TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ የፀጥታ ኃይሎች ፍፁም ህግን ባልተከተለ እንዲሁም ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን ሲደበድቡ ፣ በጥይት ተኩሰው ሲገድሉ፣ በህይወት ያለን ሰው በእሳት ሲያቃጥሉ ተመልክተናል። የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ከወራት በፊት በአዲስ አበባ (አንዲት እናት በፖሊስ ስትደበደብ) ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም በትግራይ ክልል የተፈፀሙና ተቀረፃው…
#Update

2 ጉዳዮች ከጋምቤላ፦

ዛሬ የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አጉቱ አዲንያግ በወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ክልሉ ንፁሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመቆጣጠር ከፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል። ኃላፊው በከተማይቱ ብሄርን መሰረት አድርጎ ጥቃት አልተፈፀመም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው ወሬ ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ከከተማው ህዝብ ጋር ተመሳሳይለው ተጨማሪ ጥቃት ሊከፍቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጣቂዎቹ ጦር ላይ እርምጃ ተወስዷል ሲሉ ገልፀዋል።

ሌላው ኃላፊው ከሰሞኑ ግጭት ጋር በተያያዘ የስነ- ምግባር ጉድለት ያለባቸው የፀጥታ አካላት እንዳሉ መንግስት ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልፀው ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ እርምጃ መዉሰድ መጀመሩን አስታውቀዋል።

እርምጃው ምን እንደሆነ እንዲሁም የፈፀሙትን ድርጊት ግልፅ አድርገው አላብራሩም።

በቀጣይም ያልተገባ ተግባር የፈፀሙና የሚፈፅሙ የፀጥታ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለዉ ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ማስታወሻ፦ ከቀናት በፊት በጋምቤላ በተፈጠረው ክስተት የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ መግታት ከተቻለ በኃላ ንፁሃንን ከአማፅያን (ታጣቂዎች) ጋር አደባልቆ የማየት እና በአንዳንድ ሰፈሮችም ንፁሃንን የማንገላታት ከዚህም አልፎ የማጥቃት ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን የሞቱ ሰዎችም ስለመኖራቸው እንደሰሙን ይህ ህጋዊ ያልሆነ ድርጊት በአፋጣኝ እንዲቆም የጋምቤላ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥቆማ መስጠታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ሌላው፥ አንድ ወጣት እጁን ወደኃላ ታስሮ የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ እና ባለበሱ ሰዎች በጥይት ሲደበደብ የሚያሳይ ቪድዮ መሰራጨቱን ተከትሎ ማብራሪያ እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነበር፤ በዚህ ላይ ግልፅ ማብራሪያ አልተሰጠም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UK አሜሪካ #በጥብቅ የምትፈልገው የ " ዊኪሊክስ " መስራች ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላፎ እንዲሰጥ የብሪታኒያ ፍርድ ቤት ዛሬ ወስኗል። አሳንጅ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲያጸድቀው ነው ተብሏል። አሳንጅ የአሜሪካን ወታደራዊ መረጃዎች አውጥቷል ፤ አትሟል ፤ ወታደራዊ ሚስጥሮችን የያዙ ሰነዶች ለውጭ ኃይሎች…
#UK #USA

አሜሪካ በጥብቅ የምትፈልገው ጁሊያን አሳንጅ ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል ተብሏን።

የዊክሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ ለአሜሪካ ተላልፎ የመሰጠቱ ጉዳይ በUK የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓቴል ተቀባይነት እንዳገኘ ቢቢሲ ዘግቧል።

ጁሊያን አሳንጄ ውሳኔውን ይግባኝ ለማለት 14 ቀናት እንዳለውም የዩናይትድ ኪንግደም ሃገር ውስጥ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ፍርድ ቤቶች ጁሊያን አሳንጄን አሳልፎ የመስጠት ጉዳይ " ከሰብዓዊ መብቱ ጋር የማይጣጣም " መሆኑን ቢገነዘቡም በአሜሪካ ውስጥ " በተገቢው ሁኔታ እንደሚስተናገድ " ማረጋገጣቸውን ገልጿል።

ጁሊያን አሳንጄ በአውሮፓውያኑ 2010 እና 2011 አሹልኮ ባወጣቸው ሰነዶች ምክንያት በአሜሪካ ባለስልጣናት ይፈለጋል።

በዊክሊክስ የታተሙት እነዚህ ሾልከው የወጡት ሰነዶች ከኢራቅና አፍጋኒስታን ጦርነት ጋር የተያያዙ ናቸው።

የአውስትራሊያ ዜግነት ያለው ጁሊያን አሳንጅ በለንደን ቤልማርሽ እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን ተላልፎ ላለመሰጠትም ከፍተኛ ትግል እያደረገ ነው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት ነገ በአዲስ አበባ ግዮን ግሮቭ ጋርደን ዋክ ይካሄዳል።

ዝግጅቱ ከጥዋት 3:30 ጀምሮ ነው የሚካሄደው።

ውድ ፤ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ እንስቶች የነገ ፕሮግራማችሁን አመቻችታችሁ አንድአፍታ ወደ ዝግጅቱ ቦታ ጎራ ብላችሁ የጡት ካንሰር ምርመራ በነፃ እንድታደርጉና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቱን እንድትታደሙ መልዕክት እናስተላልፋለን።

ወንዶችም መልዕክቱን ለእናቶቻችሁ፣ ለእህቶቻችሁ ፣ ለጓደኞቻችሁ እንዲሁም ለትዳር አጋሮቻችሁ በማድረስ አሳውቋቸው።

@tikvahethiopia
#AmharaBank

የአማራ ባንክ ነገ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል።

ባንኩ ነገ በይፋ ስራ የሚጀምርበትን የምረቃት ስነስርአት ከጥዋት 3:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ያካሂዳል።

ነገ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያካሂደውን የምርቃ ስነስርዓት በማስመልከት በልዩ ሁኔታ ለአዲስ አበባ እና ዙሪያው #አንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በሙሉ የሙሉ ቀን (ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡ዐዐ ሠዓት) የጉዞ ክፍያን ሸፍኗል።

የአዲስ አበባ እና የዙሪያዋ የአንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በነጻ ወደሚፈልጉባቸው ቦታዎች መጓጓዝ ይችላሉ።

በተጨማሪም ባንኩ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም " የእንኳን ደስ አላችሁ " ስጦታ የሚያበረክት ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 2 ጉዳዮች ከጋምቤላ፦ ዛሬ የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አጉቱ አዲንያግ በወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህም ክልሉ ንፁሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመቆጣጠር ከፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል። ኃላፊው በከተማይቱ ብሄርን መሰረት አድርጎ ጥቃት አልተፈፀመም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው ወሬ ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል። ነገር ግን…
ጋምቤላ ክልል ፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች

ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጠዋት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸው ይታወሳል።

ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች የተከፈተ እንደነበር እና ክስተቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የክልሉ መንግሥት አሳውቋል።

በዕለቱ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የከተማዋ ፀጥታ የተረጋጋ እና በአሁኑ ወቅት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በከተማው የሚገኝ ቢሆንም እስከ አሁንም ድረስ የተሟላ መረጋጋት አለመስፈኑን፣ የነዋሪዎች የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ አለመጀመሩን እና በተለይም የንግድ አካባቢዎችን ጨምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች ዘረፋ እንደተፈጸመ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስረድተዋል። 

በተጨማሪም ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች (በክልሉ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ) በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተጋለጡ መሆናቸውን እና ከሕግ ውጭ ግድያ ስለመፈጸሙ ለኢሰመኮ መረጃዎች እየደረሱት ይገኛል።

በተለይም በጥቃቱ ተሳትፈዋል ወይም ተባብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ #ቤት_ለቤት በመሄድ ጭምር ግድያዎች እንደተፈጸሙ ኢሰመኮ ከምስክሮችና የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃዎች ጭምር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል። 

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሰዎችን ደኅንነትና የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አስታውሰው፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ የሰብአዊ መብቶችን መርሆች ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ያላየነው ብዙ ጭካኔ ይኖር ይሁን ?

በርካቶች በጋምቤላ ተቀርፆ በተሰራጨው ጨካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ቪድዮ የተሰማቸውን ሀዘን በአግባቡ ሳይወጡ ዛሬ ደግሞ አንድ ቀኑ ሆነ አድራሻው የት እንደሆነ የማይታወቅ የጅምላ ርሸና ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ለጊዜው ድርጊቱ መቼ .. ? የት ? እንዴት ? ተፈፀመ ስለሚለው ማወቅ ቢያዳግትም ከዚህ ቀደም እንዳየናቸው እጅግ በጣም ዘግናኝ እና ህጋዊ ያልሆነ የጭካኔ ተግባር ጋር ተመሳሳይ ነው።

ቀኑና ቦታው የማይታወቀው ቪድዮ በርከት ያሉ የታጠቁ ፤ የፀጥታ ኃይል ልብስም የለበሱ ፤ አንዳንዶቹ ጭንቅላታቸው ላይ ጥቁር ሻሽ ያሰሩ ሰዎች በአይሱዙ መኪና ተጭነው የነበሩ ሰዎችን እየቀጠቀጡ እያስወረዱ የጥይት እሩምታ ሲያዘንቡባቸው ይታያል።

ቪድዮውን የቀረፀው ሰው ደግሞ በጥይት ከሚደበድቡት ሰዎች አንዱ መሆኑን ንግግሩ በግልፅ ያስረዳል።

ጉዳዩ እና ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሰዎቹን በህግ አግባብ መጠየቅ አይቻልም ? ወደ ህግ ፊት ማቅረብ አይቻልም ነበር ? በቪድዮ እየቀረፁ የዚህን ያህል ጭካኔ ሰው ላይ መፈፀሙ ምን ይፈይዳል ?

ማነው ስለዚህ ጉዳይ ወጥቶ መቼ ፣ የት ፣ እንዴት ተፈፀመ ስለሚለው የሚያብራራው ? የትኛው አካል ነው ጉዳዩን የሚያስረዳ ? እንዲህ ያደረጉ ሰዎች ምን ተደረጉ ? በጥይት የተደበደቡትስ ፍትህ አገኙ ?

ትልቁ ጥያቄ #የፍትህ_ተቋማት መኖራቸው ፋይዳው ምንድነው ?

ባለፉት በርካታ ወራት ብዙ የጭካኔ ተግባራት አይተናል ፤ አሁንም ማየታችን ቀጥለናል፤ በቪድዮ እና በፎቶ ተቀርፀው ያልተቀመጡ እንጂ በርካታ ህጋዊ ያልሆኑ ከሰውነት ተራም የወጡ ድርጊቶች ይኖራሉ ፤ ጊዜ እየጠበቁ ይወጡ ይሆናል።

አንዳንዴ ምነው በዚህ ጊዜ ባልተፈጠርን ጭምር የሚያስብል ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ሮይተርስ ባወጣው የምርመራ ሪፖርት " በሺሕዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ያለፍርድ በጊዜያዊ እስር ቤቶች ተይዘው ይገኛሉ " ብሏል።

እንደ ምርመራ ሪፖርቱ በአሁኑ ወቅት ላይ 9‚000 የሚኾኑ ተወላጆች በእስር ቤቶቹ ሲገኙ፣ ቢያንስ 17 እስረኞች ለኅልፈት ተዳርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የሚካሔደው ጦርነት 19 ወራትን በአስቆጠረበት ኹኔታ፣ 3‚000 የሚሆኑ እስረኞች፣ በሚዛን ተፈሪ ከተማ በሚገኙና በእጅጉ በቆሸሹ 18 የእስር ቤት ክፍሎች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ ብሏል ሪፖርቱ።

በተመድ (UN) እንደተገመተው መንግሥት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ከኅዳር እስከ የካቲት ባሉት ወራት 15,000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተይዘዋል።

ሮይተርስ ምርመራ ሪፖርት በበኩሉ ከ17 የቀድሞ እስረኞች እና በሳተላይት ፎቶ ተደግፎ ባደረገው ማጣራት፣ ያለፍርድ ተይዘዋል ያላቸው እስረኞች ብዛት ተመድ ከሚገምተው ቢያንስ በ3‚000 እንደሚበልጥ ተመልክቷል።

ሪፖርቱ ፤ መንግሥት አብዛኞቹ እስረኞች ተለቀዋል ቢልም 9,000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ታስረው ይገኛሉ።

አብዛኞቹ የእስር ቦታዎች ለሌላ ተግባር የተሠሩ፣ ጠባብና የቆሸሹ ናቸው ይላል የምርመራው ሪፖርት ። ሪፖርቱ በመቀጠል የእስረኞቹ አያያዝም ዓለም አቀፍ ሥርዓትን ያልተከተለ ነው ብሏል።

ያንብቡ

#አማርኛhttps://telegra.ph/Reuters-Amh-06-18

#እንግሊዘኛhttps://www.reuters.com/investigates/special-report/ethiopia-conflict-prisoners/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaBank የአማራ ባንክ ነገ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል። ባንኩ ነገ በይፋ ስራ የሚጀምርበትን የምረቃት ስነስርአት ከጥዋት 3:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ያካሂዳል። ነገ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያካሂደውን የምርቃ ስነስርዓት በማስመልከት በልዩ ሁኔታ ለአዲስ አበባ እና ዙሪያው #አንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በሙሉ የሙሉ ቀን (ከጠዋቱ…
ፎቶ ፦ አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራውን በይፋ ጀምሯል።

የባንኩ የምረቃ እና ስራ ማስጀመሪያ ሰነ ስርዓት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ነው የተካሄደው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፦
- የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፣
- የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣
- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ባንኩ ከ70 በላይ የሚሆኑ ቅርንጫፎቹ በይፋ ስራ መጀመራቸው ተነግሯል።

አማራ ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የኮር ባንኪንግ ሲስተም በመጠቀም ከ165,000 በላይ ባለአክሲዮኖችን በመያዝ የተመሰረተ ባንክ ነው።

አማራ ባንክ ከቀደሙት ባንኮች ብዙ በመማር በተለይም ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል ለማቀፍ ተደራጅቶ " ከባንክ ባሻገር " በሚል መሪ ቃል የተመሰረተ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለው ግድያ በአሜሪካ ! ትላንት አንድ የ23 ዓመት ወጣት በምዕራብ ሜሪላንድ ስሚዝበርግ ገጠራማ አካባቢ በሚገኝ የማምረቻ ድርጅት (Columbia Machine) ተኩስ ከፍቶ 3 ሰራተኞችን ገድሏል። ግለሰቡ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኛ ሲሆን ተኩስ ከፍቶ 3 ሰራተኞችን ለመግደል ያነሳሳው ጉዳይ ምን እንደሆነ አልታወቀም። ተኩስ ከፍቶ ከገደላቸው 3 ሰዎች በተጨማሪ ከአንድ ሜሪላንድ ግዛት ፖሊስ ጋር ተኩስ…
በአሜሪካ የቀጠለው ግድያ !

ደቡባዊ አሜሪካ በምትገኘው በአላባማ ክፍለ ሀገር ጥቂት ሰዎች በተሰባሰቡበት ቤተ ክርስቲያን ታጣቂ ተኩስ ከፍቶ 3 ሰዎች ገድሏል።

ባለሥልጣናት በርሚንግሃም ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ተይዟል ብለዋል።

አሜሪካ ውስጥ ሰሞኑን የመሳሪያ ጥቃት በተከታታይ መድረሱ የመሳሪያ ቁጥጥር ለውጥ እርምጃን አስፈላጊነት የሚመለከተውን ክርክር መቀስቀሱን ቪኦኤ ዘግቧል።

ባለፈው ወር ኒው ዮርክ ባፈሎ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የምግብ እና ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር በዘረኛ ጥቃት አስር ጥቁር አሜሪካውያን ተገድለዋል።

ከዚያም ወዲህ ቴክሳስ ዩቫልዴ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ ተኩስ የከፈተ አጥቂ አስራ ዘጠኝ ተማሪዎች ጨመሮ ሃያ አንድ ሰዎች ገድሏል።

በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት በተለያዩ ከተሞች በተከፈቱ ተኩሶች እና ጥቃቶች 9 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው እንዲሁም በምዕራብ ሜሪላንድ ገጠራማ አካባቢ በሚገኝ የማምረቻ ድርጅት ተኩስ ተከፍቶ 3 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia