#የሀሳብ_ቅኝቶች (ልዩ የወጣቶች መድረክ)
ሀሰተኛ መረጃ እንዲሁም የጥላቻ ንግግርን ለመግታት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ትኩረት ያደረገ " የሀሳብ ቅኝቶች " የተሰኘ መድረክ የፊታችን መስከረም 30 እና ጥቅምት 1 በአዲስ አበባ " ሸራተን አዲስ ሆቴል " ተሰናድቷል።
በዚህ መድረክ የፖናል ውይይት ፣ የአንድ ሰው ተውኔት፣ የሙዚቃና ልዩ ልዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች የተካተቱበት ሲሆን የተለያዩ ሀሳቦችም ተነስተው የሚመከርበት የወጣቶች ዝግጅት ነው።
በመድረኩ ላይ ይመለከተኛል ፣ ሀሳብ አለኝ ፣ ማወቅ እፈልጋለሁ ለሚሉ ወጣቶች ሁሉ የተመቻቸ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር ለመገናኘት ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርላቸዋል።
በዝግጅቱ መሳተፍ ለሚፈልጉ ወጣቶች የመመዝገቢያ አማራጭ በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Peace የአፍሪካ ኅብረት #የሰላም_ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ኦፊሴላዊ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል። ይኸው በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ የቀረበው ጥሪ እንደሚያሳየው፦ - የውይይት ቦታ 👉 ደቡብ አፍሪካ - የውይይቱ ቀን 👉 ከፊታችን ጥቅምት 8/2022 ጀምሮ - የሰላም ውይይቱ የሚመራው 👉 በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ…
#Update
ህወሓት በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።
ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቆርጠኞች ነን ሲልም ገልጿል።
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለአፍሪካ ህብረት ሊቀንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በፃፉት ደብደቤ ፤ ለሰላም ሂደቱ ይረዳል ያሉትን " ግጭት ማቆም " ዋናው የድርድሩ የአጀንዳው አካል ተደርጎ ስለመያዙ ጠይቀዋል።
" ተደራዳሪዎቻችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጁ ነን " ሲሉም አሳውቀዋል።
" ግብዣው ቀደም ብሎ ያልተማከርንበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ቢሰጠን " ሲሉ በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
እነዚህም ፦
- በሰላም ውይይቱ ተጨማሪ ተዋናይን እንደ ተሳታፊዎች፣ ታዛቢዎች ወይም ዋስትና ሰጪዎች የሚጋበዙ ይኖሩ እንደሆነ፤
- ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን አይነት ሚናዎችን ሊሰጥ እንደታሰበ ፤
- ለተደራዳሪ ቡድኑ የሎጅስቲክስ ፤ #የጉዞ እና የደህንነት ዝግጅቶችን በተመለከተ እንዲብራራላቸው ዶ/ር ደብረፅዮን ለፋኪ በላኩት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
ዛሬ ጥዋት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በደቡብ አፍሪካ የሚደረገውን የሰላም ንግግር ግብዣ መቀበሉን ማሳወቁ ይታወቃል።

አሚና መሀመድ ኬንያ ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ ኬንያ የሚገኙ ሲሆን ዛሬ ከኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር በ " ስቴት ሀውስ " ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ስቴት ሀውስ ፤ ፕሬዝዳንቱ እና ምክትል ዋና ፀሀፊዋ ፤ " ኬንያ እንደ ተፅእኖ ፈጣሪ ሀገር በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ሁኔታ ላይ ስላላት ጉልህ ሚና ተወያይተዋል " ሲል አሳውቋል።
በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ እና በኑሮ ላይ እያሳደረ ስለለው ተፅእኖ እንዲሁም በቀጠናው ስላለው ድርቅና ረሃብ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በዚሁ ውይይት ወቅት ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ፤ ሀገራት አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጠይቀዋል።

አሚና መሀመድ ኬንያ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ ኬንያ የሚገኙ ሲሆን ዛሬ ከኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር በ " ስቴት ሀውስ " ተገናኝተው ተወያይተዋል። ስቴት ሀውስ ፤ ፕሬዝዳንቱ እና ምክትል ዋና ፀሀፊዋ ፤ " ኬንያ እንደ ተፅእኖ ፈጣሪ ሀገር በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ሁኔታ ላይ ስላላት ጉልህ ሚና ተወያይተዋል " ሲል አሳውቋል። በተጨማሪ…
በሌላ መረጃ ፦
ምንም እንኳን በኬንያ " ስቴት ሀውስ " ኦፊሴላዊ መረጃ ባያሰራጭም ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊየም ሩቶ በነገው ዕለት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተሰምቷል።
ℹ️ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሪያ ልዩ መርሃ ግብር ነገ ከአመሻሽ ጀምሮ እንደሚያካሂድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማወቅ የቻለ ሲሆን ከዚህ ቀደም ብሎ ነገ ጥዋት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።
NB. ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት የሙከራ ኔትዎርክ አገልግሎቱን በአወዳይ፣ ጎንደር ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ማስጀመሩ ይታወቃል።

በሌላ መረጃ ፦ ምንም እንኳን በኬንያ " ስቴት ሀውስ " ኦፊሴላዊ መረጃ ባያሰራጭም ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊየም ሩቶ በነገው ዕለት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተሰምቷል። ℹ️ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሪያ ልዩ መርሃ ግብር ነገ ከአመሻሽ ጀምሮ እንደሚያካሂድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ…
#Kenya #Ethiopia
የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሀገር ጉዟቸውን ወደ #ኢትዮጵያ እንደሚያደርጉ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል።
ነገ በአዲስ አበባ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚታደሙ የተነገረላቸው ሩቶ ፤ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ይመክራሉ።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ምርጫ ማሸነፋቸው በIEBC በተገለፀበት ዕለት ከዓለም ሀገራት መሪዎች ሁሉ በቅድሚያ የ " እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት ያስተላለፉላቸው መሪ እንደነበሩ ይታወሳል።

#ሼር
የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት መስከረም 30 /2015 ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ የዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አድራሻ አሰራጭቷል ፤ ከላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopia
የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት መስከረም 30 /2015 ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ የዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አድራሻ አሰራጭቷል ፤ ከላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሌላ መረጃ ፦ ምንም እንኳን በኬንያ " ስቴት ሀውስ " ኦፊሴላዊ መረጃ ባያሰራጭም ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊየም ሩቶ በነገው ዕለት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተሰምቷል። ℹ️ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የማስጀመሪያ ልዩ መርሃ ግብር ነገ ከአመሻሽ ጀምሮ እንደሚያካሂድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ…
#Update
" ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።
መግለጫውን ተከታትለን የምንልክላችሁ ይሆናል።
በሌላ በኩል ፤ ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ደንበኞች በአቅራቢያቸው ካሉ የሳፋሪኮም መለያ ከተለጠፈባቸው ሱቆች በመሄድ ሲም ካርድ መግዛትና አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።
@tikvahethiopia
" ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።
መግለጫውን ተከታትለን የምንልክላችሁ ይሆናል።
በሌላ በኩል ፤ ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ደንበኞች በአቅራቢያቸው ካሉ የሳፋሪኮም መለያ ከተለጠፈባቸው ሱቆች በመሄድ ሲም ካርድ መግዛትና አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya #Ethiopia የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሀገር ጉዟቸውን ወደ #ኢትዮጵያ እንደሚያደርጉ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል። ነገ በአዲስ አበባ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚታደሙ የተነገረላቸው ሩቶ ፤ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ይመክራሉ። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ዶ/ር…
#Update
የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዜዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተቀብለዋቸዋል።
ሩቶ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የቴሌኮም ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።
ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያው የአፍሪካ ሀገር ጉዟቸውን ወደ #ኢትዮጵያ በማድረግ ነው ጀምረዋል።
ፎቶ ፦ ኢብኮ

#Update " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን ተከታትለን የምንልክላችሁ ይሆናል። በሌላ በኩል ፤ ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ደንበኞች በአቅራቢያቸው ካሉ የሳፋሪኮም መለያ ከተለጠፈባቸው ሱቆች በመሄድ ሲም ካርድ መግዛትና አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል። @tikvahethiopia
#Live
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መጀመሩን እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ በይፋ አሳውቋል።
መግለጫውን በዙም መከታተል የሚቻል ሲሆን ጥያቄ / አስተያየት ያላችሁ ጥያቄያችሁን / አስተያየታችሁን በዙም #በቀጥታ ማቅረብ ትችላላችሁ።
ሊንክ ፦ https://safaricom-co-ke.zoom.us/webinar/register/WN_45w3LkggTpan9rlQJhO9dg
@tikvahethiopia
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መጀመሩን እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ በይፋ አሳውቋል።
መግለጫውን በዙም መከታተል የሚቻል ሲሆን ጥያቄ / አስተያየት ያላችሁ ጥያቄያችሁን / አስተያየታችሁን በዙም #በቀጥታ ማቅረብ ትችላላችሁ።
ሊንክ ፦ https://safaricom-co-ke.zoom.us/webinar/register/WN_45w3LkggTpan9rlQJhO9dg
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Live ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መጀመሩን እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ በይፋ አሳውቋል። መግለጫውን በዙም መከታተል የሚቻል ሲሆን ጥያቄ / አስተያየት ያላችሁ ጥያቄያችሁን / አስተያየታችሁን በዙም #በቀጥታ ማቅረብ ትችላላችሁ። ሊንክ ፦ https://safaricom-co-ke.zoom.us/webinar/register/WN_45w3LkggTpan9rlQJhO9dg @tikvahethiopia
#Update
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሰጠው መግለጫ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ተጠይቀው ምላሽ ተሰጥቷል።
የሮይተርስ በኢትዮጵያ ወኪል ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ፤ " ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገባ ከተፎካካሪው ጋር ምን የሚለይ ነገር ይዞ ይመጣል ? " የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
• የሳፋሪኮም ምላሽ ፦
" እኛን ከተፎካካሪዎቻችን የሚለየን የ4G ኢንተርኔት አገልግሎታችን ጥራትና ፍጥነት ነው። የደንበኞች አገልግሎት እንዲሁም በሌሎች ሀገራት ያሉን ልምዶች ናቸው። "
የኬንያው ሬድዮ ሲትዝን ጋዜጠኛ Epha Muiruri ደግሞ እስካሁን " ምን ያህል ደንበኞች አገኛችሁ ? " የሚል ጥያቄን አንስቷል።
• የሳፋሪኮም ምላሽ ፦
" በ8 ከተሞች ከሁለት ቀናት በፊት በነበረ መረጃ ወደ 200 ሺህ ደንበኞች መዝግበናል። "
የብሉምበርግ የኢትዮጵያ ወኪል ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ ፤ " የኢትዮ ቴሌኮምን መሰረተ ልማት ለመጠቀም የነበራችሁ ድርድር ጨርሳችኋል ? ከጨረሳችሁስ በምን ያህል ፐርሰንት ለመጠቀም ተስማማችሁ ? ካሰባችሁበትስ ቀን ዘግይታችሁ ለምን ጀመራችሁ ? " የሚል ጥያቄ ጠይቃለች።
• የሳፋሪኮም ምላሽ ፦
" የኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማትን ከመጠቀም አንጻር በፋይበር መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ የተስማማን ሲሆን ከታወር መሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ ግን ምንም በሚባል ደረጃ የኢትዮ ቴሌኮምን መሰረተ ልማት አንጠቀምም።
የዘገየንበትም ዋነኛው ምክንያት የራሳችንን የታወር መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት በመወሰናችን ነው።
በዚህም አዳዲስ ኮንትራቶችን ሰጥተናል፣ ለታወር የሚሆኑ ቦታዎች መረጣ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ጊዜ ወስደዋል።
ዓለም አቀፍ የሎጀስቲክ ዝውውር በኮቪድ-19 ምክንያት መቀዛቀዙም አንዱ ምክንያት ነው። "