TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 #በኢትዮጵያ_መንግስት እና #በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይዘት የሚገልፅ 12 ነጥብ ያለው #የጋራ_መግለጫ ከላይ ተያይዟል። ነገ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለትና ህዝቡም እረፍት እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ፣ አርሶ አደሮችም ወደ እርሻቸው ፣ ሰራተኞችም ወደ ስራቸው፣ ነጋዴዎችም ወደንግዳቸው እንዲመለሱ አጠቃላይ…
ስለ " ሰላም ስምምነቱ " ምን ተባለ ?

🕊 የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኢትዮጵያ ለሰላም ያላት ቁርጠኝነት አሁንም የፀና መሆኑን ገልፀው " ስምምነቱ #ወደተግባር እንዲለወጥ አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ጠንካራ አቋም / ቁርጠኝነት አለን " ብለዋል።

🕊 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (አንቶኒዮ ጉተሬዝ) ፦

በደቡብ አፍሪካ የተደረሰው የ " ሰላም ስምምነት " የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈውና ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን አስከፊ ጦርነት ለማስቆም ወሳኝ የሆነ የመጀመሪያ እርምጃ ነው ብለዋል።

#ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል አመራሮች ለሰላም የወሰዱትን እርምጃ እንዲደግፉ አሳስበዋል።

የጦርነት ማቆም የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ለተቸገሩ ሰላማዊ ዜጎች ሁሉ ሰብአዊ እርዳታን ከፍ ለማድረግ እና በጣም አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

🕊 አሜሪካ ፦

ከአፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ፣ ኢጋድ እና ከሌሎችም ጋር በመሆን የተደረሰው ስምምነት #ተግባራዊ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ድጋፏን እንደታደርግ ገልጻለች። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነቱ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እና ለልማት ያላቸውን ፍላጎት እንደምትደረግፍም አሳውቃለች።

🕊 የአውሮፓ ህብረት (ጆሴፕ ቦሬል) ፦

የሰላም ስምምነቱ ባስቸኳይ ሊተገበር ይገባል ያሉ ሲሆን በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ማቅረብ ፤ በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንደገና መጀመር #ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-03

@tikvahethiopia
" በደቡብ አፍሪካ በነበረው ድርድር ኢትዮጵያ መቶ በመቶ ያቀረበችው ሀሳብ ተቀባይነት አግኝቷል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በስራ ጉብኝት በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ይገኛሉ።

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ለአርባምንጭና ለአካባቢው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ ወቅት ስለ ደቡብ አፍሪካ ድርድር ስምምነት የተወሰኑ ሀሳቦችን አንስተው ተናግረዋል።

ምን አሉ ?

- የኢትዮጵያ #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለድርድር አይቀርብም በሚለው በሁለቱም ወገን (በመንግስት እና ህወሓት ማለታቸው ነው) ተቀባይነት አግኝቷል።

- በአንድ ሀገር ወስጥ #ከአንድ መከላከያ በላይ አያስፈልግም በሚለውም ጉዳይ ከስምምነት ተደርሷል።

- በትግራይ ክልል ህገወጥ በሆነ መንገድ የተደረገው ምርጫ በህጋዊ ምርጫ መተካት አለበት የሚለውም በሁለቱም ወገኖች (በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት) ተቀባይነት አግኝቷል።

- በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ያለው የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው እና አከራካሪ ቦታዎች የሰው ልጆችን ህይወት ሳይጠይቁ በሰላም፣ በድርድር እና በሀገሪቱ ህግ መሰረት ብቻ ምላሽ እንዲያገኙ በሁለቱም ወገኖች መተማመን ላይ ተደርሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በደቡብ አፍሪካ በነበረው የሰላም ድርድር ኢትዮጵያ መቶ በመቶ ያቀረበችው ሀሳብ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ይህ የሰላም ጥረት ወደ ሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች ይስፋፋ " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሐመድ ከደቡብ አፍሪካ፤ የተሰማው ዜና አበረታች መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት እንዲሁም አደራዳሪዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት የሰላም ስምምነቱን ተፈጸሚ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

" ይህ የሰላም ጥረት ወደ ሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች ይስፋፋ " ያሉት አቶ ጃዋር በተለይ ጦርነት እየተካሄደባት ነው ባሉት የኦሮሚያ ክልል ልዩነቶች በድርድር እንዲፈቱ እና በመላው ሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

በመልዕክታቸው #ሁሉን_አቀፍ_ሰላም ለኢትዮጵያ እንደሚያስፈልግ ነው ያስገነዘቡት።

በደቡብ አፍሪካ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ፤ ተደራዳሪ ቡድኖችን ፣ የአፍሪካ ህብረት (AU) አሸማጋዮችን ፣ ታዛቢዎች እና አስተናጋጇን ሀገር ደቡብ አፍሪካ አመስግነዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ከከፋ እልቂት ለመታደግ አሁን እየታየ ባለው በዚህ የሰላም መነቃቃት እንስራ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#Update

• ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው ኔትዎርክ ጀምሯል ፤ አላማጣና ኮረም በሰዓታት ውስጥ አገልግሎት ያገኛሉ።

ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው የኔትዎርክ አገልግሎት ጀመረ።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ፤ የኔትዎርክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩት ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው ዳግም የኔትዎርክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ዛሬ ገልፀዋል።

የጄኔሬተር ነዳጅ ወደ አካባቢው በመላክ #አላማጣ እና #ኮረም ከሰዓታት በኋላ ሙሉ ለሙሉ የኔትዎርክ አገልግሎት እንደሚያገኙ ገልፀዋል።

በጥገና እና የተጎዱ የቴሌ መሠረተ ልማቶችን በመተካት ከዚህ ቀደም አገልግሎት ካገኙ አካባቢዎች ባለፈ በሌሎች የኔትዎርክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው አካባቢዎች በቅርቡ አገልግሎት ለማስጀመር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
አባታዊ የደስታ መልዕክት !

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በወቅታዊ ጉዳይ አባታዊ የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ውድ ወገኖቻችን ጦርነትን የሰሙ ጆሮዎቻችን ዛሬ #ሰላምን እና #እርቅን በመስማታቸው ደስታችን ወደር የሌለው መሆኑን ለኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያውያት ልጆቻችን ለመግለጽ እንወዳለን።

አገራችን ኢትዮጵያን ከአስከፊ የጦርነት ታሪክ ለማውጣት፣ እግዚአብሔር በሰጣት መልካም ዕድል፣ የተፈጥሮና የሃይማኖት ሀብት እንድታድግ ሰላምን መናፈቅና የሰላም መልእክተኛ መሆን ያስፈልጋል።

ሀሳብ የበላይ ሲሆን የጦር መሣሪያ የእርሻ መሣሪያ ወደ መሆን ይለወጣል። እኛም በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪያችንን እያስተላለፍን የቆየን እንደመሆኑ መጠን በዚህ መልካም የምሥራች ደስ ብሎናል።

አሁንም ኢትዮጵያውያን በሙሉ አገሩ የሁላችን ነውና ልንጠብቀው፤ አለመግባባታችንን በውይይት ልንፈታው ፤ ቃላችንን ከመሬት ላይ አሳርፈን እርቁን እውነተኛ ልናደርገው ይገባናል።

#ወጣቶች ሲሞቱ ሳይሆን ተምረው ሲመረቁ ፤ ተዋደው ጋብቻ ሲመሠርቱ ለማየት እንናፍቃለን።

የተዘጉ ደጆች ሁሉ በምሕረት እንዲከፈቱ ፤ የተጨነቁ ሁሉ ፀሐይ እንዲወጣላቸው በብርቱ እንሻለን።

ለዚህ እርቀ ሰላም መምጣት በብርቱ የደከሙትን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አባላትንና የሰላም ጥሪ የተቀበሉት ልጆቻችንን እግዚአብሔር አምላካችን ዐስበ ሐዋርያትን እንዲከፍልልን እንመኛለን። ለሞቱት ዕረፍተ ነፍስን ለታመሙት ፍጹም ጤንነት እንዲሰጥልን እንለምናለን። "

(የቅዱስነታቸው መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA🇪🇹

ከቀናት በፊት በጎረቤታችን #ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በ "አልሸባብ" በተፈፀመ የሽብር ጥቃት እጅግ በርካታ ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ፤ የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህንን ጥሪ ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት ዶክተሮችና የህክምና ቁሳቁሶችን እየላኩ ይገኛሉ።

ዛሬ ሀሙስ የሀገራችን #ኢትዮጵያ ዶክተሮች ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚደረገውን የአደጋ ጊዜ ምላሽ ለመቀላቀል ሞቃዲሾ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ዶክተሮች አዳን አብዱሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሶማሊያ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሊ ሀጂ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል እንደተደረገላቸው ከሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update • ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው ኔትዎርክ ጀምሯል ፤ አላማጣና ኮረም በሰዓታት ውስጥ አገልግሎት ያገኛሉ። ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው የኔትዎርክ አገልግሎት ጀመረ። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ፤ የኔትዎርክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩት ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው ዳግም የኔትዎርክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ዛሬ ገልፀዋል። የጄኔሬተር ነዳጅ ወደ አካባቢው በመላክ…
በየትኞቹ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ጀመረ ?

ኢትዮ ቴሌኮም ፤ የቴሌኮም አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩና ዳግም ያስጀመረባቸውን አካባቢዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

የቴሌኮም አገልግሎት የጀመረባቸው አካባቢዎች ፦

- አላማጣ፣
- ኮረም፣
- ዓዲ አርቃይ፣
- ጸለምት፣
- ጪሮ ለና፣
- ጎብዬ ቆቦ፣
- ቆቦ ሮቢጥ፣
- ዞብል
- ዋጃ ናቸው።

#በሌሎችም የቴሌኮም አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች #በቅርቡ አገልግሎት ለማስጀመር እየሠራ እንደሚገኝ ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግጭት አካባቢዎች ተቋርጦ የከረመውን የባንክ አገልግሎት በፍጥነት ለማስቀጠል በከፍተኛ ርብርብ እንደሚሰራ ማምሻውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የፀጥታ_ችግር ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ  ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ…
* የፀጥታ ችግር

በአርሲ ጀጁ ወረዳ በ " ሒሩታ ዶሬ " ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ምሽት ታጣቂዎች ከፈቱት ጥቃት 4 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ ጥቃቱ ምሽት 2:00 - 3:00 ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

በአከባቢው ኔትዎርክ በመቋረጡ የጉዳቱን መጠን በዚህ ብቻ የሚወሰን አይደለም ይህ መረጃም ከጥቃቱ ተርፈው ለህክምና ወደ አዳማ ከመጡ ሰዎች እንዲሁም በአከባቢው አቅራቢያ ኔትዎርክ በሚሰራባቸው ቦታዎች ካሉ ሰዎች ጠይቀው መረዳታቸውንም ነው የነገሩን።

" ይህ ጥቃት የመጀመሪው አይደለም " ያሉት መረጃውን ያደረሱን ሌላው የቤተሰባችን አባል ከ5 ቀናት በፊት አንድ ወጣት ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደለ አስረድተዋል።

ከትላንት በስቲያ ህይወታቸው ያለፈው 4ቱ ሰዎች በእድሜ የገፉ መሆናቸውን እንዲሁም ከመካከላቸውም አካል ጉዳተኞች መኖራቸውን ጠቅሰዋል። አንዷ የጥቃቱ ሰለባ በጾታ ሴት መሆናቸውን ገልጸዋል። የሚመለከተው አካል የከፋ ጥቃት ከመከፈቱ በፊት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በዚህ ጉዳይ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት ብናደርግም አልተሳካም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* የፀጥታ ችግር በአርሲ ጀጁ ወረዳ በ " ሒሩታ ዶሬ " ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ምሽት ታጣቂዎች ከፈቱት ጥቃት 4 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል። አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ ጥቃቱ ምሽት 2:00 - 3:00 ላይ መድረሱን ገልፀዋል። በአከባቢው ኔትዎርክ በመቋረጡ የጉዳቱን መጠን በዚህ ብቻ የሚወሰን አይደለም ይህ መረጃም ከጥቃቱ ተርፈው ለህክምና ወደ አዳማ ከመጡ ሰዎች እንዲሁም…
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦

- በምስራቅ ሸዋ ዞን ፤ በፈንታሌ ወረዳ መተሃራና አካባቢው ባንክ እና ኔትዎርክ ተቋርጦ ህዝቡ እየተጉላላ ነው። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ይፈልጉ ዘንድ ቤተሰቦቻችን ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ አካባቢ በሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮ በተደጋጋሚ ጊዜ ሰዎች መገደላቸው ፣መቁሰላቸው ፣ የኔትዎርክ አገልግሎትም ሲቋረጥ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

- አሁን ላይ ወቅቱ ዩኒቨርሲቲዎች ለእረፍት የወጡ ተማሪዎችን እየጠሩ ያለበት መሆኑን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ባሉ የፀጥታ ችግሮች ሳቢያ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ለመመለስ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ናቸው / አንዳንዶቹ በእግር ሁሉ ለመጓዝ መገደዳቸው ተጠቁመናል። በፀጥታ ችግር መንገድ የተዘጋባቸው አካባቢዎች ስላሉ ተቋማት ይህን ታሳቢ እንዲያደርጉ መንግስትም የፀጥታ ችግር ባለባቸው መንገዶች ደህንነትን የማረጋገጥ ስራ እንዲሰራ ቤተሰቦቻችን ጠይቀዋል።

- በኦሮሚያ ክልል ፤ የፀጥታ ችግሮች ባለባቸው አካባቢዎች ቤተሰቦቻቸው ያሉ አባላት የንፁሃን ሰዎች ህይወት እያለፈ ፣ ኢኮኖሚው እየደቀቀ፣ ሰላም ወጥቶ ለመግባት፣ ለተማሪዎች ትምህርት፣ ለመነገድ ፣ ለማረስ ፈተና እየሆነ ከመጣ አመታት ማለፉን በመግለፅ መፍትሄ እዲፈለግ ፤ ለሰሜን ኢትዮጵያው ችግር ከታሰጠው ትኩረት ትንሽ እንኳን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶ ለመፍትሄ ርብርብ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
ዛሬን ጨምሮ የዕረፍት ቀናቶችን የት ለማሳለፍ አስበዋል ?

የአዲስ አበባ ከተማን ገፅታ ከቀየሩ ፕሮጀቶች አንዱ " የወዳጅነት ፓርክ " ነው።

የዚህ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተከፍቶ በርካቶች እየጎበኙት እንደሆነ ይታወቃል ፤ ከቀናት በፊት ደግሞ የሁለተኛው ምዕራፍ በይፋ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተከፍቶ በነፃ እየተጎበኘ ነው።

የምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ምን ይዟል / ስለፓርኩስ የሚታወቀው ምንድነው ?

ይህ የምዕራፍ 2 የወዳጅነት ፓርክ በ11 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ነው ያረፈ ሲሆን 3 ክፍሎችም አለቱ።

1ኛ. የህፃናት መጫወቻ ስፍራ ፦

ሰፊውን የፓርኩን ክፍል የሚሸፍን ሲሆን ልጆች አካላዊ እና አእምሯዊ እድገታቸውን ለመጨመር እንዲያግዝ ተድረጎ ያተገነባ ነው። በተጨማሪ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን መለማመድ ያስችላቸዋል።

2ኛ. የወጣቶች የስፖርት ስፍራ፦

የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያው ስፍራ ወጣቶች የአካል ብቃት የሚሰሩበት እና አእምሯቸውን ዘና የሚያደርጉበት ሲሆን በውስጡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የቴኒስ መጫወቻ ፣ የመሮጫ መም ፣ የባስኬት መጫወቻ የያዘ ነው።

3ኛ. የሰርግ አፀድ፦

ይህ የፓርኩ ክፍል ጥንዶች የሰርግ ስነስርዓታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያዘጋጁ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ነው። ጥንዶች ጋብቻቸውን ሲፈፅሙ እንደአንድ አማራጭ አድርገው ሊወስዱት የሚችል ደረጃውን የጠበቀ ስፍራ ነው።

የወዳጅነት ፓርክ ምዕራፍ 2 እንደ ፕሮጀክት 1 ሁሉ ለፎቶ፣ ቁጭ ብሎ እራስን ለማዝናናት፣ ከራስ ጋር ለመሆን ምቹ ስፍራ ነው።

መግቢያ አለው ?

ፓርኩ ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ ከነገወዲያ እሁድ ድረስ #በነፃ ለጎብኝዎች ክፍት ሲሆን በቀጣይ ተመጣጣኝ የሆነ የመግቢያ ዋጋ ይፋ ይደረግለታል ተብሏል።

ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር እስከ እሁድ መጎብኘት ትችላላሁ።

@tikvahethiopia