TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደራሽ

በሳምንት ለአምስት ቀናት የሚታየው ተከታታይ ድራማ ፦

በኢትዮጵያ ያለው የፊልም ኢንደስትሪ በተቀዛቀዘበት በዚህ ወቅት በተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማዎች ኢንዱስትሪውን ለመነቃቃት ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

በዘርፉ ላይ ተግዳሮት ሆኖ የቆየውን የአቅም ችግር በመጠኑም ቢሆን በመቅረፍ ለሙያተኞች እንዲሁም ለተመልካቾች ትልቅ እድል ይዞ የመጣው አቦል ቲቪ ተጠቃሽ ነው፡፡

የሀገራችን የፊልም ኢንዱስትሪ ፈተና ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት አቅም ያላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀላቀላቸው ሰፊ የሥራ ዕድል ለሚፈጥረው ለዘርፉ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ሆኗል።

አቦል ከኤምኔት ቻናሎች አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ80 በላይ #የኢትዮጵያ ፕሮዳክሽን ካምፓኒዎች በተለያየ መልኩ አብረው የመስራት ዕድል አግኝተዋል።

አቦል ቴሌቪዥን ለተመልካች ካቀረባቸው ውስጥ '' ደራሽ '' የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ አንዱ ሲሆን ከ200 በላይ ባለሞያዎችን በማሳተፍ ከሰኞ እስከ አርብ በተከታታይ ይተላለፋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/ደራሽ-08-03
#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን !

በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች ፦

• መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

• ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው።

• የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ ጠይቀዋል።

• በመንግስት የተደረገው የደረጃ ማሻሻያ ረጅም ጊዜ በዩንቨርሲቲ ያስተማሩ መምህራንን ልምድ ያላገናዘበ በመሆኑና በመምህራን መካከል በቀጣይ ፍትሀዊ የደምወዝ ልዩነት እንዲኖር ስለማያስችል የደረጃ ማሻሻየው የመምህራንን ልምድ እና ማዕረግ ያገናዘበ እንዲሆን ጠይቀዋል።

• የረዳት ፕሮፌሰር የአካዳሚክ ማዕረግ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የ3ኛ ዲግሪ መደረጉን በተመለከተ ያለን ቅሬታ አላቸው።

• የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ መሆኑ ላይ አቤቱታ አላቸው።

• የቺፍ ቴክኒካል ረዳት II የትምህርት ደረጃን ፒ ኤችዲ ዲግሪ መሆኑም ላይ አቤቱታ አላቸው።

ጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጣቸው እያሉ የሚገኙት መምህራኑ ይህ ካልሆነ እስከ ስራ የማቆም አድማ መምታት ድረስ ዕርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

👉 ትምህርት ሚኒስቴር ለሪፖርተር ፥ " ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን። ነገር ግን አሁን ላይ ለውጦች ለማምጣት ጥናት እየተካሄደ ነው። ከዚህ ባለፈ የምንለው ነገር የለም። የደመወዝ ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴር ብቻ አይደለም የሲቪል ሰርቪስ ጉዳይም ነው "

ያንብቡ : telegra.ph/ETH-08-07-2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሶማሊያ ፓርላማ ነገ እሁድ ይሰበሰባል። በነገው ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ባሬ የቀረበውን የካቢኔ አባላት ላይ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከቀናት በፊት ጠ/ሚኒስትሩ የቀድሞ " አልሸባብ " ምክትል መሪ ሙክታር ሮቦው የሀይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ያደረጉበት 26 የካቢኔ አባላት ፓርላማው እንዲያፀድቅላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል። @tikvahethiopia
የትላንቱ የጎረቤት ሶማሊያ ፓርላማ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?

• 229 ድጋፍ
• 7 ተቃውሞ
• 1 ድምፀ ተአቅቦ

በትላንትናው ዕለት የጎረቤታችን ሶማሊያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጠ/ሚ ባቀረቡት የካቤኔ አባላት ላይ ድምፅ ለመስጠት ተሰብስቦ ነበር።

በዚህም ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ያቀረቡትን የካቢኔ አባላት በ229 ድጋፍ፣ በ7 ተቃውሞ ፣ በ1 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካቢኔያቸው ያካተቷቸው የቀድሞ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ምክትል መሪ የነበሩት ሙክታር ሮቦው የሶማሊያ የሀይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ፤ የቀድሞው የአልሸባብ ሰው በካቢኔ ውስጥ መካተታቸው አሜሪካን እንዳላስደሰታት በአንድንድ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ቢነገርም አሜሪካ በካቢኔው ደስተኛ እንደሆነች በመግለፅ ለፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሙሀሙድና ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ " እንኳን ደስ አላችሁ " ስትል ሶማሊያ በሚገኘው ኤምባሲ በኩል መልዕክቷን አስተላልፋለች።

አሜሪካ ፤ ለሶማሊያ የምታደርገውን ድጋፎች አጠናክራ እንደምትቀጥልበትም ገልፃለች።

ሀገሪቱ በሶማሊያ የሚኒቀሳቀሰው " አልሸባብ "ን ለመዋጋት ሰፊ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ሀገራት በቀዳሚነት ስሟ የሚነሳ ሲሆን በኢኮኖሚያዊና ሰብዓዊ ድጋፍ በኩልም በሚሊዮን ዶላሮችን ለሶማሊያ ድጋፍ ታደርጋለች።

@tikvahethiopia
#መግለጫ

ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ጠቅላላ የመብቶች ጥሰት በተመለከተ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።

ማህበሩ በላከልን መግለጫ ፥ የተደራሽነት መብትን ጨምሮ የትምህርት፣ የጤና፣ የስራ እና የቅጥር መብቶች እና ሌሎች የአካል ጉዳተኞች መብቶች በየግዜው እየተጣሱ እና ለጥሰቶቹ ሀላፊነት የሚወስድ አካል ሳይኖር እንዲሁም ጥፋተኞችም ተጠያቂ ሳይደረጉ የመብት ጥሰቶቹ ተድበስብሰው በመታለፍ ላይ ናቸው ብሏል።

የአካል ጉዳተኞችን የመብት ጥሰቶችን ተከትሎ ተጠያቂነት ባለመኖሩም ጥሰት የሚፈጸምባቸው ሰዎች ሳይካሱ እየቀሩ እና ጥሰት ፈጻሚዎችም ድርጊታቸውን ትክክል አድርገው እንዲወስዱትና የመብት ጥሰቱም ያለከልካይ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል ብሏል።

አሁን በተግባር እንደሚታየው የአካል ጉዳተኞች የመብት ጉዳዮች በግለሰቦች መዳፍ ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው፤ አካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ መብቱን እንደምጽዋት እንዲጠይቅና እንዲቀበል ተገዷል ሲልም ገልጿል።

ማህበሩ ፥ በአካልጉዳተኛ ግለሰቦች ላይ ከሚፈጸሙ አይነተብዙ የመብት ጥሰቶች በተጨማሪ ከመንግስት በኩል አካል ጉዳተኞችን በቁልፍ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአካታችነት መሻት በሚመነጭ ተነሳሽነት የማካተት ስራዎች በበቂ ሁኔታ እየተሰሩ አይደለም ብሏል።

ከሀገሪቱ ህዝብ ቁጥር ከ17.6 በላይ የሚሸፍነው አካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ እንደሆነ ያታወቃል ያለው ማህበሩ የተለየ በጀት የማይበጀትለት መሆኑና የመብት ጥያቄ በሚያነሳበት ግዜም ፖለቲካዊ ውክልና የሌለው ማህበረሰብ መሆኑን ተከትሎ ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረት ላይ ነው ብሏል።

ማህበሩ እየተባባሰ መጥቷል ላለቸው የመብቶች ጥሰት መፍትሄ ያለውን በዝርዝር አስቀመጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ጠቅላላ የመብቶች ጥሰት በተመለከተ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል። ማህበሩ በላከልን መግለጫ ፥ የተደራሽነት መብትን ጨምሮ የትምህርት፣ የጤና፣ የስራ እና የቅጥር መብቶች እና ሌሎች የአካል ጉዳተኞች መብቶች በየግዜው እየተጣሱ እና ለጥሰቶቹ ሀላፊነት የሚወስድ አካል ሳይኖር እንዲሁም ጥፋተኞችም…
#መፍትሄ

በአካል ጉዳተኛ ግለሰቦችና በአካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመቀነስ ያግዝ ዘንድ መንግስት የሚከተሉትን የተግባር እርምጃዎች ይውሰድ ፦

(የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር)

1. መንግስት ከአመታዊ በጀቱ ውስጥ ለአካል ጉዳተኛ ዜጎች የመብት ማስፈጸሚያ እንዲውል የተለየ እና በአሀዝ እና በቁጥር የሚገለጽ ተግባር ላይ የሚውል በጀት መመደብ ይጀምር።

2. መንግስት በአካል ጉዳተኛ ዜጎች ላይ የመብት ጥሰት የሚፈጽሙ ተቋማትን እና ግለሰቦችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እና ተበዳይ አካል ጉዳተኛ ዜጎች የሚካሱበት ስርአት እንዲዘረጋ በሀላፊነት ስራዎችን መስራት ይጀምር።

3. መንግስት የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽ በሖነ መንገድ እና አካል ጉዳተኛ ዜጎችን ባካተተ መንገድ እንዲሰጡ ያድርግ።

4. መንግስት በቁልፍ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አካል ጉዳተኞች እንዲደመጡ እና አካታችነትን ከመሻት መንፈስ በሚመነጭ ቁርጠኝነት፣ አካል ጉዳተኞች ተገቢ ውክልና እንዲያገኙ እንዲያደርግ እና በአጠቃላይም አካልጉዳተኛ ዜጎች በተወካዮች/ምክር/ቤት፣ በክልል ምክር/ቤቶች እንዲሁም በየደረጃው በሚገኙ ምክር/ቤቶች ውክልና እንዲያገኙ ያድርግ።

5. መንግስት የጀመረው የህግ ሪፎርም የአካል ጉዳተኞች መብቶች የሚከበሩበት ይሆን ዘንድ፤

- አለምአቀፉ የአካልጉዳተኞች መብቶች ኮንቬንሽን ታትሞ በነጋሪት ጋዜጣ ይውጣ።

- የማራካሽ ስምምነት ማስፈጸሚያ አዋጅ እንዲጸድቅ እና የተግባር ስራ ይጀመር።

- የአካል ጉዳተኛ መብቶች አዋጅ የአካል ጉዳተኛ ዜጎችን ሁለንተናዊ መብቶች በሚያስጠብቅ መንገድ ተዘጋጅቶ እንዲጸድቅ ይደረግ።

- ሌሎችንም የአካል ጉዳተኛ ዜጎችን መብቶች ሊያስከብብሩ የሚችሉ የህግ እና የፖሊሲ ሪፎርሞችን ያደርግ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ICRC የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት ህይወታቸውን እንደሚታደግ ገልጾ ፦ በሐይቅ፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ኮምቦልቻ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ዓዲግራት፣ መሆኒ፣ ሽሬ፣ ኣክሱም፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ዋድላ፣ ባህር ዳር፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢዶሎ ሆስፒታሎች ያሉትን የአንድ መስኮት የአገልግሎት ማዕከላትን በመደገፍ…
#ICRC #Tigray

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በተለያዩ ክልሎች በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል።

ኮሚቴው #በትግራይ_ክልል በግጭት የተጎዱ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ ፦

👉 በማዕከላዊ፣
👉 በምስራቅ ፣
👉 በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ዞኖች ለሚገኙ ለ20,000 አባውራዎች (120,000 ግለሰቦች) የአፈር ማዳበሪያ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ዛሬ አሳውቋል።

ICRC ፤ ከሰሞኑን በትግራይ፣ አማራ እንዲሁም ኦሮሚያ ክልል ከተሞች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ እና ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተቀብረው ሳይፈነዱ ሚቀሩ ፈንጂዎች በሰዎች አካል ላይ የሚያደረሱትን ጉዳት ተንተርሶ ተጎጂዎችን ለመርዳት በተለያዩ ከተሞች የአካል ማገገሚያ ማዕከላትን በማጠናከር ላይ እንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Wanted #ይፈለጋሉ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ አይተንፍስ እንደሻው ስለሺ እና ያቤል መንገሻ የተባሉ ግለሰቦችን (በፎቶ ከላይ ይታያሉ) በወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ብሏል።

ፖሊስ እነዚህን 2 ግለሰቦች የሚፈልጋቸው #በከባድ_የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቦቹን ያየ አልያም ያሉበትን የሚያውቅ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30 በ01115309047 / 01111711206 እና በማንኛውም ሰዓት በ0111119475 / 0111711012 በመደወል እንዲያሳውቀው የጠየቀው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ኢሠፓ

በደርግ ዘመነ መንግስት ገዢ ፓርቲ የነበረውን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲን (ኢሠፓ) ዳግም ለማቋቋም የተሰባሰቡ ግለሰቦች፤ የምስረታ ሰነዶቻቸውን ለምርጫ ቦርድ አስገብተው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ለማግኘት እየተጠባበቁ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የፓርቲው የምስረታ ሰነዶች እንደደረሱት አረጋግጧል።

ኢሠፓን ከ30 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ለመመለስ የተሰባሰቡት ግለሰቦች፤ የምስረታ ሰነዶችን ለምርጫ ቦርድ ያስገቡት ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ መሆኑን የፓርቲው አደራጆች ገልጸዋል።

ከአደራጆቹ መካከል የሆኑ እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር በሰጡት ቃል ፤ " የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተን [ለቦርዱ] አስገብተናል " ብለዋል።

" በአዲስ መልክ ተመልሶ ይመሰረታል " የተባለለትን ኢሠፓን በማደራጀት ላይ ከሚገኙት ውስጥ #የቀድሞው የፓርቲ አባላት ይገኙበታል ተብሏል።

ከእነዚህ የቀድሞ አባላት ውስጥ በኢሠፓ #በከፍተኛ_አመራርነት ያገለገሉ እንዳሉበት እኚሁ አደራጅ ቢገልጹም ማንነታቸውን ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል። 

" የቀድሞዎቹ የኢሠፓ አመራሮች በእስር ቤት ያለፉ ሰዎች ናቸው። ከስህተታቸው ብዙ ትምህርት ተምረዋል " የሚሉት አደራጁ፤ ግለሰቦቹ እንደገና በሚቋቋመው ፓርቲ የሚኖራቸው ሚና ከኋላ ሆነው ልምዳቸውን የማካፈል መሆኑን አስረድተዋል።

በአደራጆቹ ስብስብ ውስጥ ከቀድሞዎቹ የኢሠፓ አመራሮች እና አባላት በተጨማሪ #ወጣቶችም መካተታቸውን መግለፃቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#የትምህርት_እድል

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች አወዳድሮ ለማስተማር እንደሚፈልግ ገልጿል።

የምዝገባ መስፈርቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ሲሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተማሪዎች ተመዝግባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።

ሀ/ የውድድር መስፈርቶች

1ኛ. ክልላዊ የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት (average) (ጥሬ ማርክ) ለወንድ 78 እና ከዛ በላይ ለሴት 75 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገበ / ያስመዘገበች

2ኛ. ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ከፍተኛ ፍላጎት ያለው/ያላት 10ኛ ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ መቀጠል የሚፈልግ/የምትፈልግ

ለ. ዝርዝር መረጃ

• የምዝገባ ቀን ከ09/12/14 - 13/12/14
• የምዘገባ ቦታ-በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፡ በቀድሞው ቀዳማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ት/ቤት፡፡ ከአራዳ ክ/ከተማ ፊት ለፊት
• የምዝገባ ሰዓት ከረፋዱ 3፡00 - ቀኑ 10:00

ሐ/ ተወዳዳሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ

• ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ውጤት የሚገልጽ ዋናውንና 1 ፎቶ ኮፒ
• የመመዝገቢያ ብር 400
• አንድ ክላሰር ይዛችሁ ተገኙ

መ. ተጨማሪ መረጃ

• የጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 18/12/14 ከቀኑ 7፡30 - 10፡30
• ፈተና የሚሰጥበት ቦታ በካምፓሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ተብሏል።

ት/ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎች በማፍራት በሀገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎችም እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ያፈራ ት/ቤት ነው።

ለአብነት በ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና 78 ተማሪዎችን አስፈትኖ 42 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በኢትዮጵያ ትልቁ ውጤት የመጣውም 659 ከዚሁ ሲሆን በት/ቤቱ ዝቅተኛ ውጤት የነበረው 529 ነበር።

@tikvahethiopia
#ውብ_አረቢያን_መጅሊስ

ከአውሮፓና ከእስያ በሚመረቱ ጥሬ እቃ በብቁ ባለሞያ በዘመነ ማሽን ውብ አረቢያን መጅሊስ የሚያመርታቸውን ውብ እና ማራኪ የሆኑ መጅሊሶቻችን እና ሶፋዎችን እንካቹ ስንል 👉 በ9 ቅርጫፎቻችን ስንጠበቅዎ በታላቅ ደስታ ነው 0910222244 / 0954111133 / 0954111100
ተጨማሪ ፎቶ ለመምረጥ ሊንኩን የጫኑት https://t.iss.one/wubeare
የኬንያ አዲስ ፕሬዝዳንት ማን ይሆን ?

የጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዝዳንት ምርጫ ዛሬ ነሃሴ 3 እየተካሄደ ነው።

ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት አራት ዕጩዎች ቀርበዋል።

🇰🇪 ዴቪድ ሙዋሬ ፦

የኬንያ አጋኖ ፓርቲ፣ በሙያቸው ጠበቃ እንዲሁም ሰባኪ የሆኑት ዴቪድ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ያሰቡት በአውሮፓውያኑ 2013 ነበር። በኋላ ግን በውድድሩ ተሳታፊ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዘንድሮው ምርጫ አገሪቱን ለቀጣዩ አምስት ዓመት ለመምራት እየተፋለሙ ይገኛሉ።

🇰🇪 ራይላ ኦዲንጋ ፦

የአዚሚዮ ላ ኡሞጃ ጥምረት፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና አንጋፋው ፖለቲከኛ፣ አገሪቱን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ለአምስተኛ ጊዜ ሙከራቸውን እያደረጉ ነው።

🇰🇪 ዊሊያም ሩቶ ፦

የተባበሩት ዲሞክራቲክ አሊያንስ : አገሪቷን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ለሚመሩት ዊልያም ሩቶ ይህ የመጀመሪያ የፕሬዝዳንትነት ምርጫቸው ነው።

🇰🇪 ጆርጅ ዋጃኮያ ፦

የኬንያ ሩትስ ፓርቲ : ጠበቃውና ፕሮፌሰሩ ዋጃኮያ ለየት ባለ ሃሳባቸው ለፕሬዝዳንትነት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተወዳደሩ ነው።

ኬንያውያን ድምፃቸውን እየሰጡ ሲሆን የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን በአራት አካባቢዎች ላይ የሚደረጉ ምርጫዎችን አግዷል። እገዳ የተጣለው ከምርጫ ካርድ ህትመቶች ጋር በተፈጠረ ስህተት ነው ተብሏል።

ምርጫ የማይደረግባቸው አካባቢዎች ፦ ሞምባሳ እና ካካሜጋ የሚገኙባቸው ሲሆን፣ በእነዚህ ቦታዎች በቀጣይ እስኪገለጽ ድረስ ምርጫ ታግዷል።

ሌሎቹ ፖኮት ሳውዝ እና ካቺሊባ ግዛቶች ናቸው ምርጫ የማይደረግባቸው። የታቱሙት ካርዶች የያዟቸው ዕጩዎች ዝርዝርና ምስሎች የተሳሳቱ ናቸው ተብሏል።

Via BBC NEWS

@tikvahethiopia