TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሀያት ሆቴል ኦፕሬሽን !

በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በሚገኘው " ሀያት ሆቴል " ባለፈው ዓርብ " አልሸባብ " ጥቃት ፈፅሞ ፤ ህይወት አጥፍቶ ፣ ንብረት አውድሞ በሆቴል ውስጥ የነበሩ ሰዎች አግቶ ለሰዓታት ቆይቷል።

በኃላም የሶማሊያ ጦር በካሄደው ኦፕሬሽን ሆቴሉን ከአልሸባብ ታጣቂዎች ነፃ ማድረግ ችሏል።

በሆቴል ሀያት ምን ተፈጠረ ?

የአልሸባብ ታጣቂዎች " ሀያት ሆቴል " ውጭ ላይ ሁለት ፈንጂ ያፈነዱና ወደ ሆቴሉ ሕንጻ በመግባት ተኩስ ይከፍታሉ።

በዚህ ጥቃት ብቻ በሰዓቱ 12 ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ ተገነግሯል (ቁጥሩ ከፍ ሊል ይችላል)።

የ "አልሸባብ" ታጣቂዎች የሽብር ድርጊት በዚህ አላበቃም ወደ ሆቴሉ ከገቡ ከሰዓታት በኋላ በሕንጻው የመጨረሻ ፎቅ ላይ መሽገው ይቆያሉ፤ ሆቴሉንም ይቆጣጠራሉ።

ይህ ሁሉ በሚሆን ሰዓት በሆቴሉ ውስጥ ታግተው የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ነበሩ።

የሶማሊያ ጦር 30 ሰዓታት ከወሰደ ኦፕሬሽን በኃላ ታጣቂዎቹን በመግደል ሆቴሉን ነፃ ማድረግ እንደቻለ ተነግሯል።

ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች አግተው የነበሩት የአልሸባብ ታጣቂዎች መተለላፊያ ደረጃዎችን በቦምብ በማፍረሳቸው የጸጥታ ሃይሎች ለሰዓታት ያህል እንግዶች ያሉበት ስፍራ ለመድረስ ሲቸገሩ ነበር።

የሶማሊያ ጦር ታጣቂዎቹ ሆቴሉን ከያዙበት ሰዓት አንስቶ ባካሄደው ኦፕሬሽን በርካታ የሆቴሉ እንግዶች እና ሠራተኞችን ከታጣቂዎቹ ማትረፍ ችሏል።

ከሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን በተገኘ መረጃ 106 ሰዎችን ከሽብር ጥቃቱ ማትረፍ ተችሏል።

ዓርብ አንስቶ ነበረ ጥቃት ትክክለኛ ቁጥራቸው እስካሁን ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል።

የሶማሊያ መንግስት በሽብር ጥቃቱ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት ያሳውቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

#SNTV #BBC
Video Credit : SM

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sport ተጋጣሚውን 9 ለ 0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ክለብ ! ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው በ #CECAFA ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የኢትዮጵያው ንግድ ባንክ ቡድን ተጋጣሚውን ዋሪየርስ ኩዊን በሰፊ የግብ ልዩነት 9 ለ 0 አሸንፏል። መዲና አዎል 4 ግቦችን እንዲሁም ሎዛ አበራ 5 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል ። More : @tikvahethsport
#TikvahSport | በተጋጣሚዎቻቸው ላይ የጎል ናዳ ያወረዱት 2ቱ ኢትዮጵያውያን !

በታንዛንያ ሀገር ፤ ዳሬሰላም ከተማ የ #CECAFA የሴቶች ሻሚዮንስ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ በመሳተፍ ላይ ሲሆን የዚሁ ክለብ ተጫዋቾች የሆኑት ሎዛ አበራ እና መዲና አዎል በታጋጣሚ ቡድኖች ላይ የጎል ናዳ አውርደውባቸዋል።

እስከሁን ባለው ከ3 ክለቦች ጋር በተደረገ ጨዋታ ሎዛ አበራ 9 ጎሎችን እንዲሁም መዲና አዎል 6 ጎሎችን አስቆጥረዋል።

የጎል ናዳው የወረደው በየትኞቹ ክለቦች ላይ ነው ?

👉 ዋሪየርስ ኩዊን በተባለው የእግር ኳስ ክለብ ላይ ሎዛ ብቻዋን 5 ጎል ፤ መዲና 4 ጎል አስቆጥረውባቸዋል።

👉 ፎፊላ በተባለው የእግር ኳስ ክለብ ላይ ደግሞ ሎዛ 3 ጎሎችን መዲና 1 ጎል አስቆጥረዋል።

👉 ኤፒ አር ኪጋሊ በሚባለው ክለብ ላይ ሎዛም መዲናም አንድ አንድ ጎል አስቆጥረዋል (ይሄ ጨዋታ ዛሬ የተካሄደ ነው)

በድምሩ ሁለቱ ተጫዋቾች ብቻ በውድድሩ 15 ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ቲክቫህ ስፖርት👇
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

በ2015 የትምህርት ዘመን ከሚጀምረው የመውጫ ፈተና (ለመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ብቻ) ጋር በተያያዘ ከፈተናው በፊት ሊቀድሙ የሚባቸው ነገሮች አሉ በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ።

የግብዓት አቅርቦት ችግር ባለበት ሁኔታ ፣ የትምህርት ተቋማት አቅም በሚፈለገው ደረጃ ባልሆነበት ፣ የመምህራን ብቃት በራሱ ሳይመዘን / መምህራን ሳይመዘኑ ተማሪዎችን መመዘን እንዴት ይሆናል ፤ እንዴትስ ውጤት ያስገኛል በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ላይ ምላሽ አለኝ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) ከተናገሩት ፦

" አቻ ምሳሌ ላይሆን ይችላል ግን አንድ ምሳሌ ላንሳ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አሉ ከሺህ በላይ የሚሆኑ በሁሉም ት/ቤቶች ያለው አቅም ፣ የመምህራን፣ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰረተ ልማት አቅም እና መምህራኑ የተመዘኑ / ምዘናውን ያለፉ መሆን አለመሆናቸው ያለው ምጣኔ በጣም የተለያየ ነው። እንደዛም ሆኖ ግን አንድ ወጥ የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ያስፈልገናል እንደ ሀገር።

የ2ኛ ደረጃ ፈተና የምንሰጠው አንድ ሰው በሁለተኛ ደረጃ የሚሰጠውን ትምህርት በእርግጥ አጠናቋል ለሁለተኛ ደረጃ አጠናቃቂ ነው ተብሎ በቅቷል ወይ ለማለትና ለመለካት ነው።

ይሄ ፈተና ስታንዳርድ ፈተና ነው። በየሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አቅም አይደለም የሚዘጋጀው ፣ በሁለተኛ ደረጃ ያሉ መምህራንን አቅም ብቻ አይደለም ታሳቢ የሚያደርገው፤ እንደ ሀገር ሁለተኛን ደረጀን የጨረሰ ሰው ምን አይነት እውቀት እና ስብዕና ሊኖረው ይገባል የሚለውን የሚፈትሽ ነው።

መምህራኑ ሁሉም ተፈትነው ብቁ ሆነው እስኪያልፉ ፣ ያለን መሰረተ ልማት በትምህርት ቤቶች ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ያለን አቅም ተመጣጣኝ እስክናደርግ ድረስ አንድን ሪፎርም አንጀምርም ካልን ዝንተዓለም ያንን ሪፎርም አናደርግም።

ሪፎርሙ መጀመር አለበት የሆነ ጊዜ ላይ መጀመር አለበት የተባሉ ጉድለቶች እንዳሉ አውቃለሁ፤ እንደ ትምህርት ሴክተርም እንደትምህርት ሚኒስቴርም እንገነዘበዋለን።

የመምህራኖቻችንን ብቃት ለማሳደግ በየአመቱ ከልማት አጋሮችም ፣ ከመንግስትም ግምጃ በሚሊዮኖች እያፈሰስን መምህራን በ2ኛ ፣ 3ኛ ዲግሪ እናስተምራለን።

እንደሚታወቀው መንግስት ለትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት በሀገራችን 4ኛው ትልቁ በጀት የሚመደብለት ሴክተር ነው ሰፊውን የሚወስደው የከፍተኛ ትምህርት ነው የውስጥ መሰረተ ልማታቸውን፣ አደረጃጀታቸውን ለማሳደግ የሚውል ሀብት አለ እነዚህ ቁርጠኝነቶች በመንግስት በኩል የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሚውል ነው።

መምህራኖቻችን በቀጣይነት እያበቃን መሄድ አለብን እርግጥ ነው እንደዛም ሆኖ ግን ይሄ ስራ መጀመር አለበት ፤ አሁን ካልጀመርነው ከበቂ በላይ ጉዳት ደርሷል የትምህርት ጥራቱ ላይ።

በፈተና ብቻ አይደለም ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ በትኩረት በመለየት ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ፣ የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና በጥራት በመስጠት ፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን አነስተኛውን መስፈርት በፖሊሲው መሰረት 50 ፐርሰንት በማድረግ እነኚህ ሪፎርሞች መምህራን ልማት ላይ የምንሰራውን ፤ የዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያን ገድበን የወሰድናቸውን ሪፎርሞች ድምር ውጤት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው ፤ ይሄንን ማድረግ ተገቢ ነው ጊዜው አሁን ነው ብለን ነው የገባንበት። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
እንኳን አደረሳችሁ !

ለኦርቶዶክስ እና ለካቶሊክ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለቅድስት ድንግል ማርያም ትንሳኤ እና ዕርገት / ጾመ ፍልሰታ ፍቺ አደረሳችሁ።

@tikvahethiopia
#በወንጀል_ይፈለጋሉ #Wanted

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በፎቶ የሚታዩትን ተጠርጣሪዎች በወንጀል እየፈለጋቸው ይገኛል።

የተጠርጣሪዎቹን አድራሻቸውን የሚያውቅ አልያም በአጋጣሚ የተመለከተ ማንኛውም ገለሰብ በስልክ ቁጥር ፦

👉 0115309139 ዘውትር (በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30)

👉 በ0111119475 / 0111711012 በማንኛውም ሰዓት ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።

ነፃ የስልክ መስመር 861 መጠቀምም ይቻላል።

ግለሰቦቹ በሞጆ፣ አንድ ወርቅ ቤት በመግባት ሲዘርፉ የሚታይ ሲሆን ከመካከላቸው የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሰ ይገኝበታል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወደ ወርቅ ቤቱ በመግባት በሰዓቱ ስራ ላይ የነበረችውን ግለሰብ በማዘናጋት ብዛት ያለው ለሽያጭ የቀረበ ንብረት ዘርፈው ሲወጡ በቤቱ የደህንነት ካሜራ አይን ውስጥ ገብተዋል።

@tikvahethiopia
#Gambella

በጎርፍ አደጋ ወገኖቻችን ተፈናቀሉ።

በጋምቤላ ክልል በ4 ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከአራት ሺህ በላይ አባዎራና እማዎራ ወገኖቻችን ከመኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዋል።

ከክልሉ አደጋ ስጋት አመራር በተገኘው መረጃ በሃገራችን ደጋማዉ አካባቢ በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በላሬ፣ በመኮይ በዋንቱዋና በኢታንግ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷታ።

የጎርፍ መጥለቅለቅ ከደረሰባቸዉ 4 ወረዳዎች ዉስጥ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ አባዎራና እማዎራ ከመኖሪያ ቀያቸዉ የተፈናቀሉ ሲሆን ለጊዜዉ ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል።

የደረሰው ጉዳት ዝርዝር ፦
- በኢታንግ ልዩ ወረዳ 2040 አባወራና እማወራ፣
- በላሬ ወረዳ 1000፣
- በዋንቱዋ ወረዳ 619፣
- በመኮይ 480 አባወራና እማወራ የተፈቀሉ ሲሆን በጂካዎ ወረዳም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የጎርፍ አደጋዉ በቤት ዉስጥ ያሉ ቁሳቁሶች እንዲሁም በቁም እንስሳት ላይ ጉዳት አድርሷሳ።

በጎርፍ አደጋ ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተገለፀ ሲሆን ከክልሉ መንግስትና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በመነጋገር አፋጣኝ ድጋፍ የሚደርስበት ሁኔታ ይመቻቻል ሲል የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አስታውቋል።

መረጃው ከክልሉ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia