TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደሴ

በቆሻሻ ማቃጠያ ውስጥ የነበረ የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ስልክ አምባ ትምህርት ቤት በተለምዶ ሚካኤል ጀርባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በነበረ የቆሻሻ ማቃጠያ ቦታ ከቆሻሻ ማቃጠያው የወዳደቁ የቁራሊዬ እቃዎችን እየሰበሰቡ የነበሩ ሶስት የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በሶስቱም ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም በአሁኑ ሰአት የህክምና አገልግሎት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የከተማው ማህበረሰብ አካባቢውን በሚገባ በመፈትሽ የተለየ ነገር ካገኘ ባቅራቢያ ለሚገኝ የጸጥታ ሀይል ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው የደሴ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ ፦ ለቲክቫህ ቤተስብ አባላት ፦

" የተለያዩ ገንዘብ የማግኛ / ሀብት ማፍሪያ መንገዶች " እየተባለ በዲጅታል ሚዲያው በኩል ከቀርብ ጊዜ ወዲህ በርካቶች እጅግ በስፋት እየተከሰቱ ነው።

እነዚህ አካላት ፍቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው ፤ የመስሪያ አድራሻቸው ይታወቅ አይታወቅ ፣ የሚመራቸው / የሚያስተባብራቸው ግለሰብ ይኑር አይኑር የሚለውን በግልፅ ለማወቅ አዳጋች ነው።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከዚህ በፊትም እንዳልናችሁ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል እንቅስቃሴ ውስጥ ስትገቡ / ኢንቨስት ስታደርጉ እነዚህ ጥያቄዎች እንድትጠይቁ አደራ እንላለን ፦

1. ድርጅቱ / ተቋሙ እውቅና ያለው ፣ ፍቃድ ያለው ነው ? የሚሰራበትን ፍቃድ በይፋ አሳውቋል ?

2. በትክክል የሚታወቅ አድራሻቸው የት ነው ? ቢሯቸው ?

3. ለሚደርስብኝ ማኛውም አይነት ነገር ማንን ተጠያቂ ማድረግ እችላለው ?

4. የሚሰራው ስራ ምን ያህል ቀጣይነት አለው ? ነገ እንደማይቆም ምን ማስተማመኛ አለ ? ይህንን ማንስተማመኛ ማን ይሰጠኛል ? የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ያስፈልጋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊቶች እየሰፉ በመሆናቸው ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ብዙሃንን ሊጠቅም ያሚችል ማንኛውም ህጋዊ ስራ በሚስጥር፣ በድብቅ ፈፅሞ ሊሰራ አይችልም እና ውድ ቤተሰቦቻችን ማኛውም እንቅስቃሴ ስትጀምሩ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በቅድሚያ መልስ እንዳያገኙ አድርጉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ነጻሥልጠና

ስቴም ፖወር፣ ቪዛ እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን የመሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ትምህርት እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና በተለያዩ ምዕራፎች በመስጠት ከ600 በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።

አሁን ላይ ይህ ስልጠና ተደራሽነቱን ለማስፋት የኦላይን አማራጭ በመጠቀም ስልጠናውን ለመስጠት ዝግጅት ያጠናቀቅን ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ ለሥልጠናው እንድትመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ከሥልጠናው በተጨማሪ የንግድ ማማከር እና ድጋፍ (Business development and consultation, including coaching, mentorship, and pitching) መከታተል እንዲችሉ፤ እንዲሁም ቢዝነሱ ፕሮቶታይፕ (prototype) የሚያስፈልገው ከሆነ ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን በመጨረስ ላይ እንገኛለን።

ዝርዝር መስፈርቶች https://telegra.ph/ጥቆማ-06-09

ለመመዝገብ : https://bit.ly/3tNHRKL

@tikvahethiopia
#PopeFrancis

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳሳ ፖፕ ፍራንሲስ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በጎረቤታችን ደቡብ ሱዳን ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።

ጉብኝቱ በቀጣይ #ሃምሌ ወር ይካሄዳል ተብሎ የነበረ ሲሆን ከጤናቸው ጋር በተገናኘ ምክንያት ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
#USA

አሜሪካ በአውሮፕላን ከውጭ አገራት የሚገቡ ተጓዦች ወደ ሀገሪቱ ከመግባታቸው በፊት ሲጠየቅ የነበረው የኮቪድ-19 ምርመራ ማረጋገጫ እንዲቀር ማድረጓን ቢቢሲ አስነብቧል።

አገሪቱ ቫይረሱን ለመዋጋት ባደረገችው " ከፍተኛ መሻሻል " ምክንያት ከቫይረሱ ነጻ የመሆን የምርመራ ውጤት ማቅረብ አስፈላጊነት እንዲያበቃ ማድረጓን አሳውቃለች።

ይህ ቅድመ ሁኔታ እንዲቀር የጉዞ አገልግሎት ዘርፉ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል። በፖሊሲው ምክንያት ብዙዎች መጓዝ ስለሚፈሩ እንግልት ተፈጥሯል ብለዋል። 

ለውጡ ከነገ እሁድ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል መባሉን የቢቢሲ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#MoE

የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ሆኖ የመመራት መብት የሚሰጥበት የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሄዷል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በሂደት ወደ ነጻ ዩኒቨርሰቲነት እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ውጪ በመሆን ነጻ ተቋም እንዲሆን የተወሰነውም መንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በራስ ገዝ አስተዳደር እንዲተዳደሩ የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ መሆኑን መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#icog

iCog-ACC ልጆችን በለጋ እድሜያቸዉ መሠረታዊ የኮምፒዉተር እና ኮዲንግ ስልጠና በመሰጠት ለወደፊት ለሚጠብቃቸዉ በዲጂታል የጎለበተ አለም ዝግጁ ያደርጋቸዋል፡፡

በአሜሪካ፥ ካናዳ እና በአዲስ አበባ ብቻ ሲሰጥ የነበረው ይህ የክረምት ፕሮግራም አሁን ደግሞ በባህር ዳር፣ ሃዋሳ፣ ጅማ እና ሐረር ይሰጣል ፡፡

ልጆቻችሁን በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ወላጆች በስልክ ቁጥራችን +251904262728 በመደወል ይህንን ቦት @iCogACCBot ወይም ይህንንማስፈንጠሪያ በመጠቀም ከዛሬ ጅምሮ ማስመዝገብ ትችላላችሁ https://icogacc.com/register/summer+camp+program+2022
ፎቶ : እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ነው የተባለ የሰብዓዊ ድጋፍ ኮንቮይ ትግራይ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) አሳውቋል።

ድርጅቱ በዚህ ሳምንት 308 ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን ያመለከተ ሲሆን 800 ሺህ ለሚደርሱ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ በቂ ምግብ የያዙ ናቸው ብሏል።

በሌላ በኩል አሁን በአማራ እና አፋር ክልል እየተካሄደ ያለው የምግብ ስርጭት እንደተጠናቀቀ በቀጣይ የ6 ሳምንት ዙር የምግብ ስርጭት እንደሚጀመር አሳውቋል።

በሌላ መረጃ #ትግራይ ፦ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ዛሬ ከሰዓት ለስድስተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችን እና አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ይዞ መቐለ ገብቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል ለዓለም ዓቀፉ የቁርዓን ውድድር ማጣሪያ ሲካሄድ ውሏል። የፊታችን እሁድ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ልዩ ውድድር ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ዛሬ የማጣሪያ ውድድሩ እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ በዓለም ዓቀፍ ዳኞች የተመራ ነበር። በእሁዱ ውድድር የሶማሌ ክልሉ ተወላጅ…
#እጅግ_በጣም_አስቸኳይ

በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል።

ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ጊዜያት የምናሳውቅ ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፦ ከሀገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ ወደ አዲስ አበባ እየመጣችሁ ያላችሁ እንግዶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን በመገንዘብ ሳትለፉ ባላችሁበት እንድትከታታሉ እንጠይቃለን።

(አዘጋጅ ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር)

የነገውን ፕሮግራም ተካፋይ ለመሆን ስትጠብቁ የነበራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን የአዘጋጆቹን መልዕክት ያልሰሙ ካሉ #ሼር አድርጓቸው / ላኩላቸው።

@tikvahethiopia
#icog

iCog-ACC ልጆችን በለጋ እድሜያቸዉ መሠረታዊ የኮምፒዉተር እና ኮዲንግ ስልጠና በመሰጠት ለወደፊት ለሚጠብቃቸዉ በዲጂታል የጎለበተ አለም ዝግጁ ያደርጋቸዋል፡፡

በአሜሪካ፥ ካናዳ እና በአዲስ አበባ ብቻ ሲሰጥ የነበረው ይህ የክረምት ፕሮግራም አሁን ደግሞ በባህር ዳር፣ ሃዋሳ፣ ጅማ እና ሐረር ይሰጣል ፡፡

ልጆቻችሁን በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ወላጆች በስልክ ቁጥራችን +251904262728 በመደወል ይህንን ቦት @iCogACCBot ወይም ይህንንማስፈንጠሪያ በመጠቀም ከዛሬ ጅምሮ ማስመዝገብ ትችላላችሁ https://icogacc.com/register/summer+camp+program+2022
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ እጅግ አስከፊ በነበረበት ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች ፦

" እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን።

ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል።

የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት እንደተቀጠርን በደብዳቤ ገለፀው ነበር ከአንድ አመት በፊት ፤ አሁን ግን ኮንትራት ጨርሳችዋል ምንም የምናደርገው ነገር የለም ብለው ደብዳቤ ደረሰን።

ምንም አንኳን ባንመሰገን ሲያልቅ መወርወር አልነበረብንም።

ሰው እያገለለን ከቤተሰብ ተለይተን ህዝብ አገልግለን እንዲ መሆኑ ያሳዝናል።

ደብዳቤዎችን ከላይይ አያይዘናል፤ ህዝብ እንዲሰማው ብቻ ነው ምንፈልገው ፤ ጉዳዩን በተመለከተ በሲቪል ሰርቪስ በኩል ያለውን ምላሽ ሰምተን ወደ ፍርድ ቤት ለመሔድ በዝግጅት ላይ ባለንበት ሰዐት ነው የላኩት።

ከኮንትራት ደሞዝ 13k ወደ 9k ለውጠው ወጪ ለመቀነስ ነበር ፤ ነገር ግን በህጉ መሠረት ቋሚ ሠራተኛ ሳንሆን በኮንትራት እየሠራን ነው አመቱን የጨረስነው። የአሁን ምላሻቸው ግን አንገት ያስደፋል 520 ባለሙያ ከስራ ገበታው በደብዳቤ እየተባረረ ይገኛል።

መፍትሄ እንሻለን !!! "

[ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ስናገኝ እናሳውቃለን / እንልካለን]

@tikvahethiopia