TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦

" ከባህር ዳር የተነሱ ወደ 9 ባስ ወደ አዲስ አበባ መግባት ተከልክለው ቆመዋል።

በባሶቹ ውስጥ ተማሪዎች ይገኛሉ።

ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ስለሆነ በርካታ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ጋር እየሄዱ ነው።

በየፈጠረው ሁኔታ ቤተሰብ ጭንቀት ላይ ነው። አ/አ ለመድረስ 80 ኪ/ሜ ሲቀረን ነው የተከለከልነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦ " ከባህር ዳር የተነሱ ወደ 9 ባስ ወደ አዲስ አበባ መግባት ተከልክለው ቆመዋል። በባሶቹ ውስጥ ተማሪዎች ይገኛሉ። ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ስለሆነ በርካታ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ጋር እየሄዱ ነው። በየፈጠረው ሁኔታ ቤተሰብ ጭንቀት ላይ ነው። አ/አ ለመድረስ 80 ኪ/ሜ ሲቀረን ነው የተከለከልነው። " @tikvahethiopia
" ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለን እየተንገላታን ነው ፤ ወደ መጣችሁበትም ተመለሱ ተብለናል " - መንገደኞች

መነሻቸዉን ከአማራ ክልል አድርገዉ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱ መንገደኞች በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኀይሎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን ገለፁ።

በዚህ ምክንያትን እንግልት እየደረሰባቸው መሆን ጠቁመዋል።

ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸኖ ከተማ ጀምሮ ወደ አ/አ ለመግባት የሞከሩ መንገደኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፤ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ከነበረባቸው ሰዎች መካከል የህክምና ክትትል ያላቸው ዜጎች እንደሚገኙበት ገልፀዋል።

እራሳቸውን የሚገልፅ በቂ ማስረጃ፣ መታወቂያ ቢይዙም ወደ አ/ አ እንዳያልፉ መከልከላቸውን ጠቁመዋል።

ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የተለከለከሉት የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ እንዲሁም የአዲስ አበባ መታወቂያም ያላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ባወጣው ዘገባ ፤ ከመንገድ ተመልሰዉ በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ መንገደኞች የኢሬቻ በዓል እስኪያልፍ ድረስ አዲስ አበባ መግባት አትችሉም መባላቸዉን አስረድተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ የሆኑ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ለሚዲያው በሰጡት ቃል ፤ " እኛ ኢሬቻ በዓል ላይ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ ፍተሻ እያደረግን እንጅ መንገደኞችን አልመለስንም። "  ብለዋል።

ሚዲያው መንገደኞቹ እየተጉላሉ እንደሆነ መመልከቱን ገልጾ ላነሳው ጥያቄ  " ይህንን ጉዳይ አላዉቀዉም ችግሮች ካሉም እናስተካክላለን " ብለዋል፡፡

ም/ቢሮ ኀላፊዉ መንገደኞቹ ስለመመለሳቸዉና መንገዱ ስለመዘጋቱ እንደማያዉቁም ለክልሉ ሚዲያ ተናግረዋል።

ፎቶ ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
#Irreecha2015 #እንድታውቁት

ነገ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚከበረውን የ2015 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ተከትሎ በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ከለሊቱ 11፡00 ጀምሮ ፦
- የአንበሳ
- የሸገር
- የድጋፍ ሰጪ
- የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

እንደ ቢሮው መረጃ ፦

👉 ከአባኪሮስ አደባባይ፣
👉 ከአያት አደባባይ፣
👉 ከቱሉዲምቱ አደባባይ፣
👉 ጎሮ አደባባይ፣
👉 አዲሱ ገበያ፣
👉 ከቁስቋም፣
👉 ከሳንሱሲ፣
👉 ከአየር ጤና አደባባይ
👉 ከጀሞ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለን እየተንገላታን ነው ፤ ወደ መጣችሁበትም ተመለሱ ተብለናል " - መንገደኞች መነሻቸዉን ከአማራ ክልል አድርገዉ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱ መንገደኞች በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኀይሎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን ገለፁ። በዚህ ምክንያትን እንግልት እየደረሰባቸው መሆን ጠቁመዋል። ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸኖ ከተማ ጀምሮ ወደ አ/አ ለመግባት የሞከሩ…
" አሁንም እዛው ነን " - መንገደኞች

" ወደ አዲስ አበባ መግባት አይቻልም " ተብለናል ያሉ መነሻቸውን ከአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ያደረጉ መንገደኞች አሁንም በዛው ባሉበት እንደሉ ጠቁመዋል።

ከመንገደኞቹ መካከል የባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።

እኚህ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች ከግቢ እንዲወጡ የተቀመጠው የመጨረሻው ቀን ዛሬ መሆኑን በመግለፅ በርካታ ተማሪዎች ወደ ቤተሰባቸው እየተመለሱ ሳሉ ወደ አዲስ አበባ መግባት አይቻልም በሚል እየተንገላቱ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ሳቢያ ቤተሰብም መጨነቁን ጠቁመዋል።

መልዕክታቸውን የላኩት የቤተሰባችን አባላት ፤ " በርካታ ባሶች ቆመው ነው የሚገኙት እነዚህ ባሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ አቅመ ደካማ አረጋውያንን ይዘዋል ሁላችንም እየተጉላላን ነውና መፍትሄ ይፈለግልን " ብለዋል።

ሌሎች የቤተሰባችን አባላት የሆኑ ተማሪዎችም በተመሳሳይ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ወደ ፊቼ እንዲመለሱ መደረጉን ጠቁመው፤ " ስንት ቀን እንደምንቆይ አናውቅም፤ በጣም ነው የተጨነቅነው ቤተሰብም ተጨንቋል፤ እኛ ተማሪዎች ነን ለምን እንሰቃያለን ? " ብለዋል።

ያነጋገርናቸው ተማሪዎቹና ሌሎችም መንገደኞች በወቅታዊነት ያለውን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ አስፈላጊው አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ ከሰዓት የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ ምክትል ኀላፊ የሆኑ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከመገደኞች መንገላታት ጋር በተያያዘ ለአሚኮ በሰጡት ቃል " እኛ ኢሬቻ በዓል ላይ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ ፍተሻ እያደረግን እንጅ መንገደኞችን አልመለስንም። " ብለዋል።

ም/ቢሮ ኀላፊዉ መንገደኞቹ ስለመመለሳቸዉና መንገዱ ስለመዘጋቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ነው የተናግሩት።

@tikvahethiopia
#Irreecha2015

ለ " ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል " ወደ አዲስ አበባ የመጡ እንግዶችን ከተማዋ እያስተናገደች ነው።

በአዲስ አበባ የበዓሉን ድባብ ለመቃኘት በተለያዩ ስፍራዎች ተዘዋውረን እንደተመለከትነው የተለያዩ እንግዳ መቀበያዎች ተዘጋጅተው እንግዶችን እያስተናገዱ ነው።

በየመንገዱም የተለያዩ የባህል አልባሳት ፤ በዓሉን ማድመቂያ ቁሳቁሶች እየተሸጡ ይገኛሉ።

ለዚሁ ለኢሬቻ በዓል የጎረቤት ኬንያ ልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እየመጣ የሚገኝ ሲሆን ልኡካን ቡድኑ አርቲስቶችንና ሌሎች ታዳሚያንን ያካተተ ነው።

Photo Credit : Vist Oromia , Mayor Office of AA , OBN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቱን ለቀው እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይሁን እንጂ ጦርነትና የፀጥታ ችግር ካለባቸው የትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ለመሄድ እንደማይችሉ እና ውጪ ለመቆየት አቅም እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ገልጿል።

ፈተና እስከሚጠናቀቅ ተማሪዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ እንዲመቻችላቸው ህብረቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን የህብረቱ ፕሬዝዳንት ሚካኤል ያቦነሽ ለቲክቫህ ተናግሯል።

ህብረቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ተማሪዎቹ ብሔራዊ አደጋና ስጋት ኮሚሽን ማዕከላት እንዲቆዩ ጥያቄ ቢያቀርቡም ኮሚሽኑ እንደማይችል ገልጿል።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች የቴሌቪዥን ማሳያ ክፍሎችና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ተማሪዎቹ የሚቆዩበት መመሪያ እንዲሰጥ ህብረቱ ጠይቋል።

ተማሪዎቹ ለፈተና አሰጣጡ ስጋት እንዳይሆኑ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ከማደሪያቸው እንዳይወጡና ምግብም ከተፈታኞቹ በኋላ እንዲመገቡ በማድረግ ችግር እንዳይፈጠር ህብረቱ እንደሚሰራ የህብረቱ ፕሬዜዳንት ለቲክቫህ ገልጿል።

ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም በሁሉም የዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምንም አይነት መደበኛ ተማሪ እንዳይገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

More : @tikvahuniversity