TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ሰቆጣ መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል። #ኮምቦልቻ ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር። በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው…
#Update

#ወልድያ

ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችው ወልድያ ዛሬ ወደ ቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷ ተገልጿል። ከከተማዋ ወጥተው የነበሩም ተመልሰዋል። መደበኛ ትራንስፖርት ፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ጀምረዋል።

ዛሬ ጥዋት ላይ አቢሲንያ እና ህብረት ባንኮች ስራ መጀመራቸው እና ሌሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል ፤ በዚሁ መሰረት ከሰዓት በከተማው ውስጥ ያሉ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

#ደሴ

ደሴ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለች ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ በመራቅ ሰላሙን ሊያስጠብቅ ይገባዋል። በሀሰተኛ መረጃ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

#ኮምቦልቻ

ዛሬም እንደትላንቱ ኮምፖልቻ ከተማ እና ነዋሪዎቿ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሆኑ አሁንም ነዋሪው ተረብሾ አካባቢውን ለቆ ፣ ንብረቱን ጥሎ እንዲወጣ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና አሉባልታዎች ሊኖሩ ይችላሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

#ሐይቅ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨ የሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን የመመለስ ስራ በከተማው አስተዳደር እየተሰራ ነው። በተጨማሪ በከተማው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲሁም የኬላ ላይ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን መላው ነዋሪ የወጡትን ክልከላዎች እና ገደቦች እንዲያከብር ተጠይቋል።

#ሸዋሮቢት

በትላንትናው ዕለት " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች የተገደሉት የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን መፈፀሙን ከተማ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን #ለውጭ_ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ውጤታማነትና ቀልጣፋነት በመጨመር በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ረቂቅ ፖሊሲ በዛሬው ዕለት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።

@tikvahethiopia
#አጋምሳ

ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ፤ ሆሩ ጉዱሩ ወለጋ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ተገናግረዋል።

በአጋምሳ ከተማ በተፈፀመው ጥቃት በርከታ ሰዎች መገደላቸውን የሚገልፁት የአይን እማኞች ለተለያዩ ሚዲያዎች ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን በትንሹ ከ55 በላይ ንፁሃን ሰዎች እየደተገደሉ የአይን እማኞቹ ገልፀዋል።

ለእነዚህ የንፁሃን ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት ያደረሱት " የፋኖ ታጣቂዎች ናቸው " ሲሉ ቃላቸውን የሰጡት ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አንድ ቃላቸውን ለቢቢሲ የሰጡ ነዋሪው ፤ " በኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከምትባል ቦታ ፋኖ የሚባሉ ታጣቂዎች ወደ አጋምሳ ከተማ ገቡ። ሰው ገደሉ። ቤት አቃጠሉ። ንብረት ዘረፉ። . . . ሕዝቡም ተፈናቅሎ ወጣ።  እኔ ባለኝ መረጃ 87 የሚደርሱ ሰዎች የት እንደደደሱ አይታወቅም። 55 ሰዎች ቀብረናል። 55ቱም ሲቀበሩ ነበርኩ። " ብለዋል።

በወቅቱ ባንኮች መዘረፋቸውንም ያስረዳሉ።

በሌላ በኩል ፤ የእዛው የአካባቢው ነዋሪ መሆናቸውን የሚገልፁና ቃላቸው የሰጡ ባለፈው እሁድ ዕለት በአካባቢው የነበረው ልዩ ኃይል ሲወጣ " ሸኔ " ገብቶ እዛው ካሉ ነዋሪዎች መሳሪያ መሰብሰቡን ፣ ባንክ መዝረፉን፣ ንፀሃንን መግደሉን እና ማገቱን ይገልፃሉ።

ሰዎች ታገቱብን ያሉ ቤተሰቦች በመምጣት ከሸኔ ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው እንደነበር በዚህም የሰዎች ህይወት እንደጠፋ ፤ ከታገቱት ውስጥ ስምንት የሚደረሱ ሰዎች እንደተገደሉ ያስረዳሉ። " የፋኖ ታጣቂዎች " የሚባለውም ሀሰት ነው " ፋኖ " ኦሮሚያ ውስጥ ምን ይሰራል ? ሲሉም ይጠይቃሉ።

ከ" ሸኔ " ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ በከተማው ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች አይጎዱም ማለት አይደለም ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የሰዎች መገደል እና መታገት ነው ይህንን ሚዲያዎቹ አልተናገሩም ብለዋል።

የሚዲያዎች ዘገባ ገለልተኛ ያልሆነና አድሎ ያለበት ነው ሲሉም ይወቅሳሉ።

እስካሁን ድረስ የፌዴራል መንግስት ሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይፋዊ መረጃ አልሰጠም ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

በአጋምሳ ምንድነው የሆነው ? ያንብቡ 👇

https://telegra.ph/AGAMSA-09-03
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #US የማይክ ሐመር ስለ ኢትዮጵያ ቆይታቸው ምን አሉ ? አሜሪካ የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነቷን እና #የግዛት_አንድነቷን_በማክበር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ፍላጎት እንደሚያረጋገጡ የሀገራቸውን አቋም ገልፀዋል። በአሜሪካ ህዝብ ለጋስነት ሀገሪቱ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አመልክተዋል። ሰላምን በማረጋገጥ በኩል የጋራ ፍላጎቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት…
#USA

በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሏል።

ልዩ መልዕክተኛው ከነገ ጀምሮ ወደ እስከ መስከረም 5 /2015 ኢትዮጵያ እና ወደ ቀጠናው ሀገራት እንደሚጓዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ዳግም ያገረሸው ግጭት እንዲቆም እና የሰላም ንግግር እንዲጀመር ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።

አምባሳደር ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው የኢትዮጵያ መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናትን ያነጋግራሉ።

በተጨማሪ የተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎችን ከሚወክሉ የሲቪል ማህበራት እና የፖለቲካ ተዋናዮች ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ህዝብ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልፅግና ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማጎልበት እንደሚቻል ይወያያሉ።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #ለግዛት_አንድነት ቁርጠኛ ነኝ ስትል በድጋሚ አረጋግጣለች።

አምባሳደር ሐመር ከሳምንታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አዲስ አበባ እና መቐለ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እና ህወሓት አመራሮች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ከትግራይ ውጭ እየፈፀመ ያለውን ጥቃት ፤ የኢትዮጵያ መንግስትን የአየር ጥቃት እና የኤርትራን ዳግም ወደ ግጭት መግባቷን እንደምታወግዝ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን በኩል አሳውቃለች።

ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ የሚደረገውን ጥረት እንዲያጠናክሩ ጠይቃለች።

Via US Embassy AA

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

በእረፍት ጊዜዎ የብርሃን ባንክ ኤቲኤም ካርድዎን በመያዝ ግብይትዎን ያቅልሉ! ኑሮዎን ያዘምኑ !

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
Facebook: www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
YouTube: www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ወልድያ ! የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን አካባቢ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል። በዚህም ፦ • ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ #ተከልክሏል። • ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ…
#ATTENTION

ወልድያ !

በዛሬው ዕለት የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ ቤት ከዚህ ቀደም ካሳለፈው ውሳኔ ተጨማሪ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የከተማውን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ ከተማ በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ መውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ክልከላዎችን ማስቀመጥ አስፈልጓል ተብሏል።

ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ፦

- ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም ተከልክሏል።

- ከተፈቀደላቸው የመንግስት የፀጥታ አባላት ውጭ የሰራዊቱን አልባሳትን መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- በከተማው የሚገኙ የራያና ቆቦ ከተማ ተፈናቃዮች ውጭ ሌላው አካል ወደ መጣበት አካባቢ እንዲመለስ በጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የከተማውን ማህበረሰብ የሚያውኩ አሉባልታዎችን በሚዲያዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ማዋከብ በጥብቅ ተክልሏል።

- በከተማ  የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ የንግድ ተቋማት እና የመሳሰሉትን መዝጋት ፍጹም ተከልክሏል።

- ከነሀሴ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀበሌ መታወቂያ መስጠት ተከልክሏል።

- አግባብነት የሌለው የዋጋ ንረት መፍጠር፣ በሸቀጦችና በግብርና ምርቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምሮ ህዝቡን ማስቃየት፣ በማንኛውም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ መገኘት በህግ ያስጠይቃል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የ2015 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስከረም 3 ቀን 2015 እንዲሁም የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ነገር ግን በከተማ ደረጃ ወጥ አድርጎ ማስጀምር በማስፈለጉ ፤ ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ለአጀማመሩ ሙሉ ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

መስከረም 3 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች #ማጠናከሪያ_ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

በሁሉም የትምህርት ተቋማት መስከረም 9 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሃደት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ሶማሊያ

በጎረቤታችን ሶማሊያ " አልሸባብ " የሽብር ቡድን በፈፀመው ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎች ሲገደሉ 7 ተሽከርካሪዎች በቡድኑ ተቃጥለዋል።

የሶማሊያ ብሄራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ፤ ጨካኙ የሽብር ቡድን ትላንት ምሽት በሂራን ክልል 20 ሰዎችን ገድሎ ምግብና ሌሎች የንግድ ሸቀጦችን ጭነው ለማሃስ ወረዳ የአካባቢው ነዋሪዎች ይዘው ሲጓዙ የነበሩ 7 ተሽከርካሪዎችን አቃጥሏል ብሏል።

አንድ የአካባቢው ባለስልጣናት ደግሞ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል  ፤ ጥቃቱ የተፈፀመው በክልሉ ዋና ከተማ በለድዋይ እና በማሃስ ወረዳ መካከል ባለው ጎዳና ላይ መሆኑን ገልፀው 22 ሰዎች መገደላቸውን አስረድተዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ምግብ ጭኖ ይጓዝ በነበረ ልዑክ ላይ መሆኑን አመልክተው ቡድኑ 17 ሰዎች እዛው ገድሎ ተጎጆዎቹን ሊረዱ በመጡ ሲቪሎች እና ቆፋሪዎች ላይ በተቀበረ ፈንጂ በማነጣጠር 5 ሰዎችን ገድሏል ብለዋል።

አልሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን በጥቃቱ 20 የአካባቢውን ታጣቂዎች መግደሉን ገልጿል።

የሶማሊያ መንግስት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን አጥብቆ አውግዞ " አረመኔ እና አሳፋሪ " ሲል ገልጿል።

መንግስት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጎን እንደሚቆም ገልጾ ለደረሰው " አሰቃቂ " ጥቃት ጠንከር ያለ ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል መግባቱን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#UPDATE

ሸዋሮቢት !

በሸዋሮቢት በተላለፈው የሰዓት ገደብ ክልከላዎች ላይ ማሻሸያ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ፦

- ለባጃጅና ለሞተር ሳይክል የተቀመጠው የስአት ገደብ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰአት የነበረው ወደ አንድ ሰአት ፤

- ለሰው እና ለመጠጥ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተቀመጠው የሰአት ገደብ ተሻሽሎ እስከ ምሽቱ አንድ ሰአት ተደርጓል።

በሌላ በኩል ፤ የከተማው አስተዳደር የከተማውን ከንቲባ የገደሉት ታጣቂዎች መሆናቸውን ገልጾ ታጣቂዎቹን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል። በዚህ ሂደት አንዳንድ ግለሰቦች ጉዳዩን ወደ ሌላ ነገር ለመቀየር ጥረት እያደረጉ ነው ብሏል።

አስተዳደሩ ፤ " ወደ ሌላ ነገር " ያለውን ጉዳይ በግልፅ ያላብራራ ቢሆንም የከተማው ነዋሪዎች ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲያዩት እና ህግን ለማስከበር በሚደረግ እንቅስቃሴ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
በአርጆ ዲዴሳ ምን ሆነ ?

የገንዘብ ሚኒስቴር ለግል ባለሀብቶች በጨረታ ለመሸጥ የፍላጎት መግለጫ ካወጣባቸው 8 የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ በሆነው አርጆ ዲዴሳ ባለፈው ማክሰኞ በታጣቂዎች ጥቃት ተፈፅሞበት ነበር።

ታጣቂዎቹ የፋብሪካውን ተሽከርካሪዎች እንዳቃጠሉና ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ ከአካባቢው መውጣታቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታውቋል፡፡

የግሩፑ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ክፍል ዋና ኃላፊ አቶ ረታ ዘለቀ ለሪፖርተር የተናገሩት ፦

" በተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰውን ትክክለኛ ጉዳት ለማጣራት ጥናት እየተደረገ ነው።

እስካሁን ፋብሪካው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የደረሰ መረጃ የለም።

አንድ ሠራተኛ ላይ ከደረሰ ድብደባ በስተቀር በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

በግቢው ውስጥ የሸንኮራ ማሳ ማሽነሪዎች፣ ትራክተሮችና የፋብሪካው ተሽከርካሪዎች አሉ በየትኞቹ ላይ ምን ያህል ጉዳት ደርሷል የሚለው እየተጣራ ነው።

በፋብሪካው ላይ የደረሰው ጥቃት በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ ካገረሸው ጦርነት ጋር የሚያያዝ ነው ፤ ታጣቂዎቹ በጦርነቱ ምክንያት አካባቢው ላይ የተፈጠረውን #ክፍተት ተጠቅመዋል፡፡

ኦነግ ሸኔ ተብሎ በዚያ ደረጃ የሚጠቀስ አይደለም ግርግር ተጠቅመው ታጣቂዎች ሊገቡ ይችላሉ ወለጋ አካባቢ ስለሆነ ግን እንደዚያ [ኦነግ ሸኔ] ተብሎ ነው የሚታወቀው።

በክረምት ወራት ላይ ሁሉም የስኳር ፋብሪካዎች የስኳር ምርት አቁመው ሙሉ ማሽነሪ ጥገና ላይ ነው የሚሰማሩት ጥቃቱ ሲደርስ የፋብሪካው ሠራተኞች በማሽነሪ ጥገና ላይ ነበሩ።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ በፋብሪካው ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደቆዩ አልታወቀም። ነገር ግን የፋብሪካው ሠራተኞች ወደ ፋብሪካው ተመልሰው የጥገና ሥራውን እያከናወኑ ነው። "

Via ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናት አድራጊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ፖለቲከኞች በተገኙበት ለ2 ቀናት የቆየ ከፍተኛ የፖሊሲ ፎረም አካሂዷል።

በፎረሙም በ4 ዋና ጉዳዮች ላይ የትዘጋጁ ጥናቶች ለውይይት ቀርበዋል።

ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጂዲፒውን በ1% ሊቀንስ እንደሚችልና 71 ሚልዮን የሚጠጋው ህዝብ ደግሞ በዋጋ ግሽበት የተነሳ ከድህነት ወለል በታች ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያም 33% የዋጋ ግሽበት ያስተናገደች ሲሆን ከዚህም ውስጥ 13% ሚሆነው በጦርነቱ ምክንያት የመጣ መሆኑ በተደረጉ ጥናቶቾ ተመላክቷል።

በሀገሪቷም ተጨማሪ 3 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ከድህነት ወለል በታች ሊገቡ እንደሚችሉና ጂዲፒያችንም ወደ 7% ሊቀንስ ይችላል ነው የተባለው።

ከ40% በላይ ከሁለቱ ሀገራት ምርቶች የምታስገባው ኢትዮጵያ ነዳጅ፣ ማዳበሪያና ምግብ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሮባታል፤ የኮሮና ወረርሽኝ፣ በሀገሪቱ የተከፈተው ጦርነት ፣ የተለያዩ ብድሮች፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና ሌሎች ምክንያቶች ግሽበቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደቻለ ተገልጿል።

ለዚህ ሁሉ ችግር ምርታማነትን ማሳደግ፣ የነዳጅ አጠቃቀማችንን ማስተካከል ቢቻል መቆጠብ፣ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ማምረት፣ የአረንጓዴ ኋይልን ማጠናከር፣ ግጭትን ማስቆምና ሌሎችም እንደ መፍትሔ ተጠቁመዋል።

የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በመስራት ለውይይት የሚያቀርበው ማኅበሩ ባለፈው ዓመት 10 ጥናቶችን ያቀረበ ሲሆን ሌሎች የምርምር ስራዎችንም እንደሚያቀርብ አስታውቆ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በጋራ እየሰራ ያለ ገለልተኛ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia