TIKVAH-ETHIOPIA
* ብሔራዊ ፈተና የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው። በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ…
" በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን ፦
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤
- ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ፈተናው የተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወስን በመሆኑ በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡
(የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ)
@tikvahethiopia

#AddisAbaba
" ከቤት ውጣ ብላኛለች " በሚል ምክንያት ሴት አያቱን የገደለው ተከሳሽ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት በፅኑ እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ነሃሴ 26 ቀን 2012 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቀጠና 5 ወጣት ማዕከል አካባቢ ነው፡፡
ተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስ የ79 ዓመት ዕድሜ ካላቸው ከአባቱ እናት ጋር ይኖር የነበረ ሲሆን " ከቤት ውጣ ብላኛለች " በሚል ምክንያት ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ላይ አያቱን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ጭንቅላታቸውን በመዶሻ ደጋግሞ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
ፖሊስ ክስ ለመመስረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የቴክኒክና የታክቲክ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል፡፡
የተከሳሽ ሮቤል ቴዎድሮስን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት ግለሰቡ ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጡ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
(አዲስ አበባ ፖሊስ)

#ATTENTION ወልድያ ! በዛሬው ዕለት የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ ቤት ከዚህ ቀደም ካሳለፈው ውሳኔ ተጨማሪ ውሳኔዎችን አሳልፏል። የከተማውን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ ከተማ በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ መውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ክልከላዎችን ማስቀመጥ አስፈልጓል ተብሏል። ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ፦ - ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ…
#Update
ወልድያ !
የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ የማሻሻያ ውሳኔ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2015 ዓ/ም አሳልፏል።
ሌሎች ክልከላዎች እንደቀጠሉ ሆኖ በሰዓት እላፊ ገደብ ላይ የተደረገው ማሻሻያ ፦
- ከቀኑ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የተሽከርካሪ የሰዓት እላፊ ወደ ምሽቱ 1:00 ሰዓት፤
- ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የነበረው የሰዎች እንቅስቃሴ የሰዓት እላፊ ገደብ ወደ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ተራዝሟል።

#Djibouti
የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጅቡቲ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጅቡቲ ያቀኑት ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ነው።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ጅቡቲ በደረሱበት ወቅት ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው።
ትላንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ኢማኤል ኦማር ጌሌ ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ኬንያ ፣ ናይሮቢ እንደነበሩ ይታወሳል።
#Update
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሻሻል ባደረጉት ጥረት፣ እ.ኤ.አ የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል ሽልማታቸውንም በጅቡቲ ተቀብለዋል።

#AU_led_PeaceProcess
" መንግስት በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ ነው " - አቶ ደመቀ መኮንን
" የአውሮፓ ህብረት (EU) በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ይደግፋል " - ሪታ ላራንጂንሃ
ዛሬ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሆኑት ሪታ ላራንጂንሃ ውይይት አካሂደው ነበር።
በዚህም ወቅት አቶ ደመቀ ፤ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ምትክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በሰሜን ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ስላደረገው የሰላም ግንባታ ጥረት ገለጻ እንዳደረጉ ተገልጿል።
አቶ ደመቀ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው ፤ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሪታ ላርንጃንሃ በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነቱን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
ዳይሬክተሯ ፤ የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደሚደግፍ ገልፀው ፤ የሰላም ሂደቱን መደገፍ በሚፈለግ ጊዜ ለመርዳት ህብረቱ ፍላጎት እንዳለው አፅንኦት ሰጥተዋል።
መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#ETHIOPIA
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ከተቀሰቀሰ በኃላ እስካሁን ምን ሆነ (እጅግ በጥቂቱ) ?
- ህወሓት ቆቦና የአካባቢው ቦታዎችን መቆጣጠሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ሰላም እና ደህንነት ፍለጋ ወደ አጎራባች ከተሞች እንዲፈናቀል ምክንያት ሆኗል።
- እንደ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በመቐለ በተፈፀመ የአየር ጥቃት 4 ሰዎች ተገድለዋል ፤ 2ቱ ህፃናት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ንፁሃንን ዒላማ ያደረገ ጥቃት እንደማይፈፅም በመግለፅ የወጡ ክሶችን አስተባብሎ ነበር።
- ህወሓት በአፋር ክልል " ያሎ " በኩል በሰነዘረው የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የዱብቲ ጠቅለላ ሆስፒታል የገለፀ ሲሆን በጥቃቱ ህፃናት ተገድለዋል። አንዲት እናት ሁለት ህፃናት ልጆቿ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ተገድለውባታል። የቆሰሉም በርከት ያሉ ናቸው።
- የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር እንደገለፀው " ወለህ " አካባቢ ህወሓት 10 ሰላማዊ ሰዎችን በግፍ መግደሉን፣ ከሟቾች መካከል አንዲት እናት ከነ ልጆቿ እንደምትገኝበት ገልጿል። በተጨማሪ ቡድኑ ወደ ወለህ መጠለያ ጣቢያ በመግባት 25 ሰዎችን መግደሉን አስተዳደሩ ገልጿል።
- ህወሓት በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ለሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኑ በገለፀ በሰዓታት ውስጥ ይዟቸው በሚገኙ የራያ ቆቦ ወረዳዎች በንፁሃን ላይ ጥቃት መዘንዘሩን ነዋሪዎች መግለፃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። ህወሓቶች በቀበሌ 02 ሰው መግደላቸው፣ ማቁሰላቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከጥቂት ቀናት በፊትም አራዱም ላይ ሰላማዊ ሰው መግደላቸውን ገልፀዋል። ባለፉት 18 ቀናት ሌሎች ያልታጠቁ ንፀሃን ሰዎችን መግደላቸውና በተጨማሪ ዝርፊያ እንደፈፀሙ ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።
- የመቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል እንደገለፀው 2 ጊዜ በተፈፀመ የአየር ጥቃት 10 ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ የመጀመሪያዎቹን ተጎጂዎች ለመርዳት በተሰበሰቡበት ወቅት በተፈፀመ ጥቃት የተገደሉ ናቸው ብሏል። (ይህ የሆነው ትላንት ነው)
- UN OCHA በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ባገረሸ ግጭት በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል።
እንደ UN OCHA መረጃ ፦
👉 በአማራ ፣ አፋር፣ እና ትግራይ ክልሎች በ10 ሺዎች መፈናቀለቸውን ገልጿል።
👉 የሰብዓዊ እርዳታ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ መግባት እንዳቆሙ፣ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በረራ እንደተቋረጠ መሆኑን ገልጿል።
👉 በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ለመገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
👉 በመርሳ ከተማ በ5 ት/ቤቶች አብዛኞቹ #ህፃናት እና #ሴቶች ከቆቦ እና አካባቢው ተፈናቅለው ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ለእነሱ ምግብ እና ምግብ ያልሆኑ ድጋፎችን ማሰራጨት ጀምራለሁ ብሏል።
- የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል በዞኑ የተፈናቃዮች ቁጥር እጅግ እየጨመረ መሆኑን ገልጾ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልጿል። መርሳ በሚገኙ ት/ቤቶቹ ውስጥ ያሉት ሴቶች እና ህፃናት ሲሆኑ ወንዶች ወጣቶች እንዲገቡ አልተደረገም። በአጠቃላይ ወልድያ እና መርሳ ከተሞች ላይ 92,400 ተፈናቃይ አለ።
- ጦርነቱ ዳግም ካገረሸ ወዲህ በርካታ ንብረቶች ወድመዋል።
- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ወደ ባህርዳር ቢሮው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መልዕክቶች እየመጡለት ሲሆን አካባቢዎቹ ላይ ምቹ ሆኔታ ሲፈጠር ምርመራ አድርጎ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
NB. የተዘረዘሩት ክስተቶች ግጭት ዳግም ካገረሸ ወዲህ #በተለያዩ_ጊዜያቶች የተሰሙ ናቸው።
የሰላም ሂደቱ ምን ያህል ተስፋ ሰጪ ነው ?
የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ለሰላማዊ ንግግር ዝግጁ መሆኑን ከሳምንታት በፊት ገልጾ ነበር።
ህወሓት በአፍሪካ ህብረት (AU) አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦባሳንጆ ላይ እምነት እንደሌለውና በሂደቱ መተማመን እንደሌለው ሲገልፅ ከቆየ በኃላ ከቀናት በፊት በህብረቱ መሪነት ለሚደረግ የሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
ይህንን የህወሓት የሰላም ሂደት መቀበል እና ግጭት ለማቆም ዝግጅቱነት እንዳለው መግለፁን በተመለከተ በርካታ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ውሳኔውን በማድነቅ የሰላም ሂደቱ እንዲፋጠን ጥሪ አቅርበዋል።
ዳግም ያገረሸው ጦርነት ግን አሁንም አልቆመም።
የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ህወሓት ላወጣው መግለጫ በግልፅ ቀጥተኛ ምላሽ ባይሰጥም ትላንት ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር በተወያዩበት ወቅት መንግስት ለአፍሪካ ህብረት የሰላም ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ቁርጠኛ መሆኑን በዩናይትድ ኪንግደም ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።
የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ እንዲያገኝ መንግስት ዝግጁነት እንደነበረው ነገር ግን ህወሓት በቅርቡ ወረራ መፈፀሙን ኤምባሲው ዛሬ አመልክቷል።
አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ግጭቱ እንዲፈታ የሚያምንበት ብቸኛ አማራች ሰለማዊ መፍትሄ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ አልጀዚራ ላይ ባወጡት ፅሁፍ መንግስት በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ለሰላም ውይይት ዝግጁ እንደሆነ አስታውሰው ህወሓት የሰላም ጥሪ ገፍቶ ጦርነት ከፍቷል ብለዋል።
ህወሓት የጀመረውን ጥቃት በማቆምም ወደ ሰላም ድርድር እንዲመለስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል።
በአፍሪካ ህብረት ስር ለሚደረገው ድርድር ፍላጎቱን ማሳየቱን ተከትሎ በቃሉ እንዲፀና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከዝምታው በመውጣት የመንግስትን የሰላም አማራጭ በመደገፍ ህወሓት ታጣቂዎቹን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ድርድር እንዲገባ ጫና ማድረግ አለበት ሲሉም አሳውቀዋል።
ህወሓት ወደሰላም እንዲመለስና ሰላምን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ማድረግ ያለበት አሁን ነው ያሉት አምባሳደሩ ይህ ካልሆነ መንግስት ህዝብን የመጠበቅ ግዴታ ስላለበት ግዴታውን ይወጣል ብለዋል።
ከቀናት በፊት " ህወሓት " ፤ በአፍሪካ ኅብረት (AU) የሚመራ ተዓማኒ የሰላም ሒደት እንደሚጠብቅ ፤ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ፤ ለድርድሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ፣ ለአፋጣኝ እና በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ተግባራዊ ለሚደረግ የተኩስ አቁም ዝግጁ መሆኑን መግለፁ እንዲሁም ለግጭት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማምጣት የሚቻለድ በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንደሆነ እግጠኛ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል።

" ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመሩን በበጎ እቀበለዋለሁ " - ኢሰመኮ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመር እንዲሁም የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በበጎ እንደሚቀበለው ገልጿል። ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በአፋር ክልል፣ ሰመራ ከተማ የሚገኙትን አጋቲና እና…
ምስጋና !
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፦
" የአፋር ክልላዊ መንግሥት በሰመራ እና አጋቲና መጠለያ ጣቢያዎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች በኢሰመኮ ምክረ ሃሳቦች መሰረት እንዲለቀቁና በፍላጎታቸው መሰረት ወደመጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ በማድረጉ ኢሰመኮ እውቅና ይሰጠል።
በተለይ በዚህ ሥራ ላይ በዋናነት የተሳተፉትን የአፋር የክልል አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ቢሮ፣ የክልሉ የጤና ቢሮ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም በዚህ ሂደት ለክልሉ መንግሥት ድጋፍ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ኮሚሽኑ ለማመስገን ይወዳል። "

#Volvo
ታዋቂው የመኪና አምራች ኩባንያ " ቮልቮ " በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን የጥገና እና የሽያጭ ማዕከል በዱከም ከተማ ይፋ አድርጓል።
ይፋ በማድረጊያው መርሃ ግብር ላይ እንደተገለፀው ቮልቮ በመላው ዓለም ካሉት 2201 ቅርንጫፎቹ መካከል አንዱ የሆነው ይህ በዱከም ከተማ የተመረቀው ማዕከል ነው።
በስነስርዓቱ የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሾመ አዱኛን ጨምሮ የቮልቮ የአፍሪካ ዳይሬክተር ፣ የስዊድን አምባሳደር እንዲሁም በርካታ ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።
(ዋፋ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን)

#Dubai #Ethiopia
የዱባይ ቱሪዝም የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ተካሄደ።
ዱባይ ቱሪዝም የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች ኤግዚቢሽን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ተካሂዷል።
ኤግዚቢሽኑ በኢትዮጵያ ካሉ የዘርፉ ባለድሻዎች ጋር በቅርበት በመስራት ዱባይ በውድ ዋጋ ብቻ ሳይሆን በተመጣጣኝ ክፍያ መጎብኘት የሚቻልባቸውን መንገዶች ማመላከት ዓላማ አድርጎ መካሄዱ ነው የተገለጸው።
በዚህ ዝግጅት ከዱባይ ቱሪዝም ጋር ወደ አዲስ አበባ ከ25 የማያንሱ ድርጅቶች ተወካዮቻቸውን የላኩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሥራቸውን በማቅረብ በኢትዮጵያ ካሉ የአስጎብኚ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር ትውውቅ አድርገዋል።
ዛሬ ከተካሄደው የዱባይን የቱሪዝም ገብያ ከማስተዋወቅ ባለፈ በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለቁጥራቸው 200 ለሚጠጉ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አስጎብኚ ድርጅቶች ሥልጠና ተሰጥቷል።
ከሁለት ቀኑ መርሐግብር በተጨማሪ በዛሬው የመዝጊያ መርሐግብርም በዕለቱ ከተገኙ የቢዝነስ አጋሮች እንዲሁም የአስጎብኚ ድርጅቶች ዕጣ በማውጣት የነጻ ጉዞ ዕድሎች እንደሚመቻችላቸው አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።
ይህና መሰል የትውውቅ መድረክ ከዚህ ቀደም ሳይኖር #ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ዱባይ በሚደረግ የንግድና የቱሪዝም ጉዞ ከናይጄሪያ ቀጥላ ሁለተኛ ሀገር ናት።
በቀጣይም በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሰፊ ሥራዎች ለመስራት ታቅዷል።
ፎቶ : ዛሬ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል የተካሄደው የትውውቅ መድረክ