TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ_አይለያችሁ !

የ " FIAS 777 " ጉዳይ ከተነሳ በኃላ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ልክ እንደ " FIAS 777 " ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን እየጠቆሙ ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት ያለብንን የኢኮኖሚ ችግር ተገን አድርገው " በአጭር መንገድ ትርፋማ የሚሆኑበት የማለፋ ስራ " እያሉ በርካታ ወጣቶችን እየቀሰቀሱ ገንዘባቸውን ላፍ እያደረጉ ናቸው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ተጠያቂ የምታደርጉት ሰው በሌለበት፣ ቢሮ ሆነ አድራሻ በሌላቸው ሰዎች ፣ ነገ ይቀጥል አይቀጥል የሚለውን በማታውቁት ሂደት በአሰቸጋሪ ሁኔታ ደክማችሁ ለፍታችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ፣ ተበድራችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ ፣ ተማሪዎችም ከቤተሰብ የተቀበላችሁትን ገንዘብ ለቀማኞች እንዳታውሉት አደራ እንላለን።

ብዙሃንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ በሚስጥር አይሰራምና ገንዘባችሁን ከሚያሳጣ ማንኛውም የአጭበርባሪዎች እንቅስቃሴ ራቁ።

ሌላው ደግሞ የስልክ ቀፎ፣ ቴሌቪዥን፣ ላፕቶፕ... የመሳሳሉ እቃዎችን በርካሽ ከደቡብ አፍሪካ ፣ ከኬንያ በሞያሌ በኩፓ እናስመጣለን እያሉ ቅድመ ክፍያ እየተቀበሉ እብስ የሚሉ አሉና ተጠንቀቁ።

ሰዎችን ማታለያ መንገዶች አይነታቸውን እየቀያየሩ እየበዙ ነውና ህጋዊ ተጠያቂነት ያለባቸው ስራዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ።

ሁሌም ጥንቃቄ ማደረጋችሁን አትዘንጉ።

@tikvahethiopia
#DoubleA

የ “Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

መተግበርያውን ለማውረድ:
Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or
https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
#ጥንቃቄ | ዩኒቨርሲቲዎች፣ ተማሪዎችና አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ማህበረስብ አባላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላለፈ !

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

ግብረ ኃይሉ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህውሃት ቡድን ፋይናንስ ያደርጋቸዋል ያላቸው ሚዲያዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማደናቀፍ ተማሪዎች በብሄርና በሀይማኖት በመከፋፈል ግጭት እንዲፈጠር ለማነሳሳት ሌት ተቀን እሰሩ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል።

እነዚሁ ሚዲያዎች ሰሞኑን «በአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ እና የሌሎች ብሄር ተማሪዎችን ለማጥቃት የተደራጀ የደህንነት ቡድን ወደ አማራ ክልል ተልኳል» የሚል በዩኒቨርሲቲዎች ግጭት ለማስነሳት መልዕክት አስተላልፈዋል ብሏል።

የዩኒቨርሲቲዎችን ሰላም ለማናጋት እና ተማሪዎች በሰላም እንዳይማሩ የሚያደርጉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ያሳሰበው ግብረኃይሉ ይህን ተላልፈው በሚገኙት ላይ ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወድ አስጠንቅቋል።

ዩኒቨርሲቲዎች፣ ተማሪዎችና ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ሆን ተብሎ ግጭት ለማስነሳት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በመገንዘብ እራሳቸውን በመጠብቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል።

(የግብረ ኃይሉ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በርካቶች በምዕራብ ወለጋ በንፁሃን በተለይ በህፃናት እና ሴቶች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ እያወገዙ ይገኛሉ። በተለይ በአማራ ክልል በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ፍትህ እንዲሰፍን፣ መንግስት ንፁሃንን የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ሰልፍ በማድረግ ጭምር እየጠየቁ ይገኛሉ። ዛሬ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተጠያቂነት እንዲሰፍን፣ በአማራ…
ፎቶ / ቪድዮ ፦ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለወገናችን ድምፃችንን ለማሰማት ሰልፍ ብናደርግም ፀጥታ ኃይሎች የአስለቃሽ ጭስ በመተኮስ በተኑን ሲሉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዎን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች እንደሁም አንዳንድ ሰራተኞች ቅሬታቸውን አቀረቡ።

ምዕራብ ወለጋ ላይ የተከሰተውን አጸያፊ ተግባር የሚያወግዙ መልዕክቶችን ይዘን ነበር ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምፃችንን እያሰማን ነበረው ግን በኃይል ተበትነናል ብለዋል።

" አማራ ተኮር ዘር ጭፍጨፋ ይቁም ፤ ያለማቋረጥ ለሚፈሰው ለአማራ ደም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የተኛው መንግስት አካል ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፤ እኛ የጤና ባለሙያዎች የታመሙትን የሚያድን እንጂ ጤነኞችን የሚገድል ሀይላትን አንቃወማለን የሚሉ መልዕክቶችን አስተገጋብተናል ነገር ግን ድምፃችንን አሰምተን ሳይጨርስ ፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም በኃይል በትነውናል " ሲሉ አስረድተዋል።

አንዳንድ የወደቁና በመጠኑ የቆሰሉ ቢኖሩም ሌላ ተጨማሪ ጉዳት እንዳልነበር አመልክተዋል።

ፎቶ / ቪድዮ ፦ NAT. (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በሐዋሳ ከተማ ወደ ከተማዋ የመግቢያ በርና የፓርክ ልማት ኘሮጀክት በይፋ መጀመሩን የከተማው አስታዳደር አሳውቋል።

ወደ ከተማዋ የመግቢያ በር ፕሮጀክት ዛሬ ተጀምሯል።

ይህ የሐዋሳ መግቢያ ኘሮጀክት በቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) በኩል የሚገነባ ሲሆን የሐዋሳን እንዲሁም የሲዳማን ባህል ታሪክና ትውፊት የሚያስተዋውቅ እና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጠርም እንደሆነ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ከ1,500 በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል ይፈጥራል የተባለ ሲሆን በአንድ ዓመት የሚጠናቀቅ ፤ አንድ መቶ ሚሊየን ብር የሚፈጅ መሆኑም ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር

@tikvahethiopia
#ቹ

በዓለም በስፋት (በተናጋሪ ብዛት) ከሚነገሩ ቋንቋዎች በአንደኝነት የሚቀመጠውን፣ የተባበሩት መንግስታት የስራ ቋንቋ የሆነውን፣ ቻይንኛ ቋንቋን ይማሩ!!

* ቻይንኛ እና ቻይንኛ ብቻ የሚማሩበት የከተማችን የቋንቋ ት/ቤት ነው፡፡
*ለተማሪዎች በክረምት ወቅት የሚሰጥ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

አድራሻ፡
*ቦሌ፡ ፋንቱ ሱፐር ማርኬት አካባቢ፣ ሳይ ኬክ ቤት ያለበት ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
*ስታድየም፡ ትንሸዋ ስታድየም ጀርባ፣ ናሽናል ታወር ፣ 3ኛ ፎቅ
*አያት 49 የአየር መንገድ ቤቶች ፊት ለፊት ማይ ፕላዛ ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በ 0947202020 ይደውሉ፡፡
#NewsAlert

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት #በሰላማዊ_መንገድ ለመፍታት ሰላማዊ ድርድሮች እንዲጀመሩ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀመጠ።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አስታወቁ።

ዶ/ር ጌዲዮን ፓርቲው ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ ዉሳኔ አሳልፏል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተካሄደው ጦርነት መንግሥት ተገዶ የገባበት መሆኑን ገልፀው ፤ መንግሥት ይህንን ለመፍታት እየሠራ ስለመሆኑም አስረድተዋል ።

ፓርቲዉ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዳይኖር ታሳቢ በማድረግ #ለሰላም_ቅድሚያ_ይሰጣል ነው ያሉት።

ዶክተር ጌዲዮን እንዳሉት ፓርቲዉ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የሰላም አማራጩ፡-

1. ሕገ መንግሥታዊ እና ሕጋዊነትን የሚያስከብር መሆን አለበት፡፡

2. የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ መሆን አለበት፡፡

3. በሀገር ዉስጥ መፍታት ካልተቻለ #በአፍሪካ_ሕብረት ጉዳዩ መታየት እንዳለበት በሥራ አስፈጻሚ እና በማእከላዊ ኮሚቴ ዉይይት ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል።

በተጨማሪም ትንኮሳዎች ካሉ ሕግ አስከባሪዉ አካል እርምጃ እንዲወሰድ ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል። ሕዝቡም ለዚህ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ETHO_SUDAN

ኢትዮጵያ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በተከሰተ ግጭት በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኗን ገለፀች።


ጎረቤት ሃገር ሱዳን በኢትዮጵያ ጦር 7 ወታደሮቿ እና 1 ሲቪል እንደተገደለባት ክስ አሰምታለች። ግድያው በዚህ ወር አጋማሽ የተፈፀመ ነው ብላለች።

በዚህም ለተመድ ፀጥታ ም/ቤትና ለሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋም ክስ አቅርባለሁ ብላለች።

በተጨማሪ ቁጣዋን ለመግለፅ በአዲስ አበባ የሚገኙትን መልዕክተኛዋን ወደ  ካርቱም ጠርታለች፣ በአገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደርም ጠርታ ማብራሪያ እንዲሰጡ ብላለች።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ ግጭት የተከሰተው በህወሓት ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበርን አልፈው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች መሆኑን ገልጿል።

በሱዳን ሠራዊትና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል በተከሰተው በዚህ ግጭት በጠፋው ህይወት የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያዝን ገልጾ ምርመራ እንደሚደረግም አመልክቷል።

ክስተቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለማደናቀፍ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን በማመልከት፣ የሱዳን መንግሥትም ሁኔታውን የበለጠ ከሚያባብስ እርምጃ እንደሚቆጠብ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ፥ ሱዳኖቹ በአማራ ክልል ምእራብ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ “ገላል ውሀ” የተባለ አካባቢን በከባድ መሳሪያ ሲደበድቡ ውለዋል።

ጥቃቱ ካለፈው ሰኔ 15 ጀምሮ አልፎ አልፎ የነበረ ሲሆን ታጣቂዎቹ ተመትተው ከአካባቢው ከተባረሩ በኋላ እንደገና ዛሬ ከጠዋቱ ከ2 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት የከፋ ጉዳት ባይደርስም ጥቃት መሰንዘራቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ ዶቼቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሮይተርስ፣ ዴቼቨለ እና ቢቢሲ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ህግ ይከበር ፤ ፍትህ ይሰጠን " ለማስፋፊያ ስራ ተብሎ #ህግን_ባልተከተለ መልኩ ቤታችን ፈረሰብን ያሉ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል። ያሉበት ቦታ ለማስፋፊያ ስራ ይፈለጋል የተባሉ ዜጎች ለማስፋፊያ አንደሚፈለግ ያወቁት ሰኔ 29/2013 ዓ/ም አንደሆነ ከዛ በፊት ስለጉዳዩ ምንም እንደማያቁ / እንዳልተነገራቸው ፤ ጉዳዩን የሚያውቁት ከወረዳው…
#Update

• " ... ከመሬት ጋር በተያያዘ ከሳሽም ተከሳሽም ቤተክርስቲያኗ አይደለችም " - አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን

• " የድሆችን የምስኪኖችን ቤት አስፈረሰ፤ አፈናቀለ የተባለው ፍፁም ሀሰት ከዚህም አለፈ ሲል የስም ማጥፋት ወንጀል ነው ጉዳዩን ወደ ህግ ወስጄዋለሁ " - አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ

• " ቤቶችን ያፈረሱት የመንግስት ኃይሎች በኃይል ፣ በጉልበት እና ህግን ባልተከተለ መልኩ ነው። አሁንም ቢሆን ህግ ይከበር ነው እያልን ያለነው። የተበደሉት ሁሉ ፍትህ ያግኙ " - ነዋሪዎች

ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለማስፋፊያ በሚል ቤታቸው ህግን በጣሰ አካሄድ እንደፈረሰባቸው ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ሲባል ቆይቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ስሟ የተነሳው የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥታለች።

የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን የአምልኮ ቦታ ከመጠየቀ በዘለለ የዜጎችን ቤት እንዲፈርስ እንዳላደረገች ገልፃለች።

ቤተክርስቲያኗ የሰዎችን ቤት የማፍረስ እና አፍራሽ ግብረኃይልን የማዘዝ አንዳችም ስልጣን እንደሌላት ገልፃለች።

በተጨማሪም ፤ ቤተክርስቲያኗ ከመሬት ጋር በተያያዘ ከሳችም ተከሳሽም እንዳልሆነች፣ የወሰደችው ቦታ ሆነ ዶክመት እንደሌለ እና በቤተክርስቲያን እጅ የሚገኘው የካቢኔ ውሳኔ ብቻ መሆኑን አስገንዝባለች።

በዚህም የሰው ቤት እንዲፈርስ የምታዝበት መብትም ሆነ ስልጣን እንደሌላት ግልፅ አድርጋለች።

" መንግስት የወሰንኩላችሁ ቦታ ይሄ ነው ተረከቡና አምልኩ መብቱ ነው፣ ተገቢውን ቤት፣ ካሳ ሰጥቶ በህግ አግባብ ፣ በመመሪያ እና በአሰራር ማድረግ ያለበትን ማድረግ መብቱ ነው ቦታው ለቤተክርስቲያኗ አይገባም ማለትም መብቱ ነው፣ ወደ ሌላ ቦታ ሂዱ ማለት እንዲሁ የመንግስት መብት ነው ቤተክርስቲያኗ አንዳችም ነገር አያገባትም ፤ በመንግስት አሰራር ውስጥም ጣልቃ አልገባችም " ስትል አስገዝባለች።

አካሄዱ ትክክል ሆነ ስህተት ምንም እንደማያገባት ገልፅ አድርጋለች።

ቤተክርስቲያኗ ምንም ስለማይመለከታት በመንግሥት ጉዳይ እና ስራ ውስጥ ገብታ በዝርዝር ማብራራት እንደማይጠበቅባት ገልፃለች።

ያንብቡ ⬇️
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-27

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት #በሰላማዊ_መንገድ ለመፍታት ሰላማዊ ድርድሮች እንዲጀመሩ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀመጠ። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አስታወቁ። ዶ/ር…
#Peace

የተደራዳሪ ቡድኑ !

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት #በሰላም_ድርድር እንዲፈታ ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙ ተረጋግጧል።

የቡድኑ አባላት ፦

1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን ➡️ ሰብሳቢ
2ኛ. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ➡️ አባል
3ኛ. አቶ ተመስገን ጥሩነህ ➡️ አባል
4ኛ. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ➡️ አባል
5ኛ. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ➡️ አባል
6ኛ. ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ ➡️ አባል
7ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር ➡️ አባል መሆናቸውን የኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethiopia