#ወልዲያ
• ንግድ ፍቃድ ያላሳደሳችሁ አሳድሱ ፤ ጊዜው ካለፈ 20 ሺህ ብር ቅጣት ትከፍላላችሁ።
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን ባላሳደሱ ነጋዴዎች ላይ በአዋጁ የተቀመጠውን የገንዘብ ቅጣት ተግባራዊ እንደሚያደርግ የወልዲያ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
ታህሳስ 30 2014 ዓ.ም ለማጠናቀቅ የታቀደው የንግድ ፈቃድ እድሳት ሰራ በአካባቢው በነበረው የሰላም እጦት ምክኒያት ወደ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አራዝሞ የለምንም ቅጣት አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝ የግለፀው ፅ/ቤቱ ከሃምሌ1 ቀን 2014 ዓ.ም በኃላ ለማሳደስ የሚመጡ ነጋዴዎች በአዋጁ መሰረት 20 ሸህ ብር ቅጣት እንደሚከፍሉ አሳስቧል።
በተያዘው ዓመት 6 ሽ 101 ነጋዴዎች ፈቃዳቸውን እንዲያሳድሱ ታቅዶ እስካሁን 4 ሽህ 248ቱ ብቻ ማሳደሳቸውን የተገለፀ ሲሆን በተለያዩ ምክኒያቶች ያላሳደሱ ነጋዴዎች በከተመዋ በሚገኙ 3 የንግድ ማዕከላት በመገኘት እንዲያሳድሱ ጥሪ ቀርቧል።
መረጃው የወልዲያ ኮሚኒኬሽን ነው።
@tikvahethiopia

የተዘነጋችው አጣዬ !
ከዚህ ቀደም በተፈፀመባት ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደመችው አጣዬን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ደካማ መሆኑን እና ለዚህም ትኩረት የሚሰጥ የመንግስት አካል ማጣቷ ተነግሯል።
ፌዴራል እና የክልል መንግስት ከተማውን እንዲያቋቁሙ ጥሪ ቀርቧል።
የከተማው ከንቲባ አሰለፍ ደርቤ መልሶ ማቋቋምን በተመለከተ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የሰጡት ቃል ፦
" ከአሁን በፊት በአንድም በሌላ የስራ እድል የተፈጠረለት አካል አሁን ስራ አጥ ሆኖ ነው ያለው።
የንግድ ተቋማቱ ተቃጥለዋል ፤ ሀብቱ ወድሟል ፤ አብዛኛው አጣዬ ላይ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ስራዎች እየተሰሩ ስላልሆነ ከስራ አጥ ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ አሁን ላይ የተወሰነ የመቆዘም አዝማማያዎች እና አጠቃላይ የመልሶ ግንባታ ትኩረት አናሳ በመሆኑ የሚስተዋሉ ችግሮች አሉ። እኛ በምንችለው እንደ ከተማ እየሰራን ነው።
ከከተማ ውጭ ያለው በከተማ አቅም የሚገነባ ስላልሆነ የፌዴራል መንግስት የክልል መንግስት እዚህ ላይ ትኩረት አድርጎ ካላገዘ ከስራ እድል ፈጠር ሆነ ከመልሶ ግንባታ ጋር ወድሞ ነው የሚቀረውና አሁን ባለው ደረጃ ከቀጠለ ትኩረት ያልተሰጠው ተግባር ስለሆነ እሱ ጋር መሰረታዊ ችግር ፈጥሮብናል ከማህበረሰቡ ጋር ፤ ትልቅ ችግር የሆነብን ከመልሶ ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው።
ሰላም ላይ ካለው የመንግስት መዋቅር ጋር ትኩረት አድርገን እየሰራን ነው። "
አጣዬ በተፈፀመባት ጥቃት 1400 መኖሪያ ቤቶች፣ ሆቴል፣ ግሮሰሪ ፣ መጋዘን እንዲሁም 50 ቤቶች፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ማምረቻ ተቋማት 1550 ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ነበር።
ከተቃጠሉት ምን ያህሉ ተሰሩ ?
የከንቲባው ምላሽ ፦
" ከኮንቴነር አኳያ የተወሰነ ቆርቆሮ ዳጋፍ በማድረግ የንግዱ ማህበረሰብ በራሱ እንዲሰራ ጥረት አድርገን የተወሰነ የተሰሩ አሉ።
ሆቴል እስካሁን ያስጀመርነው አንድም የለም። ሆቴል የተቃጠለባቸው መልሰን የገነባንባት ያቋቋምንበት የለም ፤ ቁጥር 50 ይደርሳል ብዙ ስራ አጥም የያዘ ነው። በዚህ ላይ ካለው አቅም እና ከመልሶ ግንባታ ትኩረት አኳያ የሰራነው ስራ የለም።
የሞከርነው በዋና ቤት ደረጃ የተቃጠሉትን ከ423 ቤት ውስጥ በመንግስት 45 ቤት፣ በይፋት ልማት ማህበር 10 ቤት አሁን በአልማ 10 ቤት እየሰራን ነው በድምሩ 65 ቤት ነው እየተሰራ ያለው። "
ከንቲባው ከተማውን መልሶ ለማቋቋም ትኩረት የሚሰጥ የመንግስት አካል ማጣቷን ገልፀው የፌዴራል እና ክልል መንግስት ከተማውን በማቋቋሙ በኩል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቃለመጠይቁ /መረጃው ከ SHEGER FM 102.1 ሬድዮ የተወሰደ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
የተዘነጋችው አጣዬ ! ከዚህ ቀደም በተፈፀመባት ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደመችው አጣዬን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ደካማ መሆኑን እና ለዚህም ትኩረት የሚሰጥ የመንግስት አካል ማጣቷ ተነግሯል። ፌዴራል እና የክልል መንግስት ከተማውን እንዲያቋቁሙ ጥሪ ቀርቧል። የከተማው ከንቲባ አሰለፍ ደርቤ መልሶ ማቋቋምን በተመለከተ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የሰጡት ቃል ፦ " ከአሁን በፊት በአንድም…
#አጣዬ
📩 " ከተዘነጋችው አጣዬ የግቢ ተማሪ ነኝ ፤ አሁን ክረምት የት እንደምንገባ አላውቅም። ቤት ንብረት ዜሮ ነን 😭 " - ሰዒድ (Tikvah Family - Atatye)
📩 " በአጣዬ ስር ባሉ ቀበሌዎች ውስጥ ነኝ ፤ ከቤት ንብረታችን ከተፈናቀልን አመት ሞልቶናል " - ሃያት አሊ (Tikvah Family)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#ሳዑዲ_አረቢያ
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሪያድ የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን እቃዎች ከሱቆች እና ከመደብሮች እየሰብሰበ ይገኛል።
የሳዑዲ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃል በሚል የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን አሸንጉሊቶች፣ ቲሸርቶች፣ የጸጉር ማስያዣዎች፣ ኮፊያ፣ እና የእርሳስ መያዣወችን ከየመደብሩ እንዲሰበሰቡ እያደረገ ነው።
የሀገሪቱ መንግስት ህፃናትን ለመጠበቅ ሲል " መርዛማ መልዕክት " የያዙ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚያስተዋውቁ ቀለም ያላቸውን እቃዎችን ከሱቅ እና ከመደብር እየሰበሰበ መሆኑን ገልጿል።
አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እቃዎቹ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነውን ማህበረሰብ ሞራልና እሴት የሚጻረሩ እንዲሁም አዲሱን ትውልድ ለተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት የሚያበረታቱ ናቸው ብለዋል።
የሳዑዲ ንግድ ሚኒሰቴር በትዊተር ገፁ ፤ እቃዎቹን የመሰብሰብ ዋና ትኩረት " ለሳውዲ ህዝብ እሴቶች የማይመጥን ቀለም ያላቸው እቃዎች " ማስወገድ ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ መሰል እቃዎችን ሲሸጡ በሚገኙ ሱቆች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ከዚህ ባለፈ ሳዑዲ አረቢያ በቅርቡ ሁለት የዲስኒ እና ማርቭል ፊልሞችን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃሉ በሚል አግዳለች።
በሳዑዲ አረቢያ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ህገወጥ ሲሆን #እስከሞት ድረስ ያስቀጣል።
ቪድዮ - DW

ፎቶ - ቪድዮ ፦ ለህፃን ማርኮን የሻማ ማብራትና የፀሎት ሰነ ሰርአት በላዛርስት ትምህርት ቤት አካባቢ እየተከናወነ ይገኛል። እጅግ ብዙ ሰዎች ተገኝተዋል። ህፃን ማርኮን ከትምህርት ቤት ሲወጣ በጎርፍ ከተወሰደ እንሆ ወደ 8ኛ ቀን እየተሸጋገርን ሲሆን እስካሁን ሊገኝ አልቻለም ፤ ፍለጋው ግን ቀጥሏል ። (ዳኒ - Tikvah Family) @tikvahethiopia
#Update
ህፃን ማርኮን እስካሁን አልተገኘም።
በአዲስ አበባ ከተማ ከላዛሪስት ት/ቤት በጎርፍ የተወሰደው ማርኮን ይገረም እስካሁን አለመገኘቱ ታውቋል።
ዛሬ 9ኛ ቀን ነው።
@tikvahethiopia
ህፃን ማርኮን እስካሁን አልተገኘም።
በአዲስ አበባ ከተማ ከላዛሪስት ት/ቤት በጎርፍ የተወሰደው ማርኮን ይገረም እስካሁን አለመገኘቱ ታውቋል።
ዛሬ 9ኛ ቀን ነው።
@tikvahethiopia
#ማስታወሻ
አዋሽ ባንክ አንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያስገኝ የሥራ ፈጠራ ውድድር ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
የሥራ እድል ፈጠራን የሚያበረታታውና "ታታሪዎቹ" የተሰኘው ውድድሩ፤ አንድ ሺህ ተወዳዳሪዎችን እንደሚያሳትፍ ይጠበቃል።
አዳዲስ እና ችግር ፈቺ የሆኑ የሥራ ሀሳቦች ያላችሁ አመልካቾች በውድድሩ መሳተፍ ትችላላችሁ።
የማመልከቻ ቅጹ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አማራጭ ሊንኮች ይገኛሉ፦
ለአማርኛ 👉
https://formfaca.de/sm/ibm6Nojej
ለአፋን ኦሮሞ👉
https://formfaca.de/sm/WZwSVKhOY
ለእንግሊዝኛ 👉
https://formfaca.de/sm/WFbP8sJNG
በተጨማሪም በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በመቅረብና የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት ማመልከት ይቻላል ተብሏል።
የማመልከቻ ጊዜ 👉
ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 15/2014 ዓ.ም
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

Photo
china S.pdf
418.9 KB
#MoE
በቻይና ሀገር ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ መፈቀዱ ይታወቃል።
ትላንትና ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠው አድራሻ እንደማይሰራ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ገልፃችኃል።
የሚሞላው ፎርም ከላይ የተያያዘው ሲሆን በዚህ Email [email protected], [email protected] ነው የሚላከው።
መላክ የሚቻለው እጅግ ቢዘገይ እ.ኤ.አ. እስከ June 20/2022 ብቻ ነው።
ይህ የሚመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት የላካቸውን ብቻ ነው ተብሏል።

#ጥንቃቄ
በኢትዮጵያ " የዶሮ በሽታ " መከሰቱን ተከትሎ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው የዶሮ በሽታ በኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ከተማ ተከስቷል።
በሽታው እስካሁን በቢሾፍቱ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች መከሰቱን እና ከ50 ሺህ በላይ ዶሮዎች መሞታቸውን ሚኒስቴሩ ለአል አይን ኒውስ የሰጠው መረጃ ያሳያል።
በሽታው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይሰራጭም ልዩ ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑንና የሞቱ ዶሮዎችንም ሳይንሱን በጠበቀ መንገድ በማስወገድ ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ፤ እስካሁን በሽታው ተከስቷል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልፃዋል።
እስካሁን በሰው ላይ አለመከሰቱን ተናግረዋል።
በሽታው ከተከሰተባቸው አካባቢዎች ዶሮዎች እንዳይንቀሳቀሱ ግብርና ሚኒስቴር እገዳ መጣሉ በሽታው እንዳይስፋፋ ያደርጋል ብለዋል።
የዶሮ በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችም የዶሮ ስጋ እና እንቁላል ከመመገብ እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

Forwarded from Tikvah-University
#የትምህርት_ምዘናና_ፈተናዎች_አገልግሎት_ሹመት
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አዲስ ዋና ዳይሬክተር ተሹሞለታል።
እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ከሰኔ 02/2014 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ሰኔ 08/2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተፈርሞ የወጣ የሹመት ደብዳቤ ያሳያል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው መመደባቸውን ተከትሎ ተቋሙ በምክትል ዋና ዳይሬክተር ሲመራ ቆይቷል።
የቀድሞ መጠሪያው ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የነበረው አገልግሎቱ፤ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሠረቅና ውጤት ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሱበት መቆየቱ አይዘነጋም።
@tikvahuniversity

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለኢዜአ የሰጡት ቃል ፦
" ባሳለፍነው ሳምንት በቢሾፍቱ እና በአዲስ አበባ ከተሞች ውስን የዶሮ እርባታ ቦታዎች የዶሮ በሽታ ተከስቷል።
በሽታው በንክኪ የሚዛመት በመሆኑ በእርባታ ቦታዎች በተወሰኑ ዶሮዎች ላይ ከተከሰተ ሌሎች ዶሮዎችን ሙሉ በሙሉ ስለሚያጠፋ ጥንቃቄ ያሻል።
በሽታው ከተከሰተ ጀምሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ በሽታውን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።
የበሽታውን መንስኤና ምንነት ለማጥናትም የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ናሙና እየተሰባሰበ መሆኑን ገልጸው፤ ውጤቱ ሲታወቅ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል።
በሚኒስቴሩ የተቋቋመው ግብረ-ኃይል በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ብቻ ተወስኖ እንዲቀር እየሰራ ነው።
በሸታው እንዳይዛመት እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች መካከል ዶሮ አርቢዎች ለተሻሻሉ የዶሮ ዝርያዎች እርባታ ከውጭ የሚገባውን የበሽታው መንስኤ እስኪጣራ የለማ እንቁላል ዝውውር ታግዷል። የለማ እንቁላል ሲባል ለዶሮ እርባታ ከውጭ የሚገባ እንጂ ለሰው ምግብ ፍጆታ የሚውል አይደለም።
የተከሰተው በሽታ በቅጡ መቆጣጠርና መከላከል ካልተቻለ በአገር የዶሮ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ዶሮ አርቢዎችና ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።
በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር እንዲሁም የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል። አሁን ላይ ሥርጭቱና የሞት መጠኑ ቀንሷል።
የታመሙ ዶሮዎችን ወደ ገበያ የማውጣት አዝማሚያዎችን በግብረ-ኃይሉ በተሰራ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሻሻሎች አሉ። አሁንም የበሽታው ምንነት እስኪታወቅ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።
በሽታው ባልተከሰተባቸው ቦታዎች ሌሎች ዶሮዎችን ባለማስገባት እና የራሳቸውንም ወደ ሌሎች ሥፍራዎች ባለማዘዋወር ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
በሽታው የተከሰተባቸው አርቢዎች ገበያ ባለማውጣት እና የሞቱ ዶሮዎችን በመቅበር እንዲሁም በሽታው የተከሰተባቸውን የእርባታ ጣቢያዎች ኬሚካል መርጨት ይገባል።
በሽታው በሰው ጤና ላይ ያደረሰው ጉዳት እስካሁን ባይኖርም ሕብረተሰቡም በዶሮ እና በዶሮ ውጤቶች አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።
በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ እየሰራን ነው "

#DiamondLeague 🇪🇹
በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀቁ።
በኦስሎ ከተማ ዳይመንድ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ሲሆን ከጥቂት ደቂቃ በፊት በተጠናቀቀው የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ፦
1ኛ. ዳዊት ስዩም (የግል ሰዓቷን በማሻሻል 14:25.84)
2ኛ. ጉዳፍ ፀጋይ
3ኛ. ለተሰንበት ግደይ ተከታትለው በመግባት ማሸነፍ ችለዋል።
ሌሎች በውድድሩ ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አልማዝ አያና 6ኛ፣ ሀዊ ፈይሳ 7ኛ፣ ፅጌ ገብረሰላማ 10ኛ እንዲሁም አበራሽ ምንሰዎ 11ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በኦስሎ እየጣለ ያለው ዝናብ ለአትሌቶች ፈታኝ መሆኑ ተገልጿል።
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethiopia @tikvahethsport

#DiamondLeague 🇪🇹 በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀቁ። በኦስሎ ከተማ ዳይመንድ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ሲሆን ከጥቂት ደቂቃ በፊት በተጠናቀቀው የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ፦ 1ኛ. ዳዊት ስዩም (የግል ሰዓቷን በማሻሻል 14:25.84) 2ኛ. ጉዳፍ ፀጋይ 3ኛ. ለተሰንበት ግደይ ተከታትለው በመግባት ማሸነፍ ችለዋል። ሌሎች በውድድሩ ላይ የተካፈሉት…
#Update 🇪🇹
በወንዶች 5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀቁ።
1ኛ ጥላሁን ሃይሌ ፣ 2ኛ ሳሙኤል ተፈራ፣ 3ኛ ጌትነት ዋሌ በተከታታይ በመግባት አሸንፈዋል።
ሌሎች ውድድሩን የተካፈሉ አትሌቶች ሚልኬሳ መንገሻ 5ኛ፣ አሊ አብዱለመና 10ኛ ሆነው አጠናቀዋል።
ቲክቫህ ስፖርት https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x