TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sudan #June30March

ዛሬ በሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ዛሬ #June30 በጎረቤት ሱዳን በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራውን ወታደራዊ ጁንታን በመቃወም ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በተቃውሞ ሰልፉ ወታደራዊው ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ እና የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም ይጠየቅበታል ነው የተባለው።

ተቃውሞውን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች የተለያዩ መንገዶችን ዘግተዋል። በተጨማሪ የፀጥታ ኃይሎች ሰልፍ የሚያስተባብሩትን አክቲቪስቶች እያደኑ እያሰሩ ነው ተብሏል።

የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኃላ በሱዳን ዜጎች የሚደርስበት ተቃውሞ እስካሁን የቀጠለ ሲሆን ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ ግፊት እየተደረገበት ይገኛል።

እስከዛሬ ድረስ በነበሩት ተቃውሞዎች የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች ብዙ ሰዎች ሞተዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan #June30March ዛሬ በሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ዛሬ #June30 በጎረቤት ሱዳን በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራውን ወታደራዊ ጁንታን በመቃወም ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። በተቃውሞ ሰልፉ ወታደራዊው ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ እና የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም ይጠየቅበታል…
ሱዳን ኢንተርኔት ዘጋች።

ሱዳን ዛሬ ሀሙስ ከሚካሄደው ታላቁ የ #June30 የተቃውሞ ሰለፍ ጋር በተያያዘ ከጥዋት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጣለች።

የኢንተርኔት ጉዳይን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ ፤ ዛሬ #June30 ሊካሄድ ከታሰበው የሱዳን ፀረ ጁንታ (ወታደራዊ አገዛዝ) ተቃውሞ እና የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ከሚጠይቀው ሰልፍ ጋር በተገናኘ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የናፍጣ እጥረት እና ምክንያቱ ምንድነው ? ከ2 ሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ የናፍጣ እጥረት በአዲስ አበባ ከተማ እየተፈጠረ ሲሆን ለምን እጥረቱ እንደተፈጠረ በሚሰጡት ምላሽ ላይ መንግሥትና የነዳጅ አቅራቢዎች ሊግባቡ አልቻሉም፡፡ ማደያዎችና ነዳጅ አመላላሾች እጥረቱ የተፈጠረው ከጂቡቲ የሚመጣ ነዳጅ በመጥፋቱ ነው በማለት መኪኖቻቸው ለቀናት ነዳጅ አጥተው ጂቡቲ መስመር ላይ መቆማቸውን ገልጸዋል፡፡ ቃላቸውን…
#ነዳጅ

" 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ ርምጃ ይወሰዳል " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

ከጂቡቲ ተነስተው አዲስ አበባ እና የተለያዩ ዋና ከተሞች መድረስ የነበረባቸው 200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰዓረላ አብዱላሂ በሰጡት መግለጫ " በተለይ አዲስ አበባና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት ተከስቷል " ብለዋል።

ይህም በህገወጥ መንገድ የነዳጅ ቦቴዎቹ በየመንደሩ ተደብቀው የኢኮኖሚ አሻጥር በፈጠሩ የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፋር ፣ መተሃራ ፣ በሞጆ ፣ በአዳማ እና በተለያዩ ከተሞች ተደብቀው የተገኙት ቦቴዎች ዛሬ እስከ 10 ሰዓት ድረስ ነዳጁን በሚፈለገው ማደያ ማድረስ እንዳለባቸው ለባለቤቶቹ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በተጨማሪ 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ ርምጃ እንደሚወስድ ጠቁመው ይህንን ቁጥጥር የሚመራ ግብረሃይል ተቋሟል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች በየመንገዱ እና በየሰፈሩ ተደብቀው የሚቆሙት / ነዳጁን ለማድረስ የሚዘገዩት ገና ለገና የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር በአዲሱ ዋጋ ተመን ከፍተኛ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ነው።

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ እጥረት ነዋሪዎች እየተንገላቱ ነው ፤ የህዝብ ትራንስፖርት የሚጠቀመው ነዋሪው ወደ ጉዳዩ ለመሄድ በዚህ ክረምት በዝናብ ረጅም ሰዓት ተሰልፎ ትራንስፖርት ለመጠበቅ ተገዷል። ታክሲዎችም አንድ ቀን ስራ አንድ ቀን የነዳጅ ሰልፍ ላይ ነው የሚውሉት።

(ፎቶ ፦ ከአፋር ክልል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን #በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል። እንደሚኒስትሩ…
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል ?

የትምህርት ሚኒስቴር የብሄራዊ ፈተና መሰረቅንና ኩረጃን ለመከላከል ፈተናው በኦንላንይ መስጠት እስኪጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

የፈተናውን አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም የ2014 ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20 / 2015 ዓ/ም በኃላ እንደሚሰጥ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም ፤ እስካሁን ድረስ የተቀየረም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለፀ አዲስ ነገር የለም።

ከትላንት ጀምሮ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተናው ሃምሌ እና ነሃሴ ላይ ነው የሚሰጠው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ ያልታወቀና ሀሰተኛ በመሆኑ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በጥናታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ወላጆችም ልጆቻችሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እገዛችሁን እንድታጠናክሩ ይሁን።

እጅግ በርካታ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች የሚከታተሉት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ የሚወጡ መረጃዎችን አምናችሁ አትቀበሉ። አንድን መረጃ ስትሰሙ ከትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን አረጋግጡ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት ዛሬ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) አመራር የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከታሰሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ክሱን ያቀረበውም የፌዴራል ፖሊስ መሆኑን የፓርቲው መረጃ ያመለክታል። ፖሊስ አቶ ስንታየሁ ፤ ሕዝብን ለተቃውሞ የሚያነሳሳ ፅሁፍ በፌስቡክ…
#Update #ችሎት

እነ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በዋስ እንዲወጡ ታዘዘ።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 23/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ስንታየሁ ቸኮል ፣ ያለለት ወንድዬ ፣ ዋሴ ቢረሳው እና ደምስ አያሌው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ያየ ሲሆን በክርክሩ ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙ ክርክር አዳምጦ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ዋስትና እንዲወጡ አዟል።

መረጃው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።

#Update

በ30ሺ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ የተፈቀደላቸው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከማረሚያ ቤቱ ሲወጡ በር ላይ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንደያዟቸው ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኔሞ የሽናሻ_ታምሩ ዳኘው.pdf
ዘወልድ.pdf
403.7 KB
#5

#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

#ዘወልድ (የራያ ቆቦ ማህበረሰብ ባህላዊ የእርቅ ስርዓት)

አዘጋጅ፦ ዮሐንስ ቢሰጥ

እንደ አሁኑ ዘመናዊ የፍትህ ስርዓት ባልሰፈነበት ጊዜ በራያ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች የአካባቢያቸውን ባህል መሰረት በማድረግ ህግ አውጥተው ይተዳደሩና በመረጧቸው ሽማግሌዎች ይዳኙ ነበር ፡፡

- የዘወልድ ሽማግሌዎች የዕርቅ ሥነ-ስርዓት ከጠፋው የሰው ልጅ ህይወት ተጨማሪ የአካልና የህይወት እንዲሁም የንብረት ጉዳት እንዳይደርስ የመከላከል ስራ ይሰራሉ፡፡

- የሽምግልና ሂደቱን የሚመሩት አባቶች የሚመረጡት በአካባቢው ማሕበረሰብ ሲሆን መስፈርቱም አርቆ አሳቢነት፣ ታማኝና ሐቀኛ የሆኑ፣ የችግር ቋጠሮ የመፍታት እይታቸው ላቅ ያለ አባቶችን በመመልመል ይሰይማል፡፡

- ከዕርቅ ሽማግሌዎች አፈንግጦ የሚወጣ ተበዳይ የአካባቢውን ማህበረሰብ በመሰብሰብ ‹‹እንበደዲ›› በማለት ይወስናሉ፡፡ እንበደዲ ማለትም ይህን ግለሰብ /ተበዳይ/ ከማንኛውም የማህበራዊ ህይወት ማግለል ማለት ነው፡፡

- ከወንድ ሽማግሌዎች ባልተናነሰ ሁኔታ በአካባቢው መጠሪያ የዱበርቲዎች ወይንም የሴቶች ሚና የሟች ቤተሰብ የበቀልና የቁጭት ስሜት እንዳያሳዩ ልብ የሚያራራ የምልጃና የልመና ዜማ ለሟች ቤተሰቦች ያቀርባሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዕርቁ ዕለት ምግቡን በማቀራረብና ሟችና ገዳይ አብረው እንዲበሉ በማድረግ ይቅር ባይነትን ያስተምራሉ።

(ሙሉውን ከላይ በPDF ያንብቡ)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በላከልን መልዕክት በዛሬው ዕለት የመሰረተ ልማት መጋራት እና #በደንበኞች_መካከል_የግንኙነት_ልውውጥ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ከበርካታ ዙር ውይይቶች በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጾልናል። ውይይቶቹ በኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን የተመሩ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ላሳየው ብቁ የአመራር ጥበብ ምስጋና…
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከምን ደረሰ ?

ሳፋሪኮ ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እንዲሁም አሁናዊ የተቋሙን እንቅስቃሴ በተመለከተ በቀጣይ ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ተቋሙ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት ሊጀምር ነው " የሚሉ፣ ቀኖች እና ሌሎች ተቋማዊ መረጃዎችን ያካተቱ ዜናዎችና መረጃዎች በማሕበራዊ ድረገጾች መውጣታቸውን እንዳስተዋለ ገልጿል።

#በያዝነው_የፈረንጆች_ዓመት ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና #በሁሉም_የኢትዮጵያ_ክፍሎች ምርጥ የደንበኞች አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉትን ዝግጅቶች እያደረግ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለዚህም፦

- የኔትወርክ ግንባታ፣

- የሰው ኃብትን #በኢትዮጵያዊያን_ሠራተኞች ማደራጀት

- የጥራት ፍተሻዎችን እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በቀጣይ ሳምንት ስለተቋሙ እንቅስቃሴ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን የአገልግሎቱን መጀመረ የሚጠባበቁ ሁሉ ትክክለኛ መረጃዎችን ከተቋሙ ትክክለኛ አድራሻ ብቻ እንዲካታተሉ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#BahirDar

በባሕር ዳር የባጃጆች ሰዓት ገደብ ተጣለ።

በባሕር ዳር ከተማ የባጃጅ ወይም የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ እንዲሆን ገደብ ተጣለ።

የባሕር ዳር ከተማ ፀጥታ ም/ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ ምክር ቤቱ በአደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስጠብቁ ያላቸውን ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቋል።

በዚህም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን እስከ ምሽት 2 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ትዕዛዝ ተላልፏል።

ምክር ቤቱ አሁን ካለው ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ለከተማው ሰላምና ደኅንነት ሲባል ውሳኔው መተላለፉን አሳውቋል።

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውም የባጃጅ ወይም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የተባለ ሲሆን ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪ ላይ ለሚወሰድበት ማንኛውም ቅጣትና እርምጃ ኀላፊነቱን ባለቤቱ ወይም አሽከርካሪው ይወስዳል ሲል ምክር ቤቱ አሳስቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሱዳን ኢንተርኔት ዘጋች። ሱዳን ዛሬ ሀሙስ ከሚካሄደው ታላቁ የ #June30 የተቃውሞ ሰለፍ ጋር በተያያዘ ከጥዋት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጣለች። የኢንተርኔት ጉዳይን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ ፤ ዛሬ #June30 ሊካሄድ ከታሰበው የሱዳን ፀረ ጁንታ (ወታደራዊ አገዛዝ) ተቃውሞ እና የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ከሚጠይቀው ሰልፍ ጋር በተገናኘ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ገልጿል። @tikvahethiopia
" የቡርሃን አገዛዝ ይውደቅ ፤ ብንሞትም እንኳን ወታደሩ አይገዛንም " - የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝን ሊያወግዙ አደባባይ የወጡ ዜጎች

ዛሬ ሱዳን በተቃውሞ ስትናጥ ዋለች።

ዛሬ ሀሙስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ጎዳናዎች ላይ ወታደራዊ አገዛዙን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኙት ሱዳናውያን ባለፈው አመት በመፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን ስልጣን የተቆጣጠሩት የጦር ሰራዊት አዛዥ ሌ/ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃንን በመጥቀስ " የቡርሃን አገዛዝ ይውደቅ ፤ ብንሞትም እንኳን ወታደሩ አይገዛንም " ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ከካርቱም በተጨማሪ በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች የተቃውሞ ሰልፍ ስለመካሄዱ ለማወቅ ተችሏል።

ከሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ በተገኘው መረጃ በዛሬው ሰልፍ ላይ 5 ሰዎች ተገድለዋል (አንድ ከካርቱም ፤ 4 ከኦምዱርማን)። ከጥቅምት 25/2021 አንስቶ እስከዛሬ የሞቱ ሰዎች 108 ደርሰዋል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ከጥዋት ጀምሮ የኢንተርኔት እና የስልክ መስመሮች ተቋርጠዋል።

መረጃው ፦ ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እና ከሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፋቱዋ ቤንሱዳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት፤ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር ያቋቋመውን ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን በሊቀመንበር ሲመሩ የነበሩት ፋቱዋ ቤንሱዳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። በምትካቸው ኬንያዊቷ የህግ ባለሙያ ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ ተሹመዋል። ጋምቢያዊቷ ፋቱዋ ቤንሱዳ ለምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በፃፉት ደብዳቤ ከሊቀ መንበርነታቸው…
#UN #NewsAlert

የተመድ መርማሪዎቹ አዲስ አበባ እንዲገቡ ፍቃድ ማግኘታቸውን አስታወቁ።

በሰሜን ኢትጵያ በተካሄደ ጦርነት ተፈፀሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲያጣሩ የተሰየሙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች አዲስ አበባ እንዲገቡ ፈቃድ ማግኘታቸውን ዛሬ ሀሙስ አስታወቁ። ሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች መግባት እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል።

የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶችን የሚመረምር በየዓመቱ የሚታደስ ሥልጣን የተሰጠውና ሦስት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያዎች ያሉበትን አጣሪ ኮሚሽን ባለፈው ታኅሳስ መሰየሙ ይታወሳል።

የኮሚሽኑ ምርመራው ዋና ትኩረት የሆኑት የሰብዓዊ መብቶች፣ የሰብዓዊነትና የስደተኛ ህግጋት ጥሰቶች እና በደሎች አሁንም በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፉ ባሉ የተለያዩ ወገኖች ያለምንም ተጠያቂነት መቀጠላቸው እንደሚያሳስባቸው የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ ለምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር አመልክተዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥት በግዛቱ ውስጥ የሚፈፀሙ ጥሰቶችን የማስቆምና ተጠያቂዎችን ለፍርድ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት ኮሚሽኑ አበርትቶ እንደሚያሳስብ መግለፃቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

“ ኦሮምያ ክልል ውስጥ የተፈፀሙትን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ የጭካኔ አድራጎቶች በጥልቅ አሳስበውናል” ሲሉ ሊቀመንበሯ አክለው ተናግረዋል።

“ሲቪሎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚያቀጣጥል የጥላቻ ንግግርና በጎሣ ማንነትና በፆታ ላይ የተመሠረቱ ጥቃቶች እንዲፈፀሙ ቅስቅሳ ማካሄድ የጭካኔ ወንጀል አድራጎቶችን እንደሚያስከትሉ እንደቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚወሰድ ነው” ብለዋል

በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን በግጭቱ ውስጥ በሚሣተፉት በሁሉም ወገኖች ተፈፅመዋል የተባሉትን ጥሰቶች የሚመረምር ሲሆን የሽግግር ፍትኅና የብሄራዊ ዕርቅ መመሪያም በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

ከኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስትር ጋር ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የተገናኙት የተመድ መርማሪዎች ግጭት በተካሄደባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች የመብቶች ጥሰቶች ሰለባዎች ናቸው የተባሉ ሰዎችን ለማነጋገር ፈቃድ የጠየቁ ሲሆን አዲስ አበባን ለመጎብኘት ከኢትዮጵያ መንግሥት አዎንታዊ ምላሽ ማግኘታቸውን የኮምሽኑ ሊቀ መንበር አስታውቀዋል።

ሊቀመንበሯ በማከል “አዲስ አበባ ላይ በምናደርገው ውይይት መርማሪዎቻችን ጥሰቶች ወደተፈፀሙባቸው አካባቢዎች መግባትና ከተጎጂዎችና ከዕማኞች ጋር ለመነጋገር እንዲችሉ ፈቃድ ያገኛሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

መረጀውን አጃንስ ፍረንስ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ያጋራው ቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia