TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ነገ የሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ... የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የተናገሩት ፦ " በእጣው ብቁ የሚሆኑት የ20/80 (ስቱዲዮ ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን የ84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ።…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት ዕጣ #ዛሬ_ከሰዓት ይወጣል።

ይኸው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሚጠብቀው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ይተላለፋል ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ/Addis TV የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በቀጥታ ስርጭት እንደሚያስተለልፈው ቀደም ብሎ አሳውቋል።

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፃ ፤ ዛሬ ዕጣ የሚወጣባቸው በ20/80 18,930 ቤቶች እና በ40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25, 791 ቤቶች ሲሆኑ ከፍተኛ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የባለ ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት #ተጨማሪ 300 (ሶስት መቶ) ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባርና ለአዲሰ ተመዝጋቢዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR ዛሬ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ይካሄዳል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ቀርበው ከም/ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ፤ የመንግስትንም አቋም ያሳውቃሉ። @tikvahethiopia
#Live

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር 1ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

የምክር ቤት አባላት ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ እየተሰጠባቸው ይገኛል።

የምክር ቤት አባላቱ ፦

- የስምምነቱ ሂደት እንደምታውና ፋይዳው ምንድነው ?

- በጦርነቱ የተጐዱ አካባቢዎችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመልሶ ለመገንባት ምን ዝግጅት ተደርጓል ?

- አንዳንዶቹ ስምምነቱ ከTPLF እንጂ ከ TDF ጋር እይደለም ? ... ወዘተ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦችን እየሠነዘሩ ይገኛሉ ፤ የእነኚህ አካላት ፍላጎት ምንድን ነው ? ውሳኔዎችንስ ተግባራዊ ለማድረግ እነቅፋት አይሆንም ወይ?

- የምክክር ኮሚሽን የእስካሁኑ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ እንዲሁም በውይይት ሂደቱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች ምንድን ናቸው ?

- ውይይቱ ተሳክቶ መላው የሀገራችን ሕዝቦች ወደ ሚናፍቁት ልማት ፊታቸውን እንዲያዞሩ ከባለድርሻ አካላት ማለትም ከምሁራ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ወጣቶችና ከመላው ሕዝብ ምን ይጠበቃል ? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች መሰንዘራቸውን ከህ/ተ/ም/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በአሁን ሰዓት ጠ/ሚኒስትሩ ለተጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡበት ይገኛል።

የምክር ቤቱን ጉባኤ በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ፣ እና በሌሎችም የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች መከታተል ይቻላል። በጉዞ ላይ ያላችሁም በሬድዮ ማድመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Live የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር 1ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው። የምክር ቤት አባላት ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ እየተሰጠባቸው ይገኛል። የምክር ቤት አባላቱ ፦ - የስምምነቱ ሂደት እንደምታውና ፋይዳው ምንድነው ? - በጦርነቱ የተጐዱ አካባቢዎችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመልሶ ለመገንባት ምን ዝግጅት ተደርጓል ? - አንዳንዶቹ…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ " ወልቃይት " ምን አሉ ?

ዛሬ በፓርላማ ቀርበው ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ " ወልቃይት " ጉዳይ ይህን ብለዋል ፦

" ብዙ አነባለሁ ፤ ብዙ እሰማለሁ ወልቃይትን በሚመለከት የሚነገሩ ሽረባዎች ፣ ሴራዎች ... Conspiracy ብዙ እሰማለሁ።

የኢትዮጵያ መንግስት በእነዚህ ሽረባዎች ውስጥ እጁ የለበትም።

የወልቃይት ህዝብ እንዲገነዘብ የምንፈልገው የሚወራው የሚናፈሰው አሉባልታ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት እጁ የለበትም።

እኛ ደቡብ አፍሪካ የሄድነው ወልቃይት ወደ አማራ ይሁን ወደ ትግራይ ይሁን የሚለውን ለመወሰን አይደለም ፤ የፕሪቶሪያው Summit ይሄን ለመወሰን ስልጣን የለውም።

ምን አገባውና ነው የኢትዮጵያን መሬት እዛ ይሂድ እዚህ ይሂድ የሚለው ?

እኛ እዛ የሄድነው እንዴት ሰላም አምጥተን ችግሮቻችንን በንግግር እንፍታ ለማለት ነው። ለምን ወልቃይት ተስቦ እዛ ውስጥ እንደሚገባ አላውቅም።

ወልቃይት ብቻ አይደለም ሰሜን ሸዋ ላይ ኦሮሚያ እና አማራ ጥያቄ አላቸው እሱም ደቡብ አፍሪካ ይሂድ ? ሲዳማ እና ወላይታ ብላቴ ላይ ጥያቄ አላቸው እሱም ደቡብ አፍሪካ ይሂድ ? እኛ አሰራር የለንም ? ልምምድ የለንም ? ቦታው አይደለም።

የተስማማነው በኢትዮጵያ ህግ እና ስርዓት ይፈፀም ነው። ከህገመንግስት በፊት ነው የተወሰደው ፤ በጉልበት ነው የተወሰደው ላሉት የእኔ ፍላጎት ያ ስህተት እንዳይደገም ነው።

ዛሬን በጉልበት ነገ ታግሰን በጉልበት ከሆነ ዘላቂ ሰላም አያመጣም። ወልቃይት ብንፈልግም ባንፈልግም የተወላገደ አማርኛ፣ የተወላገደ ትግርኛ የሚናገር የሁለቱ ህዝቦች ድልድይ የሆነ ህዝብ ነው።

ሁለቱንም ቋንቋ የሚናገር፣ የተጋባ የተዋለደ ህዝብ ነው። ወልቃይቴነቱን ነው አትንኩብኝ ያለው እንጂ ከእንግዲህ ከትግራይ ጋራ አልገናኝም አልነጋገርም አላለም ፤ አይችልም ቢልም።

ይሄንን በህግ እና ስርዓት ብንፈፅም ለወልቃይትም ይጠቅማል ፣ ለአማራ ይጠቅማል፣ ለትግራይ ይጠቅማል የሚጎዳው ነገር የለም።

በህግ እና ስርዓት እንፈፅም የሚለውን ነገር ከብዙ ተንኮል ጋር ማያያዝ አስፈላጊ አይደለም።

እዛ አካባቢ ጥያቄ ረዘም ላለ ጊዜ ነበረ ፤ ለዛ ብለን ነው ኮሚሽን ያቋቋምነው ከዚህ ቀደም ገልጫለሁ ፤ አሁንም ያኔም የነበረን አቋም በህግ አግባብ በምክክር በውይይት ይፈታ የሚል ነው። ይህ ማንም ይጎዳል ብዬ አልገምትም ውጤቱን በጋራ እናየዋለን።

ዋናው ፍላጎት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ንግግር ያስፈልጋል።

የተሰጣቸውን ስራ በትክክል የማይሰሩ ሰዎች የፌዴራል መንግስት እያሉ ብዙ ሽረባ እንደሚሰሩ እናውቃለን። ሂደቱን ላለማበላሸት ነው ዝም ያልነው። ሂደቱ መስመር ከያዘ በኃላ ለህዝብ ግልፅ እናደርጋለን።

ስራውን መስራት አለበት እያንዳንዱ ዞን ፣ እያንዳንዱ ወረዳ ተንጠልጥሎ ፌዴራል ምናንም ሳይሆን ስራውን መስራት አለበት መሬት ላይ ያለውን ያን ካደረገ ሌላው ጉዳይ እዳው ገብስ ነው ፤ ብዙም የሚያስቸግር አይደለም።

... ሁለት ነገሮች አሉ ፤ ከአማራ ወገን ላለፉት 30 ዓመታት ብዙ ወልቃይቴዎች ሲፈናቀሉ፣ ሲሰደዱ ኖረዋል እነሱ በሌሉበት ሪፈረንደም ቢባል የተመናመነ ህዝብ ነውና እንጎዳለን፤ በትግራይ በኩል አሁን በተፈጠረው ግጭት ብዙ ሰው ወጥቷል ስለወጣ አሁን ባለው ቢወሰን አማራ ክልል advantage ይወስዳል የሚሉ ስሞታዎች ይሰማሉ።

ወይቃይት የወልቃይቴ ነው ይታወቃል። ከአድዋም የሄደ ከደብረ ማርቆስም የሄደ ሰው ሊኖር ይችላል ግን ወልቃይቴ ይታወቃል ፤ አትላንታም ይኑር አውስትራሊያም ይኑር ጅማም ይኑር ስለዛ ቦታ ሃሳብ እንዲሰጥ እድል ካልተሰጠው በስተቀር ዘላቂ ሰላም አያመጣም።

ጉዳዩ ወደዛ ስለሄደ ወደዚህ ስለመጣ ሳይሆን ያ ህዝብ የራሱን fate እንዲወስን ዲሞክራሲያዊ እድል እንዲያገኝ ማድረግ ከቻልን ብቻ ነው መፍትሄ የሚመጣው። እና እነዛን ችግሮች በሚቀርፍ መንገድ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ። ጊዜ የወሰድነው ፣ ጊዜ የጠበቅነው ለዛነውና ብዙ ስጋት ባይኖር በተረጋጋ መንፈስ ቢሰራ ዘላቂ ሰላም ያመጣል ቢባል መልካም ነው።

አለበለዚያ ከህገመንግስት በፊት TPLF በግድ ስለወሰደ አሁን እኛ በግድ ወስደን እዛ ዘመን በሙሉ ወታደር ልናቆም አንችልም። በስምምነት ካልሆነ በወታደር ነው የሚሆነው በወታደር ከሆነ ዘላቂ አይሆንም ጊዜ ይፈታዋል። አሁን ያለን ሰዎች ስናረጅ ስንደክም ልክ አሁን የተፈጠረው ይፈጠራል። ያ አካባቢ ሊለማ ስለሚችል ሰላማዊ በሆነ መንገድ ወደልማት እንዲገባ ቢደረግ ለሁሉም ጠቃሚ ይመስለኛል ።

እዚህ አካባቢ ያሉ ተንኮሎች፣ conspiracy ቢቀሩ ጥሩ ነው። መሬት ላይ ያለው ግን ስራውን ቢሰራ መልካም ይሆናል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከደቂቃዎች በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በይፋ ይካሄዳል።

ይኸው የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ይሰራጫል።

ዛሬ ዕጣ የሚወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፦

👉 በ20/80 18,930 ቤቶች
👉 በ40/60 6,843 ቤቶች
👉 አጠቃላይ 25, 791 ቤቶች

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፃ #ተጨማሪ 300 (ሶስት መቶ) ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባርና ለአዲሰ ተመዝጋቢዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ ተደርጓል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ የዕጣውን አወጣጥ ሥነሥርዓት ተከታትለን የምናሳውቅ ሲሆን የሚመቻችሁ በአዲስ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት መከታተል እንደምትችሉ ለመጠቆም እንወዳለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት #በቀጥታ እንደሚያሰራጨው አሳውቋል፤መከታተል ትችላላችሁ። ስነስርዓቱ ከ 8:30 ጀምሮ ነው የሚካሄደው። @tikvahethiopia
#Update

ከዚህ ቀደም ተሰርዞ የነበረው የአ/አ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በይፋ መካሄድ ጀምሯል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የከተማው አስታዳደር የስራ ኃላፊዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ታዛቢዎች ተገኝተዋል።

የዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱን በብሄራዊ ቴሌቪዥን (etv) እንዲሁም በአዲስ ቴሌቪዥን በቀጥታ መከታተል ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከዚህ ቀደም ተሰርዞ የነበረው የአ/አ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በይፋ መካሄድ ጀምሯል። ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የከተማው አስታዳደር የስራ ኃላፊዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ታዛቢዎች ተገኝተዋል። የዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱን በብሄራዊ ቴሌቪዥን (etv) እንዲሁም በአዲስ ቴሌቪዥን በቀጥታ መከታተል ይቻላል። @tikvahethiopia
#Update

በአሁን ሰዓት እያተካሄደ ባለው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ላይ

በ20/80 ፦

- ባለ 1 መኝታ  3300 ቤቶች
- ባለ 2 መኝታ  7171 ቤቶች
- ባለ 3 መኝታ  300 ቤቶች ይወጣሉ ።

በ40/60 ፦

- ባለ 1 መኝት 1870 ቤቶች
- ባለ 2 መኝታ 8159 ቤቶች
- ባለ 3 መኝታ 753  ቤቶች ናቸው
በአጠቃላይ 25 ሺ791 ቤቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል

Credit : AMN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በመመሪያ ቁጥር 3/2011 በተገለፀው መሰረት ፦ - የመንግስት ሰራተኞች 👉 20 በመቶ (20%) - ሴቶች 👉 30 በመቶ (30%) - አካል ጉዳተኞች 👉 5 በመቶ (5%) - አጠቃላይ ተመዝጋቢዎች 👉 45 በመቶ (45%) በዕጣ የቤት ባለዕድለኞች ይለያሉ። @tikvahethiopia
እንደ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ፤ በዛሬው ዕለት በዕጣ ለባለ ዕድለኞች የሚተላለፉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ግንባታ  ፦

👉 የ20/80 ከ96 በመቶ (96%) በላይ
👉 የ40/60 ከ80 በመቶ (80%) በላይ የደረሱ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እንደ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ፤ በዛሬው ዕለት በዕጣ ለባለ ዕድለኞች የሚተላለፉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ግንባታ  ፦ 👉 የ20/80 ከ96 በመቶ (96%) በላይ 👉 የ40/60 ከ80 በመቶ (80%) በላይ የደረሱ ናቸው። @tikvahethiopia
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩ ፦

- አሁንም ማንኛውም ችግር ቢያጋጥም በፍጥነት እናርማለን፤ በኦዲት ጭምር እናረጋግጣለን።

- በ20/80 93,352 በ40/60 54,540 በድምሩ 146,892 ከባንክ በተገኘው መረጃ መሰረት እንዲጣራ ተደርጎ ወደ ሲስተሙ ገብቷል። በዚህም ብቁ እና ንቁ ተብለው ለዕጣው ተዘጋጅተዋል።

(ከንቲባዋ በንግግራቸው በድምር ሲሉ የገለፁት ቁጥር (93,352 + 54,540) 146,892 አጠቃላይ ድምሩ የሚመጣው 147,892 ነው ፤ ይህ ትላንትም በከተማው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ተገልጾ የነበር ሲሆን ለምን ይህ ሊሆን እንደቻለ የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ እንጥራለን።)

- በ1997 ተመዝጋቢ የነበሩ ባለ 3 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ባለፈው ከዕጣ አወጣጡ ውጭ ተደርገው ነበር ፤ በዚህም በቀረበው ቅሬታ ከ2005 ቆጣቢዎች ጋር ዛሬ ለዕጣ ብቁ እንዲሆኑ ተደርገዋል።

- ዛሬ ለዕጣ የተዘጋጁት 25,791 ቤቶች ከ1997 ብቁ እና ንቁ ተመዝጋቢዎችን ሙሉ በሙሉ በመያዝ ለዕጣው መውጣት ዝግጅቱ የተደረጉ ናቸው።

- ከዚህ በኃላ በ1997 የሚጠራ ብቁ እና ንቁ ተብለው የሚጠሩ ዕጣ የሚወጣላቸው የተለየ ሁኔታ ሳያስፈልግ ሙሉ ተመዝጋቢዎች ዛሬ ይስተናገዳሉ።

@tikvahethiopia