TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somali #Afar #ሰላም #ውይይት

ትላንት የአፋርና የሱማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ኮንፈረንስ በአዳማ ተካሂዶ ነበር።

የሰላም ኮንፈረንሱ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት ዓላማ ያደረገ ነው መሆኑን ሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

በአካባቢዎቹ የሚታዩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ሰላምን ለማምጣት ወደ ግጭት ለሚያመሩ ጉዳዮችም መፍትሔዎች ተለይተው የተቀመጡበት መድረክ ነው ተብሏል።

የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ማድረግ፤ በግጭት ምክንያት ከኖሩበት ቀዬአቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠልለው እየኖሩ ችግሮችን እየተጋፈጡ ያሉ ወገኖች ወደ ቀደመው ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ ሊደረጉ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችንም በመድረኩ መነሳቱን ከሰላም ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ ያሳያል።

ባለፈው ዓመት በተነሳ ግጭት ከዘጠኝ ወር በላይ ቤታቸው ተፈናውለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በየዘመዶቻቸው ቤት የተጠለሉ በርካታ ወገኖች እንዳሉ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DawitNega በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል። የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው። ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣…
#DawitNega

የአርቲስት ዳዊት ነጋ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ለቢቢሲ ትግርኛ የሰጡት ቃል ፦

" ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዓርብ ዕለት ነው አዲስ አበባ አዲስ ህይወት ሆስፒታል የገባው።

ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በጉንፋን መልክ የጀመረ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ዓርብ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እስከ ቅዳሜ ድረስ ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል።

ትናንት እሁድ ከሰዓት በኋላ ህመሙ ሲጸናበት ወደ ጽኑ ህሙማን ክትትል ክፍል ገብቷል ማታ 1፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ ህይወቱ አልፏል።

ወደሆስፒታሉ ከመምጣቱ በፊት ህመሙን ለማስታገስ በቤት ውስጥ ግሉኮስ ይወሰድ ነበር።

ህመሙ ሲበረታበት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ የስኳር መጠኑ መጨመሩን እና ህመሙ ወደ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ) መቀየሩን ተነግሮታል።

የዳዊት አስከሬን ላይ ተጨማሪ ምርመራ ይደረጋል። "

Via BBC Tigrinya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DawitNega የአርቲስት ዳዊት ነጋ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ለቢቢሲ ትግርኛ የሰጡት ቃል ፦ " ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዓርብ ዕለት ነው አዲስ አበባ አዲስ ህይወት ሆስፒታል የገባው። ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በጉንፋን መልክ የጀመረ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ዓርብ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እስከ ቅዳሜ ድረስ ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል። ትናንት እሁድ ከሰዓት በኋላ ህመሙ ሲጸናበት ወደ ጽኑ ህሙማን ክትትል…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አርቲስት ዳዊት ነጋ ማን ነው ?

- ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል ፤ መቐለ ከተማ እንዳማርያም ነው።

- ትምህርቱን የተከታተለው በዓይደር ት/ቤት ነው ፤ የሙዚቃ ስራንም አንድ ብሎ የጀመረው በመቐለ ሲሆን በ15 ዓመቱ የሙዚቃን ስራ መጀመሩን በአንድ ወቅት ተናግሯል።

- በመጀመሪያ ለመዝፈን ' ሰርከስ ትግራይ ' የሄደው ዳዊት አንዳልተቀበሉት ፤ በኃላም ወደ ማርሽ ባንድ ገብቶ በድራመርነት ለ6 ዓመት ተጫውቷል።

- ህይወት ብዙ የፈተነችው ዳዊት ነጋ ፤ መሰናክሎችን አልፎ ስኬታማ ለመሆን ብቅቶ ነበር። እናት እና አባቱን በ10 ዓመቱ ያጣው ዳዊት ህይወቱን ለማስቀጠል ገና በልጅነቱ ትንንሽ እቃዎችን እየሸጠ እራሱን ለመቻል ብዙ ታግሏል።

- ከእናት እና አባቱ ህልፈት በኃላ የእናቱ የቅርብ ሰው ወደሆኑ ጎረቤቱ የገባው ዳዊት በአንድ ወቅት ምግብ የሚበላበትን ፣ የ200 ብር ቤት ክራይ የሚከፍለውን አጥቶ ነበር።

- ከልጅነቱ አንስቶ አስራ አምስት ዓመታትን በሙዚቃ ውስጥ ያሳለፈው ዳዊት 15 ዓመት ሙሉ በዚህ ሞያ ብር ሳያገኝ፣ አንዳንዴም ምግብ ሳይበላ እያደረ ፣ የቤት ኪራይ ሚከፍለው ሲያጣ ለሊት በአጥር ዘሎ እስከመግባት አንዳንዴም ጓደኞቹ ቤት እስከማደር ደርሶ ነበር።

- ምግብ መብያ አጥቶ ብዙ የተቸገረው ዳዊት እንደሱ የተቸገር ኢትዮጵያዊ ስለመኖሩ እንደሚጠራጠር በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለ ምልልስ ተናግሮ ነበር።

- ምንም እንኳ ብዙ የህይወት ውጣውረድ ፣ ፈተና ከፊቱ ቢያጋጥመውም ያን ሁሉ ችግር በትጋት አልፎ የወጣበትን የትግራይ ህዝብ ባህል ፣ መዚቃ በስራው ለዓለም አስተዋውቋል። በትግርኛ የሙዚቃ ዘርፍ ውስጥም የራሱን አሻራ አሳርፏል።

አርቲስት ዳዊት ነጋ በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

@tikvahethiopia
#HoPR

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቃል የሚሰጡትን ምላሽ ያዳምጣል።

ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚካሄደው በዚህ መደበኛ ጉባዔ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተያዘው አጀንዳ መሠረትም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ጥያቄዎችን ያቀርባሉ። እንደዚሁም አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ።

ስብሰባው በቀጥታ ለህዝብ ይሰራጫል ተብሏል።

Via HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዋስትናው ተሻረ ! ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ እና ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ የተፈቀደው የ10 ሺህ ብር ዋስትና ተሻረ ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ በስር ፍርድ ቤት የተፈቀደላቸውን የ10 ሺህ ብር ዋስትና ሻረ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዋስትና ትዕዛዙ ላይ ይግባኝ…
#Update

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነገ ፍ/ ቤት እንዲቀርብ ታዘዘ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ፍርድ ቤት ነገ እንዲቀርብ ዛሬ መጥሪያ ደርሶታል።

ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ እንደተናገሩት " ለነገ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ ዛሬ እንደደረሰው አረጋግጫለሁ " በለዋል።

" በዚህ መሰረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ቻሎት ነገ ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ ቤት ይቀርባል " ሲሉ መግለፃቸውን ከጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለመስማት ተችሏል።

ከቀናት በፊት (ሰኔ 2) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በስር ፍርድ ቤት የተፈቀደ የ10 ሺህ ብር ዋስትና መሻሩ እንዲሁም 8 ቀናት ለምርመራ መፍቀዱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

Be A Legend!
Pay online with your BoA Visa card like Drogba!
የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በአሁን ሰዓት በ አዲስ አበባ ስታዲየም " ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር " እየተካሄደ ይገኛል። ፕሮግራሙ በርካታ ህዝበ ሙስሊም በተገኘበት ነው እየተከናወነ የሚገኘው። በዚህ ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር ኢብራሒም አብዱራህማን ኢብራሒም ሀገራችን #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ወክሎ የውድድሩ ተሳታፊ ነው። ፕሮግራሙ እንደተጠናቀቀ ተጨማሪ መረጃዎችን የምንልክላችሁ ይሆናል። @tikvahethiopia
#Update

ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድር በአዲስአበባ ስታዲየም ተካሂዷል።

ዚያድ ፈሪጃ ከሉብናን በአዛን ውድድር 1ኛ ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆኗል።

ሙሀመድ ኑር ከኦርዶን በሂፍዝ ውድድር አንደኛ ደረጃ በመውጣት 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር አሸናፊ መሆኑን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስአበባ ስታዲየም የተካሄደው አለምአቀፍ የቁርአን ሒፍዝ እና አዛን ውድድር በሰላም ተጠናቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አርቲስት ዳዊት ነጋ ማን ነው ? - ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል ፤ መቐለ ከተማ እንዳማርያም ነው። - ትምህርቱን የተከታተለው በዓይደር ት/ቤት ነው ፤ የሙዚቃ ስራንም አንድ ብሎ የጀመረው በመቐለ ሲሆን በ15 ዓመቱ የሙዚቃን ስራ መጀመሩን በአንድ ወቅት ተናግሯል። - በመጀመሪያ ለመዝፈን ' ሰርከስ ትግራይ ' የሄደው ዳዊት አንዳልተቀበሉት ፤ በኃላም ወደ ማርሽ ባንድ ገብቶ በድራመርነት ለ6 ዓመት…
#DawitNega

የአርቲስት ዳዊት ነጋ የቀብር ስነስርዓት ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን እንደሚፈፀም ታውቋል።

አርቲስት ዳዊት ነጋ በህይወት ሳለ " ካሌብ ሾው ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቃለመጠይቅ በሰጠበት ወቅት ለወጣቶች ያስተላለፈው መልዕክት ፦

" ... ስኬት አጠገብህ ነው ያለው። በጣም ሩቅ መስሎ የሚታያችሁ ፣ በጣም ጨለማ መስሎ የሚታያችሁ ነገር ከናተ ጋር ነው ያለው።

ለምንም ነገር መሸነፍ የለብህም። ማንም ሰው የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል በእኔ መማር አለበት።

እኔ ትልቅ ነገር ሰርቼ ሳይሆን በአቅሜ የምችለውን ነገር እየሰራው ነው፤ ቢያንስ ትላንት የምተኛበት ቤት አልነበረኝም፤ ለረጅም ጊዜ የእራት መብያ እንኳን አልነበረኝም እንደኔ ያጣ ኢትዮጵያዊም ያለ አይመስለኝም።

ተስፋ አልቆርጥም። አንድ ጊዜ ሰው ሆናለሁ ብዬ አልሸነፍም ነበር። የ200 ብር የቤት ኪራይ መክፈል ሲያቅትህ አስበው ...

ወጣቱ በእኔ እንዲማር እፈልጋለሁ። የሚፈልገውን ስራ ዶክተር ፣ መሃንዲስ ሊሆን ይችላል የፈለገውን አይነት ሞያ ያለው ሰው እኔ ሰርቼ እቀየራለሁ ብሎ እራሱን ማሳመን አለበት ፤ ከዛ ለራሴ ሆኜ ለሀገሬ ፣ ለህዝቤ ሆናለሁ ብሎ ማሰብ አለበት ፤ ተስፋ ካልቆረጠ ማንም ሰው ምንም ማደረግ ይችላል። "

@tikvahethiopia
#Gambella

ጋምቤላ በተኩስ ልውውጥ እየተናጠች ነው።

በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ " ጋምቤላ " ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን እና ከፊል የከተማው ክፍል ውስጥ ታጣቂዎች እንደሚታዩ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።

ጋምቤላ ውስጥ ታጣቂዎች ዛሬ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ከንጋት 11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ነው ተኩስ ከፈቱ የተባለው። እስካሁን ጥቃቱን የሰነዘሩት ታጣቂዎች እነማን መሆናቸው የታወቀ ነገር የለም።

የታጣቂዎቹ ጥቃት ኢላማ የርዕሰ መስተዳደሩን ጽ/ ቤት ለመቆጣጠር ያለመ ሳይሆን እንደማይቀር የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት በዚሁ ክስተት ሳቢያ ፦
- የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣
- የንግድ ሥራዎች
- መደበኛ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን ነዋሪዎችም በቤታቸው ዘግተው መቀመጣቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ አካባቢም ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ላለፉት አራት ሰዓታት እየተሰሙ እንደሚገኙ አንድ በአቅራቢያው ያሉ ነዋሪ አክለዋል።  

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በከተማዋ ስለተከሰተው የተኩስ ልውውጥና አሁን ስላለው ሁኔታ " ምንም የምንሰጠው መረጃ የለም’ " ሲሉ መናገጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ በኩል የጋምቤላ ቲክቫህ አባላት የላኳቸው መልዕክቶች ፦

📩 " Gambella lay cheger ale mesarya yetateku sewoch bezat eyegebu new tekus betam ale "

📩 " Here Gambella city upto now high fighting really we are worried please inform for concerned body "

📩 " እባካችሁ ጋምቤላ ሰላም አደለም "

በሌላ መረጃ የክልሉ መንግስት ፥ " በጋምቤላ ከተማ ያለውን አንፃራዊ ሰላም ለማደፍረስ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የፀረ ሰላም ሀይሎችን ለመመከት የከተማው ማህበረሰብ ሳይረበሽ ከፀጥታ ሀይሉ ጎን እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን " ብሏል።

ዛሬ ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ የጠላት ጦር እና የመንግስት የፀጥታ ሀይል የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ናቸው። " ሲል ገልጾ ዝርዝር ዜናው ይገለፃል ብሏል።

ጠላት ሲል የጠራውን ኃይል በስም አልገለፀም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gambella ጋምቤላ በተኩስ ልውውጥ እየተናጠች ነው። በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ " ጋምቤላ " ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን እና ከፊል የከተማው ክፍል ውስጥ ታጣቂዎች እንደሚታዩ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። ጋምቤላ ውስጥ ታጣቂዎች ዛሬ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ከንጋት 11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ነው ተኩስ ከፈቱ የተባለው። እስካሁን ጥቃቱን የሰነዘሩት ታጣቂዎች…
የጋምቤላ ክልል ሁኔታ፦

ዛሬ ከታጣቂዎች ጋር እየተደረገ ካለው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ በፊት ባለፉት ቀናት በክልሉ ፀጥታ ላይ ያተኮሩ ውይይቶች፣ ስብሰባዎች እና መግለጫዎች ሲሰራጩ ነበር።

የክልሉ መንግስት ፀጥታ ምክር ቤት በክልሉ እየተስፋፋ መጥቷል ያለውን " ህገወጥነትን ለመቆጣጠር እና ህግን ለማስከበር " በየደረጃው የጸጥታ ኃይሎችን ማጠናከር በሚያስችል ሁኔታ ዙሪያ ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

የጸጥታ ም/ቤቱ ትላንት ባደረገው ስብስባ “ሕገ-ወጦችን እና ሥርዓት አልበኞች” ያላቸውን አካላት መቆጣጠር እና የክልሉን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ “ግንባር ቀደም የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን” ከውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል።

የክልሉ የጸጥታ ም/ቤት በስብሰባው የክልሉን ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ ገምግሞም ነበር።

እነዚህን ህገ-ወጥ ተግባራት በከተማም ሆነ በገጠር በአጭር ጊዜ ማረም ካልተቻለ የጋምቤላ ክልል ልማት የሚያስቀጥል እንዳልሆነ የፀጥታ ም/ቤቱ መግባባት ላይ ደርሶ ነበር።

በክልሉ ያለውን ሰላምና ልማት የሚያመክን የህገ-ወጥነትና የሥርዓት አልበኝነት መናኸሪያ የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት፤ ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል መልክ መያዝ እንዳለባቸው የክልሉ የጸጥታ ምክር ቤት ወስኖ ነው የተለያየው።

ከቀናት በፊት ሰኔ 4/2014 ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ከተማ እየተፈጠረ ያለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አመራሩ እና ህብረተሰቡ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረው ነበር።

ያንብቡ telegra.ph/Gambella-06-14

@tikvahethiopia