TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና የሰጠው ት/ቤት !

በሀገር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና መስጠቱን የአረካ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታዉቋል።

ይህም ሀገራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ የቴክኖሎጂ ችግር እንዳይገጥማቸው ያግዛል ነው የተባለው።

ፈተናው በሙክራ እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ #በራሱ_መምህር አማካኝነት በበለጸገው ሥርዓት አማካኝነት ነው።

የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ የዛሬው ተግባት እጅግ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

የዚህን ትምህርት ቤት ተሞክሮ ወደ ሌሎች በዞን ወደሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአጭር ጊዜ ለማስፋፋት እንደሚሰራ ገልጿል።

ይህ የኦንላይን (Online) ፈተና ዝግጅት ከማዳበር ባሻገር ለተማሪዎች የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና እንድያጎለብቱ መልካም እድል መሆኑን ትምህርት ቤቱ አሳውቋል።

ትምህርት ቤቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ዉጤታማ ለመሆን እየጣራ መሆኑን አመልክቷል።

ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ እና ግብፅ እየተፋለሙ ነው።

ሀገራችን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከግብፅ አቻዋ ጋር እየተፋለመች ትገኛለች።

እስካሁን ድረስ የበላይ ሆናል ኳስን በመቆጣጠር 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ጫዋታውን እየመራችን ሲሆን የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ይቀራሉ።

በጫወታው አንድ ኳን አንግል ሲመልስብን አንድ ኳስ ገብቶ በኦፍሳይድ ተሽሯል።

ሀገራችን ጨዋታውን በድል ታጠናቅቅ ዘንድ እንመኛለን።

#LIVE

ውድ ቤተሰቦቻችን የኢትዮጵያ እና ግብፅ ጨዋታን በቀጥታ ፦

- በDStv ልዩ ቻናል 240 ላይ ፤

- በetv መዝናኛ ቻናል ላይ

- በbein Sports 3 ላይ መመልከት ትችላላችሁ።

- የበፅሁፍ መልዕክቶችን በ @tikvahethsport

@tikvahethiopia
#የኢትዮጵያ_እና_ግብፅ_ፍልሚያ !

ሀገራችን ኢትዮጵያ ፍፁም የበላይ ሆና ባጠናቀቀችበት የመጀመሪያው አጋማሽ ግብፅ አንድም የጎል ሙከራ አላደረገችም።

የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤትና የበላይነት በሁለተኛው አጋማሽም እንዲቀጥል እየተመኘን ድል ለሀገራችን 🇪🇹ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

የሁለተኛው አጋማሽ ፍልሚያ ጀምሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የኢትዮጵያ_እና_ግብፅ_ፍልሚያ ! ሀገራችን ኢትዮጵያ ፍፁም የበላይ ሆና ባጠናቀቀችበት የመጀመሪያው አጋማሽ ግብፅ አንድም የጎል ሙከራ አላደረገችም። የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤትና የበላይነት በሁለተኛው አጋማሽም እንዲቀጥል እየተመኘን ድል ለሀገራችን 🇪🇹ይሆን ዘንድ እንመኛለን። የሁለተኛው አጋማሽ ፍልሚያ ጀምሯል። @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ❤️

75 ' ኢትዮጵያ 2 - 0 ግብፅ

በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል እየተደረገ የሚገኘው ፍልሚያ 75ኛ ደቂቃ ደርሷል። አሁንም ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 በሙሉ የበላይነት ድንቅ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች። ግብፆቹ እስከሁን ይህን ነው የሚባል የሚያስፈራ ሙከራ አላደረጉብንም።

ቲክቫህ ስፖርት https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ❤️ 75 ' ኢትዮጵያ 2 - 0 ግብፅ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል እየተደረገ የሚገኘው ፍልሚያ 75ኛ ደቂቃ ደርሷል። አሁንም ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 በሙሉ የበላይነት ድንቅ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች። ግብፆቹ እስከሁን ይህን ነው የሚባል የሚያስፈራ ሙከራ አላደረጉብንም። ቲክቫህ ስፖርት https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ድል አደረገች 💚💛❤️

ሀገራችን ኢትዮጵያ ግብፅን በፍፁም የበላይነት ድል አደረገቻት።

የዛሬውን ጨዋታ ለማስተናገድ ብቁ ሜዳ አጥታ በሰው ሀገር ማላዊ ከግብፅ አቻዋ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የተፋለመችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ግብፅን አሸንፋለች።

ሀገራችን ሙሉ ጨዋታውን በከፍተኛ የበላይነት ነው ያጠናቀቀችው።

ማላዊያን አንድም የግብፅ ሽንፈት ለሀገራቸው የሚሰጠውን ከምድብ የማለፍ እድልን ታሳቢ አድርገው በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሜዳ ውስጥ ባሳየችው ድንቅ እንቅስቃሴ ተስበው ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጡ ታይተዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገሩ እና ለኳስ ያለው ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ ይታወቃል የዛሬው ጨዋታ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጎ ቢሆን አሁን ካለው የበለጠ ድባብ ይኖረው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በተከፈቱ ተኩሶች እና ጥቃቶች 9 ሰዎች ሲገደሉ ፤ በርካቶች ቆስለዋል። 1. ቅዳሜ ምሽት በርካታ ሰዎች በሚበዙበት በፊላደልፊያ ሳውዝ ስትሪት ላይ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ተኩስ ከፍተው 3 ሰዎች ሲሞቱ ከ10 በላይ ሰዎች በጥይት ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። 2. ቅዳሜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቻታኖጋ፣ ቴነሲ ውስጥ በሚገኝ ባር አቅራቢያ ተኩስ ተከፍቶ…
የቀጠለው ግድያ በአሜሪካ !

ትላንት አንድ የ23 ዓመት ወጣት በምዕራብ ሜሪላንድ ስሚዝበርግ ገጠራማ አካባቢ በሚገኝ የማምረቻ ድርጅት (Columbia Machine) ተኩስ ከፍቶ 3 ሰራተኞችን ገድሏል።

ግለሰቡ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኛ ሲሆን ተኩስ ከፍቶ 3 ሰራተኞችን ለመግደል ያነሳሳው ጉዳይ ምን እንደሆነ አልታወቀም።

ተኩስ ከፍቶ ከገደላቸው 3 ሰዎች በተጨማሪ ከአንድ ሜሪላንድ ግዛት ፖሊስ ጋር ተኩስ ተለዋውጦ ፖሊሱን አቁስሎ እሱም ቆስሎ ተይዟል።

አሁን ላይ ተጠርጣሪው እንዲሁም የፖሊስ አባሉ ህክምና ላይ ናቸው ተብሏል።

እንደ Gun Violence Archive መረጃ የትላንቱ ሞት የተስተናገደበት ክስተት በዚህ አመት ብቻ 254ኛው የጅምላ ተኩስ ነው።

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ ከተሞች በተከፈቱ ተኩሶች እና ጥቃቶች 9 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ይታወሳል ፤ ከዛ ቀድም ብሎ በቴክሳ ግዛት 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ህፃናት የተገደሉበት አሰቃቂ ግድያ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#Berbera 📍

ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻዋን ማጣቷን ተሰምቷል።

የሶማሌላንድ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት ማሟላት የነበረበትን የባለቤትነት መስፈርቶች በጊዜው ባለሟሟላቱ ባለቤትነቱን ተነጥቋል።

ሚኒስቴሩ እንዳመለከተው ከቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ ለወደቡ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን ኢትዮጵያ ይህን ማድረግ ሳትችል ቀርታለች።

Via Capital Newspaper

@tikvahethiopia
#Gambella 📍

ትላንት ምሽት በጋምቤላ ከተማ 01 ቀበሌ ኒዉላንድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ ፤ ተኩስ ከፍቶ የነበረው ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ድርጅት ነው ብሏል።

" ቡድኑ ህዝብ የማሸበር ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል " ያለው ፅ/ቤቱ ትላንት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በ01 ቀበሌ በከፈተው ተኩስ በአንድ የመንግስት ልዩ ሀይል ላይ ጉዳት አድርሷል ሲል አመልክቷል።

መንግስት የፀጥታ ሀይሉን በማደራጀት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ የመከላከል ስራ እያከናወነ መሆኑን የጠቀሰው ፅ/ቤቱ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመሆን ተገቢውን መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
ተፈትኖ የወደቀው ፌስቡክ

ፌስቡክ ፤ በኢትዮጵያ ሶስት ብሔሮች ላይ ያነጣጠሩ #የጥላቻ_ንግግሮች ያዘሉ ማስታወቂያዎች ይለይ እንደሆነ የተሰጠውን ፈተና መውደቁ ተሰምቷል።

ፌስቡክን የሙከራ ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የፈተኑት " ግሎባል ዊትነስ " እና " ፎክስ ግሎቭ " የተባሉ ሁለት ተቋማት ከቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር ዳግም አፈወርቅ ጋር በመተባበር ነው። 

ምርመራው የተከናወነው የፌስቡክ የጥላቻ ንግግር መለያ ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ ለመፈተን እና የኩባንያው የደህንነት መቆጣጠሪያ ስልቶች ሁከት የሚያባብሱ ማስታወቂያዎችን መከላከል ይችል እንደሁ ለመፈተሽ ነበር።

በአማርኛ ቋንቋ በፌስቡክ የተጻፉ 12 የከፉ የጥላቻ ንግግሮችን የለዩት ምርመራ አድራጊዎቹ እነዚሁኑ ይዘቶች ለኩባንያው እንደ ማስታወቂያ በማቅረብ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለመለጠፍ ይፈቅድላቸው እንደሁ ሙከራ አድርገዋል።

የኩባንያውን የቁጥጥር አቅም ለመፈተሽ በምሳሌነት የተመረጡት የጥላቻ ንግግሮች የተካተቱባቸው ማስታወቂያዎች፤ የአማራ፣ የትግራይ እና የኦሮሞ ብሔሮች ላይ እኩል ያነጣጠሩ ናቸው።

በማስታወቂያዎቹ አረፍተ ነገሮች መካከል " ሰዎች እንዲገደሉ፣ እንዲራቡ ወይም ከአንድ አካባቢ እንዲጠፉ በቀጥታ ጥሪ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን ከእንስሳት ጋር የሚያነጻጽሩ እና ሰብዓዊነት የጎደላቸው” ገለጻዎች እንዳሉበት ተገልጿል።

አብዛኞቹ የማስታወቂያዎቹ ይዘቶች የዘር ማጥፋት እንዲፈጸም ጥሪ የሚያቀርቡ መሆናቸውም ተገልጿል። ከእነርሱ ውስጥ አንዳቸውም ለመተርጎም ውስብስብ እንዳልነበሩ ተመላክቷል።

ግሎባል ዊትነስ ፤ " የትኞቹንም ማስታወቂያዎች አላተምናቸውም። የሚታተሙበትን ቀን ወደ ፊት እንዲሆን በማድረግ፤ ፌስቡክ ማስታወቂያዎቹን መቀበል እና አለመቀበሉን ካሳወቀን በኋላ አጥፍተናቸዋል " ብሏል።

የጥላቻ ንግግሮቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለህዝብ ይፋ አለመደረጋቸውን አረጋግጧል።

በምርመራው መሰረት ፌስቡክ የቀረበሉትን 12ቱንም የጥላቻ ንግግሮች በማስታወቂያ መልክ በገጹ እንዲቀርቡ ፈቃድ ሰጥቷል።

ሁሉም ማስታወቂያዎች ፌስቡክ በአጠቃቀም መመሪያው (community standards) የጥላቻ ንግግር ብሎ ከሚበይናቸው ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

በሙከራ ደረጃ ፌስቡክ የተፈተነባቸው ማስታወቂያዎች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ላይ ለዕይታ ቢበቁ ኖሮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከ57 አመታት በፊት የጸደቀውን ስምምነት የሚጥሱ ነበሩ።

ስምምነቱ ማናቸውም አይነት የዘር መድሎዎ ለማስወገድ የጸደቀ ነው።  

በድርጅቶቹ ምርመራ የተገኘው ውጤት በስተመጨረሻ የቀረበለት ፌስ ቡክ፤ ማስታወቂያዎቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው እንዲታተሙ መፈቀድ እንዳልነበረበት ማመኑን ግሎባል ዊትነስ አሳውቋል።

ፌስቡክ ለኢትዮጵያ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የደህንነት ቁጥጥሩን ለማጥበቅ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን መግለጹንም ምርመራውን ካከናወኑት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ግሎባል ዊትነስ አመልክቷል።

Credit - www.ethiopiainsider.com

@tikvahethiopia