TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እገዳው_ተነስቷል !

ሳዑዲ አረቢያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ወደ ኢትዮጵያ፣ ቱርክ፣ ቬትናም እና ህንድ በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ጥላ የነበረውን ጊዜያዊ እገዳ ዛሬ ማንሳቷን ከሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘን መረጃ ዋቢ አድርጎ Saudi Gazette ዘግቧል።

ሀገሪቱ በዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ዜጎቿ ወደተለያዩ የውጭ ሀገራት እንዳይጓዙ እገዳ ጥላ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት በጥሬ ዕቃ ምክንያት ላለፉት 3 ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ የመስጠት አገልግሎት ከ1 ሣምንት በኋላ መሥጠት ይጀመራል ተብሏል። የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን አንባቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍቢሲ) በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦ " በጥሬ ዕቃ ምክንያት እና በውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ላለፉት 3 ሣምንታት አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ…
#Update

ኮድ 2 ሠሌዳ !

በአዲስ አበባ ከሚንቀሳቀሱ አ.አ ሠሌዳ መካከል የኮድ 2 ሠሌዳ አቅርቦት ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በውክልና የወሰደው የፐፕሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግብዓት እጥረት ምክንያት ለወራት አቅርቦቱ መቋረጡ ይታወቃል፡፡

የገጠመውን የአቅርቦት ችግር በመቅረፍ የምርት ስራው ስለተጀመረ ኮድ 2 አዲስ ሠሌዳ ፈላጊዎች ከ14/10/2014 ዓ/ም ጀምሮ ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በ11 ቅ/ጽ ቤቶች በመኖሪያ አድራሻቸው አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑንበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዋስ እንዲፈታ ታዘዘ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በ10 ሺ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከቀናት በፊት ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ በዋስ ከእስር መፈታቱ ይታወሳል ፤ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድም በዛሬው ዕለት ከ23 ቀን እስር በኃላ መለቀቋን የምትሰራበት ሮሀ ሚዲያ አረጋግጧል። @tikvahethiopia
#Update

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከእስር ተፈቷል።

ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ማዘዙ ይታወሳል።

ይኸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተከብሮ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከእስር መፈታቱን ጠበቃው ታደለ ገብረመድህን አረጋግጠዋል፡፡

@tikvahethiopia
መቆሚያው የት ነው ?

ባለፉት ዓመት ንፁሃን ዜጎች በተለይ ህፃናት እና ሴቶች እጅግ በጣም አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ሲጨፈጨፉ ፣ ሲሳደዱ፣ ከገዛ ቤታቸው ሲፈናቀሉ አይተናል።

ይህን ተከትሎም በርካቶች ሀዘናቸውን እና ቁጣቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ ያጋራሉ ፤ ከልባቸው ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይወተውታሉ። መንግስት ተቀዳሚ ስራው የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሆነ ደጋግመው ያሳስባሉ።

በአንፃሩ የንፁሃንን ሞት እንዲሁም ጭፍጨፋ ለፖለቲካ መጠቀሚያ እንዲሁም በውስጣቸው ያለውን ጥላቻ ለማንፀባረቅ የሚጠቀሙም ብዙ ናቸው።

አንድ ቦታ ላይ ችግር ሲፈጠር እኩል ከማውገዝ ይልቅ ጉዳዩን ለማብራራት እና ለማስረዳት ወንጀለኞችንም ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ከሀዘንም በላይ ሀዘን ላይ የሚጥል ነው።

ለአብነት ፦ ወደ ኃላ ብዙ ሳንሄድ ከሰሞኑን በጋምቤላ ዜጎች ሲገደሉ ተመልክተናል ፤ ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን ሰዎች ናቸው የተገደሉት ይህን እኩል ማውገዝ ሲጠበቅ የተወሰነ ወገን ብቻውን ስለፍትህ ሲጮህ ነበር።

ቀጠለ ፦ በአማራ ክልል ውስጥ አንድ እጅግ አሰቃቂ ቪድዮ ወጣ ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን ህገወጥ እና አረመኔያዊ ግድያ መሆኑን እርግጥ ነው የተወሰነ ወገን ፍትህ እያለ ጮኸ ፤ ድርጊቱን እኩል ከማውገዝ ጥፋተኞች እንዲጠየቁ ከመጠየቅ ይልቅ ጉዳዩን ለመተንተን እና አድበስብሶ ለማለፍ የጣሩ ሰዎች ብዙ ታይተዋል። ጭራሽ በሌላ በኩል ከሰውነታቸው ይልቅ የማን ወገን ናቸው በሚል የሚከራከሩ ሁሉ ነበሩ ፤ በግልፅ በሚታዩ ሰዎች በጥይት ተረፍርፈው የተገደሉት የሰው ልጆች ሳያሳዝናቸው ጥፋተኞቹን ከለላ ሊሰጡ የሞከሩ በርካታ ነበሩ። ይህ ምን ያህል ከሰውነት እየራቅን እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ቀጠለ ፦ ምዕራብ ወለጋ ዜጎች በተለይ አንዳች ጥፋት የሌለባቸው ምስኪን ህፃናት እና ሴቶች እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ተገደሉ ጉዳዩን ለማብራራት ብቅ ያሉ አልጠፉም ፤ እንዴት ምንም ነገር የማይውቁት ጨቅላ ህፃናት አያሳዝኑንም ? ይህ ንፁሃን ላይ የተፈፀመ ግፍ ማብራሪያ ይፈልጋል ? የዛሬውን ጥቃት ከትላንትናው ጋር በማነፃፀር ለማቅለል የጣሩም በርካቶች ናቸው። ጉዳዩን እንዴት ታስጮሃላቹ ለማለት የዳዳቸው ፤ ዓለም ማወቁ ያስከፋቸውም አልጠፉም።

ትንሽ ወደኃላ ብንመለስ በትግራዩ በኃላም ወደ አማራ እና አፋር በተስፋፋው አስከፊ ጦርነት ወቅት ሴቶች አልተደፈሩም ፤ ንፁሃንም አልተገደሉም ሁሉም ነገር ውሸት ነው እያሉ ሲያላግጡ የነበሩም ብዙ ናቸው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ ይህ የቅርብ ጊዜው ነው ባለፉት ዓመታት ምን ሲሆን እንደነበር ከናተ አንዳች የተደበቀ አይደለም ፤ በአንድ ሀገር ውስጥ አንዱ ቦታ ሰው እያለቀሰ ሌላው እየተደሰተ በሰው ሀዘን እያላገጠ ፤ እንዴት የአንድ ሀገር ዜጎች ነን ማለት ይቻላል ? ሌላው ይቅር እኩል መደሰት ባንችል እኩል ማዘን እንዴት ያቅተናል ? የግድ ሀዘን ሁሉም ጋር መድረስ አለበት ? ከሰውነት ተራ እየወጣን ነው ፤ ያለፈው መማሪያ ሆኖ ዛሬ ካልታረምን የነገው ያስፈራል።

ስለዚህ መቆሚያው የት ነው ? ብለን ነገ ሳይሆን ዛሬ ልጓም ልናበጅለት ይገባል። ሁሉም ዜጋ ለፍትህ እና ለንፁሃን እኩል ካልቆመ ለውጥ ሊመጣ አይችልም።

ሌላው ይቅር ቢያንስ ለቀጣዩ ትውልድ ፤ ለታዳዊዎቹ ስንል ውስጣችን መፍተሽ ይኖርብናል ፤ እውነት የሰው ልጅ ሞት ስቃይ በሰውነቱ ብቻ ይሰማኛል ? ወይስ የኔ ብሄር፣ ዘመድ ፣ ጓደኛ ፣ ተመሳሳይ ሃይማኖት መሆን አለበት ለማዘን ? ደግመን ደጋግመን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።

በሰሜን፣ ደቡብ፣ ምሥራቅ ፣ ምዕራብ ሀገራችን ክፍል ስንቶች ወጥተው ቀሩ፣ የስንቶች ተስፋ መና ሆኖ ቀረ፣ የስንት እናቶች እና አባቶች እንባ ፈሰሰ፣ ስንት ትንንሽ ልጆች ያለቤተሰብ ቀሩ፣ ስንት ወጣቶች ረገፉ፣ ስንት ወገኖቻችን ሜዳ ላይ ወደቁ ፍትህ ለሁሉም ተጎጂዎች ይገባል።

የዜጎች ደህነት እንዲሁም በህይወት የመኖር ዋስትና በመግለጫ ጋጋታ አይጠበቅም ፤ አይረጋገጥምና ሁሉም መሬት ላይ የሚታይ ስራ ሰርቶ ፣ የሚከፈለው ዋጋ ተከፍሎ ንፁሃንን መጠበቅ፤ የተበደሉትን መካስ ፤ ያዘኑ የዜጎችን እንባ ማበስ እንዲሁም ደግሞ ህግና ስርዓት ነው የሚያስተዳድረን ከተባለ ጥፋተኞችን ፣ ከላይ እስከታች ያሉ ኃላፊነታቸውን ያልተወጡትን መቅጣት ያስፈልጋል። ወሬ ያለተግባር ምንም ለውጥ አያመጣም።

በዚሁ አጋጣሚ ፥ #ልጆች_ያላችሁ የቲክቫህ አባላት ወላጆች ልጆቻችሁ የሚያዩትን እና የሚሰሙትን ነገር እንድትቆጣጠሩ ይሁን ፤ የማህበራዊ ሚዲያው በጥላቻ በአስከፊ ድርጊቶች፣ ምስሎች ፣ ቪድዮዎች ተሞልቷል። ቢያንስ ቀጣዩን ትውልድ መታደግ ይገባል በጥላቻ ታውሮ እንዳያድግ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ያስፈልጋል።

(Tikvah Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OromiaRegion ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ። በዛሬው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ…
#Update

" ፍትህ እንፈልጋለን፣ ጥፋተኞች በጠቅላላ ይጠየቁ " - የምዕራብ ወለጋ ቲክቫህ አባላት

ከቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ ሲገልፁ የነበሩ የቤተሰባችን አባላት ህዝብ እና ሀገር አስተዳደራለሁ የሚል አካል ካለ ጥፋተኞች እንዲጠየቁ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ቤተሰቦቻቸውን በግፍ የተነጠቁ የቲክቫህ አባላት በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆነው ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

ፍትህ ለተጎዱ ወገኖች ይገባል ፤ ከፌዴራል አንስቶ ክልል እና ዞን እንዲሁም ወረዳ ድረስ ያሉ አካላት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ባለመቻላቸው ሊጠየቁ ይገባል ፤ ንፁሃንን ስለ ፖለቲካ ሆነ ስለምንም ነገር የማያውቁ ምስኪን ህፃናትን፣ እናቶችን በግፍ የገደሉ ታጣቂዎችም ሊቀጡ ይገባ ሲሉ ገልፀዋል።

የተፈፀመንብን ግፍ እና በደል እንዲሁ በመግለጫ የሚታለፍ አይደለም አሁንም የደህንነት ስጋት አለብን ትላንት ይህን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን ምንም ማድረግ ካልተቻለ እኛ ተረፍነው ምን ዋስትና ይኖረናል ? ሲሉም ጠይቀዋል።

በአካባቢያችን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እንዳለ፣ የደህንነት ስጋት እንዳለ ክልሉ ሆነ ፌዴራል መንግስት አያውቁም ማለት አይቻልም፤ በዕለቱም ጥቆማ ስንሰጥ ቶሎ አልተደረሰልንም አሁንም ቢሆን የቀሩ ሰዎችን ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ ከላይ እስካታች ኃላፊነትን ባለመወጣት ተጠናቂነት ሊሰፍን ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

በየጊዜው የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች የአንድ እና ሁለት ቀን አጀንዳ ሆነው ይረሳሉ፤ የማበራዊ ሚዳያውም ለተወሰነ ቀናት በዚህ ላይ ካተኮረ በኃላ በሌላ አጀንዳ ይጠመዳል የተጎዱት፣ የሚወዱትን ያጡት፣ ቤተሰብ አልባ የሆኑት፣ ልጆቻውን የተነጠቁት በህይወት እስካሉ ድረስ ሀዘኑ አብሯቸው ነው። ያጡትን መመልስ ባይቻል እንኳን ፍትህን በማስፈን ሊካሱ ይገባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኮድ 2 ሠሌዳ ! በአዲስ አበባ ከሚንቀሳቀሱ አ.አ ሠሌዳ መካከል የኮድ 2 ሠሌዳ አቅርቦት ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በውክልና የወሰደው የፐፕሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግብዓት እጥረት ምክንያት ለወራት አቅርቦቱ መቋረጡ ይታወቃል፡፡ የገጠመውን የአቅርቦት ችግር በመቅረፍ የምርት ስራው ስለተጀመረ ኮድ 2 አዲስ ሠሌዳ ፈላጊዎች ከ14/10/2014 ዓ/ም ጀምሮ ማሟላት…
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ የ ' ኮድ 02 አአ ' ሰሌዳ ፈላጊዎች ማሟላት ያለባቸውን መረጃ በማሟላት ከሰኔ 14 ጀምሮ በ11 ቅርጫፍ ፅህፈት ቤቶች በመኖሪያ አድራሻቸው ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ መግለፁ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ መረጃ ማዕከል ባሰራጨው ማሳሰቢያ ሰሌዳ መስጠት የተጀመረባቸዉ አገልግሎት አዲስ ተሸከርካሪ እና በጨረታ የተገዙ ተሽከርካሪዎች መሆኑን ገልጿል።

የአገልግሎት ለዉጥ እንዲሁም የፋይል ዝዉዉር አገልግሎቶች ሰሌዳ መስጠት ሲጀመር እንደሚገለፅም አሳውቋል።

(የኮድ 02 አአ ሰሌዳ አዲስ ተሽከርካሪ ምዝገባ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ፓርላማው

የህ/ተ/ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፦

" ... በዛሬው ዕለት የተያዙ አጀንዳዎች አንደኛ የምክር ቤቱ አንደኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ ፤ 2ኛ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የ2013 በጀት ዓመት የሂሳብ፣ ፋይናንስ እና ህጋዊነት ኦዲት እና የክንዋኔ ኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ ናቸው ፤ ...የሚቀርቡ ማስተካከያዎች እና እርማቶች ካሉ "

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን " እ... "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " ቃለ ጉባኤ ላይ ነው ? "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " ቃለ ጉባኤው ላይ ሳይሆን "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " አይቻልም "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " አጀንዳው ላይ ቀዳሚ አጀንዳ እንዲያዝልን ለመጠየቅ ነው "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " አይቻልም ፤ ባለተያዘ አጀንዳ አንወያይም። "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " የተከበሩ አፈጉባኤ ...አንድ ደቂቃ እድል እንዲሰጠኝ ጥያቄ ለማቅረብ "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " ስነስርዓት ፤ ድምፅ ማሰማት አይቻልም ስነስርዓት "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " ቀዳሚ አጀንዳ እንዲያዝልን ጥያቄ ለማቅረብ ነው "

አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ማይክራፎኑን ይዝጉት "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ " ቀዳሚ አጀንዳ አለን የአብን ተወካዮች እሱ እድል ይሰጠን "

አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ማይክራፎኑን ይዝጉት፤ አጀንዳ ካለ በአማካሪ ኮሚቴ አባል ስለሆኑ በአማካሪ ኮሚቴ እንነጋገራለን "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ " አስቸኳይ ነው ዛሬ ም/ቤቱ እንዲያይልን የምንፈልገው "

አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ቃለ ጉባኤ ላይ ሚቀርቡ እርማቶች እና ማስተከከያዎች ካሉ ..."

ከዚህ በኃላ ዶ/ር ደሳለኝን ጨምሮ 4 አብን ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል። አቶ ክርስቲያን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆናቸው አልወጡም።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #EU

የአውሮፓ ህብረት (EU) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺች ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ የመጡት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ዙርያ ያሉ ሁኔታዎችን ለማየት ነው።

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ትላንት ዣኔዝ ሌናርቺች በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ላላት አጋርነት ትልቅ ትኩረት እንደምትሰጥ እና ከኮሚሽኑ እና ከአባል ሀገራቱ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር እየሰራች መሆኑን አቶ ደመቀ ተናገረዋል።

አቶ ደመቀ ፤ በግጭት ለተጎዱ ወገኖች እየተደረገ ያለን የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ ለትግራይ ክልል የሚደርሰው ዕርዳታ ተመድ በሳምንት 500 የጭነት መኪኖች ከያዘው ግብ ባለፈ የማድረስ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረው አጋር አካላት የአማራ እና አፋር ክልሎችምንም ጨምሮ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገውን ድጋፍ እንዲያፋጥኑ ጠይቀዋል።

ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺች ፤ መንግስት በዚህ ረገድ የሚያደርገውን ጥረት ያደነቁ ሲሆን ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ አጋሮች ተጨማሪነዳጅ፣ ጥሬ ገንዘብ እና ሌሎችም ድጋፎች ወደ ትግራይ ክልል እንዲሄዱ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁለቱ አካላት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ግጭት ጊዜ በተከሰቱት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የተጠያቂነት እርምጃ፣ ይህንን የሚያረጋግጥ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በማቋቋም እና በሰብአዊ መብት አያያዝ እና በተመድ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ላይ ስላሉ ጉዳዮች ተወያይተዋል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #EU የአውሮፓ ህብረት (EU) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ዣኔዝ ሌናርቺች ኢትዮጵያ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ የመጡት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ዙርያ ያሉ ሁኔታዎችን ለማየት ነው። የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ትላንት ዣኔዝ ሌናርቺች በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ላላት…
#EU

ዣኔዝ ሌናርቺች ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ ከተማ በማቅናት ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መክረዋል።

የአውሮፓ ህብረት (EU) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ትላንትና በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ከመከሩ በኃላ ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መክረዋል።

በውይይቱ የተለያዩ የጋራ ጉዳዮች መነሳታቸውን ከሚገልፅ መረጃ ውጭ ዝርዝር ነገር አልተገለፀም።

ኮሚሽነሩ ከውይይቱ ቀደም ብሎ የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል መጎብኘታቸውን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
" ሁንዳኦል ተማሪ እንጂ ፖለቲካኛ አልነበረም " - ፍራኦል ቤኛ

ባለፈው አርብ በነቀምቴ ከተማ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆኑት ለሚ ቤኛ ወንድም የሆነ ሁንዳኦል ቤኛ ተገድሏል።

የሁንዳኦል ቤኛ አስከሬን ለ3 ቀናት ያህል ከተከለከለ በኋላ የቀብር ስነስርዓቱ ሰኞ መፈጸሙን ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ አስነብቧል።

አሁን በእስር ላይ የሚገኘው የኦነግ አመራር ለሚ ቤኛ ወንድም የሆነው ሁንዳኦል ቤኛ የተገደለው ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲዘጋጅ ነው ሲል ወንድሙን ፍራኦል ቤኛ ገልጿል።

ሁንዳአኦል ቤኛ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በነቀምቴ ከተማ ነበር ትምህርቱን ሲከታተል የነበረው አርብ ማምሻውን ግን ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ተገድሏል።

ወንድሙ ፍራኦል ቤኛ ፥ " ባለፈው አርብ በነቀምቴ ከተማ የተኩስ ልውውጥ ነበር ፤ በማግስቱ በጥይት አንድ ሰው መሞቱን ሰምተናል፤ ከዚያም ሰዎች የወንድሜን ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩ ነው ያየሁት " ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

" ምስሉን ባየሁ ጊዜ እውነት መሆኑን በመመርመር አረጋገጥኩ " ሲል ፍራኦል አክሏል።

ወንድሙ ሲገደል አብሮት እንዳልነበር የተናገረው ፍራኦል ስለሁኔታው በአካባቢው ያሉትን ሰዎች መጠየቅ እንደጀመራና ወንድሙ ከሌሎች ልጆች ጋር እቤት ውስጥ እያጠኑ ከቆዩ በኃላ ምሽት ላይ " ሪፍት ቫሊ " አካባቢ ለሻይ እንደወጡ በኃላም ትእዛዛቸውን ሲጠብቁ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ ከፍተውባቸው ሁንዳኦል ስገደል ፣ ጓደኞቹ ደግሞ መያዛቸውን ገልጿል።

አብረው ከነበሩ ውስጥ የቆሰሉ መኖራቸውን አመልክቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Nekemte-06-21

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሲሚንቶ አከፋፍላለሁ በሚል ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ያጭበረበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ።

ፖሊስ ፤ ሲሚንቶ አከፋፍላለሁ በማለት ከተለያዩ ግለሰቦች ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብሯል ያለውን ተጠርጣሪ ግለሰብ ዛሬ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ግለሰቡ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ ሁለት የሩዋንዳ አካባቢ ነዋሪ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ የ ' ሲሚንቶ አከፋፋይነት ' ሕጋዊ ፍቃድ አለኝ በማለት ከተለያዩ ግለሰቦች ሲሚንቶ አቀርባለሁ በማለት የቅድመ እና ሙሉ ክፍያ ቼክ እየሰጣቸው ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብስቦ መሰወሩን ፖሊስ ገልጿል።

Via Addis Ababa Police

@tikvahethiopia
#Mali 🇲🇱

በአፍሪካዊቷ #ማሊ የታጠቁ አማፂያን በፈጸሙት ጥቃት ከ100 በላይ ንፁሀን ዜጎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

ጥቃቱ ማዕከላዊ ማሊ ውስጥ መፈፀሙ ነው የተነገረው።

ጥቃቱን ' Katiba Macina ' የተባለው የታጠቀ ቡድን አባላት ቅዳሜ ለሊት ለእሁድ አጥቢያ የፈፀሙ ሲሆን ፤ ሞፕቲ ክልል ውስጥ በሚገኘው ባንካስ የገጠር ማህበረሰብ ውስጥ ቢያንስ በሶስት መንደሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 132 ንፁሃን ሰዎች በግፍ መደገላቸውን የሀገሪቱ መንግስት ገልጿል።

ጥቃቱን ተከትሎ የማሊ መንግስት ዛሬ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሀዘን አውጇል።

@tikvahethiopia
ፎቶ / ቪድዮ ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ፈረንሳይ 41 እየሱስ አካባቢ በፎቶው እና በቪድዮው የምትመለከቱትን ይመስል ነበር። ከዚህ አካባቢ በተጨማሪ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ ከ1 ሰዓት በላይ በረዶን የቀለቀለ ዝናብ ጥሎ ነበር።

ወቅቱ ክረምት በመሆኑ በሚቻለው አቅም ጥንቃቄ እናድርግ ፤ በተለይ ደግሞ አሽከርካራዎች ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ ጥንቃቄያችንን ከምን ጊዜውም በላይ እናጠናክር።

(ዧ - Tikvah Family)

@tikvahethiopia