TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ብሔራዊ_ፈተና

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከቀናት በኃላ መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ይታወቃል። ተማሪዎች መብታቸው ፣ ግዴታቸው፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዘው መሄድ የሚችሉት እና የተከለከሏቸው ነገሮችን ከላይ በምስሉ በዝርዝር ተቀምጧል።

በተጨማሪም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ቀርቧል።

➤ የመጀመሪያ ዙር (የሶሻል ሳይንስ) ፦

🗓 ከመስከረም 26 - 28 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

🗓 መስከረም 29 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

🗓 ከመስከረም 30 - ጥቅምት 2 (ፈተና ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 (ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ)

➤ ሁለተኛ ዙር (የተፈጥሮ ሳይንስ) ፦

🗓 ከጥቅምት 5 - ጥቅምት 6 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

🗓 ጥቅምት 7 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 8 - ጥቅምት 11 (ፈተና ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 12 - ጥቅምት 13 (ተፈታኞች ወደየአከባቢያቸው ይመለሳሉ)

(ትምህርት ሚኒስቴር / የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወልድያ ! የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ የማሻሻያ ውሳኔ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2015 ዓ/ም አሳልፏል። ሌሎች ክልከላዎች እንደቀጠሉ ሆኖ በሰዓት እላፊ ገደብ ላይ የተደረገው ማሻሻያ ፦ - ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የተሽከርካሪ የሰዓት እላፊ ወደ ምሽቱ 1:00 ሰዓት፤ - ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የሰዎች እንቅስቃሴ የሰዓት…
#ATTENTION

ወልድያ !

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ቤት ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ ክልክለዎችን አስተላለፈ።

የፀጥታ ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ  ክልከላዎችን ማስቀመጡ ይታወሳል።

ሆኖም ነባራዊ ሁኔታ በማየት ተጨማሪ ክልከላዎች በማስፈለጉ ከነገ መስከረም 22 / 2015 ዓ.ም ጀምሮ  የሚተገበሩ ተጨማሪ ዉሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል።

በዚህ መሰረት :-

1. ከነገ መስከረም 22  ቀን ጀምሮ ጫት ወደ ከተማዋ ማስገባት በጥብቅ ተከልክሏል።

2. ከነገ ጀምሮ ጫት መቃም ሆነ ማስቃም በጥብቅ ተከልክሏል።

3. ከነገ ጀምሮ የጎዳና ላይ ቁማር (ቢንጎ የመሳሰሉትን) መጫወት ተከልክሏል።

ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ጨምሮ ከዚህ በፊት የተላለፉ ዉሳኔዎችን ማንኛውም አካል የማክበርና ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ አለበት የተባለ ሲሆን ውሳኔዎቹን የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

መረጃው ከከተማው ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በሰላም ገብተናል "

ትላንት አርብ ወደ አዲስ አበባ ከተማ መግባት ሳይችሉ ቀርተው መንገድ ላይ እየተጉላሉ ከነበሩ መገደኞች መካከል የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ዛሬ መንገዱ ተከፍቶ በሰላም አዲስ አበባ መግባታቸውን በፅሁፍ መልዕክት አሳውቀዋል።

በመንገድ ላይ እየተጉላሉ ከነበሩ የቤተሰባችን አባላት መካከል የባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲሁም የህምክና ክትትል የነበራቸው የቤተሰባችን አባላት እንደነበሩበት ይታወቃል።

ትላንት የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ የሆኑ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከመገደኞች መንገላታት ጋር በተያያዘ ለአሚኮ በሰጡት ቃላቸው ፥ " እኛ ኢሬቻ በዓል ላይ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ ፍተሻ እያደረግን እንጅ መንገደኞችን አልመለስንም ፤ መንገደኞቹ ስለመመለሳቸው እና መንገዱ ስለመዘጋቱ የማውቀው ነገር የለም " ማለታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት የመተሐራ ቲክቫህ ቤተሰቦች በሚኖሩበት የመተሀራ አካባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ በላኳቸው መልዕክቶች አስገንዝበዋል። ከዚህ ቀደም ወደ መተሀራ አካባቢ በርካታ ወጣቶች በመዝናኛ ቦታ እያሉ መገደላቸው በሚዲያዎችም ጭምር መገለፁ ይታወሳል። እዛው " መተሐራ " አካባቢ ከአምስት ቀናቶች በፊት አንድ የቀበሌ ሊቀመንበር ተገድሎ ነበር ፤ ከዚህ ግድያ በኃላም የአካባቢው…
#መተሐራ

ከጥቂት ቀናት በፊት በመተሐራ እና አካባቢው ያሉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እጅግ እየተደጋገመ የመጣው የታጣቂዎች ጥቃት የሰዎች ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን ፤ በአጠቃላይ የደህንነት ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለመድረሱ በዝርዝር አመልክተው ነበር።

ዛሬ ከመተሐራ ቤተሰቦች የመጣው መልዕክት ፤ ትላንት ከጠዋቱ መተሐራ አባድር 2ተኛ ካምፕ በሚባል አካባቢ ታጣቂዎች ገብተው ከ10 በላይ ሰዎችን መገደላቸውን ፤ በዚህም ጥቃት ሳቢያ ደህንነታቸው አደጋ ላይ የወደቀባቸው ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸውን ያመለክታል።

የሟቾች ስርዓተ ቀብርም ዛሬ ተፈፅሟል ብለዋል።

ትላንት መልዕክት እንዳይልኩ ኔትዎርክ እየሰራ እንዳልነበር ገልፀዋል።

ከዛው ከመተሐራ አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ አባድር ሁለተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት 12 ወጣቶች መገደላቸውን ገልጾ ነዋሪው ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል ሲል አመልክቷል።

ተፈናቃዮችም በትምህርት ቤት ውስጥ እንደሚገኙ የገለፀው የቤተሰባችን አባል" ከወረዳውም ሆነ ከክልል በኩል እንዳች የተባለ ነገር የለም " ብሏል።

" ችግሩ አስከፊ እና አሳሳቢ ነው " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል የህዝቡን ጩኸት የፌደራል መንግስትና ሌሎችም የሚመለከታቸው ሁሉ ሰምተው ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልጉና አስተማማኝ ደህንነት እንዲረጋገጥ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከታሪፍ ውጪ አትክፈሉ !

" የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ምንም አይነት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አልተደረገም " - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ከቀናት በፊት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ፤ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘረጋው ብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ህዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።

ይህም ማለት ቀደም ሲል ይቀርብ በነበረበት የነጭ ናፍጣና ኬሮሲን ዋጋ ብር 40.86 ፣ የቢንዚን ብር 41.25 ነው እየቀረበ የሚገኘው።

#በታለመለት_የነዳጅ_ድጎማ_የታቀፉ_ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል በወጣላቸው ታሪፍ ሀብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን ህብረተሰቡ ይህን አውቆ መንግስት ካስቀመጠው ታሪፍ ውጪ ባለመክፈል ተባባሪ እንዲሆን ተጠይቋል።

በተጨማሪም ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ የማይወጡ አሽከርካሪዎች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ላሉ የፀጥታ አካላት #ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ መብቱን እንዲያስከብር በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ / ቪድዮ : የ2015 ዓ/ም የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበርን የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ከላይ ተያይዟል። ፎቶና ቪድዮው የተሰባሰበው ከተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ነው። @tikvahethiopia @tikvahethmagazine
ፎቶ : የ2015 የሆራ ሀርሰዴ በዓል በቢሾፍቱ ዛሬ ተከብሯል።

የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎች ተያይዘዋል።

በዓሉ በሰላም መከበሩን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

የዘንድሮው 2015 ዓ/ም የ " ሆራ ፊንፊኔ " እና " ሆራ ሀረሰዴ " በዓል በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ለአዲስ አበባ ህዝብ እና ለቢሾፍቱ ህዝብ ምስጋና ቀርቧል።

@tikvahethiopia