የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ወጣ !
የብሄራዊ ሌተሪ አስተዳደር የእንቁጣጣሽ ሌተሪ ትላንት ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ ዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት መውጣቱን አሳውቋል።
የአሸናፊ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !
ሀገራችን #ኢትዮጵያ በራሷ አቆጣጠር ዛሬ ያለፈውን 2014 ዓ/ም ሸኝታ አዲሱን 2015 ዓ/ም ተቀብላለች።
መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን እንኳን ይህችን ቀን ለማየት አበቃን ፤ እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !!
2014 ዓ/ም ሸኝተን 2015 ዓ/ምን ስንቀበል ደስታችን ሙሉ ሆኖ አይደለም፤ ልክ 2013 ዓ/ምን ሸኝተን 2014 ዓ/ምን እንደተቀበልነው ጊዜ ሁሉ ዛሬም ከጦርነት እና ከግጭት ቀጠና ያልወጡ ብዙ ወገኖቻችን አሉ።
በ2014 ዓ/ም ብዙ ወገኖቻችን በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች በነበሩ ግጭቶች እንዲሁም ጦርነት አጥተናል ፤ ብዙዎች ተጎድተውብናል፣ በርካታ ወገኖቻችን በደረሰባቸው ችግር ሰው ጠባቂ ሆነዋል። በተፈጥሮም አደጋ ያጣናቸው ወገኖቻችን ብዙ ናቸው።
በዓመቱ ችግር የደረሰባችሁ፣ የምትወዷቸውን ከአጠገባችሁ ያጣችሁ፣ ልጆቻችሁን የተነጠቃችሁ ወላጆች፣ ወላጆቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ ሁሉ ፈጣሪ መፅናናት እና ብርታትን ይሰጥልን ዘንድ እንማፀናለን። የተጎዱ ወገኖቻችንም ፈጥነው እንዲያገግሙ እንማፀናለን።
ዛሬ የተቀበልነው 2015 አዲስ ዓመት ከምንም ነገር በላይ ወገኖቻችንን ችግር የማንሰማበት ፣ የሰላም ፣ የደስታ ፣ መልካም መልካሙን ምንሰማበት ፣ ከችግሮቻችን ሁሉ ተቃላቀን ደስ የምንሰኝበት ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።
ፈጣሪ ሀገራችንን #ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!
Tikvah Family ❤️

#UpdateAU የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ዛሬ ተቀብለው ማነጋገራቸውን በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም #በአፍሪካ_ኅብረት_የሚመራውን የሰላም ሂደት ዓለም አቀፍ አጋሮች እንዲደግፉ መስማማታቸውን…
#ETHIOPIA
ዛሬ እና ባለፉት ቀናት ምን ሆነ ?
- የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል በተጨማሪ ከህወሓት መሪ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋርም በምን አይነት መልኩ እንደተነጋገሩ ባይታወቅም ተነጋግረዋል (እንደ አሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ)። ሐመር ዛሬም እዚሁ አዲስ አበባ ናቸው።
- አምባሳደር ሐመር ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ጋር ተወያይተዋል።
- የአፍሪካ ህብረት በኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ላይ " ሙሉ እምነት " እንዳለው ገልጾ ኃላፊነታቸውን አራዝሟል።
- ኦባሳንጆ እና ሙሳ ፋኪ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።
- ዛሬ በአዲሱ ዓመት ደግሞ ከዚህ ቀደም በኦባሳንጆ ላይ እምነት የለኝም ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት ጋር እደራደራለሁኝ ሲል መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ፦
• በአፍሪካ ኅብረት የሚመራ ተዓማኒ የሰላም ሒደት እንጠብቃለን ብሏል።
• በ " አፍሪካ ህብረት መሪነት " ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ፤ ለድርድሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ፣ ለአፋጣኝ እና በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ተግባራዊ ለሚደረግ የተኩስ አቁም ዝግጁ ነኝ ብሏል።
• በ2ቱ ወገኖች ተቀባይነት የሚኖራቸው አደራዳሪዎች ፣ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እና ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች በሰላም ሂደቱ ሊሳተፉ ይገባል ብሏል።
• ተደራዳሪዎቹ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ እንደሆኑ ገልጾ በፍጥነት ተደራዳሪዎቹን ለመላክ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
• ለዚህ አሳዛኝ ግጭት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማምጣት የምንችለው #በሰላማዊ_ውይይት_ብቻ እንደሆነ እርግጠኞች ነን ብሏል።
➣ ዛሬ በ "ህወሓት" በኩል በወጣው መግለጫ ላይ ቅድመ ሁኔታዎች ተብለው የተዘረዘሩ ነጥቦች የሉም።
የ " ህወሓት " ን የዛሬ መግለጫ በተመለከተ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ መንግስት የተባለ ነገር የለም። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ መሆኑን በማረጋገጥ ፤ የሰላም ድርድር ኮሚቴውን አባላት በዝርዝር ማሳወቁ አይዘነጋም።
የሰላም ሂደቱ ተፈፃሚ የሚሆነው #በአፍሪካ_ህብረት ጥላ ስር ብቻ እና ብቻ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለፁ ይታወሳል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ህወሓት ዳግም ጥቃት መክፈቱን ካሳወቀ በኃላም በተደጋጋሚ ባወጣቸው መግለጫዎች ለሰላም የዘረጋው እጅ እንዳልታጠፈና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ " ህወሓት " ወደ ተከፈተው የሰላም በር እንዲመለስ ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር።

#ETHIOPIA ዛሬ እና ባለፉት ቀናት ምን ሆነ ? - የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል በተጨማሪ ከህወሓት መሪ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋርም በምን አይነት መልኩ እንደተነጋገሩ ባይታወቅም ተነጋግረዋል (እንደ አሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ)። ሐመር ዛሬም እዚሁ አዲስ አበባ ናቸው። …
#UpdateAU #ETHIOPIA
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።
ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት ጋር እደራደራለሁ ካለ በኃላ ባወጡት መግለጫ ነው።
ሊቀመንበሩ ይህ አዎንታዊ የሆነ እድገት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምን ወደነበረበት ለመመለስ ልዩ አጋጣሚ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የትግራይ ክልል መንግስት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን በመግለፁም ሊቀመንበሩ አመስግነዋል።
ከዚህ ባለፈ ሁለቱም ወገኖች (የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት) በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ለማድረግ እንዲሰሩ እና የፊት ለፊት ንግግር እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ላይ ሁለቱም ወገኖች የሚስማሙባቸው ዓለም አቀፍ አጋሮች እንደሚካተቱ ጠቁመዋል።
ሙሳ ፋኪ መሀመት በመግለጫቸው ላይ በዚህ ወሳኝ ወቅት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

#UpdateAU #ETHIOPIA የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት…
#USA #ETHIOPIA
" አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል።
ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው።
ብሊንከን ፤ የአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሲባል ከህወሓት ጋር " በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ " ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ ያስታወሱት ብሊንከን ለዚህ የመንግስት ዝግጁነት የሚሰጥ ምላሽን እናበረታታለን ብለዋል። ህወሓት (TPLF) ግጭት ለማቆም እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያወጣውን መግለጫ እናበረታታለን ሲሉም አክለዋል።
ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰላም ሂደቱን ለማገዝ ዝግጁ ናቸውም ብለዋል።
ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማቀጣጠል ማቆም አለባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።
አሜሪካ የኢትዮጵያን #አንድነት፣ #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት እንደምትደግፍ የገለፁት አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ #ጠንካራ_አጋርነት መመለስ ትፈልጋለች ሲሉ ገልፀዋል።
" የአዲስ ዓመት መንፈስን ታሳቢ በማድረግ የአገሪቱ መሪዎች አገሪቱ መከራዋ ወደሚያበቃበት እና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኝ ወደሚያስችል መንገድ እንደሚሯት ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

#USA #ETHIOPIA " አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው። ብሊንከን ፤…
#UN #EU
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በአስቸኳይ ለማቆም እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ማሳወቁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።
በተጨማሪ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው የሰላም ሂደት ፍቃደኛ መሆኑን አበረታተዋል።
ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ይህንን እድል ለሰላም እንዲጠቀሙበት እና ግጭት እንዲቆም እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንዲሁም ለውይይት አማራጭ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
ሁለቱም በቅን ልቦና ሳይዘገዩ እንዲሁም ለውይይቱ መካሄድ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አበረታተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ዋና ፀሀፊው በመጨረሻም አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን የደስታ እና የሰላም እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፤ የአውሮፓ ህብረት የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአስቸኳይ ግጭት ለማቆም እና በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን መግለፁን ተከትሎ " አሁን ፤ ይህንን እድል ሁሉም ሊጠቀምበት ይገባል " ብሏል።
የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ ህብረትን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል።

#Harari #SafaricomEthiopia በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል። በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል። ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች…
#ADAMA #BAHIRDAR
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል።
ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል።
የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።
📍ባህር ዳር
አራት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ቀበሌ 14 - የተባበሩት ፊትለፊት፣ ቀበሌ 16 - ኖክ ፊትለፊት፣ ቀበሌ 11 - አባይ ማዶ፣ ቀበሌ 12 - ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ካምፓስ ፊትለፊት) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።
📍አዳማ
ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ፍራንኮ እና ፖስታ ቤት አካባቢ) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።
በባሕር ዳር እና አዳማ ከተማ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡
የሳፋሪኮም የጥሪ ማእከል 700 ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞችን በዚሁ ማግኝት ይቻላል። በአማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማልኛ ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይቻላል።

* ብሔራዊ ፈተና
የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።
በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ።
ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው።
በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፦
- ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ ነው።
- ተፈታኝ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመድበዋል። ምደባው ሲዘጋጅ በተቻለ መጠን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲመደቡ ተደርጓል። በአቅራቢያቸው ያለው ዩኒቨርሲቲ በመኝታ ወይም በመፈተኛ ክፍሎች ብዛት ውስንነት ካለበት ወደ ሌላ ዞንና ክልል የመሄድ ዕድል ይኖራል።
- ገጠር አካባቢዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይጓጓዛሉ።
- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች በመፈተናቸው ምክንያት ግን ወደ ተማሪዎችም ሆነ ወደ ወላጆች የሚሄድ ወጪ አይኖርም።
- ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንዲላመዱት ለማድረግ ሲባል ፈተናው ከሚጀመርበት ቀናት ቀደም ብለው ወደ ዩኒቨርሲቲው ይጓዛሉ። ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ ድምፅም ሆነ ምሥል የሚቀዳና የሚቀርፅ አሊያም ሌላ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው መግባት አይችሉም።
- በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞችም በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያድሩ ለማድረግ ታቅዷል።
ያንብቡ : telegra.ph/EAES-09-12

#UN #EU የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በአስቸኳይ ለማቆም እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ማሳወቁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። በተጨማሪ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው የሰላም ሂደት ፍቃደኛ መሆኑን አበረታተዋል። ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና…
#IGAD #ETHIOPIA
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለመመለስ ጠንካራ ፈቃደኝነት በማሳየታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።
የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ ቅሬታዎችን በውይይት እና ሁሉን አካታች በሆነ የፖለቲካ ሂደት ለመፍታት ያለውን ያልተቋረጠ ቁርጠኝነት በማንሳትም ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ወገኖች ይህን አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ተማጽነዋል።
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የትግራይ ክልል መንግስት ትላንት ያወጣውን መግለጫ፤ በኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም ሲቀርቡ ከነበሩት ተመሳሳይ ጥሪዎች ጋር የተስማማ መሆኑን በመግለፅ አበረታተዋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት ሰላም ያሳዩአቸውን ጥረቶች በትዕግስት እና በጠንካራ ቁርጠኝነት እንዲቀጥሉበት አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት እና በትግራይ ክልል ያሉ ባለስልጣናት ያልተፈቱ ጉዳዮችን ለመፍታት በግንኙነታቸው ላይ መተማመን እንዲገነቡ እንዲሁም ለሰላም ያሳዩአቸውን ጥረቶች በትዕግስት እና በጠንካራ ቁርጠኝነት እንዲቀጥሉበት ጥሪ አቅርበዋል።
ኢጋድ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለሚካሄደው የሰላም ሂደት ያለውን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጧል።

#ኬንያ
የተመራጩ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት እንግዶች ወደ ኬንያ በመግባት ላይ ናቸው።
እስካሁን ባለው ፦
- የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠ/ ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣
- የሩዋንዳ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፣
- የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣
- የሞዛምቢክ ፕሬዜዳንት ፊሊፕ ኒዩሲ ፣
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመትን ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች ገብተዋል።
በቀጣይ ሰዓታትም ተጨማሪ እንግዶች ኬንያ ይደርሳሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ከቀናት በፊት ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ለሩቶ በዓለ ሲመት የኢትዮጵያን መሪ ጨምሮ በአጠቃላይ ከ40 በላይ የሃገራት መንግሥታት እና የመንግሥታት ተጠሪዎችን መጋበዛቸው ይታወሳል።
Photo Credit : የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

#ኬንያ የተመራጩ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት እንግዶች ወደ ኬንያ በመግባት ላይ ናቸው። እስካሁን ባለው ፦ - የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠ/ ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ - የሩዋንዳ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፣ - የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣ - የሞዛምቢክ ፕሬዜዳንት ፊሊፕ ኒዩሲ ፣ - የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመትን ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች…
#ሩቶ 🤝 #ኡሁሩ
የኬንያ ተሰናባች ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ቀዳማዊት እመቤት ማርጋሬት ኬንያታ ዛሬ በስቴት ሀውስ ተመራጩን ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ እና በቀጣይ ቀዳማዊት እመቤት የሚሆኑትን ማማ ሬይቸል ሩቶን ተቀብለው አስተናግደዋል።
ኬንያታ እና ሩቶ መገናኘታቸው ለነገው በዓለ ሲመት ሲደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች ስለመጠናቀቃቸው ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል።
ነገ ስልጣናቸውን ለሩቶ የሚያስረክቡት ኬንያታ ከቀናት በፊት እንደተናገሩት ራይላ ኦዲንጋ ባለማሸነፋቸው አዝነዋል።
ኡሁሩ ፤ ኬንያን ለመምራት ትክክለኛ ሰው ናቸው ያሏቸው ኦዲንጋ በምርጫው ባለማሸነፋቸው ቢያዝኑም ህገመንግስታዊ ግዴታቸውም ጭምር በመሆኑ ስልጣናቸውን ፈገግ ብለው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል።
ራይላ ኦዲንጋ ከፕሬዜዳንታዊ ምርጫው ጋር በተያያዘ ወደ ፍርድ ቤት ማምራታቸው ፍርድ ቤቱም የሩቶን አሸናፊነት ማፅናቱ የሚታወስ ነው ፤ በዚህም ኬንያታ ህዝብ ለመረጣቸውና ፍርድ ቤት ላፀናላቸው ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ነገ ስልጣናቸውን ያስረክባሉ ፤ ሩቶም 5ኛው የኬንያ ፕሬዜዳንት በመሆን ቃለመሃላ ይፈፅማሉ።
በሌላ ዘግይተን ባገኘነው መረጃ ፤ ራይላ ኦዲንጋ በነገው በዓለ ሲመት ላይ እንደማይገኙ ገልፀዋል።
ኦዲንጋ ዛሬ ምሽት ከዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በበዓለ ሲመታቸው ላይ እንዲገኙ የስልክ ጥሪና ደብዳቤ እንደደረሳቸው ገልፀው ነገር ግን በስነስርዓቱ ላይ እንደማይገኙ አሳውቀዋል።
ከሀገር እንደወጡ እና ሌሎችም የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች እንዳላቸው በምክንያትነት አቅርበው ነው በነገው ስነሥርዓት ላይ እንደማይገኙ ያሳወቁት።
Photo Credit : State House Kenya