TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አሜሪካ ዩክሬንን ከመደገፏ በፊት የትምህርት ቤቶቿ ደኅንነት ላይ ታተኩር " - ትራምፕ
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የትምህርት ቤቶችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የምታወጣው የገንዘብ ድጋፍ ለዩክሬን ከሚቀርበው እርዳታ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ይህ የትራምፕ ንግግር የተሰማው በቴክሳስ ግዛት በት/ቤት ውስጥ 19 ህጻናት 2 መምህራኖቻቸው በአንድ በታጠቀ ወጣት ከተገደሉ በኋላ ነው።
የጦር መሣሪያን በተመለከተ እየተካሄደ በሚገኝ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ትራምፕ፣ አሜሪካ ወደ ዩክሬን ቢሊዮን ዶላሮችን መላክ ከቻለች " በአገራችን ውስጥ ያሉ ልጆቻችንን ደኅንነት ለመጠበቅ እንዲውል የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን" ብለዋል።
" በአፍጋኒስታን እና ኢራቅ ትሪሊዮን ዶላሮችን ብናፈስም ጠብ ያለ ነገር ግን ያለም” ያሉት ትራምፕ " የተቀረውን ዓለም ከመገንባታችን በፊት በአገራችን ለልጆቻችን ደኅንነቱ የተጠበቀ ትምህርት ቤት ልንገነባ ይገባል” ሲሉ አክለዋል።
በዚህ ወር መግቢያ ላይ የአሜሪካ ም/ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ የሚውል 40 ቢሊዮን ዶላር እንዲላክ ወሰኗል። ጦርነቱ ከተነሳ ጊዜ ጀምሮ 54 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን አጽድቋል።
ትራምፕ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርን የተቃወሙ ሲሆን ሰላማዊ አሜሪካውያን ራሳቸውን "ከመጥፎ" ሰዎች እንዲከላከሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብለዋል።
በጦር መሳሪያ ላይ ቁጥጥር ከማድረግ ይልቅ በት/ቤቶች ከላይ እስከ ታች የሚዘረጋ የደኅንነት ሥርዓት ሊኖር ይገባል ብለዋል።
በት/ቤቶች መግቢያ ላይ ብረት ነክ ነገሮችን የሚለዩ መሣሪያዎችን ማስቀመጥ እና ቢያንስ 1 የታጠቀ ፖሊስ እንዲኖር ማድረግን ጨምሮ የተጠናከረ ጥበቃ ሊኖር ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ እንዳይሆን እንቅፋት የሆኑት ዲሞክራቶች ናቸው ሲሉ ከሰዋል።
#ቢቢሲ
@tikvahethiopia

#ብርሃን_ባንክ
በእረፍት ጊዜዎ የብርሃን ባንክ ኤቲኤም ካርድዎን በመያዝ ግብይትዎን ያቅልሉ! ኑሮዎን ያዘምኑ ! እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ታሰረ። ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ ከእስር የተፈታው የቀድሞ የአውሎ ሚዲያ ባልደረባ አሁን ላይ " አልፋ ቲቪ " የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ መስራች እና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በፀጥታ ኃይሎች መታሰሩን ጠበቃ ታደለ ገብረመድህንን ዋቢ አድርጎ አዲስ ስታንዳር አስነብቧል። የጋዜጠኛውን መታሰር ባለቤቱ ሄለን አባተ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ፤ ትላንት የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ…
#ችሎት
ትላንት ከሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” ተጠርጥሮ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ።
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ በጋዜጠኛው ላይ ለሚያደርገው ምርመራ 12 ቀናት ፈቅዷል።
የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ “አልፋ ቴሌቪዥን” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን መስራች እና ባለቤት የሆነውን የጋዜጠኛ በቃሉ ጉዳይ ዛሬ ግንቦት 20/2014 የተመለከተው በጽህፈት ቤት በኩል ነው።
ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመጣው መርማሪ ፖሊስ በቃሉ “በተለያዩ በመንግስት ሚዲያ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ በማድረግ መንግስት እንዲጠላ እና ሀይማኖታዊ ግጭት እንዲፈጠር ተንቀሳቅሷል” ብሏል።
ፍርድ ቤት ያለ ጠበቃ የቀረበው ጋዜጠኛ በቃሉ በበኩሉ “ስራ እንዳልሰራ ተደርጌያለሁ በመንግስት ሚዲያም ቀርቤ አላውቅም” ብሏል።
በቃሉ በችሎቱ “ጉዳዩ መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሰረት ነው” ሲል የተከራከረ ሲሆን የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅለትም ፍ/ቤቱን ጠይቋል።
የጋዜጠኛውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ “ጋዜጠኛው በዋስትና ከወጣ ይጠፋል። ግብረ አበሮቹንም ያባብላል” በሚል የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ተደርጎ 14 የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ለፍ/ቤቱ ጥያቄ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የምርመራ ቀናት በሁለት ቀንሶ 12 ቀናትን ፈቅዷል።
በመጪው ሰኔ 2/2014 በሚኖረው ቀጣይ ቀጠሮ ፖሊስ በተሰጡት የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት አንዲያቀርብ በማዘዝ ፍርድ ቤቱ የዛሬውን ውሎውን አጠናቅቋል።
ትላንት 4 ኪሎ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በፖሊስ የተወሰደው ጋዜጠኛ በቃሉ ከተያዘበት ሰዓት ጀምሮ ከቤተሰብ ጋር አለመገናኘቱን ተናግሯል።
ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

እናት የፓርቲ 4 አመራሮቹ የገቡበትን ማወቅ እንዳልቻለ ገልጿል። ፓርቲው በአማራ ክልል መንግስት እየወሰደ ያለውን የሰሞኑን እርምጃ "አፈና" ሲል ገልጾ በዚህ ሂደት አመራሮቹ እንደታፈኑበት ገልጿል። ፓርቲው በስም ገልጾ በፎቶ አስደግፎ በላከልን መግለጫ፦ 1. አቶ ሙሉጌታ የሺጥላ:- የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህር፣ የእናት ፓርቲ የሳይንት ፪ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ…
#Update
እናት ፓርቲ አራት አመራሮቹ በአማራ እና በደቡብ ክልል ከየሚሠሩበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን ማወቅ እንዳልቻለ ገልጾ እንደነበር አይዘነጋም።
ፓርቲው ዛሬ በላከው መረጃ ፤ የአመራሮቹ አድራሻ አለመታወቅ በተለያዩ ሚዲያዎች ከተሠራጨ በኋላ ሞጣ አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች ታፍነው የነበሩት አቶ ምግባሩ አሥማረ ትናንት አርብ 20/09/2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 አካባቢ እንደተለቀቁና ከቤተሰባቸው ጋር እንደተገናኙ ለማወቅ መቻሉን አሳውቋል።
በሌላ በኩል ወላይታ ሶዶ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፓርቲው አመራር ወ/ሮ ስመኝ ታደመ እዚያው ሶዶ ከተማ፣ መሐል ከተማ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉና ከፍተኛ የሐኪም ክትትል የሚፈልገው የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ማወቅ መቻሉን አመልክቷል።
እናት ፓርቲ ፥ " የሁለቱ አመራሮች ሁኔታ ጥቂት እፎይታ የሰጠን ቢሆንም ከሰቆጣ፣ አቶ ሙሉጌታ የሺጥላ እና ከቲሊሊ፣ አቶ ታደለ ጋሸ የደረሱበትን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት እስካሁን መሳካት አልቻለም " ብሏል።
በሌላ በኩል ፓርቲው ፤ " እኛህ ማሳያዎች እንጂ በየቦታው የሚሳደዱ፣ የሚታፈኑ፣ የሚገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሓን ኢትዮጵያውያን ኹኔታ በእጅጉ እያሳሰበን መጥቷል " ሲል ገልጿል።

#ሀገራዊ_ምክክር 🇪🇹
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕ/ር መስፍን አርአያ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦
" በሀገራዊ ምክክሩ #ሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ የሚያስይዝበት አሰራር ይዘረጋል።
የውይይት ሃሳቦች ከታች ወደ ላይ ነው የሚሰበሰቡት።
በውይይቱ ይህ ይነሳ ያ አይነሳ የሚባል ነገር የለም ። ኮሚሽኑ በአጀንዳዎች ላይ ጣልቃ አይገባም።
ምክክሩ ልሂቁ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሐሳቡ በጥቂቶች እንዳይጨናገፍ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ እናቀርባለን።
በቀጣይ በየክልሉ እንደ አመቺነቱ ጽሕፈት ቤቶች ይቋቋማሉ ፤ የኮሚሽኑ ምክር ቤት መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን ስትራቴጂክ ዕቅዱን ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ግብዓት ይሰበሰባል።
አጀንዳ የመሰብሰብ ሥራ በገጽ ለገጽ ማህበረሰቡ በሚረዳው ቋንቋ ስለ ኮሚሽኑ በማስረዳት ሃሳቡን እንዲገልጽ ይደረጋል። በሌሎች አማራጮችም በስልክ፣ ኢሜይል እና ፖስታ በመሳሰሉት ማቅረብም ይቻላል።
ማሕበረሰቡ ሃሳቡን ከማቅረብ በተጨማሪ በማዕከል ደረጃ ለሚደረገው ምክክር ወኪሎቹን እንዲመርጥ ይደረጋል።
የአጀንዳ ሃሳቦች መሰብሰብ የሚጀመርበት ጊዜ #በቅርቡ_ይፋ ይደረጋል። "

#Moot_Court
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት ላለፉት 4 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የምስለ-ችሎት (Moot Court) ውድድር ግንቦት 20/ 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ በተካሄደው የፍጻሜ ዝግጅት ፍፃሜውን አግኝቷል።
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ዙርያ ያተኮረው የዘንድሮው ውድድር ፦
➡️ በአዲስ አበባ
➡️ በአዳማ
➡️ በሀዋሳ
➡️ በሆሳዕና
➡️ በሚዛን
➡️ በጋምቤላ
➡️ በአሶሳ
➡️ በሰመራ
➡️ በሐረር
➡️ በድሬዳዋ
➡️ በጅግጅጋ እና ጎንደር ከተሞች የተካሄዱ ሲሆን በ10 ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 63 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 130 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በክልላዊ የቃል ክርክር ውድድሮች 1ኛ እና 2ኛ የወጡ 24 ተወዳዳሪ ቡድኖች የጽሑፍ ክርክራቸውን ለኢሰመኮ በመላክ የተወዳደሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 8 ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከግንቦት 15-20 ቀን 2014 ዓ.ም. በሩብ ፍፃሜ እና ግማሽ ፍፃሜ ዙሮች ተወዳድረዋል።
ከነዚህም ውስጥ ከወላይታ ሶዳ ከተማ፣ ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የመጡት ተማሪ ሳያት ደሳለኝ እና ተማሪ አስቻለው ማቴዎስ እንዲሁም፣ ከጎንደር ከተማ፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኮሙኒቲ ት/ቤት የመጡት ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ ግማሽ ፍፃሜ አሸናፊዎች በመሆን ለፍፃሜ ውድድር መቅረብ ችለዋል።
ዛሬ በተደረጉው ውድድር ተማሪ ብሌን ሙሉጌታ እና ተማሪ አማኑኤል ዋሴ #ከጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ኮሙኒቲ_ትምህት_ቤት የ2ኛው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምስለ-ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡
(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እና ፎቶዎች ከላይ ተያይዟል)
#EHRC

#ስፖርት ፦ ዛሬ ምሽት በመላው ዓለም የእግር ኳስ ወዳጆች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይካሄዳል።
የዚህ የዋንጫ ፍልሚያ የሚካሄደው በሊቨርፑል እና ሪያልማድሪድ መካከል ሲሆን በመላው ዓለም ሚሊዮኖች ይህንን ጨዋታ ይከታተሉታል።
የስፖርት ወዳጅ የሆናችሁ የቤተሰባችን አባላት ጨዋታውን የተመለከቱ መልዕክቶች እንዲሁም ጎሎች በቲክቫህ ስፖርት በኩል ይደርሳችኃል https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethsport

#ስፖርት ፦ ዛሬ ምሽት በመላው ዓለም የእግር ኳስ ወዳጆች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ይካሄዳል። የዚህ የዋንጫ ፍልሚያ የሚካሄደው በሊቨርፑል እና ሪያልማድሪድ መካከል ሲሆን በመላው ዓለም ሚሊዮኖች ይህንን ጨዋታ ይከታተሉታል። የስፖርት ወዳጅ የሆናችሁ የቤተሰባችን አባላት ጨዋታውን የተመለከቱ መልዕክቶች እንዲሁም ጎሎች በቲክቫህ ስፖርት በኩል ይደርሳችኃል https…
#ስፖርት
ፎቶ ፦ ሊቨርፑል 0 - 1 ሪያል ማድሪድ
🏆 የ2021/2022 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ/የዋንጫ ባለቤት ሪያል ማድሪድ 🏆
የስፖርት ወዳጅ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን ስፖርታዊ መልዕክቶችን በቲክቫህ ስፖርት በኩል መቀበል ትችላላችሁ ⬇️
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
Photo Credit : UEFA Champions League