TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ የፀጥታ ኃይሎች ፍፁም ህግን ባልተከተለ እንዲሁም ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን ሲደበድቡ ፣ በጥይት ተኩሰው ሲገድሉ፣ በህይወት ያለን ሰው በእሳት ሲያቃጥሉ ተመልክተናል።

የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ከወራት በፊት በአዲስ አበባ (አንዲት እናት በፖሊስ ስትደበደብ) ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም በትግራይ ክልል የተፈፀሙና ተቀረፃው የተሰራጩ እጅግ አሳዛኝ እና ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ዋነኞቹ ናቸው።

አሁን ዳግሞ በአዲስ አበባ ከተማ እና በጋምቤላ እንደተፈፀሙ የተገለፀላቸው በፍፁም ህግን ያልተከተሉ ድርጊቶች በቪድዮ ተሰራጭተዋል።

በአዲስ አበባ አንድ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰ ተማሪ በፖሊስ አባላት ተከቦ ሲደበደብ ይታያል ፤ አንዱን ተማሪ የሚደበድቡት የነበሩት ቁጥራቸው ከሁለት በላይ የሆኑ የፖሊስ አባላት ተሰብስበው ነው።

ህግ እያለ በአግባቡ መጠየቅ እየተቻለ ይህንን ማድረግ ለምን አስፈለግ ? የፀጥታ ኃይላት ህግን ማስከበር እና የማያውቁትን ማስተማር ሲገባቸው በዚህ አይነት ድርጊት መሳተፋቸው ምን ይባላል ?

ሌላው ከጋምቤላ የወጣ ቪድዮ አንድ ወጣት እጁን ወደኃላ ተስሮ በጥይት ሲደበደብ ይታያል። ወጣቱን በጥይት ሲደበድቡ የነበሩት የፀጥታ ኃይል ልብስ የለበሱ እንዲሁም የፀጥታ ኃይል ልብስ ያለበሱ ሰዎች ተሰብስበው ነው።

በእርግጥ ከተማዋ ከቀናት በፊት ያስተናገደችው ክስተት የሚታወቅ ቢሆንም ይህን መሰል እጅግ ኢሰብዓዊ ፣ የጭካኔ ድርጊት መፈፀም ለምን አስፈለገ ? ሰው ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ እንኳን በህግ መጠየቅ አይቻልም ? ግልፅ ምላሽ ያስፈልጋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ጉዳዩን በተለመከተ ኢሰመኮ ክትትል እያደረገ እንደሆነ ጠይቀን የምንልክላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#UNHCR

" ባለፈው ዓመት ብቻ በዓለም ላይ 89.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በጦርነት፣ ጥቃት እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ ምክንያት ከሀገራቸው ተገፍተው ወጥተዋል ፤ ይህም ብዛት ከዚህ በፊት ያልታየ ነው " - የተመድ የስደተኞች ጉዳይ የዛሬ ሪፖርት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ የፀጥታ ኃይሎች ፍፁም ህግን ባልተከተለ እንዲሁም ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን ሲደበድቡ ፣ በጥይት ተኩሰው ሲገድሉ፣ በህይወት ያለን ሰው በእሳት ሲያቃጥሉ ተመልክተናል። የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ከወራት በፊት በአዲስ አበባ (አንዲት እናት በፖሊስ ስትደበደብ) ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም በትግራይ ክልል የተፈፀሙና ተቀረፃው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

የአዲስ አበባ ፖሊስ ተማሪ ላይ የድብደባ ወንጀል የፈፀሙ የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።

ፖሊስ ድርጊቱ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር ሆቴል በሚባል አካባቢ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ መፈፀሙን ገልጿል።

ተማሪው በክፍል ውስጥ ርንቺት ተኩሶ ከት/ቤት ውስጥ አምልጦ መሄዱን ከዛም በኃላ አራት የፖሊስ አባላት ተከታትለው በመያዝ የድብደባ ወንጀል እንደፈፀሙበት አስረድቷል።

ህገ- ወጥ ድርጊቱ እንደተፈፀመ ፖሊስ በደረሰው መረጃ እና ባደረገው ማጣራት ድል በር 2ኛ ደረጃ በሚባል ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ነው በሚል ፕሮግራም ላይ በክፍል ውስጥ በተደረገ ዝግጅት ተማሪው ርችት እንደተኮስ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ርችት መተኮሱ ሌሎች ተማሪዎችን እንደረበሻቸው ፖሊስ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል።

በእለቱ ድርጊቱን ፈፅሟል የተባለው ተማሪ ከት/ቤቱ ቅጥር ግቢ እንደወጣ የተነገራቸው 4 የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት ክትትል በማድረግ ሰሜን ማዘጋጃ ጋበር የሚባል ሆቴል አካባቢ ተማሪውን ይዘውት ተገቢ ያልሆነ ድብደባ ፈፅመውበታል ብሏል።

ፖሊስ መረጃው ካደርሰው በኋላ ተጠርጣሪ የፖሊስ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በማነኛውም ሁኔታ ውስጥ የህግ አስከባሪነት መነሻው ህግን ማክበር መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ የዜጎችን ህጋዊ መብት በሚፃረሩ የፖሊስ አባላት ላይ የሚወሰደውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በማንኛውም ሁኔታ ህገወጥ ተግባራት ሲፈፀሙ ህ/ሰቡ በያገባኛል ስሜት የሚሰጠውን መረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 በራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ የተነሳውን እሳት መቆጣጠር አልተቻለም። በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ 016 ቀበሌ በተለምዶ ራስ ጠቆሮ እየተባለ በሚጠራ ጥብቅ ደን ላይ ሰኔ 6/2014 ሌሊት ጀምሮ የተከሰተው የእሳት አደጋን እስካሁን ድረስ መቆጣጠር አልተቻለም። በጥብቅ ደኑ ውስጥ ወይራ፣ ጥድ፣ ኮሶ፣ ዝግባና ሌሎች የደን ሐብቶች እንዲሁም የተለያዩ እንሰሳትና አዕዋፋት እንደሚገኙ ተጠቁሟል።…
#Update

" እሳቱ 4 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ደን ላይ ጉዳት አድርሷል "

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ 016 ቀበሌ ራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ 4 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ደን ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿጻ።

ሰኔ 6/2014 ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ በራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ሰኔ 9/2014 ዓም ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተነግሯል።

የእሳት አደጋው ወደሌላ አካባቢ እንዳይዛመትና እሳቱን ለማጥፋት የአካቢቢው ማህበረሰብ፣ መምህራንና የፀጥታ ኃይሎች እርብርብ ማድረጋቸውን ተገልጿል።

በደረሰው የእሳት አደጋም ወይራ ፣ጥድ፣ ኮሶ፣ ዝግባና ሌሎች ሐገር በቀን ደኖች ላይ ጉዳት ደርሷል።

የራስ ጠቆሮ ደን ስፋት 8 ሄክታር ስፋት ሲሆን አራት ሄክታሩ መሬት ላይ የሚገኘው ጥብቅ ደን ላይ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል።

በአምባሰል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ከራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ቃጠሎ ጋር ተያይዞ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ነው ብሏል። የአደጋው መንስኤ የእርሻ ማሳን ለማስፋፋት በተለኮሰ እሳት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

መረጃው የአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Update

የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የጤና ሚኒስቴር ከግንቦት 01 - 04/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ከሰኔ 10/2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራቸውን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋቃ።

በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936/ 0118275337 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄያቸድን ማቅረብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ የፀጥታ ኃይሎች ፍፁም ህግን ባልተከተለ እንዲሁም ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ሰዎችን ሲደበድቡ ፣ በጥይት ተኩሰው ሲገድሉ፣ በህይወት ያለን ሰው በእሳት ሲያቃጥሉ ተመልክተናል። የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ከወራት በፊት በአዲስ አበባ (አንዲት እናት በፖሊስ ስትደበደብ) ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም በትግራይ ክልል የተፈፀሙና ተቀረፃው…
#Update

2 ጉዳዮች ከጋምቤላ፦

ዛሬ የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አጉቱ አዲንያግ በወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ክልሉ ንፁሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመቆጣጠር ከፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል። ኃላፊው በከተማይቱ ብሄርን መሰረት አድርጎ ጥቃት አልተፈፀመም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው ወሬ ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ከከተማው ህዝብ ጋር ተመሳሳይለው ተጨማሪ ጥቃት ሊከፍቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጣቂዎቹ ጦር ላይ እርምጃ ተወስዷል ሲሉ ገልፀዋል።

ሌላው ኃላፊው ከሰሞኑ ግጭት ጋር በተያያዘ የስነ- ምግባር ጉድለት ያለባቸው የፀጥታ አካላት እንዳሉ መንግስት ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልፀው ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ እርምጃ መዉሰድ መጀመሩን አስታውቀዋል።

እርምጃው ምን እንደሆነ እንዲሁም የፈፀሙትን ድርጊት ግልፅ አድርገው አላብራሩም።

በቀጣይም ያልተገባ ተግባር የፈፀሙና የሚፈፅሙ የፀጥታ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለዉ ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ማስታወሻ፦ ከቀናት በፊት በጋምቤላ በተፈጠረው ክስተት የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ መግታት ከተቻለ በኃላ ንፁሃንን ከአማፅያን (ታጣቂዎች) ጋር አደባልቆ የማየት እና በአንዳንድ ሰፈሮችም ንፁሃንን የማንገላታት ከዚህም አልፎ የማጥቃት ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን የሞቱ ሰዎችም ስለመኖራቸው እንደሰሙን ይህ ህጋዊ ያልሆነ ድርጊት በአፋጣኝ እንዲቆም የጋምቤላ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥቆማ መስጠታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ሌላው፥ አንድ ወጣት እጁን ወደኃላ ታስሮ የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ እና ባለበሱ ሰዎች በጥይት ሲደበደብ የሚያሳይ ቪድዮ መሰራጨቱን ተከትሎ ማብራሪያ እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነበር፤ በዚህ ላይ ግልፅ ማብራሪያ አልተሰጠም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UK አሜሪካ #በጥብቅ የምትፈልገው የ " ዊኪሊክስ " መስራች ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላፎ እንዲሰጥ የብሪታኒያ ፍርድ ቤት ዛሬ ወስኗል። አሳንጅ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲያጸድቀው ነው ተብሏል። አሳንጅ የአሜሪካን ወታደራዊ መረጃዎች አውጥቷል ፤ አትሟል ፤ ወታደራዊ ሚስጥሮችን የያዙ ሰነዶች ለውጭ ኃይሎች…
#UK #USA

አሜሪካ በጥብቅ የምትፈልገው ጁሊያን አሳንጅ ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል ተብሏን።

የዊክሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ ለአሜሪካ ተላልፎ የመሰጠቱ ጉዳይ በUK የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓቴል ተቀባይነት እንዳገኘ ቢቢሲ ዘግቧል።

ጁሊያን አሳንጄ ውሳኔውን ይግባኝ ለማለት 14 ቀናት እንዳለውም የዩናይትድ ኪንግደም ሃገር ውስጥ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ፍርድ ቤቶች ጁሊያን አሳንጄን አሳልፎ የመስጠት ጉዳይ " ከሰብዓዊ መብቱ ጋር የማይጣጣም " መሆኑን ቢገነዘቡም በአሜሪካ ውስጥ " በተገቢው ሁኔታ እንደሚስተናገድ " ማረጋገጣቸውን ገልጿል።

ጁሊያን አሳንጄ በአውሮፓውያኑ 2010 እና 2011 አሹልኮ ባወጣቸው ሰነዶች ምክንያት በአሜሪካ ባለስልጣናት ይፈለጋል።

በዊክሊክስ የታተሙት እነዚህ ሾልከው የወጡት ሰነዶች ከኢራቅና አፍጋኒስታን ጦርነት ጋር የተያያዙ ናቸው።

የአውስትራሊያ ዜግነት ያለው ጁሊያን አሳንጅ በለንደን ቤልማርሽ እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን ተላልፎ ላለመሰጠትም ከፍተኛ ትግል እያደረገ ነው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት ነገ በአዲስ አበባ ግዮን ግሮቭ ጋርደን ዋክ ይካሄዳል።

ዝግጅቱ ከጥዋት 3:30 ጀምሮ ነው የሚካሄደው።

ውድ ፤ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ እንስቶች የነገ ፕሮግራማችሁን አመቻችታችሁ አንድአፍታ ወደ ዝግጅቱ ቦታ ጎራ ብላችሁ የጡት ካንሰር ምርመራ በነፃ እንድታደርጉና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቱን እንድትታደሙ መልዕክት እናስተላልፋለን።

ወንዶችም መልዕክቱን ለእናቶቻችሁ፣ ለእህቶቻችሁ ፣ ለጓደኞቻችሁ እንዲሁም ለትዳር አጋሮቻችሁ በማድረስ አሳውቋቸው።

@tikvahethiopia
#AmharaBank

የአማራ ባንክ ነገ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል።

ባንኩ ነገ በይፋ ስራ የሚጀምርበትን የምረቃት ስነስርአት ከጥዋት 3:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ያካሂዳል።

ነገ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያካሂደውን የምርቃ ስነስርዓት በማስመልከት በልዩ ሁኔታ ለአዲስ አበባ እና ዙሪያው #አንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በሙሉ የሙሉ ቀን (ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡ዐዐ ሠዓት) የጉዞ ክፍያን ሸፍኗል።

የአዲስ አበባ እና የዙሪያዋ የአንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በነጻ ወደሚፈልጉባቸው ቦታዎች መጓጓዝ ይችላሉ።

በተጨማሪም ባንኩ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም " የእንኳን ደስ አላችሁ " ስጦታ የሚያበረክት ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 2 ጉዳዮች ከጋምቤላ፦ ዛሬ የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አጉቱ አዲንያግ በወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህም ክልሉ ንፁሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመቆጣጠር ከፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል። ኃላፊው በከተማይቱ ብሄርን መሰረት አድርጎ ጥቃት አልተፈፀመም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው ወሬ ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል። ነገር ግን…
ጋምቤላ ክልል ፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች

ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጠዋት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸው ይታወሳል።

ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች የተከፈተ እንደነበር እና ክስተቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የክልሉ መንግሥት አሳውቋል።

በዕለቱ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የከተማዋ ፀጥታ የተረጋጋ እና በአሁኑ ወቅት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በከተማው የሚገኝ ቢሆንም እስከ አሁንም ድረስ የተሟላ መረጋጋት አለመስፈኑን፣ የነዋሪዎች የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ አለመጀመሩን እና በተለይም የንግድ አካባቢዎችን ጨምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች ዘረፋ እንደተፈጸመ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስረድተዋል። 

በተጨማሪም ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች (በክልሉ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ) በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተጋለጡ መሆናቸውን እና ከሕግ ውጭ ግድያ ስለመፈጸሙ ለኢሰመኮ መረጃዎች እየደረሱት ይገኛል።

በተለይም በጥቃቱ ተሳትፈዋል ወይም ተባብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ #ቤት_ለቤት በመሄድ ጭምር ግድያዎች እንደተፈጸሙ ኢሰመኮ ከምስክሮችና የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃዎች ጭምር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል። 

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሰዎችን ደኅንነትና የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አስታውሰው፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ የሰብአዊ መብቶችን መርሆች ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ያላየነው ብዙ ጭካኔ ይኖር ይሁን ?

በርካቶች በጋምቤላ ተቀርፆ በተሰራጨው ጨካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ቪድዮ የተሰማቸውን ሀዘን በአግባቡ ሳይወጡ ዛሬ ደግሞ አንድ ቀኑ ሆነ አድራሻው የት እንደሆነ የማይታወቅ የጅምላ ርሸና ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ለጊዜው ድርጊቱ መቼ .. ? የት ? እንዴት ? ተፈፀመ ስለሚለው ማወቅ ቢያዳግትም ከዚህ ቀደም እንዳየናቸው እጅግ በጣም ዘግናኝ እና ህጋዊ ያልሆነ የጭካኔ ተግባር ጋር ተመሳሳይ ነው።

ቀኑና ቦታው የማይታወቀው ቪድዮ በርከት ያሉ የታጠቁ ፤ የፀጥታ ኃይል ልብስም የለበሱ ፤ አንዳንዶቹ ጭንቅላታቸው ላይ ጥቁር ሻሽ ያሰሩ ሰዎች በአይሱዙ መኪና ተጭነው የነበሩ ሰዎችን እየቀጠቀጡ እያስወረዱ የጥይት እሩምታ ሲያዘንቡባቸው ይታያል።

ቪድዮውን የቀረፀው ሰው ደግሞ በጥይት ከሚደበድቡት ሰዎች አንዱ መሆኑን ንግግሩ በግልፅ ያስረዳል።

ጉዳዩ እና ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሰዎቹን በህግ አግባብ መጠየቅ አይቻልም ? ወደ ህግ ፊት ማቅረብ አይቻልም ነበር ? በቪድዮ እየቀረፁ የዚህን ያህል ጭካኔ ሰው ላይ መፈፀሙ ምን ይፈይዳል ?

ማነው ስለዚህ ጉዳይ ወጥቶ መቼ ፣ የት ፣ እንዴት ተፈፀመ ስለሚለው የሚያብራራው ? የትኛው አካል ነው ጉዳዩን የሚያስረዳ ? እንዲህ ያደረጉ ሰዎች ምን ተደረጉ ? በጥይት የተደበደቡትስ ፍትህ አገኙ ?

ትልቁ ጥያቄ #የፍትህ_ተቋማት መኖራቸው ፋይዳው ምንድነው ?

ባለፉት በርካታ ወራት ብዙ የጭካኔ ተግባራት አይተናል ፤ አሁንም ማየታችን ቀጥለናል፤ በቪድዮ እና በፎቶ ተቀርፀው ያልተቀመጡ እንጂ በርካታ ህጋዊ ያልሆኑ ከሰውነት ተራም የወጡ ድርጊቶች ይኖራሉ ፤ ጊዜ እየጠበቁ ይወጡ ይሆናል።

አንዳንዴ ምነው በዚህ ጊዜ ባልተፈጠርን ጭምር የሚያስብል ነው።

@tikvahethiopia