#GONDAR
በአጣጥ የኬላ ፍተሻ ላይ 308 ሽጉጥ ተያዘ።
በጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ከተማ 308 የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በኬላ ፍተሻ መያዙን የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አሳውቋል።
ፅህፈት ቤቱ ሽጉጡ የተያዘው በክፍለ ከተማው በድማዛ ቀበሌ አጣጥ በተባለው የኬላ ፍተሻ መሆኑን ገልጾ 2 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ማለቱን ከጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

#NobelPrint
ለአዲሱ አመት ልዩ ስጦታ ለመስጠት አስበዋል ?
እንግዲያውስ ማጂክ ኩባያ በፈለጉት ፎቶና ጽሑፍ ይዘዙን ! ፎቶው የሚታየው (የሚወጣው) ሙቅ ነገር ሲገባበት ነው። እንዲሁም ትራስ በፈለጉት ፍቶ ማዘዝ ይችላሉ
እንዳያመልጦ አሁኑኑ ይዘዙ ! ለማዘዝ - 0955937183 ወይም 0988302622 / መልዕክት ለመላክ 📨 | @brill3 |
ሌሎች ለየት ያሉ ነገሮችን ለማየት - @printmagic
አድራሻ ፦ ሜክሲኮ ኬኬር አጠገብ አይመን ሕንፃ ቁ-203

ለቲክቫህ ቤተሰቦች 10% ቅናሽ !
(Fancy Kids Fashion)
" የፋንሲ የልጆች ልብስ መሸጫ " በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎቹ ጥራት ያላቸውን የልጆች ልብሶች; መጫወቻዎች እና አክሠሠሪዎችን
አስመጥቶ ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጾልናል።
ከፊታችን ያለውን አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግም ጥራት ያላቸውን አልባሳትን ፣ ቦርሳዎችን፣ ጫማዎችን እና የተለያዩ የልጆች መገልገያዎችን አስገብቷል።
ድርጅቱ በአዲስ አበባ ውስጥ #በአምስት ቦታ ቅርንጫፍ እንዳለው የገለፀ ሲሆን በቅርቡ በሀያት አከባቢ አዲስ ቅርንጫፍ መክፈቱን አመልክቶናል።
በፋንሲ የልጆች ልብስ መሸጫ ከህጻናት ልብስ በተጨማሪም የአዋቂ ልብሶችን እና ጫማዎችን ያገኛሉ።
ፋንሲ ለቲክቫህ ቤተሰቦች በሁሉም ቅርንጫፉ በተለይ አዲስ በተከፈተው ሀያት ቅርንጫፍ ለሚመጡ ቤተሰቦች በዓሉን አስመልክቶ የ10 በመቶ ቅናሽ አድርጓል።
ቅናሹን ለማግኘት በሴንቸሪ ሞል 4ኛ ፎቅ የሱቅ ቁጥር 441፣ በለቡ መብራት ኃይል ፣ ብስራተ ገብርኤል ላፍቶ ሞል ጀርባ ፣ በጋራድ ሞል 2ኛ ፎቅ እንዲሁም በሀያት ከለሚ ኩራ ክፍለከተማ ከፍብሎ ባሉት ሱቆች መስተናገድ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
0911695856, 0913519693, 0911795568

" የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ማስከፈል ባስቸኳይ እንዲቆም አድርጉ " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
በአማራ ክልል ለ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህም በርካታ ወላጆች ቅሬታ እያቅረቡ ሲሆን ይኸውም ቅሬታ ከተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ጋር የተያያዘ መሆኑ ተጠቁሟል።
በዚህም በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው እየተመዘገቡ እንዳልሆነ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ዞን/ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች በላከው ደብዳቤ ገልጿል።
በመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ወጥ የሆነ ህጋዊ መመሪያ በቢሮው በኩል እስኪዘጋጅ ድረስም የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ማስከፈል ባስቸኳይ እንዲቆም እንዲደረገ አሳስቧል።
የወላጆች የትምህርት ቤት ድጋፍ በተመለከተ ከምዝገባ በኋላ ራሱን የቻለ የውይይት መድረክ እንደሚኖር ታሳቢ ተደርጎ እንዲፈፀምም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ይህንን የቢሮውን አቅጣጫ ተላልፈው በተማሪዎች እና ወላጆች ላይ ችግር እየፈጠሩ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላይ በየአካባቢው ያለው የፀጥታ አካል የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ የሚችል መሆኑን ቢሮው አሳስቧል።

#SUDAN
በትግራይ ክልል ጦርነት ሲቀሰቀስ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል።
እነዚህ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ #የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃ እንዳለው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለቢቢሲ በሰጠው ቃል አሳውቋል።
ተቋሙ ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ " ተአማኒ ሪፖርቶች " ደርሶኛል ብሏል ለቢቢሲ በሰጠው ቃል።
ተቋሙ ይህን ካወቀ በኃላ ምን አደረገ ?
የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን " ወታደራዊ ምልመላ መኖሩን እንደተገነዘብኩኝ ጉዳዩን ለሱዳን ማዕከላዊ መንግሥትና ለአካባቢ ባለሥልጣናት ስጋቴን ገልጫለሁ " ብሏል። ይህንም ተከትሎ ሁኔታዎች የተሻሻሉ ይመስሉ ነበር ሲል መልሷል።
ምልመላውን ማነው የሚያደርገው ?
ይኸው የተመድ ተቋም " ወታደራዊ ምልመላውን ለማካሄድ #ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎች እንደነበሩ እና ይህንንም ከስደተኞች መረዳቱን ይገልጻል። ነገር ግን የትኛው ወገን ምልመላውን እንዳካሄድ " ማረጋገጥ አልቻልኩም" ብሏል።
NB : ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ሰደተኛ ነን ብለው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ከህወሓት ጋር በመሆን ሲዋጉ እንደነበር መግለፁ ይታወሳል።
ያንብቡ : telegra.ph/BBC-09-07

#ትምራን
ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ነገ ሀሙስ " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ይካሂዳሉ።
በዚህም ወቅት ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞቶ የሚተላለፍበት እንዲሁም ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ የሚጠየቅበት መርሀግብር ይኖረናል ተብሏል።
የእግር ጉዞው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ላይ በካዛንቺ ሴቶች አደባባይ ጀምሮ መስቀል አደባባይ ላይ እንደሚያበቃ ተገልጿል።
አዘጋጆቹ በዚህ የእግር ጉዞ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ መሳተፍ እንደሚችሉ ገልፀው ግብዣ አድርገዋል።

የእርዳታ ምግብ ጉዳይ !
" ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የቀረበውን እርዳታ ለጦርነት እያዋለው ነው " - ኢትዮጵያ
" ከሰብዓዊ እርዳታ ስርቆት ጋር በተያያዘ ማንኛውም ክሶች እመረምራለሁ " - USAID
ዳግም ያገረሸው የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በቀጠለበት በአሁን ወቅት በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት " ህወሓት " ለትግራይ ህዝብ የገባውን ሰብዓዊ እርዳታ ለጦርነት እያዋለው መሆኑን በተደጋጋሚ አንፅንኦት ሰጥቶ እየገለፀ ነው።
ግጭቱ የተጀመረ ሰሞን ምንም እንኳን ህወሓት ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስጃለሁ የሚል ማስተባበያ ቢሰጥም 500 ሺህ ሊተር ነዳጅ ከመቐለ WFP መጋዘን መዘረፉን የዓለም አቀፍ ተቋማት መግለፃቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን መሰል ድርጊት እንደሚያወግዝና ነዳጁ እንዲመለስ ጠይቆ ነበር።
በአሁን ወቅት ደግሞ ውጊያ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ህወሓት ለህዝብ የቀረቡ ምግቦችን ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ይገልፃል። ለአብነት ኮርን ሶያ ብሌንድ (USAID ምልክት ያለበት) የተሰኘውን አጣዳፊ የምግብ እጥረትን ለማከም የሚውል አልሚ ምግብ በውጊያ ስፍራ መገኘቱን አሳውቋል።
በተጨማሪ መከላከያው በሚሰብራቸው ምሽጎችን ለእርዳታ የተላኩ የስንዴ ክምችቶች (USAID - የአሜሪካ ምልክት ያለባቸው) መገኘታቸውን ተገልጿል።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እስካሁን #በቀጥታ ምላሽ የሰጠ ዓለም አቀፍ ተቋም ባይኖርም ትላንት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ከእርዳታ ምግብ ጋር በተያያዘ በትዊተር ገፁ አንድ ፅሁፍ አውጥቷል።
በችግር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሲቪሎች ህይወታቸው ጥገኛ የሆነበትን ምግብ ከአፋቸው ተነጥቆ በታጠቁ አካላት ጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም በታጠቁ አካላት የሰብዓዊ እርዳታ መውሰድና ጥቅም ላይ የማዋል ድርጊትን አወግዛለሁ ብሏል።

#NEBE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፦
- በጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ወላይታ፣
- ጌዴኦ፣
- ደቡብ አሞ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ደግሞ ፦
- በአሌ፣
- ቡርጂ፣
- አማሮ፣
- ባስኬቶ እና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች በምርጫ አስፈጻሚነት የነበሩ በቀጣይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ለሚካሄደው #ሕዝበ_ውሣኔ በምርጫ አስፈጻሚነት በድጋሚ ለመሣተፍ ፍቃደኛ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡለት ጠይቋል።
ፍቃደኛነታቸውን ለመግለፅም ከላይ የተጻፈው መልዕክት (text message) በእጅ ስልካቸው ሲደርሳቸው አንድን ተጭነው እንዲመልሱ መልዕክት ተላልፏል።
መልዕክቱ ከታች ከተያያዘው ማስፈንጠሪያ (Link) ጋር ከደረሳቸው የሚጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ፍቃደኝነታቸውን ማሳየት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
https://nebecertificate.org.et/recruitment

#ብርሃን_ባንክ
ካሉበት ሆነው ገንዘብ ማስተላለፍ እና መሰል ጉዳይዎትን በምቾት ይከውኑ!
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc

#አዲስአበባ_እና_አካባቢዋ!
በአዲስ አበባና አካባቢዋ በ2014 ዓ.ም በተከሰቱ 511 ድንገተኛ አደጋዎች የ115 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ከ200 በላይ ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
👉 362 የእሳት አደጋ ፤ 149 የጎርፍ፣ የኮንስትራክሽን፣ የወንዝና የኩሬ አደጋዎች ደርሰዋል።
👉 የ115 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በ200 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።
👉 ከ115 ሰዎች መካከል 14ቱ በእሳት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ቀሪዎቹ 101 ሰዎች በተለያየ ድንገተኛ አደጋ ነው ሕይወታቸው ያለፈ ነው።
👉 577 ሚሊየን 780 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ፤ በአንጻሩ በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርብርብ 39 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ድኗል።
👉 የ137 አደጋዎች መንስኤ የታወቀ ሲሆን 63 በኤሌክትሪክ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች ናቸው። አብዛኛዎቹ አደጋዎች ያጋጠሙት በጥንቃቄ ጉድለት ነው።
#ማሳሰቢያ ፦
ሰሞኑን የበዓል ወቅት እንደመሆኑ ከፍተኛ የኃይል አጠቃቀም እንደሚኖር ስለሚኖር ህብረተሰቡ ከምግብ ማብሰል ጋር ተያይዘው ለሚሠሩ ሥራዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል አሳስቧል።

#GambellaRegion
በጋምቤላ ክልል የ2014 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 79 ነጥብ 5 በመቶ ያህሉ ወደቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን ተገልጿል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ፦
👉 አማካይ ውጤት ለወንዶች 48 በመቶ እና ለወንድ አካል ጉዳተኞች 46 በመቶ / ለሴቶች 44 በመቶ እና ለሴት አካል ጉዳተኞች 42 በመቶ እንዲሆን ተወስኗል።
👉 ለፈተናው ከተቀመጡ አጠቃላይ 16 ሺህ 629 ተማሪዎች 7,395 ወንዶችና 5,843 ሴት ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል አልፈዋል።
👉 በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተማሪዎች ካርድ ይሰጣል።

#NBE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ድንበር ውስጥ መያዝ የሚቻለውን የውጭ ምንዛሪ መጠን የሚደነግገውን መመርያ በማሻሻል በአገሪቱ ድንበር ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ምንም ዓይነት ግብይት እንዳይደረግ ክልከላ ማድረጉን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
በብሔራዊ ባንክ " ልዩ ፈቃድ " ካልሆነ በስተቀር የውጭ ምንዛሪ ይዞ መገኘት የተከለከለ ሲሆን፣ በስጦታና በረድዔት መልክ ለሦስተኛ ወገን በጥሬ ገንዘብ ማስተላለፍም ተከልክሏል፡፡
ከ6 ዓመታት በፊት በወጣው ነባሩ መመርያ ውስጥ እነዚህ ክልከላዎች አልነበሩም፡፡
በአዲሱ መመርያ " በልዩ ፈቃድ " የተባለው ምናልባት ለአስጎብኚ ድርጅቶች፣ ለሆቴሎችና ለቀረጥ ነፃ መደብሮች ይሆናል የሚል ግምት ቢኖርም በመመርያው ላይ ግን አልተገለጸም፡፡
በብሔራዊ ባንክ ገዥ በሆኑት ዶ/ር ይናገር ደሴ ተፈርሞ የወጣውና ከሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው አዲሱ መመርያ መሠረት ፦
👉 ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ ይዞ ከውጭ አገር የሚመጣ ሰው በብር መመንዘር እንዳለበት ተገልጾ፣ ይህም ከተፈቀደው መጠን በላይ ከሆነና የውጭ ዜጋ ከሆነ ገንዘቡ በከፈተው ሒሳብ (አካውንት) ውስጥ እንደሚቀመጥ ተገልጿል፡፡
👉 በአዲሱ መመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚመጡና ለአጭር ጊዜ ለሚቆዩ ዜጎች የሚፈቀደው የገንዘብ መጠን ግን ከፍ ተደርጓል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡና ለሚወጡ ሰዎች መያዝ የሚፈቀድላቸውን የገንዘብ መጠን የሚደነግገውን መመርያ ከ6 ዓመት በኋላ በማሻሻል፣ የገንዘቡን መጠን ከእጥፍ በላይ ከፍ አድርጓል፡፡
• ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ዜጎችም፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን 10 ሺሕ ዶላር ወይም በሌሎች የውጭ ምንዛሪዎች ተመጣጣኝ ይዘው ሲመጡ፣ በኢትዮጵያ ብር መንዝረው መጠቀም ይችላሉ፡፡ ከ10 ሺሕ ዶላር የበለጠ ይዘው ከመጡ ግን፣ ለጉምሩክ በማሳወቅ በግላቸው የውጭ ምንዛሪ አካውንት ውስጥ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ በነባሩ መመርያ ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ ዜጎች መያዝ ይፈቀድ የነበረው 4 ሺሕ ዶላር ብቻ ነበር፡፡
• ነዋሪነታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሆኑ ሰዎች ከውጭ ሲመጡ እስከ 4 ሺሕ ዶላር ወይም በሌሎች የውጭ ምንዛሪዎች ተመጣጣኙን ይዘው መምጣት የተፈቀደላቸው ሲሆን፣ ይህ በነባሩ መመርያ አንድ ሺሕ ዶላር ብቻ ነበር፡፡
👉 የኤምባሲ ሠራተኞች፣ ጊዜያዊ ሠራተኞች፣ እንዲሁም ለስብሰባና ለተለያዩ ጊዜያዊ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ዜጎች የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ከቻሉ ከአሥር ሺሕ ዶላር በላይ ይዘው እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡
👉 ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣም ሆነ ከኢትዮጵያ የሚወጣ ሰው ከ3 ሺሕ በላይ መያዝ አይፈቀድለትም፡፡ ይህም በነባሩ መመርያ 1 ሺሕ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ጂቡቲ የሚሄዱ ሰዎች በተለየ ሁኔታ እስከ 10 ሺሕ ብር መያዝ የሚችሉ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት 4 ሺሕ ብር ብቻ ነበር፡፡
👉 በአዲሱ መመርያ ሁሉም የውጭ ምንዛሪ ይዘው የሚመጡ ሰዎች በሕጋዊ የምንዛሪ ቢሮዎች ወደ ብር መቀየር ሲኖርባቸው፣ ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ከብር ውጪ ለመገበያያ ሌላ ገንዘብ መጠቀም ስለማይፈቀድ ነው። ምንዛሪ ማድረግ የሚችለውም ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መግባቱን የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ 30 ቀናት ውስጥ ነው፡፡
👉 በድንበር በኩል የሚገቡ ሰዎች 500 ዶላር ወይም በሌሎች ምንዛሪ ተመጣጣኙን ይዘው መግባት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በድንበር አካባቢ ለሚገኙ የኢትዮጵያ የጉምሩክ ጣቢያዎች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-09-07

Telegraph
Reporter
#NBE የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ድንበር ውስጥ መያዝ የሚቻለውን የውጭ ምንዛሪ መጠን የሚደነግገውን መመርያ በማሻሻል፣ በአገሪቱ ድንበር ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ምንም ዓይነት ግብይት እንዳይደረግ ክልከላ አደረገ፡፡ በብሔራዊ ባንክ ‹‹ልዩ ፈቃድ›› ካልሆነ በስተቀር የውጭ ምንዛሪ ይዞ መገኘት የተከለከለ ሲሆን፣ በስጦታና በረድዔት መልክ ለሦስተኛ ወገን በጥሬ ገንዘብ ማስተላለፍም ተከልክሏል፡፡ ከስድስት…