠለያ ይገኛሉ ሲል ለሬድዮ ጣቢያው አሳውቋል።

#Tigray #Afar
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሎጅስቲክስ ክላስተር ትብብር ወሳኝ የሆኑ ህይወት አድን ድጋፎችን በአየር መቐለ መድረሳቸውን አሳውቋል።
መቐለ በአየር ከደረሰው ህይወት አድን ድጋፍ መካከል የUNICEF ክትባቶች እና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጎዱ እናቶች እና ህፃናት የሚውል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፍ የተካተተበት ነው።
UNICEF ይፋ ባደረገው መረጃ 1.4 ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶችን መቐለ ደርሷል። ክትባቶቹ በክልሉ 50,000 ህጻናትን እና እናቶችን ለመከተብ እንደሚውሉ የሚውሉ ናቸው ተብሏል። መቐለ ከደረሱት ክትባቶች አሁን ላይ በክልሉ ላሉ ጤና ጣቢያዎች እየተከፋፈሉ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ፤ በዩናይትድ ኪንግደም ድጋፍ በሰሜን ምዕራብ አፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የምግብ እርዳታ የያዙ ተሽከርካሪዎች ስለመንቀሳቀሳቸው ተሰምቷል።
እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል እንዲደረስ በዩናይትድ ኪንግደም የተሰጠው ወሳኝ የሆኑ ህይወት አድን ድጋፎችን የያዙ 54 ተሽከርካሪዎች መሆናቸው ተነግሯል።