TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Eritrea ባለፉት ሁለት ቀናት ከጎረቤት ኤርትራ ሠራዊት ጋር አዲስ ውጊያ መካሄዱን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ (ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2014 ዓ. ም.) የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ ነበር ብለዋል። በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና 3 የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው…
#Update

የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ህወሃት " የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ " በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም አሉ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ነው።

ዶ/ር ለገሰ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት ነው ፤ የተመቱትም ራሳቸው የህወሃት ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

በኤርትራና በህወሃት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ያደረገው እራሱ ህወሃት ነው ያሉት ሚኒስትሩ በዚህ ሁኔታ ህወሃቶች " ሬሳ እንኳን መንሳት አልቻሉም፤ በጣም ብዙ ሰው ወድሞባቸዋል "ሲሉ ተናግረዋል።

በህወሃትና በኤርትራ መካከል ያለው መካረርና አልፎ አልፎ እየተደረገ ያለው ውጊያ ፤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ወደጦርነት ሊያስገባ አይችልም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ " ወደዚያ የሚያመራ ሁኔታ የለም " ሲሉ ተናግረዋል

ህወሃት ትንኮሰውን የሚፈፅመው ሁለቱን ሀገራት ወደ ግጭት ለማስገባት እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር ለገሰ " ይህ መቼም ቢሆን አይሳከም " ብለዋል፡፡

መንግስት በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መረጃ እንዳለው ገልፀው፡ ህወሃት ኤርትራ እና ኢትዮጵያን ለማጋጨት እየሰራ ቢሆንም ሁለቱ ሀገራት መቸም ቢሆን ወደ ግጭት አይገቡም ሲሉ ለአልዓይን ተናግረዋል።

ትላንት ህወሓት ባሰራጨው መረጃ ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ እንደነበር እንዲሁም ከ4 ቀን በፊት በአዲአዋላ ውጊያ መደረጉን አሳውቆ ነበር።

በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና 3 የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮች እንደተገደሉ 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና 4 ወታደሮች እንደተማረኩ ገልጿል። 1 ድሽቃ፣ 5 የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እንደተማረከም መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የዝንጀሮ ፈንጣጣ / መንኪፖክስ / ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለን አንጠብቅም " - የዓለም የጤና ድርጅት እስካሁን በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መያዙ የታወቀው መንኪፖክስ ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለው እንደማይጠብቁ የዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛዋ የበሽታው ኤክስፐርት ተናገሩ። ያን ይበሉ እንጂ በሽታው እንዴት እንደሚስፋፋ ሆነ ከአያሌ አሰርት በፊት…
#Mokeypox

በናይጄሪያ አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ በዝንጀሮ ፈንጣጣ / Monkeypox መሞቱን የሀገሪቱ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (NCDC) ትላንት ምሽት አስታውቋል።

ይህ ሞት በዚህ ዓመት በሀገሪቱ ከተመዘገበው አጠቃላይ 21 ኬዝ (ቫይረሱ ከተገኘባቸው 21 ሰዎች) መካከል ነው።

በናይጄሪያ ከሚገኙት 36 ግዛቶች ዘጠኙ የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MonkeyPox) ተመዝግቦባቸዋል።

በሌላ በኩል በኮንጎ በ2022 9 ሰዎች በበሽታው መሞታቸው ሪፖርት መደረጉን ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል።

ከግንቦት መጀመሪያ ጀምሮ ከ200 በላይ የተጠረጠሩ ኬዞች እና በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች በአብዛኛው በአውሮፓ ውስጥ ተገኝተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እስካሁን በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መያዙ የታወቀው የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብሎ እንደማይጠብቅ ትላንት መግለፁ ይታወሳል።

ምንም እንኳን ድርጅቱ ይህን ይበል እንጂ በሽታው እንዴት እንደሚስፋፋ ሆነ ከበርካታ ዓመታት በፊት የፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ዘመቻ መቋረጡ ያስከተለው አንድምታ ይኖር እንደሆን ጨምሮ ብዙ የማይታወቁ ነገሮች መኖራቸውን ገልጿል።

ድርጅቱ የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በአየር በትንፋሽ ይተላለፍ እንደሆን በተጨማሪ የህመም ምልክት የሌላቸው ሰዎች በሽታውን ያስተላልፋሉ ወይ የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ይዞ እየመረመረ ነው።

@tikvahethiopia
#Update #ችሎት

በአዲስ አበባ የኢድ አልፈጥር በዓል ላይ በፈነዳው የአስለቃሽ ጭስ ቦንብ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የሚገኘው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል የመከላከል አድማ ብተና አባል የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ሶስተኛ ጊዜ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀረቦ ጉዳዩ ታይቷል።

መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት ከግንቦት 10 ቀን ጀምሮ በተሰጠው የ13 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ስራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

በዚህም ፦

➡️ የተጠርጣሪው ቃል የመቀበል ስራ መሰራቱን

➡️ ለተጠርጣሪው የገንዘብ ድጋፍ መኖርና አለመኖሩን ለማጣራት ለ18 ባንኮች ደብዳቤ መላኩን

➡️ የግል ስልኩ ላይ ለኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነት ተቋም ደብዳቤ ተልኮ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑ

➡️ የስልክ ቁጥር በማን ስም እንደወጣ ለማጣራት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል እንዲጣራ መጠየቁን

➡️ የፈነዳውን አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ፍንጣሪ በፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግ መላኩንና የምስክር ቃል መቀበሉን ለችሎቱ አስረድቷል።

በፍ/ቤቱ ዳኛ በኩል የስንት ምስክር ቃል እንደተቀበለ ለመርማሪ ፖሊስ ለቀረበ ጥያቄ የአንድ ሰው ምስክር ቃል ተቀብለናል የ3 ምስክር ቃል ይቀረናል በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

ምስክሮቹ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከሆኑ አስካሁን ለምን አልተቀበላችሁም ? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ አንደኛው ምስክር ለስራ ሌላ ቦታ በመሄዳቸውና ሌሎቹም ስራ ላይ በመሆናቸው ምክንያት መቀበል አለመቻሉን መርማሪ መልስ ሰቷል።

ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ በበኩሉ ከሻንጣዬ ጀምሮ ብርበራ ተደርጎል ነገር ግን ምንም ማስረጃ አላገኙብኝም እኔ ምንም ወንጀል አልሰራሁም ከታሰርኩበት ጊዜ ጀምሮ ውሃ እንኳን የሚሰጠኝ ጠያቂ የለኝም አንድ ሳምንት በር ተዘግቶብኝ ታስሬ ነበር ሲል ለችሎቱ ገልጿል።

በአሁን ወቅት ያለበት የስር ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ በችሎቱ ዳኛ የተጠየቀው ኮንስታብል አንቡላ አሁን አ/አ ፖሊስ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዲሆን መደረጉን መልስ ሰቷል።

ፍርድ ቤቱ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ የተመለከተ ሲሆን ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ማስረጃ ማሰባሰቡን እንዲሁም የ3 ሰዎች ምስክር ቃል መቀበልና ቀሪ ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረው ማረጋገጡን ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

በዚህ መልኩ የጀመረውን ምርመራውን ፖሊስ አጠናቆ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ የ10 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል። የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለሰኔ 3 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል።

በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ያወጡት እናት ፓርቲ ፣ መኢአድ እና ኢሕአፓ ሲሆኑ ፓርቲዎቹ " ሀገር በህግ እና በስርዓት እንጂ በአፈና አትመራም " ሲሉ ነው ወግለጫ ያወጡት።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው የኑሮ ውድነት፣ በአዲስ አበባ እየተሰራ ነው ስላሉት ደባ ፣ የመሬት ማዳበሪያ ጉዳይ፣ የሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል ጉዳይ፣ የፋኖን ጉዳይ፣ መንግስት እየወሰድኩ ነው ስላለው የህግ ማስከበር እርምጃ እና ሌሎች ጉዳዮችን በስፋት አንስተዋል።

ፓርቲዎቹ በሕግ ማስከበር ላይ የማያወላዳ አቋም እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን በአፈናና በግድያ ሕግ ማስከበር እንደማይቻል አጠንክረን እናሳስባለን ብለዋል።

" ማፈን መግደልና የማኅበረሰብን ቅስም የመስበር አካሄድ በአፋጣኝ እንዲቆም " ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም ፤ በሕግ ማስከበር ሰበብ የታፈኑ ንጹሓን፣ ጋዜጠኞች፣ ማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የፋኖ አባላትና ቤተሰቦቻቸው፣ ምሑራን፣ የጸጥታ ተቋማት ተመላሾችና አባላት፣ የፓርቲ አመራርና አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

መንግስት ጠረጥሬያቸዋለሁ ብሎ ካሰበም ተገቢውን የሕግ ሂደት በመከተል ለፍርድ ቤት ከማቅረብ ጀምሮ መሰል ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ሶስቱ ፓርቲዎች " ፋኖ " በጭንቅ ጊዜ ሀገር " ድረስልኝ " ብላ የጠራችው ባለውለታ እንጂ ለሹመትና ለሽልማት የመጣ ባለመሆኑ መንግስት አጉል ሥጋቱን አስወግዶ የያዘውን አካሄድ ይፈትሽ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል መንግስት ያለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ሚሊዮኖችን ለጎዳና እና ለከፋ ረሃብ ከመዳረጉ በፊት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ያለውን የገበያ ምስቅልቅል እንዲያርምና እንዲያረጋጋ ጠይቀዋል።

(ሙሉ መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#CocaCola

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፈጀ የኮካኮላ ምርት ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቋል።

ተገንብቶ የተጠናቀቀው የማምረቻ ፍብሪካ ኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያን በአመት 100 ሚሊየን በላይ እሽግ ለስላሳ ለማምረት ያስችለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የማምረቻ ግብዓቶችን እንደ የፕላስቲክ ጠርሙስ፣ የፕላስቲክ ጠርሙስ ክዳን እና ሌሎች የምርት ግብአቶችን በማምረት ከውጪ ወደ ሀገሪቷ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ እንደ " ሚኒት ሜድ ጁስ " የመሳሰሉ አዳዲስ ምርቶችን ሀገር ውስጥ በማምረት ጠቅላላ ምርት ለመጨመር የሚረዳ ነው፡፡

ኮካ ኮላ " ሚኒት ሜድ " የተሰኙ የጁስ ምርቶቹን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እያመጣ መሆኑ ዛሬ በነበረው የፋብሪካው ምረቃ ስነስርአት ላይ ተሰምቷል።

የሚመረቱት የግብአት ምርቶቹ የሲ.ሲ ቢ.ኤን ፍላጎት ከማሳካት በተጨማሪ ለውጪ ገበያ በማቅረብ የውጨ ምንዛሬን ሀገሪቷ እንድታገኝ እና በዘርፉ ያለውን የምርት እጥረት ለመፍታት ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብም ፋብሪካው እቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡

መረጃው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ካፒታል ነው።

@tikvahethiopia
ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ተወለደ።

በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ትላንት ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተገላገለች።

ይህ ክስተት " Natal teeth " ተብሎ እንደሚጠራ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልፁ ሲሆን ከዚህ በፊት ብዙም ያልተለመደ ቢሆንም አዲስ ከሚወለዱ ከ2000 - 3000 ሕጻናት ውስጥ በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ትላንትና የተወለደው ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ምንም ሳይቸገር ጡት እየጠባ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጥ የሚችል ፅሁፍ በዚህ ድረገፅ ማግኘት ይቻላል ፦ https://www.stanfordchildrens.org/en/topic/default?id=natal-teeth-90-P01862

#ወላይታዞንኮሚኒኬሽን #Stanfordchildern

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ህወሃት " የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ " በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም አሉ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ነው። ዶ/ር ለገሰ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት ነው ፤ የተመቱትም ራሳቸው የህወሃት ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል። በኤርትራና በህወሃት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ያደረገው…
#Update #Sheraro

ሮይተርስ ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ላይ የኤርትራ ጦር በሽራሮ ከተማ ላይ በከፈተው ጥቃት አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሏን እና 18 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አመልክቷል።

ሮይተርስ ፤ ከሰብዓዊ ድርጅት ተቋማት የተገኘ መረጃ የሰፈረበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ሰነድ መመልከቱን በመግለፅ ነው ዘገባውን ይዞ የወጣው።

በዚህም የኤርትራ ጦር ቢያንስ 23 ጊዜ ወደ ሽራሮ ከባድ መሳሪያ ተኩሷል።

ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2014 ዓ.ም. የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ከተማ ላይ ከፍቶት ነበረ በተባለው ጥቃት፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ተጠልለውበት የነበረ #ትምህር_ቤት ጉዳት ደርሶበታል።

የከባድ መሳሪያ ጥቃት ተፈጽሞባታል የተባለችው ሽራሮ ከኤርትራ ድንበር 11 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የምትገኝ ናት።

ሰሞኑን ኤርትራ ከፈተች ስለተባለው ጥቃት የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ

https://www.reuters.com/world/africa/eritrean-troops-shell-town-north-ethiopia-un-2022-05-31/

@tikvahethiopia
#Tigray, #Mekelle

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት መቋጫ ያገኝ እና አስተማማኝ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጥረት እያደረጉ የሚገኙት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ ናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ትግራይ ክልል ይገኛሉ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት መቐለ እንደሚገኙ በመግለጽ ከዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ጋር እንደመከሩ ገልጸዋል።

ኦባሳንጆ እና ዶ/ር ደብረፅዮን በቀጠናዊ ጉዳዮች ጋር መምከራቸው የተነገረ ሲሆን ምክክሩን የተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልሆነም።

@tikvahethiopia
#MinT

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ባለቤቶችን ለመደገፍና ለማበረታታት የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል።

በሚኒስቴሩ የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ሠላምይሁን አደፍርስ ተከታዩን ብለዋል ፦

" ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ሥራዎቻቸው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው።

አሁን ላይ ደግሞ ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ኢንተርፕራይዝ መሆን እንዲችሉ ማበረታቻዎችን የያዘ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው።

አዋጁ ሥራ ላይ ሲውል ውጤታማ የሚያደርግ ነው።

ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን አዋጁ ለመጽደቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል።

አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች ለመደገፍ ሚኒስቴሩ እያወዳደረ ይገኛል፤ ተወዳድረው ያሸነፉ ፈጣሪዎች የገንዘብ፣ የቴክኒክና የሥልጠና ድጋፎችን እያገኙ ነው።

የልማት አጋሮች አሸናፊ ለሆኑ ኃሳቦች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ሥርዓትም ተዘርግቷል።

ሚኒስቴሩ አዳዲስ የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን ልጆች ከመደገፍ ባሻገር ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆችም የሚወጡበት ሥርዓት እየዘረጋ ነው "

#ENA

@tikvahethiopia