TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ !

የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፤ የክልልነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ጉዳዩን የአመጽና የሁከት መነሻ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በስሩ የሚገኙ ዞኖችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

ጌዲኦም በአዲስ መልክ ከሚዋቀሩ ዞኖች አንዱ ሲሆን፤ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በተጨባጭ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሰሞኑን የማወያያ ሰነዶች ተዘጋጅተው የዞኑ ነዋሪ እየመከረበት ነው።

ይሁንና የጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆን ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን የሚሉ አካላት በህቡዕ ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ በተጨባጭ ተረጋግጧል።

በህቡዕ የተደራጁት አካላት የጥፋት እቅዶቻቸውን ለማሳካት ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመክፈት የተዛቡና የፈጠራ መረጃዎችን እያሰራጩ ሲሆን ማኅበረሰቡንም በተሳሳቱ መረጃዎች ለማደናገር እየሞከሩ ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት ያደራጇቸው ግለሠቦችና ቡድኖች #ቤት_ለቤት ጭምር እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ፤ ይህም ባግብረኃይሉ ተደርሶበታል።

ለዚህ እኩይ ዓላማ የተደራጁና የተሰለፉ ግለሠቦችንና ቡድኖችን በደኅንነትና በጸጥታ መዋቅር አማካኝነት ተለይተው ክትትል እየተደረገባቸው ነው። ይህን በማስገንዘብ፤ ከጥፋት ተልዕኳቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።

ይህን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ እናስጠነቅቃለን። "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ።

ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው።

ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ2022/2023 በጀትና እቅድ ውይይትና ማጽደቅ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።

የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ውሎ ከድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውና ከፍተኛ የማኔጅሜንት አባላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሰራተኞች በተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ምላሽ ተሰቶባቸዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ለተለያዩ የሰራተኛ ተወካዮች ፣ የተመሰገኑ የስራ መሪዎችን የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጠ ሲሆን ፤ የአየርመንገዱ ሰራተኞች የማህበሩን ፕሬዝዳንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳን በማህበሩ ላስመዘገቡት ለውጥ ከፍተኛ ሽልማት እንዲሁም የአየር መንገዱን ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክቷል።

በሌላ በኩል ጉባኤው ታግዷል ፣ አልተካሄደም በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩት መረጃዎች ውሸትና አሉባልታ ናቸው ያለው ማህበሩ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ። ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው። ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ2022/2023…
#ተጨማሪ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤን በሚመለከት ቲክቫህ ኢትዮጵያ አንድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መመልከት ችሏል።

ይኸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠ ነው።

ትዕዛዙም ፤ " በኢትዮጵያ አየር መንግድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር በሆኑት በተጠሪ ጥሪ ተደርጎ በስካይ ላይት ሆቴል እየተከናወነ ያለ ጠቅላላ ጉባኤ ካለ ከዛሬ 8/11/2014 ዓ/ም 6:05 ጀምሮ ከዚህ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ ጠቅላላ ጉባኤው እንዳይከናወን ታዟል። የእግድ ትዕዛዝ ትዕዛዙ ለሚመለከታቸው ይድረስ " ይላል።

ትዕዛዙ የተሰጠው 4 የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፤ በተጠሪ የማህበሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ተሊላ ደሬሳ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ አማካኝነት ነው።

የማህበሩ ዋና ፀሀፊ ትላንት እና ዛሬ ጠቅላላ ጉባኤውን በስኬት መጠናቀቁን ያሳወቁ ሲሆን ዛሬ ምንም አይነት የእግድ ደበዳቤ እንዳልደረሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጉባኤው ታግዷል፣ አልተካሄደም በሚል የሚሰራጨው መረጃ ውሸት ነው ብለዋል።

ግለሰቦቹ የማህበሩን ንብረቶች በመበዝበዝ ላልተገባ ጥቅም በማዋላቸው የማህበሩ ምክር ቤት እና ጠቅላላ ጉባኤ ያባረራቸው እና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

4 ስራ አስፈጻሚ አባላት ጠቅላላ ጉባኤን ማገድ አይችልም ያለው ማህበሩ ፤ የማህበሩ ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅላላ ጉባኤው እንደሆነ መታወቅ አለበት፤ በዚህም መነሻነት ነው የሚመለከታቸው ከፍተኛ የድርጀቱ መሪዎች በጉባኤው ላይ የተገኙት ፤ ጉባኤው ስኬታማ ነበር ብሏል።

@tikvahethiopia
ሩዋንዳ - ቤቲንግ

ሩዋንዳ በሁሉም የሀገር ውስጥ ጨዋታዎች ላይ የስፖርት ውርርድን (ቤቲንግ) ከዛሬ ጀምሮ እንዲታገድ አድርጋለች።

ውሳኔውን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመስማማት ነው ያሳለፉት።

የስፖርት ሚኒስቴር ፤ ሩዋንዳ ውስጥ ላሉ ለሁሉም የስፖርት ቤቲንግ እና የኦንላይን ጌሚንግ ድርጅቶች እንዳሳወቀው ሌላ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በሀገር ውስጥ ውድድሮች ውርርድ (ቤቲንግ) ከዛሬ ጀምሮ እንዲቆም ብሏል።

ሚኒስቴሩ ኢንዱስትሪው በማች ፊክሲንግ / በእግር ኳስ አለም ውስጥ ለተቃራኒው ተገዝቶ የመስራት ውስልትና / ላይ ያለውን አደጋ የሚገመግም ሲሆን እስከዛው (ውርርድ) ቤቲንግ ታግዶ ይቆያል ተብሏል።

የሀገር ውስጥ ጨዋታ ሁሉንም ስፖርታዊ ውድድሮችን የሚመለከት ሲሆን የ1ኛ እና 2ኛ ዲቪዝዮን ሊግ እንዲሁም የወጣቶችን ውድድር የሚያካትት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia 🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትካፈልበት ተጠባቂው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ለሊት ይጀምራል። ዛሬ ለሊት አትሌቶቻችን ውድድራቸውን ያካሂዳሉ። በዚህም መሰረት :- - ሌሊት 9:15 :- የወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ 🇪🇹 ለሜቻ ግርማ 🇪🇹 ጌትነት ዋሌ 🇪🇹 ኃይለማሪያም አማረ - ሌሊት 10:10 :- የሴቶች 1,500 ሜትር ማጣርያ 🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን የሚሳተፉበት የኦሪጎን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት የ3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ እየተካሄደ ነው።

በመጀመሪያው ምድብ ፦ የሀገራችን ልጅ ጌትነት ዋለ 8.17.49 በመግባት 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። በምርጥ ሰዓት ወደ ፍፃሜው አልፏል።

በምድብ ሁለት ፦ አትሌታችን ለሜቻ ግርማ 8.19.63 በመግባት #አንደኛ በመሆን አጠናቋል በቀጥታም አልፏል።

በምድብ ሶስት ፦ ኃይለማርያም አማረ አንደኛ በመሆን አጠናቋል። ወደ ቀጣይ ዙር በቀጥታ አልፏል።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !!

ቲክቫህ ስፖርት : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
በቀጣይ --- 10:10 ላይ ! ጉዳፍ ፀጋይ ፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ ፣ ሂሩት መሸሻ የሚሳተፉበት የ1500 ሜትር የማጣርያ ውድድር ይካሄዳል። ድል ለሀገራችን ልጆች 🇪🇹 ❤️ ! @tikvahethiopia
ሂሩት መሸሻ አንደኛ ሆና አጠናቃለች።

በመጀመሪያ ምድብ የማጣሪያ ውድድር ሂሩት መሸሻ አንደኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ሂሩት ውድድሩን እጅግ በጣም በከፍተኛ ብቃት ነው ያጠናቀቀችው።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሂሩት መሸሻ አንደኛ ሆና አጠናቃለች። በመጀመሪያ ምድብ የማጣሪያ ውድድር ሂሩት መሸሻ አንደኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ሂሩት ውድድሩን እጅግ በጣም በከፍተኛ ብቃት ነው ያጠናቀቀችው። እንኳን ደስ አለን 🇪🇹 @tikvahethiopia
ፍሬወይኒ ኃይሉ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።

በሁለተኛው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ፤ ፍሬወይኒ ኃይሉ ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር አልፋለች።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹 ❤️ !

ቲክቫህ ስፖርት : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
ፍሬወይኒ ኃይሉ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች። በሁለተኛው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ፤ ፍሬወይኒ ኃይሉ ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር አልፋለች። እንኳን ደስ አለን 🇪🇹 ❤️ ! ቲክቫህ ስፖርት : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x @tikvahethiopia @tikvahethsport
ጉዳፍ ፀጋይ አንደኛ ሆና አጠናቃለች።

በሶስተኛው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ፤ ጉዳፍ ፀጋይ አንደኛ ደረጃ ይዛ በበላይነት አጠናቃለች።

ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር አልፋለች።

በ1,500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ሁሉም ሴት አትሌቶቻችን ፦

🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ፍሬወይኒ ኃይሉ
🇪🇹 ሂሩት መሸሻ በድንቅ ብቃት ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፈዋል።

ነገ ለሊት 11:05 ላይ #የግማሽ_ፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !

ቲክቫህ ስፖርት : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia @tikvahethsport
Congratulations !

ዛሬ ቅዳሜ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን አስመርቀዋል።

በዚህም ፦

• አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 👉 5 ሺህ 58 ተማሪዎችን

• ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 👉 ከ4 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን

• ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ 👉 1 ሺህ 167 ተማሪዎችን

• እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ 👉 974 ተማሪዎችን

• ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ 👉 ከ1 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን

• ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 👉 1 ሺህ 458 ተማሪዎችን

• ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ 👉 1 ሺህ 766 ተማሪዎችን፣

• ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፦ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ 👉 8 ሺህ 236 ተማሪዎችን አስመርቀዋል።

መላው ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንኳን ለዚህ አበቃችሁ፤ የድካችሁን ውጤት እንድታዩ እንኳን ፈጣሪ ረዳችሁ፡ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።

@tikvahethiopia