#ተስፋ
በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከምንም በላይ ለበርካታ ወራት የእናት አባቶቻቸውን ፤ የእህት ወንድሞቻቸውን ፣ የወዳጆቻቸውን ድምፅ ያልሰሙ እጅግ በርካቶች ስምምነቱ በፍጥነት #ወደተግባር ገብቶ ያናፈቋቸውን ሁሉ ድምፃቸውን ሊሰሙ ጓግተዋል።
ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት በመኖሩ እያገዟቸው የነበሩ መላ ቤተሰቦቻቸውን ዳግም አግኝተዋቸው የየትኛውም የእርዳታ ድርጅት እና ተቋም /አካል ደጅ እንዳይጠኑ ለማድረግና ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ እየተጠባበቁ ነው።
ቤተሰቦቻቸው " በህይወት ይኑሩ አይኑሩ " እርግጠኛ ያልሆኑ ሚሊዮኖች የሰላም ስምምነቱ እጅግ በፍጥነት ተተግብሮ ፣ መሰረታዊ አገልግሎት ጀምሮ ለማየት ተስፋን ሰንቀዋል።
ከማንም ከምንም በላይ የጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂዎች ህመማቸው ፣ ናፍቆታቸው ፣ ሀዘናቸው የከፋ ነውና ይህ የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እና እፎይ እንዲሉ በተለይ #በማህበራዊ_ሚዲያ አፍራሽ ስራ የሚሰሩ ፣ የበለጠ ጥላቻን የሚዘሩ ፤ ሰላም በመሆኑ ጥቅማቸው የሚጎድልባቸው አካላት ከድርጊታቸው ቢታቀቡ መልካም ነው።
የሰላም ስምምነት መፈረሙ " የመጀመሪያው እርምጃ " እንጂ የመጨረሻ አይደለምና በተለይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ለስኬቱ የራሳቸውን በጎ ድርሻ መጫወት ይጠበቅባቸዋል። በሰላም ሁሉም አሸናፊ ነውና ከብሽሽቅ ፣ ከጥላቻ ከአጉል የአሸናፊነት ስሜት መራቅ ይገባል።
#ሰላም
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
#Update
የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የወታደራዊ አመራሮች #ሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም በጎረቤት ሀገር ኬንያ ፤ ናይሮቢ ሊገናኙ መሆኑ ተሰምቷል።
ይህ የተሰማው በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
በዚህ መድረክ ላይ የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ ተገናኝተዉ በትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት ላይ እንደሚወያዩ የተገለፀ ሲሆን በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ #ስራዎች_መጀመራቸው ተገልጿል።
በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።
የፊታችን ሰኞ ደግሞ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው እንደሚወያዩ መገለፃቸውን የብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

Photo
#Update
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ " መንግስት ከህወሓት ጋር ያደረገውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ የሁለት ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሯቸው ተመልሰዋል። " ብሏል።
ከውጊያ ኮማንድ ፖስት ወደ መደበኛ ማዘዣ ቢሮአቸው ከተመለሱ በኋላ በመንግስት እና በህወሓት በተደረገው የሰላም ስምምነት መሠረት በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ሲል ገልጿል።
ዛሬ ጥዋት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው በሰላም ስምምነት ሰነዱ ላይ የፈረሙት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተደረሰው ስምምነትን ተከትሎ የመንግስት እና የህወሓት ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውንና ሰኞ በጎረቤት ሀገር ኬንያ ፣ ናይሮቢ ውስጥ እንደሚገናኙ ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

" ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን ይገባዋል " - ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምሥራቅ ምድብ ችሎት የወንጀል ችሎት ዳኛ የሆኑት ፦
1ኛ ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣
2ኛ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ
3ኛ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረዋል።
ይህን ተከትሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እስራቱ ፈጽሞ ሕገወጥ እና በዳኝነት ነጻነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት በመሆኑ በአስቸኳይ ከእስር ሊለቀቁና ድርጊቱ ተጣርቶ ተገቢው እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ኢሰመኮ ስለጉዳዩ ባደረገው ማጣራት ዳኞቹ በሕግ የተሰጣቸው ልዩ ጥበቃ መብት በሕጋዊ መንገድ ሳይነሳ እና ዳኞች መሆናቸው ሳይገለጽ ከወረዳ ፍርድ ቤት ተሰጥቷል በተባለ የእስር ትእዛዝ ከሥራ ገበታቸው ላይ ተነስተው የታሰሩ መሆኑን ገልጿል።
የእስር ትእዛዙን የሰጠው የወረዳ ፍርድ ቤት ታሳሪዎቹ ዳኞች መሆናቸውን እንደተረዳ የእስር ትእዛዙን የሻረ መሆኑን አሳውቋል፡፡
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ ዳኞቹ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አጥብቀው አሳስበዋል።
ትላንት አርብ ኢሰመኮ እስሩን በተመለከተ መግለጫ እስካወጣበት አመሻሽ ድረስ ዳኞቹ በእስር ላይ ነበሩ ፤ ዛሬም ስለመፈታታቸው የተባለ ነገር የለም።
ዛሬ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የዳኞቹ መታሰር " በጣም አሳሳቢ ነው " ብለዋል።
" በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት ሥስት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በአዳማ ከተማ መታሠራቸው በጣም አሳሳቢ ነው " ያሉት ወ/ሮ መአዛ ፥ " ዳኞች የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ " ብለዋል።
ወ/ሮ መአዛ ፤ ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበው " ስለተከሰተዉ ሁኔታ የበለጠ ለመረዳት እየሞከርን ነዉ። " ሲሉ ገልፀዋል።
" ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያሉ ተመሳሳይ ድርጊቶች በአንዳንድ ክልሎች በዳኞች ላይ ሲፈጸሙ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልል ፍርድ ቤቶች ፕሌነም አውግዘው ውሳኔ አስተላልፈው ነበር ። " ሲሉ ወ/ሮ መአዛ አስታውሰዋል።

#መልዕክት🕊
አገራችን የደረሰችበትን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን መግለጫ የተላከልን ሲሆን ቤተክርስቲያኗ ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ምእመናን አጥብቀው እንዲፀልዩ ጥሪ አቅርባለች።
ከተላከልን መግለጫ የተወሰደ ፦
" የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን በሁለቱ ወገኖች የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አጥብቃ ትደግፋለች።
የስምምነቱ መተግበር የዜጎችን ሞትና እንግልት የሚያስቀር፣ ጥላቻን ከወንድማማቾች መካከል የሚያርቅ እና በአምላክ አምሳል ለተፈጥሩ የሰው ልጆች ሰብአዊ ክብር ዋስትና የሚሰጥ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ የበኩሏን አስተዋጻኦ ታበረክታልች።
በመላ አገሪቷ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤ/ክርስቲያን ምዕመናንም ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት አጥብቀው እንዲጸልዩ እና የሚጠበቅባቸውንም በጎ ምላሽ እንዲሰጡ ታሳስባለች። "
(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በላከልን አጭር መልዕክት በመንግስት እና ህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት እንደሚያበረታታ እና በደስታ እንደተቀበለው ገልጿል።
የሰላም ስምምነቱ በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ለመከላከል እና ለመቀነስ እንዲሁም ለሰው ልጆች ደህንነትና ለሰላም መስፋፋት የበኩላችንን አስተዋፅኦ ከማበርከት ጋር ተያይዞ የሚሄድ ነው ብሏል።
" እንደተለመደው መላው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ቤተሰብ አቅማቸውን ለሰብአዊ ድጋፍ እና የልማት ስራዎች ለማንቀሳቀስ ተዘጋጅተዋል ። " ብሏል ማህበሩ በላከል አጭር የፅሁፍ መልዕክት።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የፕሪቶሪያውን የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ መላው ህዝብ በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እና ለዘላቂ ሰላም እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል።
የካውንስሉ ፀሀፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ካስተላለፉት መልዕክት ፦
" የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆንና ሕዝባችን ከፍርሃት፣ ከጭንቀት፣ ከስድትና መከራ ያርፍ ዘንድ የሁሉንም ወገኖች ጥረት ይጠይቃል።
መላው ሕዝባችን አፍራሽ ከሆነ ተግባር በመራቅ እና ባለፉት ሁለት ዓመታት በደረሰባቸው ጉዳት ያዘኑትን ወገኖች በማጽናናት፣ ቤታቸውና ንብረታቸው የወደመባቸውን መልሶ በማቋቋም፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን በመደገፍ እና በማበርታት ለዘላቂ ሰላም በአንድነት እንድንነሳ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
ስምምነቱ እውን እንዳይሆንና ተመልሰን ወደ ግጭት እንድንገባ የሚያደርጉ ቅስቀሳዎች ሊኖሩ ይችላሉ ፤ በልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎች የሚተላለፉ አፍራሽ መልዕክቶችን ቸል በማለት ለስምምነቱ ተግባራዊ መሆን ተግተን ልንሰራ ይገባል።
ከዚህ በተጨማሪም በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ሕዝቦች ለጋራ ሰላምና ዕድገት በይቅርታ ተቀራርበው እውተኛ እርቅ እንዲያከናውኑ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በአንድነት በመቆም መስራት ይገባል።
... የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አቅም በፈቀደው ሁሉ ለሀገር ሰላምና ለሕዝቦችዋ ዕድገት አስፈላጊውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። "

" መሰል ሀሰተኛ መረጃ ሲነዛ በዚህ ወር ብቻ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው " ዛሬ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ " ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " እየተባለ ሲናፈስ የነበረው መረጃ #ሀሰተኛ ነው። በክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ላይ መሰል ሀሰተኛ መረጃ ሲነዛ በዚህ ወር ብቻ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከወራት በፊት ተመሳሳይ ሀሰተኛ ወሬ መሰራጨቱ እና ቤተሰቦቹን…
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል። @tikvahethiopia
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ መሀመድ (አሊ ቢራ) ማን ነበር ?
- አርቲስት አሊ ቢራ የተወለደው (በ1940 ዓ/ም) እና ያደገርው የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የመተሳሰብ መገለጫ በሆነችው ድሬዳዋ ነው።
- እናት እና አባቱ ያወጡለት ስም አሊ መሀመድ ነው።
- " አሊ ቢራ " የሚለው ስም የመጣው እኤአ 1963 በድሬድዋ ከተማ እራሱን አሊ መሀመድን ጨምሮ የሙዚቃ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች ተሰብሰበው በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ ለመጫወት በተደራጁበት ወቅት በግሩፑ ውስጥ ሶስት አሊዎች ነበሩ (አሊ ሸቦ፣ አሊ አህመድ አሊ / አሊ ቱቼ ፣ እራሱ አሊ መሀመድ) እነሱን ለመለየት ነው የመጀመሪያ እና እጅግ ተቀባይነት ባገኘው የሙዚቃ ስራው በሆነው " Birraa dha Bairhe " አሊ ቢራ የሚለውም ስም ያገኘው። ከዚህ በኃላ በፓስፖርት፣ መታወቂያ ... አሊ ቢራ እየተባለ መጠራት ጀምረ።
- አርቲስ አሊ ቢራ ፤ የሙዚቃ ስራውን የጀመረው በ14 ዓመቱ በድሬዳዋ " አፍረንቀሎ (አራቱ የቀሎ ልጆች) " የሙዚቃ ቡድን ውስጥ ነው። (በእድሜ ትንንሽ የነበሩት የሙዚቃ ቡድኑ አባላት B ቡድን ውሥጥ ነበሩ አሊ ቢራ በመጀመሪያው ስራ እጅግ ዝናን ስላገኘ ወደ A ቡድን ተቀላቀለ)
- አርቲስት አሊ ቢራ በህይወት በነበረበት ሰዓት ለ50 ዓመታት በሙዚቃ ስራ ቆይቷል። በርካታ የአልበም ፣ የነጠላ የሙዚቃ ስራዎችን ሰርቷል። በበርክታ የዓለም ሀገራት ተዘዋውሮ ከሙዚቃ ስራዎቹን አቅርቧል።
- አርቲስት አሊ ቢራ በአፋን ኦሮሞ ፣ ሀደርኛ፣ ሶማሊኛ ፣ አማርኛ ፣ አፋርኛ ከውጭ ሀገር ደግሞ በእንግሊዘኛ እና ስፓኒሽ ቋንቋዎች የመዝፈን ድንቅ ችሎታ ነበረው። የሙዚቃ መሳሪያዎችንም የሚጫወት ሲሆን የዜማ እና የግጥም ደራሲም ነበር። ከአፍረንቀሎ በተጨማሪ በተለዩ በተለያዩ የሙዚቃ ቡድኖች ውስጥ ሰርቷል።
- ለአፋን ኦሮሞ ቋንቋ እድገት ትልቅ ድርሻ ያለው ሲሆን ኢትዮጵያውያንን በጥበብ ስራዎቹ በማስተሳሰር ፣ በማዋደድ የህዝቡን ስሜት በማንፃባረቅ በመላው የኦሮሞ ህዝብ እንዲሁም በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አንጋፋ ተብለው ከሚጠሩ የጥበብ ሰዎች #ቀዳሚው ነው።
- በህይወት ዘመኑ ላበረከተው በጎ አስተዋፆ ፤ በርካታ ሽልማቶችን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ተሸልሟል። ለአብነት ፦ ከድሬዳዋ እና ከጅማ የክብር ዶክትሬት አግኝቷል፣ በድሬዳዋ ውስጥ ፓርክ በአዳማ ደግሞ መንገድ ተሰይሞለታል ፤ በኦሮሚያ ክልል ልዩ የኒሻን ሽልማት ተበርክቶለታል... ሌሎችም በርካታ እውቅናና ሽልማቶች አግኝቷል።
- ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ከባለቤቱ ጋር በመሆን " Birra Children's Education Fund " የተባለ ምግባረሰናይ ድርጅት አቋቁሞ " ለህፃናት ትምህርት " ድጋፍ ሲሰጥም ነበር።
- የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ትላንት በ75 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
(ስለ አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ ለመናገር እና ለመፅሀፍ ጊዜውም ሆነ ቦታውም ባይበቃም በአጭሩ ስለ ህይወቱ ትንሽ የሚያስረዳው ከላይ የቀረበው ፅሁፍ በተለያዩ ጊዜያት ለመገናኛ ብዙሃን ከሰጣቸው ቃለመጠይቆች የተወሰደ እንደሆነ እንገልፃለን)

" ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖበት ያለመከሰስ መብታቸዉ ከተነሳ በኋላ መሆን ይገባዋል " - ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምሥራቅ ምድብ ችሎት የወንጀል ችሎት ዳኛ የሆኑት ፦ 1ኛ ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣ 2ኛ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ 3ኛ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሚሠሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረዋል። ይህን ተከትሎ የኢሰመኮ…
#Update
ታስረው የነበሩት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ትላንት መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገልፀዋል።
ዶ/ር ዳንኤል ፤ ዳኞቹ ከተፈፀመባቸው የዘፈቀደ እስር መለቀቃቸውን ገልፀው ባለስልጣናት ግን ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል።
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎህ የወንጀል ዳኛ የሆኑት ዳኛ ደሳለኝ ለሚ፣ ዳኛ ሙሀመድ ጅማ፣ ዳኛ አብዲሳ ዋቅጅራ ጥቅምት 25 ከሚሰሩበት ፍርድ ቤት በአዳማ ከተማ በኦሮሚያ ፖሊስ ተወስደው ታስረው ነበር።
ይህን ጉዳይ ተከትሎ እስሩ ፈፅሞ ህገወጥ እና በዳኝነት ነፃነት ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው ሲል ኢሰመኮ ገልጾ ነበር ፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕ/ት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊም የኢሰመኮን ሪፖርት ተከትሎ የዳኞቹ መታሰር በጣም አሳሳቢ መሆኑን ገልፀው ዳኞች በወንጀል ሲጠረጠሩ ምክንያቱ ታምኖባት " ያለመከሰስ ማብታቸው " ከተነሳ በኃላ መሆን እንደሚገባው አስገንዝበው ነበር።