TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somalia

" ... የሶማሊያ ህዝብ ማብቂያ በሌለው የሀዘን መግለጫ እና ሀዘን መሰላቸቱን አውቃለሁ " - ሀሰን ሼክ ሞሐመድ

የጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ " አልሸባብ " ን ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ ጦርነት ለመክፈት ቃል ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጡት መግለጫ የሶማሊያ ህዝብ የሰላም ጠላት በሆኑት ጨካኞች ላይ ለሚካሄድ አጠቃላይ ጦርነት ይዘጋጅ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" የሶማሊያ ህዝብ ማብቂያ በሌለው የሀዘን መግለጫና ሀዘን መሰላቸቱን አውቃለሁ " ያሉት ፕሬዝዳንቱ አሸባሪው ቡድን በሚፈጽመው በእያንዳንዱ ግድያ እጅግ የተከበሩ ሰዎች እየሞቱ ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ከባድ ነው የተባለው የአልሸባብ ጥቃት ባለፈው አርብ ሞቃዲሾ በሚገኘው በ " ሃያት ሆቴል " ውስጥ ተፈፅሟል። በዚሁ ጥቃትም 21 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 117 ቆስለዋል።

የሶማሊያ ጠ/ሚ ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተገኙበትን የብሔራዊ የፀጥታ ኮሚቴ ስብሰባ ያካሄዱት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ " ህዝባችንን የሚያጠፉት አሸባሪዎች የሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ነጻ እስኪወጡ ድረስ ቡድኑን ለማዳከም ቆርጠን ተነስተናል " ብለዋል።

ይህንንም ፤ መንግሥታት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልፀው የእቅዱ ዝግጅትና አተገባበሩ እየተካሄደ መሆኑን ማስታወቃቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተመድ #አፍሪካ_ህብረት አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ፤ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን በመስማታቸው ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ፤ ዛሬ ከሚካሄድ የፀጥታው ም/ ቤት ስብሰባ አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ በጣም ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን የገለፁት…
#USA

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት አሜሪካን ስጋት እንዳጫረባት ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እና በመጨረሻም ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ብሊንከን ፤ ላለፉት 5 ወራት የነበረው የተኩስ አቁም የበርካቶችን ሕይወት መታደጉንና እርዳታ እንዲደርስ ማስቻሉንም ገልፀዋል።

በቅርብ ጊዜ የተቀሰቀው ጦርነት፣ ትንኮሳ የተሞላባቸው ትርክቶችና እና ዘላቂ የተኩስ አቁም እጦት እየታየ የነበረውን መሻሻል አደጋ ውስጥ መክተቱን ጠቁመዋል።

በተጨማሪ ለጋራ ደኅንነት እና ለመላው ኢትዮጵያውያን ብልጽግናና እድገት ለማምጣት ሁሉንም ያሳተፈ የፖለቲካ ሂደት እንዲፈጠር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያዘገየው ገልፀዋል።

እንደገና ወደ ጦርነት መግባት የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት ለማደፍረስ በሚጥሩት ላይ ሚና እንደሚጫወት፣ የሰዎችን መጠነ ሰፊ  ስቃይ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣና ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያስከትላል ብለዋል።

ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግሥት ተደራዳሪ ቡድን ማቋቋሙንና ለሰላም ውይይት ያለውን ፍላጎት መግለጹን መገንዘባቸውን ጠቁመዋል።

በዚህ ወቅት ሁሉም ወገኖች የሰብአዊ እርዳታ ምግብ እና የነዳጅ አቅርቦትን እንዲያስቀጥሉ፣ ከወታደራዊ ኃይል እንዲታቀቡና መሠረታዊ አገልግሎቶች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ጠይቀዋል።

" አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ እና ለአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ቁርጠኛ አቋም አላት። አገሪቷ ያጋጠሟትን ሁለንተናዊ ተግዳሮቶች ታሪካዊ ድርቅን ማሸነፍና ክልላዊ ደኅንነትን ማስፈንን ጨምሮ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ ነን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት አሜሪካን ስጋት እንዳጫረባት ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እና በመጨረሻም ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብሊንከን ፤ ላለፉት 5 ወራት የነበረው የተኩስ አቁም የበርካቶችን ሕይወት መታደጉንና…
#EU

" ወቅቱ ለሰላም ውይይት የሚደረግበት ጊዜ ነው " - የአውሮፓ ኅብረት

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና የአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦሬል በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ማግርሸቱን የሚገልፁ ሪፖርቶች የሰላም ተስፋ ላይ ጥላ ያጠላል ብለዋል።

ሁሉም ወገኖች ሁኔታው ይበልጥ ከመባባሱ በፊት እና ወደ ለየለት ጦርነት ሳይገባ ግጭቱን እንዲያረግቡ ጠይቀዋል።

" ወቅቱ ለሰላም ውይይት የሚደረግበት ጊዜ ነው "  ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ተመድ በመቐለ ነዳጅ መዘረፉን ገለፀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ ዛሬ ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ጥዋት በትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ ከተማ የሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) መጋዘን መዘረፉን ገልፀዋል። ዱጃሪች ፤ " ዛሬ ጥዋት የትግራይ ኃይሎች መቐለ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል በመግባት 12 ቦቴ…
#USA

አሜሪካ በመቐለ የህወሓት ኃይሎች 12 የነዳጅ ቦቴዎች " መውሰዳቸው " እንደሚያሳስባት ገለፀች።

ሀገሪቱ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ ፤ " ነዳጁ አስፈላጊ የነፍስ አድን ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የሚውል ነው ፤ ለኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ የሚያደርጉ ማንኛውም አይነት ድርጊት እናወግዛለን " ብላለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA አሜሪካ በመቐለ የህወሓት ኃይሎች 12 የነዳጅ ቦቴዎች " መውሰዳቸው " እንደሚያሳስባት ገለፀች። ሀገሪቱ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ ፤ " ነዳጁ አስፈላጊ የነፍስ አድን ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የሚውል ነው ፤ ለኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ የሚያደርጉ ማንኛውም አይነት ድርጊት እናወግዛለን " ብላለች። @tikvahethiopia
" አሁኑኑ የተሰረቀውን ነዳጅ መልሱ " - WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ ድርጅታቸው ለእርዳታ ሥራው የሚያውለውን 570,000 ሊትር ነዳጅ " የትግራይ ባለሥልጣናት ሰርቀዋል " ብለዋል።

" ምግብ ለማድረስ ነዳጅ ከሌለን በሚሊዮኖች ይራባሉ " ያሉት ቢዝሊ ድርጊቱን " የሚያስቆጣ እና አሳፋሪ " ብለውታል።

አሁኑን የተሰረቀው ነዳጅ እንዲመለስ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GurageZone በደቡብ ክልል ያሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው በሁለት አዲስ ክልሎች ለመደራጀት በየም/ቤቶቻቸው ወስነው ውሳኔውን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ካቀረቡ ቀናት ተቆጥሯል። በጋራ በአዲስ ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ውሳኔ አሳልፈው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄውን ካቀረቡት መካከል ግን የጉራጌ ዞን እንደሌለበት ይታወቃል። ዞኑ ከአጎራባቾቹ ስልጤ ፣ ከምባታ ጠምባሮ ፣…
#Wolkite : የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልቂጤ ከተማ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ የስራ ማቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ ተመቶ መዋሉን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የንግድ እንቅስቃሴ እና ትራንስፖርትም ተቋርጦ ነው የዋለው።

ዓድማው ከጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነበር።

ምንም እንኳን በዞኑ ውስጥ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መሰል የድማ እንቅስቃሴ እንዳይካሄድ ቢያሳውቅም ዛሬ ከተማይቱ በእንቅስቃሴ ውጭ ሆና መዋሏ ተገልጿል።

አሁን ከክልልነት ጥያቄ ጋር ያለው ጥያቄ የቀጠለ ሲሆን በዚህ ሳቢያ ከሰሞኑን ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን አረጋግጦ የሚታሰሩት ህዝብ ከህዝብ ለማጋጨት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት (በዞን ደረጃ በኃላፊነት ደረጃም ጭምር ያሉ) ናቸው ሲል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር ለሚኖሩት፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ላከበሩት ታላቁ ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና  ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን በስፖርቱ ዓለም በማስጠራት ጀምራ ለኅብረሰተብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት ለምትተጋው ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬቱን የሚያበረክተው ነሐሴ 21 ቀን 2014 በሚያካሂደው የተማሪዎች ምረቃ ላይ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት አሜሪካን ስጋት እንዳጫረባት ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እና በመጨረሻም ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብሊንከን ፤ ላለፉት 5 ወራት የነበረው የተኩስ አቁም የበርካቶችን ሕይወት መታደጉንና…
#Turkiye #UK

ተርኪዬ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ማርች 24 /2022 በፌዴራል መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ከታወጀ በኃላ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶችን በሀዘን እና ስጋት ውስጥ ሆና እየተከታተለች እንደምትገኝ ገልፃለች።

ሁሉም ወገኖች ግጭት በዘላቂነት እንዲቆም ለማድረግ እና በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ወደ ንግግር እንዲመለሱ ጋብዛለች።

ለዚህ አላማ ደግሞ ሁሉንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጣለች።

ተርኪዬ በኢትዮጵያ ሰላምን እና መረጋጋትን ለማስፈን ባሚደረገውን ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፃለች።

በሌላ በኩል ፤ ዩናይትድ ኪንግደም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶች እንደሚያሳስባት ገልፃለች።

ይህ ሁኔታ ቀድሞም አስከፊ የነበረውን የሰብዓዊ ሁኔታ ይበልጥ ያባብሰዋል ብላለች።

ዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ግጭት እንዲያቆሙና የፖለቲካ መፍትሄ እንዲመጣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ አሳስባለች።

@tikvahethiopia
#ECSOC

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ ቤት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ዳግም የተቀሰቀሰው ትጥቅን ያካተተ ግጭትን እንዲረጋጋ እና የተጀመረው የሰላም ሂደት በአስቸኳይ እንዲቀጥል አበክሮ ጠይቋል።

ም/ቤቱ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል መልሶ ያገረሸው የትጥቅ ግጭት በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿጻ።

ከዚህ በፊት የተፈጠረው የትጥቅ ግጭት ተነግሮ የማያልቅ የሰው ልጅ ስቃይ እና ከፍተኛ መሰረተ ልማቶች መውደም ምክንያት መሆኑን ይታወቃል ያለው ም/ቤቱ አሁን ዳግም የተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት እንዲረጋጋና ግጭቱ እንዳይባባስ አፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ አሳስቧል።

በተጨማሪም ም/ቤቱ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁሙ መከበር ለሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት ቀጣይነት እና ለሰላም ሂደቱ ስኬታማነት ወሳኝ እንደሆነ ገልጾ አለመግባባቶች በፖለቲካዊ ውይይት መፈታት እንዳለባቸው በጥብቅ እንደሚያምን ገልጿል።

ለዚህም የሰላም ማስፈን ሂደቱ በአስቸኳይ እንዲቀጥልና ሀገሪቱንና ዜጎቿን ከተጨማሪ ጥፋት ለመታደግ የሰላም ሂደቱ በቅን ልቦና እንዲካሄድ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግንዛቤ በማስገባት የአፍሪካ ህብረት (AU) የፌደራል መንግስትን እና ህወሃትን የማደራደር ሚናውን በእጥፍ በማሳደግ ሰላማዊ እልባት ላይ እንዲደረስ የበኩሉን እንዲወጣ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

የሰላም ማስፈን ሂደቱን አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ በማንኛውም መንገድ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት እና ዝግጁነትም በድጋሚ አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
#CARD

የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንደ አዲስ ማገርሸቱ ለጥቂት ወራት ታይቶ የነበረውን የሰላም ጭላንጭል ተስፋ እንዳደበዘዘው ገልጿል።

ካርድ ፤ የግጭቱን እና የጦርነት ፕሮፖጋንዳውን ማባባስ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጾ ሁሉም ወገኖች ጦርነቱንና ግጭቱን ከሚያባብሱ ትርክቶና ድርጊቶች እንዲታቀበ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም የዓለም ዐቀፍ ሰብዓዊነት ህግጋት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia