TIKVAH-ETHIOPIA
#እጅግ_በጣም_አስቸኳይ በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል። ይሁንና አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል። ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር…
#Update
ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድሩ በነገው እለት ጥዋት በአዲስ አበባ ስቴዲየም እንዲካሔድ በመንግስት ፍቃድ መሠጠቱ ተሰምቷል።
በዚህም መሠረት ነገ ሰኔ 6 ቀን 2014 ፕሮግራሙ እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸውን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

ዓመታትን መልስ ያላገኘው የህዝብ ሮሮ !
የዲላ-ቡሌ-ሻኪሶ መንገድ !
ነዋሪዎች ፦
🗣 " መኪና እድሜ ልክ ተሳፋሪ እንደጎተተው ነው "
🗣 " ወሊድ ሄዳ መገላገል የማትችልበት ህይወት፤ መኪና ውስጥ ብዙ ሴቶች ሞተዋል። ጭቃ ላይ ቦይ ላይ በማደር "
🗣 " አያቴም ስለዚህ መንገድ ሰያወራ ሞቷል፣ ቀጥሎ አባቴም በዚህ መንገድ ታሪክ ሲያወራ ሞቷል ፤ ሶስተኛ ወገኝ ነኝ እኔ አሁን ወደ 70 እድሜ ገብቻለሁ ልጄም መጥቷል የምንሆነውን ነገር አናውቅም ስለዚህ መንገድ ሳናወራ የቀረንበት ጊዜ የለም። "
🗣 " በፈረሶች ወደ ገበያ ጭነን ስንመጣ መንገድ ላይ ይወድቁብናል ። መንገዱ ከባድ እንግልትና ችግር ሆኖብናል። በመንገዱ ነፍሰጡር እናቶችም ለሞት እየተዳረጉ ነው "
🗣 " በዚህ የከፋ ኑሮ ውድነት ለትራንስፖርት እጥፍ ለመክፈል ተገደናል፤ በኑሮ ላይ የሚደርሰው ጫና ከባድ ነው "
🗣 " ተሳፋሪው መክፈል የማይገባውን ክፍያ ተቀብለን ነው። እኛ ደግሞ ከእሱ ተቀብለን ለስፔር ነው ። ያለጊዜው የመኪና ሞዴሉ የማይወድቅበት ሰዓት ላይ ከአገልግሎት ውጭ ይሆንብናል። " - ሹፌሮች
አካባቢው ደቡብን ከኦሮሚያ የሚያገናኝ እና ሰፊ እንቅስቃሴ እና ሃብት ያለበት ቢሆንም አስፓልት ባለመሰራቱ ነዋሪው በርካታ ዓመታት ባህላዊ የመጓጓዣ መንገዶችን ለመጠቀም ተገዷል።
ክረምት በመጣ ቁጥር ደግሞ ስቃዩ እና እንግልቱ ይከፋል።
መንገዱ ሁሌ ይሰራል እንደተባለ ነው። ከወሬ የዘለለ አንድም ጠብ ያለ ነገር የለም።
አሁንም የህዝቡ ጥያቄ የቀጠለ ሲሆን መንገዱ መቼ ይጀመራል / ያለው ሂደቱስ ምንድነው ለሚለው ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምላሽ ሰጥቷል : https://telegra.ph/Dilla-Bule-Shakiso-06-12

#ATTENTION ከ8 ወር በላይ ወደ ቄያቸው ያልተመለሱት የገደማይቱ ተፈናቃዮች የመፍትሄ ያለ እያሉ ነው። በገደማይቱ ሀምሌ 17 ቀን በነበረው ግጭት ምክንያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ዜጎች እስካሁን ወደ ቄያቸው መመለስ አልቻሉም። እነዚህ ዜጎች በየመጠለያው ካምፕ እና በየዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠልለው ወራት ማለፋቸውን ገልፀውልናል። " ዞር ብሎ የሚያየን እና የሚጠይቀን አጥተናል " ያሉት…
#Afar #Somali
ዛሬ በአዳማ ከተማ የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ውይይት ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ መሆኑን ለመስማት ተችሏል።
መድረኩ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።
በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ይህን የሰሙ ከ9 ወር በላይ በግጭት ምክንያት ከገደማይቱ የተፈናቀሉ ወገኖች መፍትሄ እንዲያገኙ አቤት በለዋል። ችግር ተፈቶ ወደ ቀደመው ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱም ፣ ፍትህም እንዲያገኙ ጠይቀዋል።
በገደማይቱ ሀምሌ 17 በነበረው ግጭር ከመኖሪያ ቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቄያቸው አልተመለሱም።
እነዚህ ዜጎች በየመጠለያ ጣቢያ እና ዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት የተጠለሉ ሲሆን ዞሮ ብሎ የሚያያቸው እና የሚጠይቃቸውን እንዳጡ ለ20 እና 30 ዓመታት ከኖሩበት ቄያቸው ተፈናቅለው ያለፍትህ ሜዳ ላይ መቅረታቸውን ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።
ዛሬም ድረስ ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖች መፍትሄ እና ፍትህን ይሻሉ።

" የጸጥታ ኃይሉ ኃይል መድቤያለው ቢልም ለሊቱን ከዚህ በፊት ተቃጥላ ዳግም የተሠራችውን የቂልጡ ማርያም ገዳምን አቃጥለዋል " - መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ በትላንትናው ዕለት የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ላይ ምዝበራና ውድመት መድረሱ እንዲሁም የሳንኩራ ቅ/ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መቃጠሉ መገለፁ ይታወሳል። የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ድርጊቱን የፈፀሙት አክራሪና ፅንፈኛ ኃይሎች ናቸው…
#Update
የደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።
በሀድያና ስልጤ ዞን በቃጠሎና ምዝበራ የወደመውን የደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም የመሠረት ድንጋይ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተቀምጧል።
በዚሁ ወቅት ፤ የስልጤ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ ሀጂ መሐመድ ከሊል መልዕክት አስተላልፈዋል።
የክርስትና እምነት ተከታዮችንም ማፅናናተቸው ተነግሯል።
ሀጂ መሐመድ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት "ችግሩን የፈጠርነው እኛው ነን ችግሩን የምንፈታውም እኛው እንሆናለን" ሲሉ ተናግረዋል። " ቤተ ክርስቲያንና መስጂድ ግጭት ፈጥረው አያውቁም " ያሉት ሀጂ መሐመድ "እንዲህ አይነቱ ችግር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጣ ነው " ብለዋል።
የፖለቲካና የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈፀም በየፌስ ቡክ የሚወራው እና የሚተላለፈው መልዕክት ለዚህ አብቅቶናልም ብለዋል። መስጂድንም ሆነ ቤተ ክርስቲያንን ከሚያፈርሱ ሰዎች ፈጣሪ ይጠብቃችሁ ሲሉ ተናግረዋል።
እንዲህ አይነት ክፋት ሲፈፀምም ፈጣሪ ዘብ ያድርን ያሉት ሀጂ መስጂድ ፈርሶ ቤተ ክርስቲያን ይኖራል ቤተክርስቲያን ፈርሶ መስጂድ ይኖራል የሚል እምነት ፈፅሞ የለንም ያሉ ሲሆን የራሱን የሚወድ የሌላውንም ይወዳል ብለዋል።
ሀጂ መሐመድ እነዚህ ቤተ ክርስቲያንን ላጥፋ የሚሉ እኛ የማናውቃቸው ከእምነት አስተምሮ ውጪ የሆኑ አጥፊዎች ናቸውም ብለዋል። አክለውም ፌስቡኩ በወሬ ቢሰራም እኛ በወሬ ሳይሆን በተግባር ለመፍታት እየታገልን ነው ብለዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/EOTC-06-12
(EOTC)

#Update ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል። ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድሩ በነገው እለት ጥዋት በአዲስ አበባ ስቴዲየም እንዲካሔድ በመንግስት ፍቃድ መሠጠቱ ተሰምቷል። በዚህም መሠረት ነገ ሰኔ 6 ቀን 2014 ፕሮግራሙ እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸውን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#መልዕክት
ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ፦
" የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል።
ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ "
@tikvahethiopia
ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ፦
" የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል።
ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ "
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መልዕክት ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ፦ " የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል። ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ " @tikvahethiopia
#መልዕክት_2
(ነገ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር)
- ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 1 ሰዐት ጀምሮ ስለሚካሄድ በጊዜ አዲስ አበባ ስታዲየም እንገኝ።
- በ500 ብር ትኬታ የቆረጠ ሁለት ሰው ሆኖ መግባት ይችላሉ። ትኬት ያልገዙ ሰዎች በ200 ብር በር ላይ እንዲገዙ ተመቻችቷል።
- ሴቶች ከወጋገን ባንክ ፊት ለፊት ያሉትን በር ቁጥር 8፣ 9 እና 11ን ብቻ ተጠቀሙ። የVIP እንግዶችም በVIP በኩል መግባት ትችላላችሁ።
- ሁሉም የራሱን መስገጃ ይዞ መገኘት አይዘንጋ
- የተጠቀምናቸውን ውሀና ብስኩቶች የምናነሳበትን ፌስታል መያዝ አይዘንጉ። በመሃል ሌባ ሊኖር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርጉ።
- አቅመ ዳካማዎችን፣ታላላቆችንና ሴቶች የተሻለ ቦታ እንዲያገኙ አድርጉ
- ለአስተናጋጆች፣ ለኻዲሞችና ለፀጥታ አካላት ፍፁም ታዛዥ ይሁኑ።
ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር
Via ኡስታዝ አህመዲን ጀበል

#DawitNega
በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።
አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል።
የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው።
ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዘመይ፣ ቸቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

#መልዕክት_2 (ነገ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር) - ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 1 ሰዐት ጀምሮ ስለሚካሄድ በጊዜ አዲስ አበባ ስታዲየም እንገኝ። - በ500 ብር ትኬታ የቆረጠ ሁለት ሰው ሆኖ መግባት ይችላሉ። ትኬት ያልገዙ ሰዎች በ200 ብር በር ላይ እንዲገዙ ተመቻችቷል። - ሴቶች ከወጋገን ባንክ ፊት ለፊት ያሉትን በር ቁጥር 8፣ 9 እና 11ን ብቻ ተጠቀሙ። የVIP እንግዶችም በVIP…
ፎቶ ፦ በአሁን ሰዓት በ አዲስ አበባ ስታዲየም " ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር " እየተካሄደ ይገኛል።
ፕሮግራሙ በርካታ ህዝበ ሙስሊም በተገኘበት ነው እየተከናወነ የሚገኘው።
በዚህ ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድር ኢብራሒም አብዱራህማን ኢብራሒም ሀገራችን #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ወክሎ የውድድሩ ተሳታፊ ነው።
ፕሮግራሙ እንደተጠናቀቀ ተጨማሪ መረጃዎችን የምንልክላችሁ ይሆናል።