TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው ጉዳፍ ፀጋይ - በውድድሩ ላይ እና ከውድድሩ መጠናቀቅ በኃላ የተወሰዱ ፎቶዎች።

Photo Credit : GettyImages

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፤ ትላንት ባካሄደው ጉባኤ መጅሊሱን ለቀጣዮቹ 4 አመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫ መካሄዱን በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።

ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ፕሬዜዳንት፣ ሸይኽ አብዱልከሪም በድረዲን ተ/ም/ፕሬዜዳንት እና አብዱልዐዚዝ አብዱልወሌ ምክትል ፕሬዜዳንት፣ ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ ዋና ፀሀፊ ሆነው መመረጣቸውን ጠቅላይ ም/ቤቱ አሳውቋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ቱፋ ከምርጫው በኃላ ባሰሙት ንግግር የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለማስጠበቅ በትኩረት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

ትላንት ከተካሄደው ጉባኤ በኃላ አዲስ የተመረጡ አመራሮች በይፋ ስራ መጀመራቸውን ያበሰሩ ሲሆን ከቀድሞው የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ጄይላን ከድር እጅ የፅ/ቤቱን ቁልፍ መረከባቸውን ምክር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

ትላንት በነበረው ርክክብ ወቅት እና በጉባኤው ላይ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ ሌሎችም አባቶች እንዳልተገኙ ለማወቅ ተችሏል። ከትላንት ምርጫ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ወገኖች ቅሬታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ከጉባኤው አንድ ቀን ቀደም ብሎም በተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ የተመራ ስብሰባ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን በዚሁ ገባኤ ላይ በትላንትናው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ባወጡት መግለጫ አሳውቀው ነበር።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ችግሮች ከተስተካከሉ ለውይይት፣ ለመፍትሄ ፣ለሰላም ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን መንግስት ያለውን ችግር በአስቸኳይ እንዲያስተካክል ፤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ዑለማውን እና የሃይማኖት አባቶችን ቀርበው እንዲያነጋግሩ እና ችግሩ እንዲያወያዩ ጠይቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/EIASC-07-19

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት📣 ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የፀጥታ ችግር ! ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ከአጣዬ አካባቢ ፦ " እንደ ሁል ጊዜው ሁሉ አጣዬ ከተማ ዳግም ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ውስጥ ገብታለች። ይሄም የሆነው በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ ነው። ትላንት ማለትም በ02/11/2014 " የቤት እንሰሶች የተዘራ ሰብልን በሉብን " በማለት ልዩ ቦታው…
#Update

" 4 የፖለቲካ አመራሮች እና አንድ የፖሊስ አመራር ላይ እርምጃ ተወስዷል " - አቶ ጀማል ሀሰን

ከጥቂት ቀናት በፊት በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት ማብረድ የተቻለ ሲሆን ችግሩን መከላከል አልቻሉም በተባሉ ላይ እርንጃ እየተወሰደ ነው።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የህዝብን ሰላም፣ ደህንነት አላረጋገጡም ባላቸው አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል።

የብሄረሰብ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ሀሰን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " አምስት አመራሮች ላይ እምርጃ ተወስዷል። አራቱ የፖለቲካ አመራሮች ናቸው አንድ የፖሊስ አመራር ደግሞ በህግ ተጠያቂ እንዲሆን በቁጥጥር ስር አውለናል " ብለዋል።

ፖሊሶች አስፈላጊውን እርምጃ ወስደው ጉዳዩን ማብረድ ይችሉ ነበር ከስምሪት እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተገምግሞ በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ተሰርቷል ሲሉ ገልፀዋል።

እየተወሰደ ያለው እምርጃ እስከ ታች ቀበሌ እንደሚደርስም ገልፀዋል።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ምክትላቸው እንዲሁም ሁለት የወረዳው የድርጅት አመራሮች የፖለቲካ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልፀው ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/VOA-07-19

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Peace የተደራዳሪ ቡድኑ ! የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት #በሰላም_ድርድር እንዲፈታ ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙ ተረጋግጧል። የቡድኑ አባላት ፦ 1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን ➡️ ሰብሳቢ 2ኛ. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ➡️ አባል 3ኛ. አቶ ተመስገን ጥሩነህ ➡️ አባል 4ኛ. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ➡️
#Update

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ የፌዴራል መንግስት የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መቋቋሙ ይታወሳል።

የተደራዳሪ ቡድን አባላቱም ይፋ መደረጋቸው አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት ተደራዳሪ ቡድን ማቋቋሙን ገልጿል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል በሰጡት ቃል ፤ ለድርድር የሚሆን ልዑክ ወደ #ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ እንሆናለን ብለዋል።

በከፍተኛ ሥልጣን ደረጃ የሚገኙ አባላት ያሉት ኮሚቴም ተቋቁሟል ሲሉ አሳውቀዋል።

ተደራዳሪ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ እንዲሁም ቁጥራቸውን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር የሚደረገው ምንም አይነት ድርድር ሊመራ የሚችለው በአፍሪካ ኅብረት ብቻ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፣ የህወሓት አመራሮች ድርድሩ በኅብረቱ ጥላ ስር ብቻ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።

" ሁሉንም የድርድር ሂደቶች ለአፍሪካ ኅብረት መስጠቱ ለእኛ በጣም ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ማንኛውም ድርድር በሰላም ጥረት ውስጥ ንቁ ሚና የተጫወቱትን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ማካተት አለበት " ብለዋል።

መረጃው የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ /ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
" ተዘርፈናል አፋልጉን "

የማየትና መስማት የተሳናቸው ህጻናት ለትራንስፖርት የሚገለገሉበት መኪና ተሰርቋል።

የኢትዮጵያ ማየትና መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር ማየትና መስማት በተሳናቸው ሰዎች የተቋቋመ ማኅበር ነው።

ማየትና መስማት የተሳናቸው ሰዎች በአካል ጉዳታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን እንግልትና ተፅእኖ ለመቀነስ፣ እንዲሁም ማየትና መስማት የተሳናቸውን ህጻናትና ሴቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና እና የሙያ ስልጠና በመስጠት እራሳቸውን እንዲችሉ እየተንቀሳቀሰ ያለ ማኅበር ነው።

ማኅበሩ ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከባድ የሆነ ዝርፊያ ተፈጽሞበታል።

በዚህ የዝርፊያ ወንጀል ማህበሩ ሲገለገልበት የነበረው 1 ሚኒባስ መኪና ኮድ 5 AA 02363 ነጭ ቶዮታ ተሰርቋል።

ሁለተኛው መኪና የቶዮታ ላንድ ክሩዘር 4 ጎማዎች ከነቸርኬያቸው ፈተው - መኪናውን በድንጋይ አንተርሰው ሄደዋል። የቢሮ መስኮቶች ተሰብረው ኮምፒውተር߹ እስካነር ያለው ፕሪንተር፣ 1 ፎቶ ኮፒ ማሽን ተውስዷል።

አፋልጉን፦
+25111 126 7600
+25111 126 7880
0911108984 ሮማን መስፍን
0924450267 እየሩሳሌም
0913587910 ቤተልሄም

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የአማራ መልሶ ማቋቋም እና ልማት ድርጅት (አመልድ) በአዲስ አበባ ከተማ ለገሃር አካባቢ ያስገነባውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ግዙፍ ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት እንደሚፈልግ አስታውቋል።

ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ማግስት ከሃምሌ 11/2014 ዓ.ም እስከ ሃምሌ 22/2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል።

ተጫራቾች የሚከራዩ ክፍሎችን ዓይነትና ስፋት ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ እንዲሁም ህንጻው በሚገኝበት ለገሃር የአማራ ባንክ ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

ዝርዝር መረጃ https://telegra.ph/አመልድ-07-19

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሳዑዲ_አረቢያ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሪያድ የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን እቃዎች ከሱቆች እና ከመደብሮች እየሰብሰበ ይገኛል። የሳዑዲ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃል በሚል የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን አሸንጉሊቶች፣ ቲሸርቶች፣ የጸጉር ማስያዣዎች፣ ኮፊያ፣ እና የእርሳስ መያዣወችን ከየመደብሩ እንዲሰበሰቡ እያደረገ ነው። የሀገሪቱ መንግስት ህፃናትን ለመጠበቅ ሲል " መርዛማ መልዕክት…
" እኛ የሙስሊም ሀገር ነን። ባህሎች እና ወጎች አሉን እናም እስልምና እነዚህን ድርጊቶች (የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን) ይከለክላል " - አል ሃማሚ

ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል እንዲሆንና ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንዲጣል እየሰራች መሆኗን አሳውቃለች።

የኢራቅ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚከለክል ህግ ለማፅደቅ ማቀዱን አስታውቋል።

ኢራቅ በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሶስት ብዙ አረቦች ከሚኖሩበት ሀገር መካከል አንዷና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #በግልፅ ወንጀል እንደሆነ ካላወጁ ሀገራት የምትጠቀስ ናት፤ ሌሎቹ ጆርዳን እና ባህሬን ናቸው።

ምንም እንኳን በግልፅ ወንጀል ነው ተብሎ ባይገለፅም ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ እጅግ በጣም የተወገዘ ነው።

አሁን ያለው ሁኔታ ያላማራት ኢራቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል እንደሆነ በህግ ለመደንገግ እየሰራች ሲሆን ህጉ ከወጣ ኢራቅ ሌሎች ድርጊቱን በህግ ወንጀል እንደሆነ ካፀደቁ ሀገራት ተርታ ትሆናለች።

አብዛኛዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በቀጥታ በግልፅ የሚከለክሉ እና ወንጀል ነው ያሉ ሲሆን ከገንዘብ ቅጣት እስከ እስራት ፤ ሳውዲ አረቢያ ደግሞ #የሞት_ቅጣት ትቀጣለች።

በኢራቅ ፓርላማ የህግ ኮሚቴ ውስጥ ያሉት የፓርላማ አባል አሬፍ አል ሃማሚ ለDW በሰጡት ቃላቸው ፥ " አዲሱ ህግ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያላቸውን በወንጀል ተጠያቂ ያደርጋል ፤ በእነሱ ላይም ከባድ ቅጣት ይጥላል " ብለዋል።

ህጉ እስካሁን ድምጽ ያልተሰጠበት ሲሆን ድምፅ እንዲሰጥበት እየተሰራ ነው።

አል ሃማሚ ፤ ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ #የሰብአዊ_መብት_ተሟጋች_ድርጅቶች ትችት ቢሰነዘርም ህጉ ይፀድቃል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ያንብቡ telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-19

@tikvahethiopia