TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሽልማት

በኦሪጎን 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎ ከዓለም ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን የተሰጠው ሽልማት ዝርዝር ፦

በቡድኑ በልዩ ልዩ ስራ ላይ የተሳተፉ ፦

- አቶ ቃሲም ገመዳ የብሄራዊ ቡድኑ ወጌሻ ፦ 50 ሺህ ብር
- ወ/ሮ ቅድስታ ታደሰ ረዳት ሀኪም ፦ 75 ሺህ ብር
- ዶ/ር አያሌው ጥላሁን የብሄራዊ ቡድኑ ሀኪም ፦ 85 ሺህ ብር
- አቶ ከተማ ይፍሩ ኦፊሻል አባል ፦ 50 ሺህ ብር
- ወ/ሮ ማስተዋል ሞላልኝ ፦ 50 ሺህ ብር
- አቶ ስለሺህ ብስራት የኮሚኒኬሽን ጉዳይ መሪ ፦ 75 ሺህ ብር
- አቶ ዮሐንስ እንግዳ ፦ 85 ሺህ ብር ተሸላሚ
- ዶ/ር በዛብህ ወልዴ የስራ አስፈፃሚ አባል ፦ 85 ሺህ ብር
- አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ ምክትል የቴክኒክ ቡድን መሪ ፦ 85 ሺህ ብር
- አቶ አስፋው ዳኜ የቴክኒክ ቡድን መሪ ፦ 100 ሺህ ብር
- ኮ/ር ማርቆስ ገነቴ ምክትል ቡድን መሪ ፦ 85 ሺህ ብር

የአትሌቶች አሰልጣኞች ፦

- አብዮት ተስፋዬ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሙሉቀም ፍቅሬ ፦ 50 ሺህ ብር
- ወንድዬ ደሳለኝ ፦ 50 ሺህ ብር
- ጌታነህ ተሰማ ፦ 50 ሺህ ብር

(ያሰለጠኗቸው አትሌቶች ዲፕሎማ ያገኙ)

- አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ ፦ 75 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ሀብታሙ ግርማ ፦ 75 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ብርሃኑ መኮንን ፦ 75 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ንጋቱ ወርቁ ፦ 75 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ኢሳ ሸቦ ፦ 75 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ ፦ 75 ሺህ ብር

(ያሰለጠኗቸው አትሌቶች ሜዳሊያ ያገኙ)

- አሰልጣኝ ኢብራሂም ዳኜ ፦ 100 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ደቻሳ ኃይሉ ፦ 100 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ከፍያለው አለሙ፦ 150 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ስንታየሁ ካሳሁን ፦ 150 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ይረፉ ብርሃኑ ፦ 150 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ፦ 200 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ ፦ 200 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ኃይሌ እያሱ ፦ 200 ሺህ ብር
- አሰልጣኝ ህሉፍ ህይደጎ ፦ 300 ሺህ ብር

አትሎቶች ተሳትፎ ያደረጉ ፦

(10 ሺህ፣ 800 ሜትር ፣ 3000 መሰናክ፣ 5000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ ማራቶን)

- ታደሰ ወርቁ ፦ 50 ሺህ ብር
- እሸቴ በክሬ ፦ 50 ሺህብር
- ጌትነት ዋለ ፦50 ሺህ ብር
- ሳይፋ ቱራ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሰለሞን ባረጋ ፦ 50 ሺህ ብር
- ድርቤ ወልተጂ ፦ 50 ሺህ ብር
- ፍሬወይኒ ኃይሉ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሂሩት መሻሻ ፦ 50 ሺህ ብር
- ኤርሚያስ ግርማ፦ 50 ሺህ ብር
- ሃብታም አለሙ ፦ 50 ሺህ ብር
- ጫሉ ዲቦ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሌሊሳ ዴሲሳ ፦ 50 ሺህ ብር
- አባብል የሻነው ፦ 50 ሺህ ብር
- ጥላሁን ኃይሌ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሙክታር እድሪስ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሂሩት መሸሻ ፦ 50 ሺህ ብር
- ኤርሚያስ ግርማ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሃብታም አለሙ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሲምቦ አለማየሁ ፦ 50 ሺህ ብር
- ኃይለማርያም አማረ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሳሙኤል አባተ ፦ 50 ሺህ ብር
- አክሱማዊት እምባዬ ፦ 50 ሺህ ብር
- ሳሙኤል ተፈራ ፦ 50 ሺህ ብር
- ጫሉ ቴሶ ፦ 50 ሺህ ብር
- አባብል የሻነው ፦ 50 ሺህ ብር
- እሸቴ በክሬ ፦ 50 ሺህ ብር

(ዲፕሎማ ያገኙ)

- ዮሚፍ ቀጀልቻ ፦ 150 ሺህ ብር
- ታደሰ ለሚ ፦ 150 ሺህ ብር
- ቶለሳ ቦደና ፦ 150 ሺህ ብር
- ቦሰና ሙላት ፦ 150 ሺህ ብር
- በሪሁ አረጋዊ ፦ 150 ሺህ ብር
- እጅጋየሁ ታየው ፦ 150 ሺህ ብር + ለቡድን ስራ 500 ሺህ ብር
- ጌትነት ዋለ ፦ 150 ሺህ ብር

(ነሃስ እና ከዛ በላይ)

- ዳዊት ስዩም ፦ 700 ሺህ ብር
- መቅደስ አበበ ፦ 700 ሺህ ብር
- ወርቀውሃ ጌታቸው ፦ 1 ሚሊዮን ብር
- ለሜቻ ግርማ ፦ 1 ሚሊዮን ብር
- ሞስነት ገረመው ፦ 1 ሚሊዮን ብር

ወርቅ ያመጡ አትሌቶቻችን !

- ለተሰንበት ግደይ (1.5 ሚሊዮን ብር + 500 ሺህ ብር ለቡድን ስራ )
- ጉዳፍ ፀጋይ (2.5 ሚሊዮን ብር - ሁለት ሜዳሊያ በማምጣቷ)
- ታምራት ቶላ (1.5 ሚሊዮን ብር + 250 ሺህ ብር ሪከርድ በመስበሩ)
- ጎተይቶም ገብረስላሰ (1.5 ሚሊዮን ብር + 250 ሺህ ብር የሻምፒዮናውን ሪከርድ በመስበሯ)

(ልዩ ሽልማት)

- የኢትዮጵያ አትሌቲክሥ ፌዴሬሽን ፕ/ት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፦ 40 ግራም የአንገት ሃብል
- የቡድን መሪ አቶ ተፈራ ሞላ ፦ 100 ሺህ ብር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ደራርቱ_ቱሉ

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በብሄራዊ ቤተመንግስት ከተናገረችው ፦

" እንደምናውቀው የትግራይ አትሌቶች ቤተሰብ የማግኘት እድል አሁንም አላገኙም ክብርት ፕሬዜዳንታችን በእርግጠኝነት ይሄንን ነገር ይቀርፋሉ ብዬ ገምታለሁ፤ መንግስታችን ይሄን ነገር ይቀርፋል ብለንም እናስባለን።

ምክንያቱም ደስታችን እውን እንዲሆን ለሚቀጥለው በሙሉ ልብ እንድንሰለፍ አትሌቶች አሉን እዛ ፣ ትግራይ አትሌቶች አሉን አልመጡልንም እዛ ባሉበት ስራቸውን እንዲጀምሩ፣ አስፈላጊ አትሌቶች እዚህ እንዲመጡ አስፈላጊውን ነገር ደግሞ መንግስት ለእነዚህ አትሌቶች መንገድ ከፍቶ ፣ መሰረታዊ ነገሮች ብዙ አሉ እሱን መንግስት ያውቀዋል እነዛ ሁሉ ነገሮች እንዲሆኑልን ከጣም እንፈልጋለን መንግስታችንን በትህትና እንጠይቃለን።

በእርግጥ መንግስታችን ፈቅዶ ምናልባትም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካልፈቀደ ስለማይሆን በእርግጠኝነት የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም ይሄን ከግምት አስገብቶ እነዚህ አትሌቶች ቤተሰባቸውን የሚያገኙበት ሁለቱ መንግስቶች የሚመለከታቸው አካላት ይሄን ያደርጋሉ ብዬ ነው የማስበው። "

@tikvahethiopia
#ሽልማት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሽልማት (በካቢኔ ውሳኔ) ፦

🇪🇹 ለመላው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን 10 ሚሊዮን ብር

🇪🇹 የወርቅ ቅብ ሰሃን " እናመሰግናለን " የሚል ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ

🇪🇹 አትሌት ዳዊት ስዩም 250 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት መቅደስ አበበ 250 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው 350 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ለሜቻ ግርማ 350 ካሬሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ሞስነት ገረመው 350 ካሬሜትር መሬት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሽልማት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሽልማት (በካቢኔ ውሳኔ) ፦ 🇪🇹 ለመላው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን 10 ሚሊዮን ብር 🇪🇹 የወርቅ ቅብ ሰሃን " እናመሰግናለን " የሚል ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ 🇪🇹 አትሌት ዳዊት ስዩም 250 ካሬሜትር መሬት 🇪🇹 አትሌት መቅደስ አበበ 250 ካሬሜትር መሬት 🇪🇹 አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው 350 ካሬሜትር መሬት 🇪🇹 አትሌት ለሜቻ ግርማ 350…
#ሽልማት

ወርቅ ያመጡ አትሌቶች #በአዲስ_አበባ 500 ካሬ ሜትር የመሬት ስጦታ ተበረከተላቸው። ሶጣታው የተበረከተው በከተማው አስተዳደር ካቢኔ ውሳኔ ነው።

🇪🇹 አትሌት ለተሰንበት ግደይ 500 ካሬ ሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ጎተይቶም ገ/ስላሰ 500 ካሬ ሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ታምራት ቶላ 500 ካሬ ሜትር መሬት

🇪🇹 አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ (ልዩ ተሸላሚ) 500 ካሬ ሜትር መሬት እና ወርቅ ቅብ " እናመሰግናለን " የሚል ስጦታ

@tikvahethiopia
የሰላም ድርድሩ መቼ ይጀመር ይሆን ?

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ድርድር እንዲቋጭ ከፍተኛ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል።

በፌዴራል መንግሥት እንዲሁም በህወሓት በኩል ለሰላም ድርድር ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸው በርካቶች ሰላም ይሰፍናል የሚል ትልቅ ተስፋን አሳድሮባቸዋል።

በሁለቱም በኩል ተደራዳሪዎች መሰየማቸው ከተሰማ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን መቼ ድርድሩ ይጀምራል የሚለው ትክክለኛ መልስ አላገኘም።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ሞሊ ፊ ግን የሰላም ንግግሩ በነሐሴ ወር ሊጀመር ይችላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ፊ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሽምግልና ለመፍታት ቁልፍ ሚና አላት ባሏት #ኬንያ ውስጥ በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ድርድሩ እንደሚጀመር ጥንቃቄ የተሞላበትን ተስፋቸውን ለአገራቸው ም/ቤት ኮሚቴ መናገራቸውን AFP ፅፏል።

በኬንያ ሊካሄድ የተቃረበው ምርጫ በድርድሩ የጊዜ ሰሌዳ ላይ መዛባትን ሳይፈጥር እንዳልቀረ ገልጸዋል።

ኬንያ ነሐሴ 3/2014 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

በሌላ በኩል በተለያዩ አገራት ጉብኝታቸውን የጀመሩት አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር "ድርድሩ ወደፊት እንዲራመድ አሜሪካ ምን ማድረግ እንደምትችል ከሁለቱም ወገኖች ጋር ይወያያሉ" ሲሉ ሞሊ ፊ ለኮሚቴው ተናግረዋል።

በተጨማሪ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ #ከአጎዋ መታገድን እያጤነው መሆኑን ተናግረዋል።

የጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ አንጻር ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለማድረግ የተሻለ ሁኔታ መኖር አለመኖሩን " በቅርበት እያጤነ ነው " ሲሉ ፊ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ፦ telegra.ph/AFP-07-29

@tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር

" ፈተናው የሚቀር አይደለም " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

* ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎቻችሁን አዘጋጁ !

የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም መሰጠት ይጀምራል። ይህን በተመለከተ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ ከሰጡት ማብራሪያ ፦

" ... በሙሉ አቅማችን እየተዘጋጀን ነው። የሚቀር ነገር አይደለም ፤ 2015 ትምህርት ዘመን ማብቂያ ላይ ፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብሎ ዲግሪ የሚሰጥበት ነገር ሀገሪቱን በጣም ክፉኛ ጎድቷታል የሚል እምነት አለን።

ይሄንንም ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች ጋር፣ ከግል ኮሌጆች ፕሬዜዳንቶች እና ኃላፊዎች ባለቤቶች ጋር ፣ ከዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግንበት ነው።

ይሄ አዲስ ሀሳብ አይደለም አተገባበሩ ነው አዲስ የሆነው። ከዚህ በፊት ተሞክሮ ተቃውሞ ስለንበር ነው የተተወው።

የህግና የህክምና ትምህርቶችን ብቻ እንዲሰጡት አድርጎ አሁንም እየተሰጡ ሌሎች በሙሉ ተትተው ነበር።

አሁን ግን በአጠቃላይ ከከፍተኛ ትምህርት ጥራት ችግር ጋር በተገናኘ ምንም ልንወጣው የማንችለው እና ያን ጥራት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲዎቹ በራሳቸው ባስተማሩበት እና እራሳቸው በሰጡት ፈተና ብቻ የሚለኩበት ሁኔታ ከጀርባው ያለ ጠንካራ የሞራል መሰረት ይጠይቃል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እራሳቸው ድግሪ ስንሰጥ ለማህበረሰቡ ይሄ ሰው እንዲህ እንዲህ አይነት ትምህርቶችን፣ እውቀቶችና ክህሎቶች አሉት ብለን ነው እየነገርን ያለነው።

... ከዚህ በፊት አንዱ የነበረው ችግር ማሳለፍ የሚባል ነገር አለ። ዝም ብሎ ማሳለፍ ምክንያቱም ተማሪዎች ከወደቁ የትምህርት ክፍሉን ድክመት ያሳያል እየተባለ ሲሳራበት የነበረው ነገር ምን ያህል ሀገሪቱን እንደጎዳት አሁን ለውይይትም የሚቀርብ አይደለም።

እኔ በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሰባት (7) ወራት በትምህርት ዘርፍ ከሚሰሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች የግል ኮሌጆች ባለቤቶች እንደዚህ አይን ያወጣ የለም መሆን የለበትም የሚል ክርክር አልሰማሁም። ሁሌ የሚሰማው ለምን በኛ ጊዜ ? ለምን ባንተ ጊዜ ለምን በሌላውስ ሰው ጊዜ የሚለውን ልትመልስ አትችልም ይሄ ዝም ብሎ ደረቅ ክርክር ነው።

በአንድ በሆነ ጊዜ መጀመር አለበት ምክንያቱም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ላይ እየደረሳ ያለው ጉዳት ሀገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ነው። ይሄንን ዝም ብለን ማለፍ አንችልም ብለን እየሄድንበት ነው።

ለተማሪዎችም ፣ ለወላጆችም፣ ለቤተሰብም አንድ (1) ዓመት የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተናል። ለኮሌጆችም ተማሪዎቻቸውን እንዲያዘጋጁበት ጊዜ ሰጥተናል ይሄን ጊዜ በደንብ ተጠቅመው ስራቸውን መስራት አለባቸው።

ይሄ የመውጫ ፈተና የተማሪዎች ፈተና ብቻ አይደለም። ከተማሪዎች በላይ የትምህርት ክፍሎች፣ የኮሌጆች ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ፈተና ነው። ምን እያደረጉ ነው ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚለውን እንደትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ የምናገኘው ፤ እነዚህ ኮሌጆች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በእርግጥም ተማሪዎችን እያበቁ ነው ? ወይስ የዲግሪ ወፍጮ ቤት እንደሚሏቸው ዝም ብሎ ጊዜ እያስቆጠሩ ድግሪ የሚሰጡ ናቸው የሚለውን የምንለይበት ነው።

ስለዚህ የሚቀር አይደለም። ሁሉም እንደማይቀር አውቆ የተሰጠውን የመዘጋጃ ጊዜ በደንብ ተጠቅሞ ትምህርትን በደንብ አስተምሮ በደንብ አስጠንቶ ቢያዘጋጅ ነው የሚሻለው "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሰላም ድርድሩ መቼ ይጀመር ይሆን ? የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ድርድር እንዲቋጭ ከፍተኛ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል። በፌዴራል መንግሥት እንዲሁም በህወሓት በኩል ለሰላም ድርድር ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸው በርካቶች ሰላም ይሰፍናል የሚል ትልቅ ተስፋን አሳድሮባቸዋል። በሁለቱም በኩል ተደራዳሪዎች መሰየማቸው ከተሰማ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን መቼ ድርድሩ ይጀምራል የሚለው ትክክለኛ መልስ አላገኘም።…
ፎቶ ፦ ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ በኢትዮጵያ አሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰንም ተገኝተው ነበር።

Photo Credit : የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት በአዲስ አበባ ከተማ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ። ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ፦ - የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ - የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ አቶ ስመኘው አባተ - የሶፍትዌር ባለሙያዎች ፦ • ሀብታሙ…
#ችሎት #Update

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ።

ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች የነበሩ ናቸው።

ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ የአዲስ አበባ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምከትል ኃላፊ አቶ አብርሃም ሰርሞሎ ይገኙበታል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዛሬው ውሎው " ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተገንዝበናል " ብሏል።

" የወንጀሉ ውስብስብነት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመስጠት ምክንያታዊ ነው " ያለው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ፤ በዚህም መሰረት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ለመርማሪ ፖሊስ መፈቀዱን ማስታወቁን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia