TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው " - የሶማሌ ክልል ፕ/ት ሙስጠፌ ሙሁመድ

በቅርቡ በሶማሊያና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ጥቃት ፈፅሞ የነበረው የአልሸባብ ቡድን 800 ታጣቂዎቹ መገደላቸውን 100 የሚጠጉት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ በተረጋገጠ ትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

የአልሸባብ ጥቃት በሽንፈት መጠናቀቁን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ እና እንዳይዳፈር የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GoE የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክተኞች እና አምባሳደሮች የመቐለ ቆይታን በተመለከተ ጉዳዩን የያዙበት መንገድ በመንግስት ላይ ቅሬታ እንደፈጠረበት ገልፀዋል። አምባሳደሩ፤ ልዩ መልዕክተኞቹ እና አምባሳደሮቹ ለሰላም ንግግር ጥረት ማድረግ ሲገባቸው በሌላ ወገን የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ላይ ተጠምደዋል ብለዋል። "…
#ድርድሩ

በአዲስ አበባ ከፌዴራል መንግስት ጋር እንዲሁም መቐለ ተጉዘው ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ካለው ህወሓት ጋር ሰሞኑን የተወያዩት የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔቴ ዌበር ከጀርመን ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በፌዴራል መንግስት እና ህወሓት መካከል ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የሰላም ድርድር " የመተማመን መጥፋት " መሰናክል መሆኑን ተናግረዋል።

ዌበር ለሬድዮ ጣቢያው " ዋነኛው መሰናክል (ለሰላም ድርድሩ) የእምነት እጦት ነው ብዬ አስባለሁ። አንዱ ከሌላው ጋር በቅን ልቦና እየተደራደሩ ለመሆናቸው የበለጠ መተማመኛ እንደሚፈልጉ 2ቱም ግልፅ አድርገዋል።

ሁለቱ ወገኖች ዝግጁነታቸውን ከማሳወቅ ባሻገር ወደ ድርድሩ እንዲመጡ የሚያስፈልገውን መተማመን የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ያጠናክራሉ ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ።

የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎች እንደሌሉት አረጋግጧል። ከመንግስት በኩል የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር ምልክት ከሰጠ ወይም ካስጀመረ ህወሓት በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በመቐለ ጉብኝታችን ተረድቻለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በተመለከተ ዌበር በጥቂት ቀናት ውስጥ ስራ ይጀምራሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ከሬድዮ ጣቢያው ጋር በነበራቸው ቃለምምልስ ወቅት ተናግረዋል።

ዌበር " እኛ አሁን እጅግ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ ከሚጀምሩበትን፤ መጀመራቸውን እየተጠባበቅን ነው። በዚህ ረገድ ከአዲስ አበባም ሆነ ከመቐለ የተቀየረ ነገር ካለ አልሰማሁም፤ ነገር ግን ይህ በማንኛውም ቀን ተግባራዊ ይሆናል ብዬ እጅግ ተስፋ አደርጋለሁ። " ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/EU-08-05

@tikvahethiopia
#የህግ_ጉዳይ

ከክልል ፍርድ ቤቶች እስከ ፌዴሬሽን ደርሶ ወደ ከፍተኛ የተመለሰው የንብረት ክርክር መጨረሻ ምን ይሆን ?

(በሪፖርተር ጋዜጣ - አሳዬ ቀፀላ)

ከ10 ዓመታት በፊት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነበር ክርክሩ የተጀመረው።

የክርክሩ መነሻ፣ በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ጌትእሸት ዲተርጀንት ማምረቻና ማሸጊያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሽያጭ ነው፡፡

ድርጅቱ የእነ ጌታቸው እሸቱ (ኢንጂነር) አራት ሰዎች ሲሆን፣ ጠቅላላ የቦታው ስፋት 11,305 ካሬ ሜትር ነው፡፡

የዲተርጀንት ማምረቻና ማሸጊያ ፋብሪካው ያረፈው በ3,015 ካሬ ሜትር ላይ ሲሆን፣ ስመ ሀብቱ የተመዘገበው በጌታቸው እሸቴ (ኢንጂነር) ስም ነው፡፡

ቀሪው 8,290 ካሬ ሜትር ደግሞ ጅምር ግንባታ ያለበት ሆኖ፣ ስመ ሀብቱ (ካርታው) የተመዘገበው በጌትእሸት ዲተርጀንት ማምረቻና ማሸጊያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስም ነው፡፡

ፋብሪካውንና ጅምር ግንባታ ያረፈበትን (በሁለት የተለያዩ ስሞች የተመዘገቡ ይዞታዎች) ሁለት ይዞታዎች እነ ጌታቸው (ኢንጂነር) (አራት ሰዎች) ለእነ ዶ/ር በዕውቀቱ ታደሰ ከአሥር ዓመታት በፊት ኅዳር 18 ቀን 2005 ዓ.ም. በ22,500,000 ብር ሸጠውላቸዋል፡፡

የሽያጭና የግዥ ውሎች የኢትዮጵያ ፍትሐ ብሔር ሕጎችን ሒደት በጠበቀ ሁኔታ ተፈጽመዋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Justice-08-06

@tikvahethiopia
#GoE

የፌዴራል መንግስት በቅርቡ ወደ ትግራይ ፣ መቐለ ተጉዞ የነበረው የዲፕሎማቶች የልዑካን ቡድን " የህወሃትን የውሽት ትርክት አስተጋብቷል፤ ይህም ስህተት ነው " ብሏል።

ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ላይ መንግሰት በራሱ ተነሳሽነት የተኩስ አቁም ስምምንት ለማድርግ ወሰኖ እንደነበር እና አሁንም #ለሰላም ውይይት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የምግብ ድጋፍ በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት ተደራሽ እየተደረገ ነው ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " መንግስት ወደ ትግራይ የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ ባላቋረጠበት እና ክልከላዎች ባላደረገበት ወደ መቐለ ተጉዞ የነበረው የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኞችን የያዘው የዲፕልማቶች ቡድን የህወሓት የውሽት ትርክት ማስተጋባቱ ስህተት ነው " ብለዋል።

መንግስት በ #አፍሪካ_ህብረት በኩል የሚካሄደው የሰላም ውይይት ሁሌም በማንኛውም ቦታ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት በህወሃት በኩል ከሰላም ድርድር ፍላጎት ይልቅ አሁንም የጦርነት ጉሰማዎችና ለሰላም ውይይት እንቅፋት የሚሆኑ ንግግሮች እየተሰሙ ነው ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ንባብ ለህይወት "

ከሐምሌ 28 ጀምሮ የንባብ ለህይወት የመፅሀፍት እና የምርምር ተቋማት አውደርዕይ በአዲስ አበባ ከተማ ኤግዝቢሽን ማዕከል ውስጥ እየተካሄደ ነው።

እስከ ነሀሴ 2 ድረስም ይቆያል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት አውደ ርዕዩን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። የተለያዩ መፅሀፍት በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የአሁን እንዲሁም ከዚህ ቀደም የታተሙ የተለያየ ይዘት ያላቸው የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ መፅሀፍት የቀረቡ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የምርምር ስራዎቻቸውን አቀርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከመፅሀፍት አውደ ርዕዩ ጎን ለጎን የተለያዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች እየተዘጋጁ ለታዳሚያን እየቀረቡ ናቸው።

በመፅሀፍ አውደ ርዕዩ ላይ የተገኙ የቤተሰቦቻችን አባላት እየተዘዋወሩ ከተመለከቷቸው የመፅሀፍ ሽያጮች መካከል ጃፋር የተሰኘው የመፅሀፍት መደብር #ከ25_ብር ጀምሮ የተለያዩ መፅሀፍት እንዲሸጡ አቅርቦ ተመልክቷል።

የአዲስ አበባ ቲክቫህ አባላት የሆናችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን ይዛችሁ ብትሄዱ ለራሳችሁም ለልጆቻችሁም የሚሆኑ መፅሀፍትን ታገኛላችሁ ለልጆችም የተዘጋጁ አስተማሪ ፕሮግራሞች አሉ።

ወጣቶችም የምትወዷቸውን እና የምትፈልጓቸውን መፅሀፍትን በቅናሽ ከማግኘት ባለፈ መሰል ፕሮግራሞችን በማበረታታ በሀገራችን ያለው የንባብ ባህል እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረግ ትችላላችሁ።

ቦታ ፦ መስቀል አደባባይ ኤግዥቢሽን ማዕከል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። ቴሌ ብር መላ፦ የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ እስከ በቀን እስከ 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው። ቴሌ ብር እንደኪሴ ፦ በቴሌብር አማካኝነት…
#ዝርዝር_ማብራሪያ

ኢትዮ ቴሌኮም ፦

• ቴሌብር መላ ፤
• ቴሌብር እንደኪሴ
• ቴሌብር ሳንዱቅ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን አስተዋውቋል።

ይህንን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ አጠናቅረናል።

- " ቴሌብር መላ " አነስተኛ የብድር አገልግሎት ሲሆን ግለሰቦች እንዲሁም ነጋዴዎች እና ወኪሎች ያለየብድር ማስያዥያ ( Collateral ) ገንዘብ መበደር ያስችላቸዋል።

ምን ያህል መበደር እችላለሁ የአገልግሎት ክፍያውስ?

- " ቴሌብር እንደኪሴ " የክሬዲት ክፍያ/ኦቨርድራፍት ብድር አገልግሎት ሲሆን ገንዘብ በጎደሎት ጊዜ ሞልቶ ይከፍላል።

እንዴት መጠቀም እችላለሁ?

- " ቴሌብር ሳንዱቅ " የቁጠባ አገልግሎትን የሚሰጥ ሲሆን ከአንስተኛ ብር ጀምረው መቆጠብ ይችላሉ።

ወለዱ እንዴት ይሰላል ?

ያንብቡ : https://telegra.ph/telebirr-08-05
#ሚኒስትሮች_ምክርቤት

ከ10ኛው የሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔዎች መካከል ፦

" ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለማስከፈል የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቷን።

ወደ አገር በሚገቡ በተወሰኑ ምርቶች ላይ አነስተኛ ቀረጥ በመጣል በሚገኘው ገቢ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማስፋፋት በመጠገን እና በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ "

(ሙሉ የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia