TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somali

የሶማሌ ክልል ፀጥታ ቢሮ ፤ ከሰሞኑን በጅግጅጋ ኤርፖርት በፀጥታ ኃይል ከተገደሉት ጄዌሪያ መሀመድ ጋር በተያያዘ ህዝቡን እና ከተማውን ለማበጣበጥ ፣ ሁከት እና ግርግር ለመፍጠር እንዲሁም ሌብነትና ዘረፋ ለመፈፀም ፍላጎት ያላቸው አካላት መኖራቸውን ጠቁሞ ህዝቡ እነዚህን አካላት አይሆንም ሊላቸው/ሊገስፃቸው እንደሚገባ መንግስት ግን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ቢሮው የጄዌሪያን መሀመድ መገደልን ተከትሎ የተለያየ አይነት ስሜትና ፍላጎት ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ይስተዋላሉ ብሏል።

አንደኛ፦

በድርጊቱ በጣም ያዘኑ እና ሀዘናቸውንም በአግባቡ መግለፅ የሚፈልጉ ፍትህ እንዲገኝ የሚጠይቁ ናቸው።

ሁለተኛ፦

በዚህ የሀዘን ድባብና ክፉ ድርጊት ጥቅማቸውን የሚፈልጉ ሁከት እና ግርግር እንዲባባስ የሚፈልጉ በዚህ አጀንዳ ተሸጋግረው ሌላ ጥቅም የሚፈልጉ ናቸው።

ሶስተኛ፦

ፖለቲካዊ ፍላጎት ባይኖረውም ግን የሌብነት፣ ዘረፋ እና ብጥብጥን በውስጡ የያዘ ነው፤ ቢሮው፤ እንደዚህ አይነት ፍላጎት ያላቸው አካላት በዚህ አይነት ምክንያት ሌላው ላይ ተፅእኖ በመፍጠር ትላንት በባለፈው ስርዓት ጊዜ እንዳደረጉት ህዝብና ከተማን መበጥበጥ እና መዝረፍ የሚሹ አካላት የሚታወቁና ያልተደበቁ ናቸው ብሏል።

ትላንት የደረሰው ግፍና ተፅእኖ፣ መከራ እና ችግር ከግምት በማስገባት መንግስት የሚያደርገውን ትዕግስት ወደ ጎን በማየት በዚህ አይነት ተልዕኮ የሚሰማሩትን ህዝቡ የትላንቱን አይነት ጥፋት መድገም የለባችሁም በማለት ሊገስፃቸውና አይሆንም ሊላቸው ይገባል ብሏል ቢሮው።

ለክልሉ ህዝቦች አብሮነት ማይጠቅም፤ የነበረውን አንድነትና ህብረት የሚያበላሽ አይነት ፍላጎት ለ2ኛ ጊዜ እንዲመለስ መንግስት አይፈቅድም ያለው የፀጥታው ቢሮ እንዲህ አይነት አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ERCS • የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአምቡላንስ ሹፌር በታጣቂዎች ተገደለ። • ማኅበሩ በባልደረባው ሞት የጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው ገልጾ ግድያውን አውግዟል። ታጣቂ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ማህበሩ ተማፅኗል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ #የአምቡላስ_ሾፌር የነበረው አቶ መንግስት ምንይል ታጣቂ ሃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ተገድለዋል። ማህበሩ፤ ግድያውን በአፅንዖት…
#Update

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የአምቡላንስ ሹፌር ግድያ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ አምቡላንስ ሹፌር አቶ መንግስት ምንይል ላይ በደረሰው አሰቃቂ ሞት ድንጋጤ እና ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ገልጿል።

" በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተበት አካባቢ በስራ ላይ እያሉ ነው የተገደሉት፡፡ " ያለው ኮሚቴው " ሀሳባችን እና ጥልቅ ሀዘናችን ከሟች ቤተሰቦች፣ ከኢቀመማ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች ጋር ነው " ብሏል።

በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ (IHL), የህክምና ሰራተኞች፣ ሆስፒታሎች እና ሌሎች የህክምና ክፍሎች እንዲሁም  አምቡላንስ እና ሌሎች የህክምና መጓጓዣዎች ለህክምና ተግባራት ወይም ዓላማዎች ብቻ የተመደቡ፣ በማንኛውም ሁኔታ #ሊከበሩ እና #ሊጠበቁ ይገባል ሲል ገልጿል።

ኮሚቴው ፤ በህክምና ሰራተኞች፣ በቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ እንቅስቃሴ ሰራተኞች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች እና የቀይ መስቀል ወይም ቀይ ጨረቃ አርማ የሚያሳዩ ነገሮችን ማጥቃት የተከለከሉ ናቸው ብሏል።

" የእርዳታ ሰራተኞች የጥቃት ኢላማ አይደሉም " ሲል አክሏል።

በተመሳሳይ ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ ግድያውን "አሰቃቂ" ሲሉ ገልፀው ለአቶ መንግስት ቤተሰቦች እና በዓለም ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለሚገኙት የICRC ሰራተኞች በሙሉ መፅናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፤ አቶ መንግስት ምንይል በትግራይ፤ ዓድዋ በግጭት የተጎዱ ሰዎችን በማገዝ ስራ ላይ እያሉ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት መገደላቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከ6,000 በላይ መፅሀፍት . . .

በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በየአመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመት የተቋረጠው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ዳግም ጀምሯል።

በሰኔ ወር 2014 በአዲስ አበባ ብቻ የጀመረው የመፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እየተሰራ እጅግ በርካታ መፅሀፍትን ማሰባሰብ ተችሏል።

በኃላም ፤ በነሃሴ ወር ላይ በሀገር ወቅታዊ ሁኔታ ተቋርጦ መስከረም ወር 2015 ዓ/ም ዳግም ተጀምሮ ነበር።

እስካሁን ባለው ቆጠራ አጠቃላይ ከ6000 በላይ መፅሀፍት ተሰብስቧል።

ይህ ከቤተሰቦቻችን #በየቤታቸው_ሄደን የተቀበልናቸው እና በመላው ቤተሰቡ ስም በማስታወቂያ ገቢ የተገዙትን ይጨምራል። (በየዓመቱ በሚሰራው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ከቲክቫህ አባላት ገንዘብ እንደማይሰበሰብ ይታወቃል)።

ይህ ዘመቻ በጥቂት ቀናት ተጠናቆ በፍጥነት መፅሀፍቱን ወደ አስፈላጊ ቦታ በማድረስ ህዳር 1/2015 የ5ኛውን ዓመት ስራ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

መፅሀፉ የሚያስፈልጋቸውን ትክክለኛ ትምህርት ቤቶችን እና ስንት መፅሀፍ እንደሚላክላቸው የመለየት ስራም በፍጥነት እየተሰራ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግሮች እንዳለቁ እናሳውቃችኃለን።

መፅሀፍቶቹ እንደደረሱም " በመፅሄት መልክ " በፎቶ ሪፖርት አቅርበን መፅሀፍ ላበረከቱ ቤተሰቦቻችን እንልካለን።

በቀጣይ ጥቂት ቀናት መፅሀፍት ለመሥጠት የምትፈልጉ ደውሉልን 0919743630 / መፅሀፍ ገዝታችሁ መስጠትም የምትፈልጉ በገንዘብ መልክ የምንቀበልበት ምንም መንገድ ስለሌለ መፅሀፉን ገዝታችሁ ያላችሁበትን ድረስ መጥተን እንወስዳለን።

አጠቃላይ የመፅሀፍት ዝርዝር በቀጣይ ሲጠናቀቅ እናሳውቃለን።

#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኤር_ኤክስፕረስ_አፍሪካ ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ በኢትዮጵያ ተመዘገበ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፤ ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ መመዝገቡን አሳውቋል። ተቋሙ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀው አለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተቀመጠውንና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን…
#ETHIOPIA

በሀገራችን ኢትዮጵያ 13ኛው የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ተመዝግቧል።

13ኛው የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የተመዘገበው " ጎልድ ስታር አቪዬሽን " ነው።

ተቋሙ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀው ዓለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተቀመጠውንና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሚተገበሩትን 5 ደረጃዎችን (five phases) በስኬት አጠናቆ በመገኘቱ ነው።

በውስጣቸው በርካታ ተግባራትን የያዙት አምስት ስታንዳርዶች pre-application, formal application, Document evaluation and Inspection and finally Certification የሚባሉ ሲሆን ጎልድ ስታር ትላንት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተፈረመበትን ሰርትፊኬት በይፋ ተቀብሏል፡፡

በአሁን ሰዓት በሀገራችን " ጎልድ ስታር አቪዬሽን " ን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ተመዝግበው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት ተቋማት 13 ደርሰዋል፡፡

" ጎልድ ስታር አቪዬሽን " የእውቁ ባለሀብት #ወርቁ_አይተነው ድርጅት መሆኑን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
" እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ

ዛሬ በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ፤ ሞቃዲሾ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገደሉ።

በዞቤ መንገድ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተነጣጠረ ነበር ተብሏል።

በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የፖሊስ አባል፣ አንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሴቶች እና ህፃናት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

ፖሊስ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር ለመግለፅ የሟቾች እና የቆሰሉ ሰዎችን መረጃ ለማሰባሰብ እየሰራ ነው።

ከተጎዱት መካከል የሮይተርስ የፎቶ ጋዜጠኛ እና የቪኦኤ ፍሪላንሰር እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

እስካሁን ለሽብር ጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል ብቅ ባይልም ድርጊቱን የፈፀሙት የአልሸባብ ሚሊሻዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ፤ የሶማሊያጠቅላይ ሚንስትር ሀምዛ አብዲ ባሬ በሞቃዲሾ ሴቶችን እና ህጻናትን ጨምሮ የንፁሀን ዜጎችን ህይወት የቀጠፈውን አሰቃቂ የሽብር ጥቃት በፅኑ ማውገዛቸውን የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ዛሬ በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ፤ ሞቃዲሾ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገደሉ። በዞቤ መንገድ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተነጣጠረ ነበር ተብሏል። በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የፖሊስ አባል፣…
#Update

በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ትላንት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች ሲሞቱ 300 ሰዎች ተጎድተዋል።

በሁለት መኪና በተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገድለዋል።

የሶማሊያ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ፤ የትላንቱን የሽብር ጥቃት " ጭካኔ የተሞላበት እና የፈሪዎች ጥቃት " ሲሉ ገልፀው ድርጊቱን የፈፀመው ሽብርተኛው አልሸባብ መሆኑን አመልክተዋል።

በጥቃቱ ሲቪሎች መሞታቸውን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይችልም ፤ ይልቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ለማሸነፍ (አልሸባብን) ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲሉ ገልፀዋል።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ የሽብር ጥቃቱ የተፈፀመበትን ቦታ በአካል የተመለከቱ ሲሆን በጥቃቱ በትንሹ 100 ሰዎች መገደላቸውን እና 300 የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነዋል።

ህዝቡም ወደ ሆስፒታል እየሄደ ደም እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በትላንቱ እንዲሁም በሌሎች የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ህፃናት ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚመቻች ፕሬዜዳንቱ ቃል ገብተዋል።

የትላንቱ የመኪና የቦምብ ጥቃት በመዲናዋ ሰው ከሚበዛባቸው መገናኛዎች ውስጥ በሚገኘው #የትምህርት_ሚኒስቴር ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ፤ " የቢጫ ወባ ክትባት " መጀመሩን እና አገልግሎቱን የሚፈልጉ በአገልግሎቱ መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቆናል።

@tikvahethiopia