TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60.9K photos
1.55K videos
215 files
4.23K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል " - ታሪኩ ደሳለኝ (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም) በእስር ላይ የሚገነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለለኝ ደብደባ እንደተፈፀመበት ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገልጿል። የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ፤ ዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ 3ተኛ ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝቶ…
#Update

ድብደባ የተፈፀመበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህክምና መከልከሉን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ አሳወቁ።

ዛሬ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ደንበኛቸውን እንዳነጋገሩት ትላንት ማታ የ3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሀኪም እንዳዩት የአይኑ ስር እብጠት መሻሻል እንዳሰየ ነገርግን በትላንትናው ድብደባ ጎኑ (ribs) እንደተጎዳ ተናግረው ለዚህም " ወጥቶ ህክምና ማግኘት አለበት" በማለት እንዲታከም ለራስ ደስታ ሆስፒታል ሪፈር ፅፋውለት ነበር ብለዋል።

ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 5:40 ላይ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በአጃቢና በመኪና መሄድ ከጀመረ በኃላ ግን በሬዲዮ መገናኛ በተሰጠ ትዕዛዝ ሆስፒታል ሳይደርስ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለስ ተደርጓል ሲሉ ጠበቃ ሄኖክ አስረድተዋል።

ጠበቃ ሄኖክ አክለውም ፤ በአሁኑ ሰዓት ጋዜጠኛ ተመስገን በፖሊሶቹ የተመታው ጎኑን (ribs) የህመም ስሜቱ እንዳልታገሰለት ተናግረው ጋዜጠኛ ተመስገን በዚህ የህመም ሁኔታ ውስጥ እያለ ህክምና መከልከሉን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
* የጋዜጠኛ ማኅበራት ጥምረት ለደኅንነት *

17 የጋዜጠኞች ማኅበራት ዛሬ " የጋዜጠኞች ማኅበራት ጥምረት ለደኅንነት " የተሰኘ የማኅበራት ማኅበር ለመመሥረት መወሰናቸውን የመግባቢያ ሰነድ በመፈረም በይፋ አወጁ።

ጥምረቱ አሳሳቢነቱ እየጨመረ ያለውን የጋዜጠኞች የደኅንነት ሥጋት ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎችን በመሥራት የመገናኛ ብዙኃን ምኅዳሩ ሰፊ፣ ደኅንነቱ የተረጋገጠ እና ጤናማ የመረጃ ልውውጥ መድረክ እንዲሆን ይሠራሉ።

ጥምረቱን ለመመሥረት የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙት ማኅበራት ፦

1) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር፣
2) የኦሮሚያ ጋዜጠኞች ማኅበር፣
3) የአማራ ጋዜጠኞች ማኅበር፣
4) የደቡብ ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር፣
5) የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር፣
6) የኢትዮጵያ ሴት ጋዜጠኞች ማኅበር፣
7) የኢትዮጵያ ባሕልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማኅበር፣
8) የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር፣
9) የኢትዮጵያ በጎ ፈቀደኛ ጋዜጠኞችና የጥበብ ሰዎች ለሰብዓዊ መብቶች ማኀበር፣
10) የኢትዮጵያ የኮሚዩኒቲ ሬዲዮ አሰራጮች ማኅበር፣
11) የኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤቶች ማኅበር፣
12) ሚዛን የጋዜጠኝነት ሙያ ተመራቂዎች ማኅበር፣
13) የትግራይ ጋዜጠኞች ማኅበር፣
14) የአማራ ሴት ጋዜጠኞች ማኅበር፣
15) የአማራ የትምህርት ሚዲያ ማኅበር፣
16) ባሕርዳር የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤቶች ማኅበር፣
17) የአማራ የግል ሚዲያ ማኅበር ናቸው።

ጥምረቱ በሒደት ሌሎችንም ማኅበራትን በማቀፍ በኢትዮጵያ ጠንካራ የጋዜጠኞች መብቶች ተሟጋች ሁኖ ለመውጣት እንዲሁም አባል ማኅበራቱን በየትኩረት አቅጣጫቸው ትርጉም የሚሰጥ ሥራ እንዲሠሩ ለማገዝ ያልማል።

Via CARD

@tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10:30 ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች !

እሁድ ግንቦት 28/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ " በመስዋዕትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል " በሚል መሪ ቃል ለፖሊስ አመራር እና አባላት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

ይህን ተከትሎ ስነ-ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፦

➤ ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር (ኦሎፒያ አደባባይ)

➤ ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ በላይና በታች

➤ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ

➤ ከቸርችል ጎዳና በሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፖስታ ቤት

➤ ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

➤ ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

➤ ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ መኪና አጎና አካባቢ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር

➤ ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሜክሲኮ አደባባይ

➤ ከሚክሲኮ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር መብራት

➤ ከሰንጋ ተራ በቴሌ ባር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች በድሉ ህንፃ አካባቢ

➤ ከንግድ ማተሚያ ቤት በውስጥ ለውስጥ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦርማ ጋራዥ አካባቢ

➤ ከሸራተን ወደ አምባሳደር ለሚመጡ ፍል ውሃ አካባቢ

➤ ከካዛንቺስ በኩል ወደ ፍል ውሃ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10፡30 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል።

ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት መሰረት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርድ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ትላንት ባካሄደው መደበኛ 53ተኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተሰምቷል።

በዚህም ፦

1. የድሬዳዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት ይዞታ ውስጥ የተሰጠን ካርታ እንዲመክን እና ይዞታው ወደድሬደዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት እንዲካተት ካቢኔዉ ውሳኔ አሳልፏል።

2. ከ1995 እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ አግባብነት ያለው አካል ሳይፈቅድ እስከ 500 (አምስት መቶ) ካሬ ድረስ የተገነቡ ግንባታዎችን በከፍተኛ የሊዝ ዋጋ ክፍያ ህጋዊ እንዲሆኑ እና ከ500 (አምስት መቶ) ካሬ በላይ ወደ መሬት ባንክ እንዲካተት በካቢኔዉ ተወስኗል።

መረጃው የከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( #ኢዜማ ) በመጪው ሰኔ 11 እና 12 / 2014 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል በዚህም ፓርቲውን በመሪነት እና በሊቀመንበርነት የሚመሩ አመራሮችን እንደሚመርጥ አስታውቋል። ፓርቲው ይህን ያሳውቀው ዛሬ በዋና ፅ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው። ዕጩ አመራሮቹ ከጠቅላላ ጉባኤው መዳረሻ በፊት ለ19 ቀናት የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ፓርቲው ገልጿል።…
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሰኔ ወር ላይ በሚያካሄደው 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለፓርቲው ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች የሚወዳደሩ እጩዎችን የአስመራጭ ኮሚቴውን ዛሬ ይፋ አደርገ።

ፓርቲው የምርጫ አመልካቾችን ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ሲቀበል ቆይቷል።

ለዕጩ ተወዳዳሪዎች ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ውጤታቸው በየግላቸው እንደተገለፀላቸው የጠቆመው አስመራጭ ኮሚቴው የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ በመጠናቀቁ የዕጩዎች አጠቃላይ ውጤትን ይፋ አድርጓል።

ለፓርቲው #መሪነት ለመጨረሻ ውድድር ያለፉ የጣንራ ተወዳዳሪዎች ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ / አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን→ 99 ፤ አቶ አንዱአለም አራጌ / ሀብታሙ ኪታባ → 84 ፤ ፀጋው ታደለ / አየለ ዳመነ → 80 ናቸው።

[ ተጨማሪ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን መረጃ ከላይ በተያያዘው ምስል ያንብቡ ]

@tikvahethiopia
" ካር በር ደም አድርቅ..." ይሁን

በአማራ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ /በሁለቱም ክልሎች/ የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ በዘላቂነት ለመፍታት በቢዝራካኒ ካር በር ላይ የአባቶች እሴት የሆነው ባህላዊ የእርቅ ስነ -ስርዓት ዛሬ ተፈጽሟል።

ከእርቅ ስነ ስርዓቱ ቀደም ብሎ በአማራ ክልል በአዊ ብሔ/አስተዳደረ የጓንጓ ወረዳና የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የድባጢና የማንዱራ ወረዳዎች ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የምክክር መድረክ ካር በር ላይ ተካሂዷል።

NB. ካር በር በሁለቱ ክልል ዞኖች መካከል የሚገኝ አዋሳኝ ቦታ ነው።

(አዊ ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopia
#ደቡብ_አፍሪካ | " በ3 ወራት በትንሹ 6,000 ሰዎች ተገድለዋል "

ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ድርጊቶች ይፈፀምባቸዋል ተብለው ከሚጠሩ ሀገራት አንዷ ደቡብ አፍሪካ ናት።

ከፖሊስ በወጣ ሪፖርት መሰረት በሀገሪቱ በሶስት ወራት በትንሹ 6,000 ሰዎች ተገድለዋል።

በጥር እና መጋቢት መካከል 6,083 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር (4,976 ነበር) የ22.2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ከግድያ በተጨማሪ የፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተፈፀሙ ወንጀሎች በ13.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን 10,818 ሰዎች ተደፍረዋል።

እገታ እና አፈናም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን 3,306 ኬዞች ሪፖርት ተደርጓል ፤ ይህም ከአንድ አመት በፊት ከነበረው በእጥፍ ይበልጣል ተብሏል።

የሀገሪቱ ፖሊስ " የዚህ አመት የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ጨካኔ የተሞላበት እና ለብዙ ደቡብ አፍሪካውያን ደህንነታቸው ያልተጠበቀ ነበር " ብሏል።

" ብቻዬን ከሚሰሩ ወንጀሎች ጋር ተፋልሜ ላሸንፍ አልችልም " ያለው የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ " ከማህበረሰቡ ጋር በጠንካራ እምነት ላይ የተገነባ ጥልቅ አጋርነት ያስፈልገኛል " ሲል ገልጿል።

#TikvahFamilySouthAfrica

@tikvahethiopia
#TikvahFamily

ስለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ፦

• ቲክቫህ/ተስፋ ኢትዮጵያ ሰውነትን ያስቀደሙ ሁሉንም የሰው ፍጡር፣ ህዝብን እና ሀገርን የሚያከብሩ ፣ በማንኛውም ጉዳይ ሚዛናዊ አመለካከት ያዳበሩ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።

• የቤተሰቡ አባላት መረጃ ማካፈል፣ አንዱ ያልሰማውን ሌላው እንዲሰማው መጠቆም ፣ በሚዲያ ላይ የሚከታተሉትን ሌላው የቤተሰቡ አባል እንዲያውቀው ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ የቤተሰብ አባላቱ እርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው። (ምንጭ በመጥቀስ)

• በቤተሰቡ / አባላት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ የሚቻል ሲሆን አንዲት ቃል ስድብ ሆነ የሰዎችን ክብር ፣ ሃይማኖት፣ ብሄር ማንነትን የሚነካ መልዕክት መላክ ከቤተሰቡ ወዲያው በቀጥታ ያስቀንሳል።

• ቲክቫህ ኢትዮ. ከተመሰረተ አንስቶ ከማንም ወገን ፣ ከየትኛውም አካል (የመንግስት ሆነ ተቃዋሚ፣ አልያም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት) ጋር ግንኙነት የሌለው ሲሆን በየትኛውም አካል አይደግፍም፤ አይታግዘም። ለስራ በሚል ከቤተሰቡ ገንዘብ አይጠይቅም አያሰባስብም።

ተቋርጠው የነበሩ የቤተሰቡን ስራዎች ስለማስቀጠል ፦

- ባለፉት ሁለት ክረምቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ዓመታዊ ለገጠር ት/ቤቶች የሚደረገው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እና የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ አመት ለማስቀጠል ዝግጅት ተደርጓል።

- ሲቆራረጥ የነበረው ለግለሰቦች የሚደረግ የህክምና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻም በዚህ ዓመት የሚጀምር ሲሆን ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ስራው ይሰራ የሚለውን ሃሳብ ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

- ከዚህ ቀደም በቤተሰቡ አባላት የሚተላለፉ አጭር የቅሬታ ፣ የጥቆማ፣ የፀጥታ ችግር ማሳወቂያ ፣ ትችት፣ ጥያቄ በስፋት መላክ ይቻላል። እንደከዚህ ቀደሙ መልዕክት ሲላክ አጭር ከጥላቻ ሃሳብ የፀዳ እና የመፍትሄ ሃሳብንም የሚጠቁም ሊሆን ይገባል።

- ለጀማሪ ወጣቶች ላለፉት ዓመታት ክፍት የተደረገው የነፃ ማስታወቂያ ስራም በዚህ ዓመት ይቀጥላል። በግል ሆነ ተደራጅተው እራስን ሆነ ሀገርን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ወጣት የቤተሰቡ አባላት ስራቸውን ሆነ አገልግሎታቸው በነፃ ያለምንም ክፍያ ለሌሎች የቤተሰቡ አባላት ማስተዋወቅ ይችላሉ መብታቸውም ጭምር ነው። ነገር ግን በሚሰሩት ስራ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል።

- በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥ ያሉ የቤተሰባችን አባላት እንዲሁም ደራስያን መፅሀፍቶቻቸውን በነፃ ለቤተሰባችን እንዲያስተዋውቁ የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመት የሚቀጥል ይሆናል።

#ማሳወቂያ፦ የ "ዕርቅ ሀሳብ አለኝ" በሚል በቲክቫህ አስተባባሪነት የተካሄደው ሀገር አቀፍ በሀገር በቀል ባህላዊ የዕርቅ ስነስርዓት ላይ ባተኮረው ውድድር ላይ የቀረቡ ፅሁፎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደቤተሰቡ ይላካል።

#ማሳሰቢያ ፦ ማስታወቂያን በተመለከተ በቀን እጅግ ውስን ማስታወቂያ ለቤተሰቡ ይላካል ፤ የሚላከው ማስታወቂያ ጠቃሚ እና ህጋዊ ሲሆን ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የሚያስነግሩትም የቤተሰቡ አባላት በመሆናቸው የእርስ በእርስ ተውውቅን ያጎለብታል። በዚህ መሃል ችግር ቢፈጠር በማስታወቂያ ስም ማጭበርበር ቢሰራ ድርጅቱን ከነስሙ የምናጋልጥ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላትን ገንዘባቸው እንዲመለስ ይደረጋል። ድርጅቱም ከቤተሰቡ ይቀነሳል።

#ከአጭበርባሪዎች_ተጠንቀቁ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
- " Tikvah Mart "
- " Tikvah Market "
- " Tikvah Business " በሚሉ አድራሻዎች/ቦታዎች አይሰባሰቡም። በእነዚህ ገፆች የሚተላለፉ ሁሉ ሀሰተኛ መልዕክቶች ናቸው። በማስታወቂያ ስም ገንዘብም እንደሚቀበሉ ደርሰንበታል ፤ ከዚህ በፊትም እንዳልነው ተጠንቅቋቸው። ቻናሎቹንና ግሩፖቹን ለቴሌግራም ሪፖርት አድርጉ ፤ ይህን ስራ ለመስራት የሚጠቀሙበትን የስልክ ቁጥር ካላቸውም ላኩልን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ ምንም አይነት የ #Youtube#TikTok#Facebook አካውንት የለም።

መልዕክት ማስቀመጫ ፦ @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia
#Monkeypox

ጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያ በዝርጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ሳይያዝ አልቀረም ተብሎ የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አሳውቃለች።

ሀገሪቱ የተጠርጣሪውን ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሴኔጋል እንዲላክ አድርጋለች።

የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሀገሪቱ የመመርመር አቅሟ ውስን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ናሙናው ወደ ሴኔጋል እንዲላክ መደረጉን አሳውቋል።

ናሙናው በትክክል ቫይረሱ መኖሩን የሚያረጋግጥ ከሆነ ሀገሪቱ በጀት መድባ ለምርመራ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በማሟላት ምርመራው በሀገር ውስጥ እንዲደረግ ለማድረግ መሰራት አለበትም ብሏል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ በአፍሪካ የዝንጀሮ የፈንጣጣ በሽታ በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቫይረሱ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

@tikvahethiopia