TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #US የማይክ ሐመር ስለ ኢትዮጵያ ቆይታቸው ምን አሉ ? አሜሪካ የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነቷን እና #የግዛት_አንድነቷን_በማክበር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ፍላጎት እንደሚያረጋገጡ የሀገራቸውን አቋም ገልፀዋል። በአሜሪካ ህዝብ ለጋስነት ሀገሪቱ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አመልክተዋል። ሰላምን በማረጋገጥ በኩል የጋራ ፍላጎቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት…
#USA
በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሏል።
ልዩ መልዕክተኛው ከነገ ጀምሮ ወደ እስከ መስከረም 5 /2015 ኢትዮጵያ እና ወደ ቀጠናው ሀገራት እንደሚጓዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።
በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ዳግም ያገረሸው ግጭት እንዲቆም እና የሰላም ንግግር እንዲጀመር ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።
አምባሳደር ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው የኢትዮጵያ መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናትን ያነጋግራሉ።
በተጨማሪ የተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎችን ከሚወክሉ የሲቪል ማህበራት እና የፖለቲካ ተዋናዮች ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ህዝብ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልፅግና ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማጎልበት እንደሚቻል ይወያያሉ።
አሜሪካ ለኢትዮጵያ #አንድነት፣ #ሉዓላዊነት እና #ለግዛት_አንድነት ቁርጠኛ ነኝ ስትል በድጋሚ አረጋግጣለች።
አምባሳደር ሐመር ከሳምንታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አዲስ አበባ እና መቐለ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ህወሓት አመራሮች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።
በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ከትግራይ ውጭ እየፈፀመ ያለውን ጥቃት ፤ የኢትዮጵያ መንግስትን የአየር ጥቃት እና የኤርትራን ዳግም ወደ ግጭት መግባቷን እንደምታወግዝ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን በኩል አሳውቃለች።
ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ የሚደረገውን ጥረት እንዲያጠናክሩ ጠይቃለች።
Via US Embassy AA
@tikvahethiopia

#ብርሃን_ባንክ
በእረፍት ጊዜዎ የብርሃን ባንክ ኤቲኤም ካርድዎን በመያዝ ግብይትዎን ያቅልሉ! ኑሮዎን ያዘምኑ !
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
Facebook: www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
YouTube: www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

#ATTENTION ወልድያ ! የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን አካባቢ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል። በዚህም ፦ • ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ #ተከልክሏል። • ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ…
#ATTENTION
ወልድያ !
በዛሬው ዕለት የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ ቤት ከዚህ ቀደም ካሳለፈው ውሳኔ ተጨማሪ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
የከተማውን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ ከተማ በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ መውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ክልከላዎችን ማስቀመጥ አስፈልጓል ተብሏል።
ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ፦
- ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም ተከልክሏል።
- ከተፈቀደላቸው የመንግስት የፀጥታ አባላት ውጭ የሰራዊቱን አልባሳትን መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።
- በከተማው የሚገኙ የራያና ቆቦ ከተማ ተፈናቃዮች ውጭ ሌላው አካል ወደ መጣበት አካባቢ እንዲመለስ በጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
- ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የከተማውን ማህበረሰብ የሚያውኩ አሉባልታዎችን በሚዲያዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ማዋከብ በጥብቅ ተክልሏል።
- በከተማ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ የንግድ ተቋማት እና የመሳሰሉትን መዝጋት ፍጹም ተከልክሏል።
- ከነሀሴ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀበሌ መታወቂያ መስጠት ተከልክሏል።
- አግባብነት የሌለው የዋጋ ንረት መፍጠር፣ በሸቀጦችና በግብርና ምርቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምሮ ህዝቡን ማስቃየት፣ በማንኛውም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ መገኘት በህግ ያስጠይቃል።
(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ የ2015 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስከረም 3 ቀን 2015 እንዲሁም የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ነገር ግን በከተማ ደረጃ ወጥ አድርጎ ማስጀምር በማስፈለጉ ፤ ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ለአጀማመሩ ሙሉ ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።
መስከረም 3 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች #ማጠናከሪያ_ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
በሁሉም የትምህርት ተቋማት መስከረም 9 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሃደት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

#ሶማሊያ
በጎረቤታችን ሶማሊያ " አልሸባብ " የሽብር ቡድን በፈፀመው ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎች ሲገደሉ 7 ተሽከርካሪዎች በቡድኑ ተቃጥለዋል።
የሶማሊያ ብሄራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ፤ ጨካኙ የሽብር ቡድን ትላንት ምሽት በሂራን ክልል 20 ሰዎችን ገድሎ ምግብና ሌሎች የንግድ ሸቀጦችን ጭነው ለማሃስ ወረዳ የአካባቢው ነዋሪዎች ይዘው ሲጓዙ የነበሩ 7 ተሽከርካሪዎችን አቃጥሏል ብሏል።
አንድ የአካባቢው ባለስልጣናት ደግሞ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ ጥቃቱ የተፈፀመው በክልሉ ዋና ከተማ በለድዋይ እና በማሃስ ወረዳ መካከል ባለው ጎዳና ላይ መሆኑን ገልፀው 22 ሰዎች መገደላቸውን አስረድተዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ምግብ ጭኖ ይጓዝ በነበረ ልዑክ ላይ መሆኑን አመልክተው ቡድኑ 17 ሰዎች እዛው ገድሎ ተጎጆዎቹን ሊረዱ በመጡ ሲቪሎች እና ቆፋሪዎች ላይ በተቀበረ ፈንጂ በማነጣጠር 5 ሰዎችን ገድሏል ብለዋል።
አልሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን በጥቃቱ 20 የአካባቢውን ታጣቂዎች መግደሉን ገልጿል።
የሶማሊያ መንግስት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን አጥብቆ አውግዞ " አረመኔ እና አሳፋሪ " ሲል ገልጿል።
መንግስት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጎን እንደሚቆም ገልጾ ለደረሰው " አሰቃቂ " ጥቃት ጠንከር ያለ ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል መግባቱን ቪኦኤ ዘግቧል።

Photo
#UPDATE
ሸዋሮቢት !
በሸዋሮቢት በተላለፈው የሰዓት ገደብ ክልከላዎች ላይ ማሻሸያ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ምሽት አሳውቋል።
በዚህም መሰረት ፦
- ለባጃጅና ለሞተር ሳይክል የተቀመጠው የስአት ገደብ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰአት የነበረው ወደ አንድ ሰአት ፤
- ለሰው እና ለመጠጥ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተቀመጠው የሰአት ገደብ ተሻሽሎ እስከ ምሽቱ አንድ ሰአት ተደርጓል።
በሌላ በኩል ፤ የከተማው አስተዳደር የከተማውን ከንቲባ የገደሉት ታጣቂዎች መሆናቸውን ገልጾ ታጣቂዎቹን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል። በዚህ ሂደት አንዳንድ ግለሰቦች ጉዳዩን ወደ ሌላ ነገር ለመቀየር ጥረት እያደረጉ ነው ብሏል።
አስተዳደሩ ፤ " ወደ ሌላ ነገር " ያለውን ጉዳይ በግልፅ ያላብራራ ቢሆንም የከተማው ነዋሪዎች ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲያዩት እና ህግን ለማስከበር በሚደረግ እንቅስቃሴ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

በአርጆ ዲዴሳ ምን ሆነ ?
የገንዘብ ሚኒስቴር ለግል ባለሀብቶች በጨረታ ለመሸጥ የፍላጎት መግለጫ ካወጣባቸው 8 የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ በሆነው አርጆ ዲዴሳ ባለፈው ማክሰኞ በታጣቂዎች ጥቃት ተፈፅሞበት ነበር።
ታጣቂዎቹ የፋብሪካውን ተሽከርካሪዎች እንዳቃጠሉና ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ ከአካባቢው መውጣታቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታውቋል፡፡
የግሩፑ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ክፍል ዋና ኃላፊ አቶ ረታ ዘለቀ ለሪፖርተር የተናገሩት ፦
" በተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰውን ትክክለኛ ጉዳት ለማጣራት ጥናት እየተደረገ ነው።
እስካሁን ፋብሪካው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የደረሰ መረጃ የለም።
አንድ ሠራተኛ ላይ ከደረሰ ድብደባ በስተቀር በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
በግቢው ውስጥ የሸንኮራ ማሳ ማሽነሪዎች፣ ትራክተሮችና የፋብሪካው ተሽከርካሪዎች አሉ በየትኞቹ ላይ ምን ያህል ጉዳት ደርሷል የሚለው እየተጣራ ነው።
በፋብሪካው ላይ የደረሰው ጥቃት በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ ካገረሸው ጦርነት ጋር የሚያያዝ ነው ፤ ታጣቂዎቹ በጦርነቱ ምክንያት አካባቢው ላይ የተፈጠረውን #ክፍተት ተጠቅመዋል፡፡
ኦነግ ሸኔ ተብሎ በዚያ ደረጃ የሚጠቀስ አይደለም ግርግር ተጠቅመው ታጣቂዎች ሊገቡ ይችላሉ ወለጋ አካባቢ ስለሆነ ግን እንደዚያ [ኦነግ ሸኔ] ተብሎ ነው የሚታወቀው።
በክረምት ወራት ላይ ሁሉም የስኳር ፋብሪካዎች የስኳር ምርት አቁመው ሙሉ ማሽነሪ ጥገና ላይ ነው የሚሰማሩት ጥቃቱ ሲደርስ የፋብሪካው ሠራተኞች በማሽነሪ ጥገና ላይ ነበሩ።
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ በፋብሪካው ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደቆዩ አልታወቀም። ነገር ግን የፋብሪካው ሠራተኞች ወደ ፋብሪካው ተመልሰው የጥገና ሥራውን እያከናወኑ ነው። "
Via ሪፖርተር ጋዜጣ

#ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናት አድራጊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ፖለቲከኞች በተገኙበት ለ2 ቀናት የቆየ ከፍተኛ የፖሊሲ ፎረም አካሂዷል።
በፎረሙም በ4 ዋና ጉዳዮች ላይ የትዘጋጁ ጥናቶች ለውይይት ቀርበዋል።
ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጂዲፒውን በ1% ሊቀንስ እንደሚችልና 71 ሚልዮን የሚጠጋው ህዝብ ደግሞ በዋጋ ግሽበት የተነሳ ከድህነት ወለል በታች ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል።
ሀገራችን ኢትዮጵያም 33% የዋጋ ግሽበት ያስተናገደች ሲሆን ከዚህም ውስጥ 13% ሚሆነው በጦርነቱ ምክንያት የመጣ መሆኑ በተደረጉ ጥናቶቾ ተመላክቷል።
በሀገሪቷም ተጨማሪ 3 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ከድህነት ወለል በታች ሊገቡ እንደሚችሉና ጂዲፒያችንም ወደ 7% ሊቀንስ ይችላል ነው የተባለው።
ከ40% በላይ ከሁለቱ ሀገራት ምርቶች የምታስገባው ኢትዮጵያ ነዳጅ፣ ማዳበሪያና ምግብ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሮባታል፤ የኮሮና ወረርሽኝ፣ በሀገሪቱ የተከፈተው ጦርነት ፣ የተለያዩ ብድሮች፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና ሌሎች ምክንያቶች ግሽበቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደቻለ ተገልጿል።
ለዚህ ሁሉ ችግር ምርታማነትን ማሳደግ፣ የነዳጅ አጠቃቀማችንን ማስተካከል ቢቻል መቆጠብ፣ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ማምረት፣ የአረንጓዴ ኋይልን ማጠናከር፣ ግጭትን ማስቆምና ሌሎችም እንደ መፍትሔ ተጠቁመዋል።
የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በመስራት ለውይይት የሚያቀርበው ማኅበሩ ባለፈው ዓመት 10 ጥናቶችን ያቀረበ ሲሆን ሌሎች የምርምር ስራዎችንም እንደሚያቀርብ አስታውቆ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በጋራ እየሰራ ያለ ገለልተኛ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

#MoE የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ሆኖ የመመራት መብት የሚሰጥበት የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሄዷል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት እስከ አምስት…
#GondarUniversity
አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል #በራሳቸው_ገቢ እንዲተዳደሩ ከተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን አሥራት አፀደወይን (ዶ/ር) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
ለዚህም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደተግባር ለመግባት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።
ፕሬዜዳንቱ ፤ ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን በሂደት እየቀነሰ የሁለተኛ እና የሦሥተኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የውጪ ሀገራት ተማሪዎችን ለመሳብ እየሰራ እንደሚገፅ የገለፁት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) በአሁኑ ወቅት 50 ዓለም አቀፍ ተማሪዎች እንዳሉት ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦሥተኛ ዲግሪ እንዲሁም በስፔሻሊቲ እና በሰብ ስፔሻሊቲ መርሃ ግብሮች ከ48 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።
Via @tikvahuniversity

#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ የእሁድ ገበያ እስከ አዲስ አመት ይዘልቃል።
የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪ እስከ አዲስ አመት ድረስ እንደሚዘልቁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባዋ መጪውን ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ለበአል ፍጆታ የሚሆኑ በርካታ ምርቶች ወደ ከተማዋ እየገባ ይገኛል ብለዋል።
ምርቶቹም በተለያዩ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች እንደሚገኙ ገልጸው፤ የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ እንደሚዘልቁ አመልክተዋል።
ህብረተሰቡ ያለ አግባብ ዋጋ ከሚጨምሩና የኢኮኖሚ አሻጥር ከሚፈጥሩ አካላት ራሱን በመጠበቅ በየአካባቢው በሚገኙ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ማህበራት ሱቆች እንዲገበያይ ጥሪ በማቅረብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Via ENA