TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የሰላም ድርድሩ መቼ ይጀመር ይሆን ? የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ድርድር እንዲቋጭ ከፍተኛ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል። በፌዴራል መንግሥት እንዲሁም በህወሓት በኩል ለሰላም ድርድር ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸው በርካቶች ሰላም ይሰፍናል የሚል ትልቅ ተስፋን አሳድሮባቸዋል። በሁለቱም በኩል ተደራዳሪዎች መሰየማቸው ከተሰማ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን መቼ ድርድሩ ይጀምራል የሚለው ትክክለኛ መልስ አላገኘም።…
ፎቶ ፦ ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ በኢትዮጵያ አሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰንም ተገኝተው ነበር።

Photo Credit : የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት በአዲስ አበባ ከተማ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ። ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ፦ - የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ - የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ አቶ ስመኘው አባተ - የሶፍትዌር ባለሙያዎች ፦ • ሀብታሙ…
#ችሎት #Update

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ።

ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች የነበሩ ናቸው።

ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ የአዲስ አበባ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምከትል ኃላፊ አቶ አብርሃም ሰርሞሎ ይገኙበታል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዛሬው ውሎው " ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተገንዝበናል " ብሏል።

" የወንጀሉ ውስብስብነት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመስጠት ምክንያታዊ ነው " ያለው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ፤ በዚህም መሰረት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ለመርማሪ ፖሊስ መፈቀዱን ማስታወቁን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Somalia #SW

ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ።

የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ።

ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው።

በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ ግድያውንና ጥቃቱን አውግዘው ከጥቃቱ ጀርባ የአልሸባብ የሽብር ቡድን መኖሩን አመልክተዋል።

ይህ ጥቃት በያዝነው ወር እኤአ በቀን 27 በታችኛው ሸበል ክልል የማርካ ወረዳ አስተዳዳሪ አብዱላሂ አሊ ዋፎውን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎችን ከገደለው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት እንዲሁም በአፍጎዬ ከተማ ፍንዳታ ተከስቶ ቢያንስ አራት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ከቆሰሉበት ጥቃት ከቀናት በኃላ የተፈፀመ ነው።

በሌላ በኩል፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ዛሬ #ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰነው የሶማሊያዋ የድንበር ከተማ " አቶ " ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ከፍቶ እንደነበር ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልወደዱ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣን በሰጡት ቃል ፤ የሽብር ቡድኑ አቶ ላይ በ2 ሳምንት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ጥቃት መሰንዘሩን ይህን ተከትሎ ውጊያ መካሄዱን አመልክተዋል።

ዛሬ ወደ አቶ ዘልቆ ጥቃት የመፈጸም ዓላማ የነበረው የአልሻባብ ታጣቂ ኃይል፤ ያሰበው ሳይሳካ #ሽንፈት እንዳጋጠመው ተናግረዋል።

በፀጥታ ኃይሎችም በኩል ጉዳት መድረሱን ያመለከቱት ባለስልጣኑ ለጊዜው ዝርዝር መናገር አልችልም ብለዋል።

አልሸባብ ከጥቂት ቀናት በፊት ኢትዮጵያን ለመዳፈር ሞክሮ በሶማሌ ልዩ ኃይል ክፉኛ መመታቱ አይዘነጋም። አሁንም በድንበር የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩን ለማወቅ ችለናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia #SW ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ። የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ። ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው። በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን…
" አልሸባብ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል " - ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው

የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት እርምጃ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በሶማሌ ክልል በ5 ትናንሽ የጠረፍ አካባቢዎች ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራ በጸጥታ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሉ ተቆርጠው የቀሩትን የሽብር ቡድኑ አባላትን የማጽዳት ዘመቻ ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ባለፉት ቀን ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡ በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ጠቁመዋል፡፡

ነገር ግን የሽብር ቡድኑ #ዛሬ_ሌሊት ላይ የተበታተነ ኃይሉን በማሰባሰብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት አካባቢ ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም መሞከሮ ነበር።

ሆኖም የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ዳግም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራዎችን ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ነው ያብራሩት፡፡

እስካሁን ባለው መረጃም ከ150 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውንና የሽብር ቡድኑ ለአጥፍቶ መጥፋት ያዘጋጃቸው ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንደተማረኩ አመልክተዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ዶሮ እና የዶሮ ውጤቶችን ያለ ስጋት መጠቀም ይቻላል " - የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ተከስቶ የነበረው የዶሮ በሽታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነሳ። በኢትዮጵያ በተከሰተው የዶሮ በሽታ ምክንያት በዶሮና የዶሮ ውጤቶች ላይ ተጥሎ የቆየው ገደብ መነሳቱን የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። ባለፉት…
" ዶሮና እንቁላል ያለስጋት መመገብ ይችላል " ግብርና ሚኒስቴር

ግብርና ሚኒስቴር በቅርቡ የተከሰተው የዶሮ በሽታ በቁጥጥር ሥር በመዋሉ ሕብረተሰቡ ያለምንም ስጋት ዶሮና እንቁላል መመገብ እንደሚችል አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ለኢዜአ በሰጠው መግለጫ ነው።

ባሳለፍነው ሰኔ ወር መባቻ በቢሾፍቱና በምዕራብ አዲስ አበባ የተከሰተው የዶሮ በሽታ ወረርሽኝ በዶሮ እርባታ ቦታዎች ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ያለው ግብርና ሚኒስቴር በሽታው እንደተከሰተ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ሌሎች ባለድርሻ ተቋማት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ተሰማርቶ የበሽታውን ሥርጭት የመግታት አፋጣኝ ምላሽ መውሰዱን አሳውቋል።

በወቅቱ ለዶሮ እርባታ አገልግሎት ከውጭ የሚገባው የለማ እንቁላልና ዶሮና የዶሮ ውጤቶች ዝውውር ባለበት እንዲገታ የጥንቃቄ መመሪያዎች ለሚመለከታቸው አካላት መተላለፉንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውሷል።

በተጨማሪ ዶሮና እንቁላል አመጋገብ ላይ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ መተላለፉን ገልጾ በሂደት የጥንቃቄ መመሪያዎች እየተሻሻሉ መሄዳቸውን አሳውቋል።

በሽታውን ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት ምክንያት በሽታውን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ያለው ግብርና ሚኒስቴር አሁን ላይ ምንም አይነት የበሽታ ስጋት ባለመኖሩ ሕብረተሰቡ ዶሮና እንቁላል ያለስጋት በማብሰል እንዲጠቀም፤ ዶሮ አርቢዎችም በሙሉ አቅማቸው ዶሮ በማርባት ለገበያ እንዲያቀርቡ መወሰኑን ገልጿል።

በዶሮ እርባታ የተሰማሩ ዜጎች ግን በማንኛውም ጊዜ የሚያደርጉትን ‘ባዮ-ሴኪዩሪቲ’ የተሰኘውን የዶሮ እርባታ ጥንቃቄ ሥርዓትን ባጠናከረ አግባብ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ተጨማሪ : telegra.ph/MoA-07-29

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ 📈 ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ 👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም 👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም 👉 ከባድ…
#ነዳጅ

ከነገ #ሐምሌ_23 ቀን 2014 ዓ.ም - #ነሐሴ_30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የአውሮፕላን ነዳጅን በሚመለከት ግን በወቅታዊ የዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ በመጣው አዲስ አበባ ላይ በሊትር 84 ብር ከ42 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑንም ገልጿል።

ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ የአሠራር ሥርዓት በነሐሴ ወር በተመሳሳይ እንደሚቀጥልም የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#DY_Technology

ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ በጣም በዝቅተኛ ሃይል መስራት የሚችል፤ ዝርዝሩን ያንብቡ👉https://t.iss.one/pls_see_more/335
#UN #ETHIOPIA

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የሰብዓዊ መብቶች ባለሞያዎችን ያካተተ ዓለም አቀፍ ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተፈፀሙ የመብቶች ጥሰቶችን ለመመዝገብ ጥሪ አቀረበ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና ተቋማት ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ የተካፈሉ ሁሉም አካሏት የፈፀሟቸውን የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ፣ ሰብዓዊነት እና የስደተኛ መብቶች ጥሰቶችን የሚያስረዱ ማንኛውንም መረጃ ለኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ ጥሪ አድርጓል።

መረጃዎቹ በተለይ ፆታን መሰረት አድርገው የተፈፀሙ ጥቃቶች እና የመብቶች ጥሰቶችን እንዲሁም የጥቃት አድራሾችን ማንነት ሊያጠቃልል እንደሚችልም አስታውቋል።

መረጃ አቅራቢዎች ከመብት ጥሰት በተጨማሪ የሽግግር ፍትህ፣ ተጠያቂነት፣ እርቅ እና ፈውስ ለማምጣት የሚያስችሉ የሚሏቸውን የመፍትሔ ሐሳቦችን የያዙ ሰነዶችን ኮሚሽኑ የጠየቀ ሲሆን መረጃዎቹ በእንግሊዘኛ፣ በአማርኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች መቅረብ እንደሚችሉ አመልክቷል።

መረጃ አቅራቢዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉባኤ ድህረ ገፅ ላይ የተቀመጠውን ቅፅ በመሙላት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን መረጃዎቹ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተጠናቀው መግባት እንዳለባቸው ማሳሰቡን ቪኦኤ ዘግቧል።

https://www.ohchr.org/en/hr-bodies/hrc/ichre-ethiopa/call-for-submissions

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ወደ ትግራይ ክልል በህገወጥ መንገድ ሊያልፍ የነበረ ከ8ነጥብ 8ሚሊዮን ብር በላይ ጥሪ ገንዘብ በቁጥጥር ስር መወሉን የፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

በሰርዶ የፍተሻ ጣቢያ የሚገኝው የፌዴራል ፖሊስ ፤ በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ይዞ በመጓዝ ላይ ከነበረ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ መኪና በህገወጥ መንገድ ሊያልፍ የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሪ ገንዘብ በቁጥጥር ማዋሉን ገልጿል።

የከባድ ጭነት ተሽከር መኪናው መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ የሰብአዊ የምግብ ድጋፍ በመያዝ እና በውስጡ የተጠቀሰውን ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የብር የአንገት ሀብሎች እና ሌሎች ያልተፈቀዱ ነገሮችን በህገወጥ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል ለማሳለፍ ሲሞክር ነው በቁጥጥር የዋለው።

(አፋር ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ወደ ትግራይ ክልል በህገወጥ መንገድ ሊያልፍ የነበረ ከ8ነጥብ 8ሚሊዮን ብር በላይ ጥሪ ገንዘብ በቁጥጥር ስር መወሉን የፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል። በሰርዶ የፍተሻ ጣቢያ የሚገኝው የፌዴራል ፖሊስ ፤ በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ይዞ በመጓዝ ላይ ከነበረ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ መኪና በህገወጥ መንገድ ሊያልፍ የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሪ ገንዘብ በቁጥጥር…
#ICRCEthiopia

" ካልተፈቀደው ገንዘብ እና እቃዎች ጋር ምንም ግንኙነት የለንም ፤ ድርጊቱንም እናወግዛለን " - ICRC

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ሰብአዊ እርዳታ በጫኑ ተሸከርካሪዎች ውስጥ ያልተፈቀደ ጥሬ ገንዘብ እና እቃዎች ማስተላለፍን አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

" በአፋር ክልል በሰርዶ ኬላ ጣቢያ ላይ አንድ በኪራይ የመጣ መኪና አሽከርካሪ ገንዘብ እና ሌሎች ያልተፈቀዱ ዕቃዎችን ሲያጓጉዝ የተገኘበት ሰብአዊ እርዳታ የጫነ ተሸከርካሪ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የህክምና እና የእርዳታ ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ በማጓጓዝ ላይ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑን አውቃለሁ " ብሏል የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ።

ያልተፈቀደው ገንዘብ እና እቃው በመደበኛው አሰራር ሰብአዊ እርዳታ በጫነው ተሸከርካሪ ላይ በተደረገው ፍተሻ በባለስልጣናት የተገኘ ሲሆን በኪራይ የመጣው መኪና አሽከርካሪም ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውሏል ሲልም አስረድቷል።

" የተከራየነው የንግድ መኪና አሽከርካሪ ሰብአዊ እርዳታውን በጣም ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ማጓጓዝ ላይ ብቻ ትኩረት መስጠት ይገባው ነበር " ያለው ኮሚቴው " ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከዚህ ያልተፈቀደ ገንዘብ እና እቃዎች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ ድርጊቱንም አጥብቆ ያወግዛል " ሲል ገልጿል።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በመላው ኢትዮጵያ በትጥቅ ግጭት እና በሌሎች ሁከቶች ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ለመከላከል እና መርዳትን ብቻ የሚፈልግ የሰብአዊ ድርጅት መሆኑም ገልጾ ይህ በኪራይ ያመጣው የከባድ መኪና አሽከርካሪ ያጋጠመው ኹነት በሰብአዊ ተግባሩ እና በአስፈላጊ እርዳታዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር እየሰራ መሆኑ አሳውቋል።

ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሙሉ በሙሉ በትብብር እየሰራ ስለመሆኑ አስረድቷል።

@tikvahethiopia