" ተኩሱ የተከፈተው ከደቡብ ሱዳን ማሉዋል ጋኦት በሚባል ቦታ ነው " - አቶ ኡገቱ አዲንግ
ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ከ 45 አካባቢ መነሻቸውን ከጂካዎ ዲልድይ አድርገው ወደ መተሀር በመጓዝ ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ከደቡብ ሱዳን ማሉዋል ጋኦት በሚባል ቦታ ላይ ተኩስ ተከፍቶ አንድ ሰው ሲገደል ፤ 6 ሰዎች መቁሰላቸውን የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት አሳውቋል።
የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲያንግ በሰጡት ቃል ፤ ተኩሱ የተከፈተው ከደቡብ ሱዳን ማሉዋል ጋኦት ከሚባል ቦታ መሆኑን ገልፀው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን 6 ሰዎች መቁሰላቸውን አስረድተዋል።
የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው መካከል 2ቱ ላይ ከባድ አደጋ በመድረሱ በጋምቤላ ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑንና 4ቱ በኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከተሳፋሪዎቹ መካከል 3 ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ መሆኑንም ገልፀው መንግስት ክትትል እያደረገ ነው ብለዋል።
@tikvahethiopia

በደፈጣ ጥቃት 5 ሰዎች ተገደሉ።
የአማሮ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ትላንት " ዶርባዴ " በተባለ ቀበሌ በደፈጣ በተፈፀመ ጥቃት 5 አርሶ አደሮች መገደላቸው እና 3 አርሶ አደሮች እንደ ቆሰሉ ገልጿል።
ልዩ ወረዳው ጥቃቱ የተፈፀመው በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀው ኦነግ-ሸኔ እና ሸኔ ባደራጃቸዉ የጥፋት ቡድኖች ነው ብሏል።
ይኸው ቡድን ሰው በመግደል፣ በማቁሰል እና ንብረት በመዝረፍ የአከባቢዉን ሠላም የማደፍረስ የጥፋት ተግባር አሁንም ቀጥሏል ሲል ልዩ ወረዳው ገልጿል
የአማሮ ልዩ ወረዳ በቀጠናው ይንቀሳቀሳል ያለው ይኸው ቡድን እና የቡድኑ ተላላኪዎች የህዝቡን የተረጋጋና ሠላማዊ እንቅስቃሴ በማደፍረስና ለማደፍረስ እየሠሩ ቆይተዋል ሲል አስታውሷል።
ሁሉም የአከባቢው ማህበረሰብ በየደረጃዉ ከሚገኙ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት አከባቢዉን በንቃት እንዲጠብቅም አሳስቧል።
ልዩ ወረዳው የፌደራሉ መንግሥት ከኦሮሚያ መንግሥት ጋር በቅንጅት በመሥራት በአጎራባች ምዕራብ ጉጅ ዞን የተጀመረዉ የሠላም ማስከበር ሥራ በአማሮ በኩል በመሥራት የአከባቢዉን ሠላም ለማስጠበቅ መሥራት እንዳለባቸውም ጠይቋል።
ትላንት ከተፈፀመው የደፈጣ ጥቃት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በልዩ ወረዳው ሲፈፀሙ የነበሩ ማንነት ተኮር ጥቃቶችን ለማጣራት ወደ ስፍራው ያቀና የፓርላማ አባላት ቡድን ውይይት ሳያከናውን ለመመለስ መገደዱ ታውቋል።
በአማሮ ልዩ ወረዳ እና በቀጠናው ከቅርብ አመታት ወዲህ በሚፈፀሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እጅግ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፤ ዝርፊያ ተፈፅሟል ፤ በርካቶችም በሰላም እጦት ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል።

" የምንሄድበት የለም፤ መፍትሄ ይፈለግልን " - ተማሪዎች
የከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል ከተለያዩ የፀጥታ ችግር ካለባቸው የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ተከትሎ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ ገልፀዋል።
የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሰጠቱን ተከትሎ ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማንኛውም ተማሪ እንዳይገኝ ተብሏል።
ይህ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ጭንቀት ውስጥ የከተተ ሲሆን ተማሪዎቹ መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።
አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልና ቤተሰቦቹ በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ፤ "ወደ መጡበት ቦታ መመለስ የማይችሉ ተማሪዎች ምን ሊደረጉ ነው ? ጦርነት ካለበት ቦታ የመጣን ተማሪዎች አለን ድምፃችን ተሰምቶ መፍትሄ ይፈለግልን፤ ወደ ቤታችን መሄድ አንችልም፤ መሄጃም የለንም" ብሏል።
ሌሎችም ተማሪዎች በተመሳሳይ መሄጃቸው እንደጨነቃቸው ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ 50 የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች መኖራቸው ለማወቅ የቻለ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ መሄጃ ለጠፋቸው ተማሪዎች ምን አሰቧል በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የቅርብ ሰው ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
እኚሁ ሰው ዩኒቨርሲቲው ለትምርህት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቦ ከግቢ ይውጡ እንደተባለና ምናልባት ከፈተና መለስ እንደሚመለሱ አስረድተዋል።
መሄጃ የሌላቸው ተማሪዎች እስከዛ የት እንዲያርፉ ታስቧል ለሚለው ጥያቄ፤ ከግቢ ወጥተው ወደየ መጡበት/ቤተሰብ ጋር ይሂዱ መባሉን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ ቢያስቀምጥ ጥሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ት/ት ሚኒስቴር ሚሰጠን ምላሽ ካለ እናሳውቃለን።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባህርዳር
የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ የከተማው የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ለአሚኮ በሰጠው ቃል አሳውቋል።
ከተማዋ የተለያዩ ሁነቶችን በሰላም እያስተናገደች መሆኑን እና #ለመስቀል_በዓል እንዲሁም #ለጣና_ፎረም ዝግጅት እያደረገች መሆኑን መምሪያው ገልጿል።
መምሪያው የተለያዩ አካላት የከተማውን ሰላም በተመለከተ የሚያራግቡት ወሬ ሀሰተኛ እና መሰረተቢስ በተጨማሪም የባህር ዳርን ህዝብ የሚወክል አይደለም ብሏል።
የከተማው የፀጥታ ኃይል ከተማውን በንቃት እየጠበቀ ነው ፤ ሌት ተቀን ፓትሮል ያደርጋል፣ የኬላ ጥበቃዎችም አሉ ፣ ፍተሻም አለ የመንደር ጥበቃዎችም በተጠናከረ ሁኔታ ነው ያሉት ሲል አሳውቋል።
ትላንት ለሊት 6 ሰዓት ገደማ የባህር ዳር ፖሊስ መምኢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ዋጋው ታረቀኝ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
ምንድነበር የተፈጠረው ?
የባህር ዳር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አትንኩት አያለው ስለ ኮማንደር ዋጋው ታረቀኝ ህልፈት ለአሚኮ የተናገሩት ፦
" ትላንት እኔ አባይ ማዶ ነበርኩ እሱ ምክትል ኃላፊ ስለሆነ በተባበሩት አቅጣጫ ነበር።
ጥይት ተተኩሶ ሲደርስ በአጋጣሚ እዛ አካባቢ የሚጠጣ በጣም የሰከረ ሰው አግኝቷል። ማነው የተኮሰ ? ሲባል እኔ ነኝ የተኮስኩት ነው የሚለው ፤ የታጠቀ አካል ነው።
ለመታወቂያ ተባበረኝ ሲለው በጣም ሰክሮ ስለነበር በመመላለስ ላይ እያለ ጥይት ተኩሶ መታው ፤ በኃላም ሆስፒታል ከገባ በኃላ ህይወቱ አልፏል።
ከዛ በኃላ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ሰውየውን ተከታትልነው ፤ ተከትለን ቁም ሲባል እኛ ላይ በከፈተው ተኩስ ፤ በተኩስ ልውውጥ ሰውየው እጁን አልሰጥም ብሎ ህይወቱን አጥቷል። "

* ብሔራዊ ፈተና የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው። በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ…
#ብሔራዊ_ፈተና
ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።
ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦
- ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።
- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።
- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚፈቀዱላቸው ፦
• መጽሐፍት፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።
ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦
• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።
- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ " SKYTRAX 2022 " የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ላይ በ4 ዘርፎች ተሸለመ።
አየር መንገዱ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተገልጿል። ደረጃው በዓለም ዙሪያ ባሉ የአየር መንገድ ደንበኞች በተሰጠ ድምጽ ነው።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሸለማቸው ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ?
🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ፤
🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ ለ4 ተከታታይ ዓመታት
🇪🇹 የ2022 የአፍሪካ ምርጥ ኢኮኖሚ ክላስ ደረጃ ፤ ለ4 ተከታታይ ዓመታት
🇪🇹 በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነትን ሽልማት አሸንፏል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Tikvah Ethiopia (Magazine) 👇
https://t.iss.one/+Rx7P5YHQp_G16wyX
Tikvah Ethiopia (አፋን ኦሮሞ) 👇
https://t.iss.one/+UTMftkYHBuOGaQ23
https://t.iss.one/+Rx7P5YHQp_G16wyX
Tikvah Ethiopia (አፋን ኦሮሞ) 👇
https://t.iss.one/+UTMftkYHBuOGaQ23
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት ከማለዳው አንስቶ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የፀጥታ ችግር መኖሩንና ንፁሃን ሰዎች ላይ በታጣቂዎች ጥቃት መከፈቱን ነዋሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ። እስካሁን ባለው ሁኔታ በቁጥር ያልተለዩ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የገለፁት ነዋሪዎች አካባቢው አሁንም ባለመረጋጋቱ ተጨማሪ ጥፋት ስለሚደርስ የመንግስት የፀጥታ ኃይል ወደ ስፍራው ገብቶ እንዲያረጋጋ ተማፅነዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የጦርነት…
#ሆሮ_ጉድሩ_ወለጋ
ከሰሞኑን ነዋሪዎች ትኩረት ይሰጠው ሲሉ ድምፃቸውን ባሰሙበት በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ንፁሃን መገደላቸውን መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ " ከሰሞኑ አሸባሪው ሸኔ ሆሮጉድሩ ወለጋ በንጹሐንና ዜጎችና በአካባቢው ሚሊሻ አባላት ላይ ግድያ ፈጽሟል። " ብሏል።
ቡድኑ በተለያዩ የምዕራብ ኦሮምያ አካባቢዎች በጸጥታ ኃይሎችና በሕዝቡ ቅንጅት ርምጃ ተወስዶበታል ያለው መንግስት እየተበተነ ወደ ሆሮ ጉድሩ ጃርደጋ ጃርቴ አካባቢ ሲሸሽ ነበር ሲል ገልጿል።
መንግስት በመግለጫው ቡድኑ በንጹሐን ላይ የወሰደው በሁለት ምክንያቶች ነው " የመጀመሪያው በትናንትናው ዕለት የተደመሰሱበትን ጃል ኡርጂ የተባለውን የአካባቢውን የሸኔ አዛዥና ጀሌዎቹን ደም ለመበቀል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የመስቀልንና የኢሬቻን በዓላት ከወዲሁ ለማወክ ነው " ሲል አብራርቷል።
መንግስት በመግለጫው ላይ ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉ ያለው ነገር የለም።

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ፓሊስ በመምሰል የአንድን ግለሰብ ቤት ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች ሙከራቸው በህብረተሰቡ እና በፀጥታ ኃይሎች ትብብር መክሸፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው " ቀጠና አንድ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን 4 የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱና 2 ሲቪሎች ሆኖው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በመግባትና ሀሰተኛ የፌዴራል ፖሊስ መታወቂያ በማሳየት በር እንዲከፈትላቸው ካደረጉ በኃላ ሰራተኛዋን አግተው ዝርፊያ ሊፈፅሙ ሲሉ በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ሀይሎች እና ህዝባዊ ሰራዊቶች የዝርፊያ ሙከራቸው መክሸፉን አስተሳደሩ ገልጿል።
የፀጥታ ሀይሎች ቀድሞም በነበራቸው ጥርጥሬ ዘራፊዎቹን ሲከታተሏቸው እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን ዘራፊዎች ከውጭ ባስቀመጧቸው ግብር አበሮቻቸው ቀድሞ አዘጋጅተውት በነበረው " ኮድ 3 ኦሮ " በሆነ ተሽከርካሪ ሊያመልጡ ችለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ቢያመልጡም በአካባቢው የደህንነት ካሜራ ስለነበረ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞት ክትትል እያደረገበት ይገኛል ተብሏል።
ማህበረሰቡ እራሱን ከመሰል አጭበርባሪዎች ሊጠብቅ ይገባል፤ አጠራጣሪ ነገሮችንም ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ሊያሳውቅ ይገባል ተብሏል።

#ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ማዕድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ኢትዮጵያን የማይመጥኑ ያሏቸው ኩባንያዎች ላይ መስሪያ ቤታቸው እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል ገለፁ።
ኢ/ር ታከለ ኡማ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው " ኢትዮጵያን የማይመጥኑ የስራ አቅም የሌላቸው (ድኩማን) ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ማዕድን ኃብታት ለዘመናት አክሳሪ ጨዋታ ተጫውተዋል " ብለዋል።
" እነዚህ ጨዋታዎች ከዚህ በላይ እንዳይቀጥሉ ተገቢ እርምጃዎችን መውሰዳችንን እንቀጥላለን " ሲሉም አሳውቀዋል።
ሚኒስትሩ " የስራ አቅም የሌላቸው (ድኩማን) " ሲሉ የጠሯቸውን ኩባንያዎች በግልፅ ከመጥራት ተቆጥበዋል።
ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ ከቆየው ፖሊ-ጂሲ.ኤል ጋር የነበራትን ውል ከረጅም ጊዜ ትእግስትና ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ማቋረጧን ኢ/ር ታከለ ኡማ አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

ፎቶ ፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለክቡር ዶክተር ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለክብር ዶክተር ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሰጥቷል። ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር የሚኖሩ፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ፤ ታላቅ አባት ናቸው። ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአትሌቲክ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ለኢትዮጵያ ብሎም…
#Update
የክብር ዶክተር ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ።
ከሀገር ውጭ የነበሩት ብፁዕ ኡቡነ ኤርምያስ ዛሬ ረፋዱን ወደ ባሕርዳር ሲገቡ ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንት፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በባሕር ዳር ዓለም አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተገኝተውም በዩኒቨርሲቲው የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።
ባለፈው ዓመት ነሀሴ 21 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለክቡር ዶ/ር ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለክብር ዶ/ር ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መስጠቱ የሚዘነጋ አይደለም።
Photo Credit : AMC