TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Congratulations !

ዛሬ ቅዳሜ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን አስመርቀዋል።

በዚህም ፦

• አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 👉 5 ሺህ 58 ተማሪዎችን

• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 👉 ከ4 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን

• ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ 👉 1 ሺህ 167 ተማሪዎችን

• እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ 👉 974 ተማሪዎችን

• ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ 👉 ከ1 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን

• ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 👉 1 ሺህ 458 ተማሪዎችን

• ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ 👉 1 ሺህ 766 ተማሪዎችን፣

• ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፦ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ 👉 8 ሺህ 236 ተማሪዎችን አስመርቀዋል።

መላው ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንኳን ለዚህ አበቃችሁ፤ የድካችሁን ውጤት እንድታዩ እንኳን ፈጣሪ ረዳችሁ፡ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AhaduBank አሐዱ ባንክ ሐምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል። ይህ አስመልክቶ ባንኩ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ ፤ 10 ሺህ በሚደርሱ ባለአክሲዮኖችንና በ564 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል እና በ702 ሚሊዮን በተፈረመ ካፒታል ተዋቅሯል ብለዋል። ሀላፊው እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም የቅርንጫፎቹን ብዛት 50 እደሚያደርስም ተናግረዋል።…
ፎቶ ፦ አሐዱ ባንክ በዛሬው ዕለት በይፋ ስራውን ጀምሯል።

በ17 አደራጅ ኮሚቴ አባላትና 10 ሺ የሚደርሱ ባለአክሲዮኖችን ያሰባሰበውን በ564 ሚሊዮን የተከፈለ እና በ702 ሚሊዮን የተፈረመ የተዋቀረዉ የአሐዱ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ባለአክስዮኖች፥
የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት፥ በተገኙበት ፍላማንጎ በሚገኘዉ ዋና ቅርንጫፋ ተመርቋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ እንደተናገሩት ባንኩ ገና ከጅምሩ በጥሩ አጀማመር አዳዲስ የቴክኖሎጂችን ይዞ የመጣና ደንበኞች ካሉበት ሆነው ራሳቸው ደንበኛ የሚያደርጉበት የቴክኖሎጂ አሰራር ማዘጋጀቱ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አትተነህ ሰብስቤ በበኩላቸው ዘመኑን የዋጀ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የኢትዮጵያውያን የምጣኔ ሀብት አሻራ ማሸረፍን ተልዕኮ በማድረግ ወደ ፈይናስ ሴክተሩ የገባው አሐዱ ባንክ በ 2025 ዓ/ም በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ መሪ የመሆን ራዕይ አንግቧል ይህን ለማሳካትም በዘመኑ ቴክኖሎጂ የተደራጀ አገልግሎት እደሚሰጥም ገልፀዋል።

ከሀምሌ 2 እስከ ሀምሌ 7 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ማህበራዊ ክንውኖች ሲያደርግ የቆየው ባንኩ በመጨረሻም የቅዱስ ላሊበላ ገደም የዕድሳት ስራን ለመደገፍ የ500 ሺህ ድጋፍ አከናውኗል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና ጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሕክምናቸውን አጠናቀው ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር አስታውቋል። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ክሊቭላንድ ክሊኒክ ሆስፒታል…
#Update

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ፣ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዱባይ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ወደ እናት አገራቸው በሰላም ተመልሰዋል ሲል የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ዛሬ አሳውቋል።

በቅርቡም ጤናቸው በተሟላ ሁኔታ ተስተካክሎ ወደ አገልግሎትና የቢሮ ስራቸው እንደሚመለሱ እምነታችን ጽኑዕ ነው ሲልም ገልጿል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የኢትዮጵያ ኮንሥትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የገነባው ባለ አራት ፎቅ የጋራ መኖሪያ ቤት ለ19 ቤተሰቦች መተላለፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ቤቱ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች የተላለፈ ሲሆን ቤቱ የተላለፈላቸው 19 ቤተሰቦች የጋራ መኖሪያ ህንጻው በተገነባበት ስፍራ የነበሩ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ቤቶቹ ስቱድዮ፣ ባለ አንድ መኝታ፣ ባለሁለት መኝታ የያዙ ሲሆን በይፋዊ ዕጣ ማውጣት ስነስርዓት መተላለፋቸው ተገልጿል።

አጠቃላይ ያሉት ቤቶች 29 ሲሆኑ ዛሬ ያልተላለፉ በቀጣይ ለዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍሎች ይተላለፋሉ ሲል የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለነገ ስኬትዎ ከብርሃን ባንክ ጋር ዛሬ ይቆጥቡ!

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc

Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc

Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
• " የረሃብ አደጋው ስጋት ተቀልብሷል " - የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP)

• " የረሃብ አደጋ ተቀልብሷል የሚለው አባባል ኃላፊነት የጎደለው ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል አንዣቦ የነበረው የረሃብ አደጋ ስጋት መቀልበሱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለጸ።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይህን ያለው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ መቻሉን ተከትሎ ነው።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኃላፊ ኤድሪያን ቫንዳክናብ ለቢቢሲ ከተናግሩት ፦

" የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ በመቻሉ፤ በትግራይ ክልል ተከስቶ የረሃብ አደጋው ስጋት ተቀልብሷል።

ይህ ማለት ግን ሁኔታዎች በዚህ ሁኔታ ይቀጥላሉ ማለት አይደለም።

አሁን ያለልው ሁኔታ እንዲቀጥል ለሰብዓዊነት ሲባል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ እንዲደርስ ስላስቻለን፤ ይህ መቀጠል አለበት።

ለ2.1 ሚሊዮን ሰዎች ምግብ ለማድረስ ታቅዶ ለ1.1 ሚሊዮን ሰዎች ደርሷል።

ጥሩ እና መጥፎ ዜናዎች አሉ። ጥሩ ነገሩ፤ ለሰብዓዊነት ሲባል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት እየተከበረ ነው። ይህም የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ ለሚያሻቸው ሰዎች ምግብ እና መሠረታዊ ቁሶችን ማድረስ አስችሏል።

የፀጥታ ሁኔታ፣ የተጨማሪ ፈንድ ጉዳይ እና የነዳጅ አቅርቦት ግን በእርዳታ አቅርቦት ሥራው ላይ አሳሳቢ ሆነው ቀጥለዋል። "

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/WFP-07-16

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ WFP በራሱ በመጋዘኑ ያለውን ድጋፍ በነዳጅ እጥረት ችግር ላይ ላሉ ለማድረስ መቸገሩን ይቀበለዋል ፤ የረሃብ አደጋን መቀልበስ ተችሏል የሚለው አባባል ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ጋዜጠኛ አላዛር ተረፈ ከታሰረ 3ኛ ቀኑን እንደያዘ ባለደረቦቹ ገልፀዋል።

" ወለጋ ላይ አማራ ተጨፍጭፏል የሚል ጹሑፍ ጽፈሃል፤ የስሪላንካን አመጽ ደግፈሃል፤ ችግኝ ተከላን ተቃውመሃል " በሚል የተጠረጠረው አላዛር ተረፈ ከታሰረ 3ኛ ቀኑን ይዟል።

ሀሙስ ዕለት ለጥያቄ እንፈልግሃለን የሚሉ ሁለት ክትትሎች ይዘውት ወደ ላምበረት ፖሊስ ጣቢያ ወስደውት ነበር።

በኋላም ቀበና ፍ/ቤት ቀርቦ በ5 ሺ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ቢወሰንም ፖሊስ ይግባኝ ጠይቆ ነበር።

ፖሊስ የጠየቀው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ በ5ሺ ብር ዋስትና እንዲወጣ የተወሰነው ውሳኔ ጸንቶ ነበር።

በመጨረሻም ጣቢያው እኛ ጋር ያለው ጉዳይ አልቋል ክ/ከተማ ግን ይፈልገዋል በሚል ክፍለ ከተማ ካደረ በኋላ 3ኛ ተወስዷል።

የስራ ባልደረቦቹ ፤ " በሚያሳዝን ሁኔታ ፍ/ቤት ከእስር እንዲለቀቅ የፈረደለትን ጋዜጠኛ ነው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወሰዱት " ብለዋል።

በቀን ሁለት ጊዜ ፍ/ቤት ቀርቦ የነበረው ጋዜጠኛው ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ከፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ ጣቢያ እየተንከራተተ ነው ሊሉም ገልፀዋል።

" የፍ/ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እየተሻረ ነው " ያሉቱ የስራ ባልደረቦቹ " አሁን ደግሞ ቤቱ ተፈትሾ ምንም አልተገኘም። ከዛም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሚሄድና እዛው እንደሚቆይ ነው የተነገረው " ሲሉ ያለውን ሁኔታ አስረድተዋል።

ጋዜጠኛ አልዓዛር የተባባሩት አረብ ኤሜሬትስ ሚዲያ የሆነው " አል አይን " የኢትዮጵያ የአማርኛ አገልግሎት ዘጋቢ ነው።

@tikvahethiopia
አይቀሬው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት እና የግብፆቹ ሚዲያዎች የፈጠራ ወሬ !

ሁሌ ጊዜም ሀገራችን የታላቁ ህዳሴውን ግድብ ባፋጠነች እና የውሃ ሙሌቱን በየዓመቱ ባከታተለች ቁጥር የግብፅ ሚዲያዎች እንቅልፍ ይነሳቸዋል።

በቅርቡ የሶስተኛው ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ ከወዲህ ያልተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ማሰራጨቱን አጥብቀው ተያይዘውታል።

አመር አዲብ የተባለ የሚዲያ ሰው በአንድ ቻናል ላይ ቀርቦ " በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ብዙ እምነት የለንም በግድቡ ላይ መሰነጣጠቆች እንዳሉ እና አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይነገራል " ሲል ያልተረጋገጠ መረጃ ሲናገር ተደምጧል።

" የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ አብዛኛው ሰው ረስቶታል። የህዳሴው ግድብ ሶስተኛው ሙሌት ሊጠናቀቅ ቀናት ቀርተዋል " ሲልም አክሏል።

የዚህን ሰው ንግግር ሚዲያዎች እየተቀባበሉት እያስጮኹ ነው ፤ በእርግጥ የግብፅ ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ፣ ምሁራን ከዚህም አለፍ ያሉ ብዙ የፈጠራ ወሬዎችን ሲያስወሩ ዓመታትን ያለፉ በሚሆንም በግንባታው ላይ ያመጡት ለውጥ የለም።

አሁንም ሶስተኛው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ የሚዲያ ዘመቻውን ተያይዘውታል።

#ItsMyDam🇪🇹

@tikvahethiopia