TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#OromiaRegion ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ። በዛሬው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ…
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት እና በታጠቁ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል። 

ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቡሌ ቀበሌ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (በተለምዶ ‘ኦነግ ሸኔ’) ታጣቂዎች መካከል ሲደረግ ከነበረው ውጊያ ጋር በተያያዘ በታጣቂው ቡድን በአካባቢው በሚኖሩ ሲቪል ሰዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በሰው ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

አሁንም በአካባቢው ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት በመኖሩ ምክንያት ነዋሪዎች በአፋጣኝ ድጋፍ እንዲደርስላቸው በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ 

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ መንግሥት በሲቪል ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም አስፈላጊ የሆኑ የመከላከል እርምጃዎችን እንዲወስድ፣ በማንኛውም ሁኔታ ሲቪል ሰዎች የጥቃት ዒላማ እንዳይደረጉ ተገቢ የሆነ ጥንቃቄና ጥበቃ እንዲያደርግ፣ እንዲሁም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያፈላልግ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ደሴ እና ወልዲያን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል።

የ66 ኪቮ ኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር ተሸካሚ የብረት ታወሮች በመውደቃቸው ፦
- ደሴ፣
- ቢስቲማ፣
- አልብኮ፣
- ኩታበር እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች እንዲሁም ከወልድያ ሳብስቴሽን የሚያገኙ በሙሉ ፦
- ወልድያ፣
- ሳንቃ፣
- በቂሎ ማነቂያ፣
- ስርንቃ፣
- መርሳ ፣
- ውጫሌ እና በአካባቢያቸው ባሉ ከተሞች ኤሌክትሪክ መቋረጡን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

ጉዳቱ የደረሰው ከኮምቦልቻ ደሴ ባለዉ 2ኛው የ66 ትራንስሚሽን መስመር ላይ 1 ታወር መዉደቅ እና 1 ታወር የመሰበር ጉዳት በመድረሱ እና በተጨማሪም ከደሴ ወልደያ ባለዉ መስመርም ብልሽት በማጋጠሙ መሆኑ ተገልጿል።

የብረት ታወሮቹ እየወደቁ ያሉት ብረቶቹ በሌቦች በመሰረቃችው ምክንያት የሚመጣውን ነፋስ መቋቋም ባለመቻላቸው ነው ተብሏል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ተሸካሚ ታወር /የብረት ምሰሶ/ ስርቆት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ማነቆ እየፈጠረበት መሆኑና ደንበኞች ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል እናዳያገኙ እያደረገ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

ይህ እኩይ ተግባር ሊቆም የሚችለው በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር አካላት በመሰረተ ልማት ጥበቃ ላይ የማህበረሰብ ንቅናቄ በመፍጠር ጥበቃ እንዲደረግላቸው የጋራ ጥረት ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው ሲል አስገንዝቧል።

በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር፣ የፀጥታ እና የፍትህ ተቋማት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ስርቆትና ውድመት በማስቆም ረገድ የድርሻቸው እንዲወጡ አሳስቧል።

ህብረተሰቡም የስርቆት ተግባር ሲፈፀም ወይም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ የአማራ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

ለነዳጅ የሚደረግ ድጎማን ከሐምሌ 2014 ዓ.ም. ቀስ በቀስ ለማንሳት በዝግጅት ላይ ያለው መንግሥት፣ ከስሌቱ በታች በአነስተኛ ዋጋ ከነዳጅ እየተሰበሰበ ያለው የኤክሳይስ ታክስና የቫት ገቢ ለታለመ የነዳጅ ድጎማ ሊያውል መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ይሁንና መንግሥት በአነስተኛ መጠን የሚሰበስበውን የኤክሳይስ ታክስና ቫት ገቢ በሕጉ መሠረት ሙሉ ለሙሉ እንዲሰበሰብ ዕቅድ አለው ተብሏል።

ይህም የነዳጅን ዋጋ ይበልጥ ያንረዋል የሚል ሥጋት በመፍጠሩ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሠራሩ እንዲቀጥል የውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡ ተሰንቷል።

ከነዳጅ የሚሰበሰበው ይህ ኤክሳይስ ታክስና ቫት ከሰኔ 2 ቀን 2002 ዓ.ም. በተላለፈ ውሳኔ፣ እንደ ሕጉ የኤክሳይስ 30 በመቶና የቫት 15 በመቶ አይደለም፡፡

በጊዜው ነዳጅ ያሳየው ከፍተኛ ጭማሪ ተከትሎ መንግሥት 30 እና 15 በመቶ በመሰብሰብ ፋንታ፣ የነዳጅ ዋጋ ሲተመን እያንዳንዱ ሊትር ናፍጣ ላይ ሁለት ብር ከ98 ሳንቲም፣ በቤንዚን ላይም እንዲሁ ከሦስት ብር ያነሰ ጭማሪ እንዲደረግ ተወስኖ እስካሁን ቀጥሏል፡፡

መንግስት ከዚህ ግብር የሚሰበሰበው ገቢ ከሐምሌ ወር አንስቶ ነዳጅ ላይ ለሚደረገው የታለመ ድጎማ እንዲውል መወሰኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አንድ የመንግሥት ኃላፊን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-06-19
Credit ፦ Ethiopian Report

@tikvahethiopia
በግብፅ ሀገር ህይወታቸው ያለፈው የደ/ሱዳን ባለስልጣን !

በግብፅ ሀገር ካይሮ ከተማ ህክምና ላይ የነበሩት የጎረቤታችን ደቡብ ሱዳን የውሃ ሃብት እና መስኖ ሚኒስትር ማናዋ ፒተር ጋትኩኦት ጓል ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

ሚኒስትሩ በደረታቸው ላይ ባጋጠማቸው ህመም ሳቢያ በጁባ ከተማ በፍሪደም እና ባራካ ሆስፒታሎች ህክምናቸውን ከተከታተሉ በኃላ አርብ ወደ ግብፅ ማቅናታቸው ነው የታወቀው።

በግብፅ ካይሮ በከፍተኛ የደም ግፊት ሲሰቃዩ እንደነበርና ዶክተሮች ህይወታቸውን ለማትረፍ ርብርብ ቢያድረጉም እንዳልተሳካላቸው ፤ ዛሬ እሁድ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ነው ተሰማው።

በአሁን ሰዓት የሚስትሩን አስከሬን ወደ ጁባ ለመውሰድ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የሀገራችን ኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ በደቡብ ሱዳኑ የውሃ ሃብት እና መስኖ ሚኒስትር ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ለቤተሰቦቻቸው፣ እና የወዳጆቻቸው መፅናናት ተመኝተዋል።

@tikvahethiopia
#አብን

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራሮቹ ያቀረቡትን ስራ መልቀቂያ አልቀበልም አለ።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል።

በስብሰባው በተለይ በፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኩል " አሁን ላሉ በርካታ ጉዳዮች ላለፉት 4 አመታት በከፍተኛ አመራርነት ያገለገልን አመራሮች ለቀን በአዲስ እንተካ " የሚለውን ሃሳብ ፓርቲው ጊዜ ሰጥቶ የተወያየበት መሆኑን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጣሂር ሞሀመድ ተናግረዋል።

ሆኖም ሊቀመንበሩ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ሃሳብ ማዕከላዊ ኮሚቴው አልቀበልም ብሏል።

አሁን እየታየ ላለ ችግር የመፍትሄ አካል ለመሆን አዳዲስ አመራሮችን ወደፊት በማምጣት እንተካካ የሚለውን ሃሳብም ፓርቲው ሀምሌ 18/2014 በሚያካሂደው ስብሰባ በጥልቀት እንደሚያየውና እስከዛም ፓርቲው በትኩረት ስራውን እየሰራ እንደሚቀጥል ተገልጧል።

የፓርቲው ውስጣዊ አንድነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን በተመለከተ የህዝብ ግንኙነት ኀላፊው አቶ ጣሂር ሞሀመድ " ማህበረሰቡ ውስጥ ላሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦችና ለድርጅቱም አቅምና ውስጣዊ አንድነት የሚበጁትን ሃሳቦችና ውሳኔዎች የምናሳልፍበት ስብሰባ ሀምሌ 18 ይካሄዳል " ብለዋል።

#AMC

@TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት እና በታጠቁ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል።  ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቡሌ ቀበሌ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (በተለምዶ ‘ኦነግ ሸኔ’) ታጣቂዎች መካከል ሲደረግ ከነበረው ውጊያ ጋር በተያያዘ በታጣቂው ቡድን በአካባቢው…
#ምዕራብ_ወለጋ

በምዕራብ ወለጋው ጥቃት የተገደሉት ብዙዎቹ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን የምዕራብ ወለጋ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

አንድ ቤተሰቦቹ የተገደሉበት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ " የኔ ወንድም ሚስቱ 7 ወር ነፍሰጡር እና ልጁ 1 አመት 350 ቀን የሆናት ታውቃላችሁ ምን እንደሚላት 40 አመት በኃላ ክብርት ፕሬዝዳት ከድጃ መሃመድ ይላት ነበር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ ሰኔ 11/2014 አራት ነብስ ጠፋ " ሲል መልዕክቱ ልኳል።

ይኸው የቤተሰባችን አባል ንብረታቸው በጠቅላላ እንደወደመ በዚህ ሰአት የሞቱ ሰዎች አስክሬን እየተሰበሰበ እየተቀበረ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።

እናቴ አባቱ እንዲሁም እህቶቹ የት እንዳሉ እንደማይታወቅም አክሏል።

እስካሁን ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ፤ አሁንም ከጫካ ውስጥ አስክሬን እየተገኘ መሆኑን የአካባቢው የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።

ወደ ስፍራው የመከላከያ ኃይል የተላከ ሲሆን አሁንም ተጨማሪ ኃይል ካልተላከ በሌላ ቀበሌ ሌላ ተጨማሪ ንፁሃንን ህይወት የሚቀጥፍ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

የመንግስት ተቀዳሚ ተግባሩ የዜጎችን ደህንነትና በሰላም የመኖር ዋስትና ማረጋገጥ ነውና ደህንነታቸውን እንዲያስጠብቅ ፤ ሌላ ጥቃት እንዳይፈፀም አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትላንት ጥቃት በተፈፀመበት አካባቢ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት በመኖሩ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ መሆኑን ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምዕራብ_ወለጋ በምዕራብ ወለጋው ጥቃት የተገደሉት ብዙዎቹ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን የምዕራብ ወለጋ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል። አንድ ቤተሰቦቹ የተገደሉበት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ " የኔ ወንድም ሚስቱ 7 ወር ነፍሰጡር እና ልጁ 1 አመት 350 ቀን የሆናት ታውቃላችሁ ምን እንደሚላት 40 አመት በኃላ ክብርት ፕሬዝዳት ከድጃ መሃመድ ይላት ነበር ግን ያ ሳይሆን ቀርቶ ሰኔ 11/2014…
#Update

አሶሼትድ ፕሬስ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ይዞት በወጣው ዘገባ በትላንቱ ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

ከጥቃቱ ያመለጠው የጊምቢ ወረዳ ነዋሪ አብዱል ሰኢድ ጣሂር ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጠው ቃል፥ " 230 አስከሬኖችን ቆጥሪያለሁ። ይህ በህይወታችን ያየነው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት ነው ብዬ እሰጋለሁ " ብሏል።

አክሎም " ሟቾችን የጅምላ መቃብር ውስጥ እየቀበርናቸው ነው፣ አሁንም አስከሬን እየሰበሰብን ነው። የፌደራል ሰራዊት ደርሰዋል ነገር ግን ከቦታው የሚለቁ ከሆነ ሌላ ጥቃት ሊደርስ ይችላሉ ብለን እንሰጋለን " ሲል አስረድቷል።

ሻምበል የተባሉ ሌላ የአይን እማኝ ለደህንነታቸው ሲሉ የመጀመሪያ ስማቸውን ብቻ የገለፁ " በአካባቢው ያለው የአማራ ማህበረሰብ " ሌላ ዙር የጅምላ ግድያ ከመከሰቱ በፊት ወደ ሌላ ቦታ እንዲወሰድ ይፈልጋል " ብሏል።

ነዋሪዎቹ የዛሬ 30 አመት አካባቢ በሰፈራ ፕሮግራም የሰፈሩ መሆናቸውን ገልጾ " እንደ ዶሮ ነው የተገደሉት " ሲል የጥቃቱን አስከፊት ገልጿል።

ሁለቱም የአይን እማኞች ጥቃቱን መንግስት በሽብርተኛ ድርጅትነት የፈረጀውን " ሸኔ " እራሱን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) እያለ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል እንደፈፀመው ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስትም ትላንት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ በሽብርተኛነት የተፈረጀው " ሸኔ " መፈፀሙን ፤ ቡድኑ የጸጥታ ሃይሎች የጀመሩትን ዘመቻ መቋቋም ባለመቻሉ ንፁሃንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ መግደሉን መግለፁ ይታወሳል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲል አስተባብሏል። ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት የእኛ ተዋጊዎች ወደዚያ አካባቢ እንኳን አልደረሱም " ብሏል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/AP-06-19

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህፃን ማርኮን እስካሁን አልተገኘም። በአዲስ አበባ ከተማ ከላዛሪስት ት/ቤት በጎርፍ የተወሰደው ማርኮን ይገረም እስካሁን አለመገኘቱ ታውቋል። ዛሬ 9ኛ ቀን ነው። @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ለህፃን ማርኮን ይገረም 12ኛ ቀን ምክንያት በማድረግ የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል ዕፀ ጳጦስ ሰንበት ት/ቤት የማጽናኛ መርሐግብር በዛሬው ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው አካሂደዋል።

ህፃን ማርኮን በጎርፍ ከተወሰደ 12ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን እስካሁን ድረስ ፈልጎ ማግኘት አልተቻለም። ፍለጋው አሁንም ድረስ አለመቋረጡን ለማወቅ ተችሏል።

(Gech - Tikvah Family)

@tikvahethiopia
#EU

ዛሬ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ በሉግዘምበርግ ይመክራል።

ስብሰባውን የህብረቱ የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል በሊቀመንበርነት ይመሩታል የተባለ ሲሆን በሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ላይ የሚወያይ ቢሆንም የኢትዮጵያ ጉዳይም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል ተብሏል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ በአጀንዳነት የተያዘው፤ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ስር ነው።

የአውሮፓ ካውንስል ለዚሁ ስብሰባ ያዘጋጀው ሰነድ የኢትዮጵያ ሁኔታ " የተወሰነ መሻሻል " እንደታየበት ቢጠቅስም አሁንም ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁሟል።

ዘላቂ የተኩስ አቁም፣ የኤርትራ ወታደሮች መውጣት፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የፈጸሙን ተጠያቂ በማድረግ ረገድ መሳካት የሚኖርባቸው በርካታ ጉዳዮች እንደሚቀሩ በዚሁ ሰነድ ላይ ሰፍሯል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የህብረቱ የሰብዓዊ መብቶች ልዩ መልዕክተኛ ኤይሞን ጊልሞር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

Credit : https://ethiopiainsider.com/2022/7198/

@tikvahethiopia